ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ሠው ምንድን ነው

ታስበው ዘንድ ብሎ መዝሙር እንደፃፈው
ትመረምረው ዘንድ ብሎ እንደቀጠለው
እኔም ልጠይቅህ የሠማይ ፈጣሪ
የብርሃናት አባት የምድርም ቀማሪ፤
እድል ፈንታው ፈቅዶ ሞትን የሸለምከው
ይሄ ያንተ አምሣል፤ ጌታ ''ሠው'' ምንድን ነው?


26/11/13
ገጣሚ : ዳዊት:ጥዑማይ

@faberfortunae
፠ሰመመን፠

ሲቃ በሚንጠው በጠቆረ ሰማይ
በዋይታ እርይታ በስቃይ ላይ ስቃይ
በትዝታ ጭሰት ጭስ በሌለው ንዳድ
በብቸኝነት ውስጥ በባይተዋር ጉድጓድ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፋቅርን ተሸክሜ
በቀቢፀ ተስፋ ላይቀለኝ ደክሜ
አለሁ!!
አለሁ እንዳለሁኝ ሞቼም አገግሜ፡፡

✍️መሊኩ [ MAJNUN ]

@Bufal
ኑ !ወደ ነፃነት እንንጎድ
እፍ እያልን
በጭስ እንባ ሳናባክን
ኑ !ለነገ እንንደድ
ኑ።

(ኤደን ሙሉነህ)

@Oritethe
መሪ ቃል

ባይሆን እሮጣለሁ፥
በዘመን ሜዳ ላይ፥ በሰው የመሆን መም፤
ባይሆን አሸንፌ፥
አውለበልባለሁ፥ የልቤን ባንዲራ፥ የ'ኔነቴን ቀለም።
ካልሆነ ግን...
ለመሮጥ የሚሆን፥ ቢያንሰኝ እንኳ አቅም፤
ሯጩን ላለመጥለፍ፥ መሙ ላይ አልወድቅም።
......የዘመኔ ምስል.......
ጉልበት ሳይዝል፤ ልብ ደከመ
ስጋ አብቦ ፤ ነፍስ ቆዘመ
በምጥ መሀል፤ ባለች ፈገግታ
ስንቱ ታለለ ፤ ህይወት ተረት'ታ. ..!!
(ነብዩ.ብ)
ቤት የለኝም

ያም ሰፈር የነሱ ይሄም የእነንትና
የትጋ ቤቴን ልስራ ከማን ልጠጋና
ዘር አልቆጥር ነገር የፈጣሪ ልጅ ነኝ
እንግዲ እኔ አልሰራም ቤቴን ራሱ ይስጠኝ🙏

ያሬድ.የ

@Yjaredy
ከትርምስ መሀል ከኖረ ፀጥታ
በክፉ ቀን መሀል ከበዛ ዝምታ
ያንን ነዉ መተርጎም አንድም ለአንድምታ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita21
1
የእሽቅድድም ህይወት

ግራን አስቀድሞ ቀኝን ለማስቀረት

አንድ አካልን ጥሎ በአንዱ መንኳተት

ሙሉነቱን ጥሎ በግማሽ እየለፋ

በግማሽ አካሉ ሰውን እየገፋ


ቀኙን ማዶ ጥሎ ግራውን እየሣበ
በአንድ አካሉ ማራቶን ያሰበ


@blessedloner
ለመደስኮሩማ ስብከት ለመስበኩ
በወርች ሱባኤ ፍቅርን ለማምለኩ
መምህር መች ሽቶኝ ለወሬ ሽንገላው እኔው መቼ አነስኩ
የቸገረኝ ቢኖር የጠፋኝ ያጠረኝ መፍትሄ ብልሀቱ
የአክስቴን ገዳይ ቆስሎ ከተኛበት ደግፎ ማንሳቱ
በቆሎ ተዘርቶ ኩርንችት ማፍራቱ


@Mahlet_Be
👍1
ትናንት ትዝ እንዳይለኝ- ከራሴ ጋ ማልኩኝ

ትናንትን ስረሳ- ለዛሬም አልኖርኩኝ

ካላየሁዋት የነገ ፀሐይ ተወዳጀሁ

እምነትን ይዤ ለተስፋ ደገስሁ

ከዛማ... በተከራየሁት የጊዜ ሰሌዳ
እኔ ሆንኩኝና የራሴ አለቃ፣ ቀጠሮን ቀጠርኩኝ

ነገ ዛሬ ሲሆን ደሞ ላባርረው

አዲስ ቅዠት ልቃዥ፣ የፈረደበትን መልሼ ልቀጥረው


@Mtesfaye7
.......የሞኝ ኑዛዜ......

ፈውስማ አለፈኝ፣ ምክኒያት ደንታን አልፎ
ተቅበዝባዥ አረገኝ፣ ከፍርሃት እብደት ተርፎ
ሃሳቤ ራስ ስቶ፣ ንግግሬ በዝቶ
ይገላምጠኛል፣ እውነቴ ተብቶ
.
ውብ ብያለሁና፣ ደማቋ ደመራ
ጭልም የሆንሽውን፣ የግሃነም ጮራ።


-ኖኔም
መንታ ፍልስፍና....

የሚንከራተተው ያ'ዳም ዘር በሙሉ:
ሲዳፋ ሲቃና ሲዋትት መዋሉ:
የመፈጠሩን ቅድ ሊደፍን ነው አሉ።



@NikoTheGreat
ወዲህም
ካየሽ ፈሶ ደም
ወዲያም
ካየሽ ፈሶ ደም
ሌላው ሌላው ቢቀር
"እኔን"ንን ለማለት ፤ አፍሽ አይሎገም
።።።።።።።።።።።።።።።፡።።።

ሳሙኤል አለሙ

@Samuelalemuu
መልካም ዜና ለሱ ሀዘኔን ላልካሰኝ
ሳላለቅስ የቻልኩት ለ"ምነው?" ሆድባሰኝ
ስወጣ ጠንካራ ተደብቆ አልቃሻ
(ተብረክርኮም መቆም፤ቢዝልም ትከሻ)
ሲፈሩት ይደፍራል ሃዘን እና ውሻ!


@Guadyeee
"ህይወት....🤔 ጢባ ጢቤ..."

ከፍታ ላይ 'ምታወጣ
አንዲት ቅጠል ጥላ ትታ!
አልያም ደ'ሞ የምትጥል
ትንሽ ድልን አስገኝታ!!
ወይም ደሞ..የለገመች...
ከፍ ላትል ላትረታ
ለሞከሯት.. ጠዋት ማታ!!!

@ZionismT
👍1
አይ ሰው

ከስር ከስራቸው እየተከተልን
ሲጠሩን ስንመጣ ሲላቸው ሲያባሩን
እኔ ነኝ ያለውን እነሱን ሊነካ
ነክሰን እየያዝን ጥበቃው ቢሳካ
የኖሩ ኖሩና ተምሳሌትን ቢያጡ
ግብሩን እየሰሩ ስሙን ለኛ ሰጡ
እጅጉንም ሳኩኝ ሆዴን አሻሽቼ
ውሻ ብሎ ስድብ ከሰዎች ሰምቼ

@sarinamard
ከጠበቅነው በላይ እስከ አሁን 26 ተወዳዳሪዎች በማግኘታችን እየተወዳደራችሁ ያላችሁትን እና ውድድሩን እየተከታተላችሁ ድምጽ እየሰጣችሁ ያላችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን! የቤተሰባችን ቁጥርም 1000ን በመሻገሩ ደስታችን ግዙፍ ነው!!!

ይህንንም በማስመልከት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡ ግጥሞችም የመጽሐፍት ሽልማት እንደምናበረክት እወቁልን!
እውነት ስለ እውነት

እውነት እልሀለሁ እውነት በመናገር
የምታጣው ነገር
በምድር ላይ ያለ ሀሰተኛን ፍጡር
አትበይኝ አትበይኝ
እስኪ አንችው ንገሪኝ
የእውነት በዝች ምድር
ስለ እውነት ኑሮ
ስለ እውነት የሞተ ንገሪኝ ማን ነበር??

ከ ፈጣሪ በቀር
ወደ ማይደርሱበት ህልም
።።።።።።።።።።።።።።።
ነገ ተስፋን
አዝሎ ልባችን ላይ በብሩህ ፊደላት ደምቆ ታተመ
ህልማችን
በሰዎች መዳፍ ተይዞ ወደ ማንደርስበት አዘገመ

በቀቢፅ እይታ
ፅልመትን ለመርታት በችኮላ አረማመድ
ተመልከቱት ሰውን
ወደ ማይደርስበት ህልም ተያይዟል መንገድ

@Dagifa