ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አይ ሰው

ከስር ከስራቸው እየተከተልን
ሲጠሩን ስንመጣ ሲላቸው ሲያባሩን
እኔ ነኝ ያለውን እነሱን ሊነካ
ነክሰን እየያዝን ጥበቃው ቢሳካ
የኖሩ ኖሩና ተምሳሌትን ቢያጡ
ግብሩን እየሰሩ ስሙን ለኛ ሰጡ
እጅጉንም ሳኩኝ ሆዴን አሻሽቼ
ውሻ ብሎ ስድብ ከሰዎች ሰምቼ

@sarinamard
ከጠበቅነው በላይ እስከ አሁን 26 ተወዳዳሪዎች በማግኘታችን እየተወዳደራችሁ ያላችሁትን እና ውድድሩን እየተከታተላችሁ ድምጽ እየሰጣችሁ ያላችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን! የቤተሰባችን ቁጥርም 1000ን በመሻገሩ ደስታችን ግዙፍ ነው!!!

ይህንንም በማስመልከት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡ ግጥሞችም የመጽሐፍት ሽልማት እንደምናበረክት እወቁልን!
እውነት ስለ እውነት

እውነት እልሀለሁ እውነት በመናገር
የምታጣው ነገር
በምድር ላይ ያለ ሀሰተኛን ፍጡር
አትበይኝ አትበይኝ
እስኪ አንችው ንገሪኝ
የእውነት በዝች ምድር
ስለ እውነት ኑሮ
ስለ እውነት የሞተ ንገሪኝ ማን ነበር??

ከ ፈጣሪ በቀር
ወደ ማይደርሱበት ህልም
።።።።።።።።።።።።።።።
ነገ ተስፋን
አዝሎ ልባችን ላይ በብሩህ ፊደላት ደምቆ ታተመ
ህልማችን
በሰዎች መዳፍ ተይዞ ወደ ማንደርስበት አዘገመ

በቀቢፅ እይታ
ፅልመትን ለመርታት በችኮላ አረማመድ
ተመልከቱት ሰውን
ወደ ማይደርስበት ህልም ተያይዟል መንገድ

@Dagifa
የወረት ትዳር


የተፋቀርን መስሎን ያኔ እደዋዛ
ጥድፍድፍ ብለን ተዋክበን እደዛ
ትዳር ወደሚሉት የስርቤት መቀጫ
ድንገት ገባንና አቃተን መወጫ
መለየት ፈልገን ታጥረን በይሉኝታ
ምን ይሉኛል በሚል አልጋ ለየን ቦታ
የእፍእፍ ፍቅር ወረታችን አልፎ
መልካሙን አስበን ተዘፈቅን በመጥፎ።

ተፃፈ በ ሃይማኖት ሙሉነህ።

@Haymika
መንገድ ወሳጅ አምጪ፣
ለመድረስ፣
ለመቅረት ፣አንተው ነህ ሰጪ፤

ከእውነት፣
ከእምነት፣አብረህ የመጓዙ፣
ፈራጁ፣
አዋጁ፣ልብህ ነው መዘዙ።

በ"ማሜ የኢክሩ አባት"

@Mohammedkemalikru
ከጠገበ ለተራበ
ያ፣ሰንጋ በቅሎ ጠገበ
ስንቱ ፈረስ እየተራበ
እርካብ የለው ኮርቻ
ልጓም የለው መቀነቻ
እሳር አይቀምስ አራሙቻ
እንዲያው ዝም ብሎ መላስ ብቻ።

@Barye1
ውዴታ
እኔ ወድሀለው ልቤ እስኪጠፍ
እመሰክራለው ላንተ ስል በኢፍ
አንተን አስባለው ሳዝንም ስደሰት
ሀዘንም ደስታዬም አንተ ጋር አስቀምቶት
አንሺ ውቡ ጨረቃ ለፍቅሬ ንገሪው
ያላንተ አታይም አትችልም በይው


ፀሀፊ ሰአደት

@Seadet476
ቆይ ግን እኔምለው ዛሬ ትናንት ነው?
🤔🤔🤔🤔
ዛሬ ተቀምጨ ነገን እያሰብኩኝ
ተውኝ እያልኳቸው ወደ ትናንት ሳቡኝ
ትናንት ጦርነት ዛሬ ደግሞ ተስፋ
ነገን ስጠብቀው....
ብርሀን አይቸ መለከት ልነፋ
ግን በጣም ይገርማል
ለክ እንደምታዩት ዛሬ ትናንት ሁኗል
😭😭😭
Maru kefale

@Maru21
ጣፋጭ ነን ላላችሁኝ
"ቸኮሌት ነን እኛ ጣፋጭ ተፈላጊ
ውድ ነን በጣሙን ለመብላት አጓጊ"
ብለው ያወራሉ ዋጋቸው እንዲገባኝ
ጣፋጭ እንደሆኑ እኔ መቼ ጠፋኝ
"እንደ ፍራፍሬ ተወዳጅ ነን" አሉ
ሊያውም ልክ እንደ ሙዝ የላቀ ከሁሉ
ደግሞ ሙዝስ ቢሆን ጣዕሙ ሚጨምረው
ሊበላሽ ሲቃረብ ማርች ሊሆን ነው።(kal ኪዳን)
ወደ ዳሞቻ ተራራ የሚደረግ ጉዞን የሚያሸልመው ውድድራችን ከ30 ደቂቃዎች በፊት ተጠናቋል! ሁላችሁም ተመስገኑልን! አሸናፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!! ተመሳሳይ ውድድሮችን እያደረግን የምንቀጥል በመሆኑ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እየተከታተላችሁን ቆዩ!

ሶስተኛ፦ ኤደን ሙሉነህ @Oritethe
192
1 #ነፍስ_ቦታ መጽሐፍ

ሁለተኛ፡- ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe
193 ነጥብ
2 #ነፍስ_ቦታ መጽሐፍት

አንደኛ፦ ናታን ኤርምያስ @UniqueDY
242 ነጥብ
@ma_trip ተጓዦች ጋር ነጻ ጉዞ ወደ ዳሞቻ

*መግለጫ፦ ሁሉም ምልክቶች እንደ ድምጽ የተቆጠሩ ሲሆን 😍👍🏾😐 ሶስቱ ምልክቶች የተዘጋጁት እኩል ውጤት ቢገኝ እንደመለያ እንዲያገልሉ ነው። ይህንን በደንብ እና ሁኔታዎች ባለማካተታችን ይቅርታ እንጠይቃለን! በቀጣይ የሚኖሩን ውድድሮች ላይም በተሳትፎ እና በዳኝነት አብራችሁን እንደምትቀጥሉ እምነታችን ነው።
አቢሲንያ እንዳለቻችሁ ስንቄን ቅዳሜ 8 ሰዓት ብሔራዊ ቲያትር ተገኝታችሁ መርቁልኝኝኝ . . . እ!. . . እንዳትቀሩ አደራአ!

https://t.me/GitemSitem
አንተ የምትወደው ሙዚቃን በሆንኩኝ
አንተ የምትወደው ግጥምን በሆንኩኝ
እንደ እሳት ነበልባል ልብህን በላስኩኝ፤
እንዲያው ወለል ወለል
እንዲያው ከንበል ከንበል
እንዲያው ፍስስ ፍስስ
ከስጋህ ለይቼ ዛትህን ብነጥቃትስ ፤
መንፈስህ ስካር ቢሞላው
ቀልብህን ነፋስ ቢነዳው
እያገለበለበ የስሜት ገሞራው
ኩራትህ በሟሟ የትም በበተነው፤
በቻልኩበት ፣
በሆንኩበት ፣
አንጀትህን መኮልኮል
ሆድህን ማባባት
አቅልህን መንሳት
ኮከብ በፊትህ መንዛት፤
በሆነና በሆነልኝ
በውበት መስዋት
ትብትብ ብለህ በታሰረከኝ
ሰውነቴ አይደል ወይ ፊትህ ያሳነሰኝ ?!

©️መቅደስ ሞገስ

https://t.me/GitemSitem
ተወኝ
ተስፋ ፤ እንደ ጥላ አልሸሸም፣
/ልቤን...
ደግፎታል ፤ናፍቆት እየመሸም።
እንዴት ነው የናፍቆት
/ምሽት
እንዴት ነው የናፍቆት
/ንጋት
እንደ ፀሐይ ኹሉ
ኹለት ፤ መግቢያ መውጫ
ኹለት ፤ ፅንፍ አቅጣጫ
(አለው ወይ እላለኹ..)
ደግሜ ሸኝቼህ ፤ ደግሜ መጠበቅ
ከጀንበር ተላልፎ ፤ ሐፀይን መታረቅ
ጊዜ ተበድሮ ፤ በጊዜ መንፏቀቅ
በዘገየ እርምጃ ፤ በምእራብ መጥለቅ
( ሲደንቅ! )
/ ምን ማለት እደሆን ፤ አልገባህም አይደል? /
በምስራቅ ማሕፀን ፤ ንጋት እንዲወለድ
ጀንበር ነበረበት ፤ ወደ ጥልቁ መውረድ።
ተስፋ እንደዚህ ፤ አይደል የሚንከራትተው
ናፍቆት ሰውቶ ነው ፤ ፍቅርን የሚያትተው።
አንተም...
አለሁ ማለት ላ'ተው፣
እኔም ተስፋ ማድረግ ላልተው፤
አለን ናፍቆትን፤ ስንመጸውተው።
ትሔዳለህ
ትመጣለህ
'ሸኝካለኹ
ጠብቃለኹ
(እንዴት ልኹን...?)
ጎዶሎ ጨረቃ ፤ ስትሞላ እያየኹ
ተስፋ ልቆርጥ ስል፤ ምክንያት አጣለኹ።
አታውቅም ወይ፤ ቆርጦ መሄድ
አታውቅም ወይ ፤ እሩቅ መንገድ፤
ደከመኝ...
እኔን ፍለጋ ፤ ወዳ'ንተ መንጎድ።
ተወኝ
ላንገናኝ አትቅጠረኝ
በትዝታ አትጠረኝ
ማረኝ
እኔን ከብቻዬ ተወኝ
ኮከብ ሆነህ አትታየኝ
(ተወኝ !)
/ በብርሃን ካንተ ላልደርስ ፤ የመውደቅ ጸጋ አይራቀኝ።/


©️መንበረማረርያም ኃይሉ
መንቢ የሎዛ
መነሻ ሐሳብ
( ተወኝ ) ፀ.ገ .መ

https://t.me/GitemSitem
Forwarded from Mn Ale Addis
What's Addis?

Sehin Tewabe, a rising eccentiric photographer. Check out for her photography works of this outshining woman in the upcoming Mn Ale Addis e-mag!

Stay tuned!

#mnaleaddis #emagazine #BakelEdition #SehinTewabe #photography
👍1
ግጥም ሲጥም ፮

በ6ኛው የግጥም ሲጥም ምሽት የዓመቱን ቆይታ ልናጠናቅቅ ነው! እስካሁን አብራችሁን የተጓዛችሁ፣ በቅርብ የተሳፈራችሁም ሆናችሁ፣ ፌርማታ ላይ እየጠበቃችሁን ያላችሁ ሁሉ ተመስገኑልን!
ከወዲሁ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን - ዝግጅታችን ላይ እንደምትገኙም ጭምር!
በሉ ሽፍታ እንገናኝ የፊታችን ረቡዕ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 ልክ 12 ሰዓት ሲሆን ጀምሮ

Gitem Sitem 6

The 6th Episode of our Open Mic Circle of Poetry and Fun is here for the last session in this Ethiopian year. Thank you for all who have been with us along the way, those who are joining us and even those who are considering to come to one of our events.
We wish you a happy Ethiopian New Year! See you at Shifta

#gitemsitem #heransyoga #seifetemam #shifta