ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Ben G
አሳብ

ስለ ማሰብ ላለማሰብ
ማሰብ ባያስፈልግ
ምንኛ ደግ ነበር አሳብ ተሰንጥቆ
አሳብ እስቲጠግግ

'ካሳብ አሳብ በልጦ
'ላሳብ አሳብ ቆርጦ
አሳብ 'ካሳብ መርጦ
የሚታሰብ አሳብ..?

...ሰበብ!
ላለማሰብ:

ሰበብ... ላለመንቃት
ሳይጀምሩ ማሰብ..
ሰበብ ማበጃጀት
እፍፍፍ...
እውነት: ይሁን ቅዠት!
ቅዠት 'ያሳብ ጉዞ
አሳብ ተያይዞ
ካሳብ ላይ ተመዝዞ
አሳብ ተጎዝጉዞ
በሰበብ ሀዲድ ላይ
እየተጓተቱ
አሳቦች በረቱ

'ላሳብ የሚታሰብ
የአሳብ ዥጉድጉዶሽ
አሳብ ያዝ ለቀቅ
የነገር አባርሮሽ
አሳብ 'ካሳብ ሲሸሽ
ሲፋተግ ሲተሻሽ

ወዴት ልሽሽ?

ይኼም ሌላ አሳብ...
እዚህ ሸብ
እዚያ ሸብ
አሳብ ማሰባሰብ
አሳብ 'ባሳብ መክበብ
አሳብ 'ባሳብ ማጥበብ
ማሳመር መቀንበብ
...ጥበብ!
ጉራማይሌ ንባብ
ባለ ቀለም ምናብ
ድምፅ አልባ ንትርክ
የሽቅድድም ታሪክ
በምናብ ብራና
ቀድሞ የሚተረክ

እንደ ሰማይ ስንጥቅ
ብሩህ ብርቅርቅታ
አድማስ የሚያዳርስ የቀለም ጠብታ
ብትንትን እያለ
አሳብ 'ካሳብ ላቀ
አሳብ 'ላሳብ ፍሞ
አሳብ ተቃጠለ

ባላስብ ምናለ?
ይኼም ሌላ አሳብ...

(የጌታነህ ልጅ)
#poeticsaturdaya #gitemsitem
👍1
አንድ ሰሞን


በህይወት ሰሌዳ ደስታና መከራ ተፃፈ
ሁሉም አንድ ሰሞን ሁኖብን አለፈ

ሁሉም አንድ ሰሞን
በደስታ መሽሞንሞን
ፌሽታ ላይ አቁሞን
አንዱ ሰሞን ሊያልፍ
በስሜት ሲያንሳፍፍ
ህላዌን ሲያስቀዝፍ
ደሞ ላንዱ ሰሞን ምንዱባን ሲወዝፍ

መከራን ስንረሳ በሀዘን ልንቀጣ
የአንድ ሰሞን ችግር ከቤታችን መጣ

ጥለቱ አደፈ
ኩታችን ጣለን
የዚህ ሰሞን ነገር ሀዘን አስጠለለን
ማቅ እየለበሰን
ሙሾ እያወረድን
ደረት እያስመታን መከራ ላይ ጥሎን
አፈር አስበትኖ
በመቀጣት እንባ አይናችንን ኩሎን
አንዱ ሰሞን ሲያልፍ ለሌላው እየታጨን
ለደስታ እስክስታ ለሀዘን ጠጉር እየነጨን
እኛ እንደሆን አለን

በህይወት ሰሌዳ ደስታና መከራ ተፃፈ
ሁሉም አንድ ሰሞን ሁኖብን አለፈ

የአንድ ሰሞን ትከሻ እስክስታ እንዳልወረደ
በዚህ ሰሞን ዝሎ ደረት ሙሾ አወረደ
እልል ይል የነበረ
አፋችን በፌሽታ
በሰሞን ተቀየረ
በዋይ ዋይ እሪታ

አንዱ ሰሞን ሲያልፍ ለሌላ እየታጨን
ለደስታ እስክስታ ለሀዘን ጠጉር እየነጨን
እኛ እንደሆን አለን

©️ዳጊፋ

#poeticsaturdaya #gitemsitem