ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ተወዳዳሪዬ ፍሰሐ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቋል ።
40 ልብ

አይ እታባ ...
እንዴት ቀለድሽ ባክሽ
ሆድ ሆዴን ቢበላው ይመጣል ማለትሽ
አልታይህ ቢለኝ የያኔው ተረትሽ
አልጨበጥ ቢለኝ የፊተኛው ተስፋሽ
ይኸው እታባዬ ...... ቧልተኛ ነሽ አልኩሽ

ቁጥር እንደው አያፍር .....

ደንደሱን አስፍቶ ደሞ እያጠበበ፤ ይከንፋል... ይበራል
ሺዘጠኙን በቅጡ ሳንኖር፤ ፪ሺ ሠፍቶ ያተራምሰናል
እሱ ምን አለበት..... እንዳባይ ይነጉዳል...
እኔ አለሁ እዚ በሀሳብ የምርድ
አርባዬን ቀርጥፌ አፋሽ የሆንኩ አመድ

እና እታባዬ.....

የታል ታድያ ያ ልብ የነገርሽኝ ቀድሞ
በ40 ዘመኔ የማገኘው ቆሞ... (አልያም ተጋድሞ)
ከብትንትን ኑሮ የሚገላግለኝ
ከ40 ልብ ህይወት የሚያሰናብተኝ

የታለ እታባ?? ... የታለ??...
👆👆👆👆👆 writer...ናትናኤል "አብራራው G12"
ውዴ
ዝምታሽ ቢጨንቀኝ ቴክስትሽ ቢርቀኝ
ስልኬ ያለልማዱ ብሬን ቢምርልኝ
አፌን አሞጥሙጬ ልነግርሽ ቆረጥኩኝ

እቱ የኔ አበባ....

ዝምታሽ ከባድ ነው ሆድን ያሸብራል
ቀልብንም አርቆ አንጀት ያላውሣል.....

ብዬ እንዳልልሽ.... ብዬ እንዳልልሽ

ቃላት አይገዙ በቂ ስንኝ የለኝ
እኔም ካንቺ የባስኩ ስንኞች የከዱኝ

ብቻ....

ጀማሪ መሆኔ እንዳይነቃብኝ
ኝ ኝ ኝ ..... እያልኩኝ
መግጠሙ ደብሮኝ
የሆዴን ሣልሸና ልተኛ ወሠንኩኝ።
(እባክሽ አደራ እንዳትስቂብኝ.ኝ ኝ ኝ..)
ኖታ
እዬዬ

ከውዶቹ መሃል አንድ ሰው አነሰኝ
ሀዘን ሆዴ ገብቶ እያንሰፈሰፈኝ
ጠቆረብኝ ውስጤ ልቤም ጨላለመ
ያሸከምኩት ተስፋ በአፈር አከተመ
እዬዬ ለራሴ እዬዬ ለሃገሬ
ታናሼ ሲቀድመኝ እኔ ተገትሬ
እዬዬ ለቋሚ ውዱን ለሸኘ ሰው
ከተመረጠማ የአብስራ ድንቅ ነው

ሰይፈ
ግዝት
አድምጡኝ እንጂ አትስሙኝ

በክፋት ጥላቻ በህይወት ገላችሁ
ከነመፈጠሬም በቁሜ ረስታችሁ
የአፈሬን ሳጥን በቅርቡ አይታችሁ
እንዳታለቅሱልኝ ...
ኻላ እንዳላዝንባችሁ
አትክልት አይደለሁ እንባችሁ አይረባኝ
ከሞት አለምልሞ ህይወት አይዘራብኝ
እንዲያው ከንቱ ድካም እንዳይሆንባችሁ
መኖሬን ከድታችሁ ሞቴን ካመናችሁ
ያኔ... በበድኔ ዙሪያ እንዳላይ ከባችሁ
በቁሜ እያለሁ ይኸው ገዘትኳችሁ።
እንዳታለቅሱልኝ...!!!
ኖታ
👍1
ሁለት አለሜ

መጀመሪያ ሳይሽ ልቤ ምቱ ጠፋው
ግጥሜ ተበላሸ
ቀለሙ እየሸሸ
መጀመሪያ ሳውቅሽ ሰው አለኝ የሚለው
ቃልሽ ልቤን ወጋ
እንዴት ካንቺ ላውጋ

ክንፍ ያለኝ ይመስልጊዜን መራመጃ
ነገን ካንቺ ከረምኩ የዛሬዬን እንጃ
ጸዳልሽን አየሁ ከጎኔ ሲበራ
የቆዘመ ገጼን በሙቀት ሲጣራ
ደሞም ደስስ እያለ መልሶ ሲያስፈራ
እኔና አንቺ ብቻ ካለንበት ቦታ
ከቦን ያለም ሃዘን ከቦን ያለም ሆታ
ቅጽበታት ደምረን ስናረገው አፍታ
ዱካክ እንዳጠረው እንቅልፍ አልባ ጊዜ
ባንኖ መታ ልቤ ባንቺው ስልት አባዜ
ሁለት አለም ኖረኝ
አንደኛው የንቃት ሌላው የትካዜ

ሰይፈ ተማም 2010
ለመስራት

ለመጨረስስ አልሰራም ለመስራት ልጨርስ እንጂ
ተጨርሶ ሲመረቅ እንደሚታደስ መንገድ
ስካሩ ጠፋ ሲባል መልሶ 'ሚንገዳገድ
እንኳን ተሻለህ ሲሉት እንደሚያቃስት ህመመኛ
ለመጨረስስ አንስራ ለመስራት እንጨርስ እኛ

ሰይፈ ተማም 2010
ከመሬት ነኝ

መሬት አይደል መነሻዬ
መሬት ያጣሁ መሬት ሁኜ
መነሳትን ተጠይፌ
የወደቅኩኝ ተንሳፍፌ
እኔም ራሴ መሬት
ለመብቀያ ያበቀለኝ
ከመሬት ነኝ?
ከምሬት ነኝ?
ከምር የት ነኝ?

ቁንጥር አፈር ዘግኖ በእጁ ካበጃጀኝ
ቁንጽል አንቀጽ ጠቅሶ በእጁ 'ሚያስፈጀኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከመሬትም መሬት
ሲረማመዱብኝ እንቁዬን ደብቄ በቀን እኩለ ሌት
ሲዘንብ እምቦካ የቋጠርኩኝ አለት
ሲያርሱ 'ምበረበር
ሲበትኑ 'ምዘር
የማያዳብረኝ የሰጡኝ ምርጥ ዘር
አለቴን ገድዬ 'ማረገው አፈር
ጨረቃን ጋርጄ ፀሃይ የምሰፍር
ፀሃይ በዛ ብዬ ደሞ ምንጨረጨር
ህዋ ላይ ተጥዬ የማርፍበት የናፈቀኝ
አዎ መሬት ያጣሁ መሬት ነኝ

ቀማሽ ምላስ ሰጥቶ ጣ'ም 'ሚያስቆጥረኝ
ጣፋጭ ስኳር ነስቶ በጨዉ ሲያስመርረኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከምሬትም ምሬት
ወዳጄ ስሞታ ወዳጄ ጣ'ም ሃሞት
የማያጣኝ ከቤት
የማያጣኝ ከሬት

ብሶት የወለደው ብሶ ያንገሸገሸኝ
ጣ'ም ያጣሁ ምሬት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት

መሬት ምሬት ምርየት

መሬቱ ሰው አለው
አለው የሰው ኩሩ
'ራሱን እማይነጥል
ከዱሩ ከአፈሩ
ሲጠብቃት ኖሮ
ከሷው ነው አዳሩ
ይኸም ሰው ጨፍግጓል
መረሮታል ጠአሙ
መጣፈጥ ጠፍቶታል
መልኩም ሆነ ስሙ
ለአንድ ቡሃቃ ሊጥ
20 ሺ እያሰሙ
ከምር ወደየት ነው
ከየት ወየት መንገድ
(ከሰከሩም እንኳን)
አይቶ ገምቶ ነው
ኋላ መንገዳገድ
ወይ የሚያቅፉ መስሎ
ትከሻ መላመድ
ወይ እራስን መብላት
ከመሬት መዋደድ
የምን ቆሞ መሄድ
የምን ሄዶ መቆም
በራስ ቤት መታሰር
ቂም ይዞ እንደመፆም
ለመዋደድ ነቅቶ
በፍቅር ነው መሾም
እንዳሹት ከምታሽ
እንደ ደማከሴ
የት እንዳለሁ ሳላውቅ
አድር ይሆን ፈውሼ?

ያለት ስንጣሪ
ከምድር የቀረፀኝ
ቅምሻ ፍርፋሪ
ኮምጥጦ አገረሸኝ
አይኔን አስጨፈነኝ
ኸረ ከምር የት ነኝ?

ታውሮ ሚመራው
መንገዴን ነጠቀኝ
እኔጠፋሁ ልበል
ካለሁስ ወዴት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
... ሆኜ ካለሁበት

ሰይፈ ተማም 2010
👍1
በጾሙ

ልቤ ጠረጠረ ነገር ነገር አለኝ
ከተኩሎቹ መሃል ፍየል ቢጤ ባገኝ
ስጋዋም ወተቷ መድሃኒት ነው አሉ
ዘምዘም እጠጣለሁ ሲያሻኝ ከጠበሉ
ወይ እታከማለሁ ደሞ በዶክተሩ
ልቤ እንዲጠራልኝ እንዲቀለኝ ቂሙ
እላለሁ ተኩሎቹም አብይን በጾሙ
አብይን በጾሙ አብይን በጾሙ

ሰይፈ ተማም 2010
ልወዳት እየጣርኩ ነው

ቁንጅናዋን አይኔ አክብዶት ከልቤ ጋር ከመከረ
ከጉያዋ የፈለቀ እሳት ውስጤን ካኮማተረ
አቅሜን የያዘችው ቢመስላት እንዳሻት የምትዘውረው
በቀና ልብ ተንደርድሬ ልወዳት እየጣርኩ ነው

ከፍታ ቢሰማው ቀልቧ የወጣ መስሎት ከማማ
ወስኜ ነበር ልረሳት ክብሬን እንዳላስቀማ
ዛሬ 'ምማትር ዞሬ ገጿን እማይ አጮልቄ
ልመራት እንጂ ደፍሬ አይደለም ብርሃን ናፍቄ

እዩልኝ ሰዎች ልብ አርጉ
ድብቅ መናፍስት ካሉበት በዐይኖቿ ሲበረግጉ
ከጠረኗ እጣን ወጥቶ ንቦች ሲውረገረጉ
ከአናብርት ቆዳ አብልጠው አዳኞች እሷን ሲወጉ
ልብ አርጉ ሰዎች እዩልኝ
የወፏ ዜማ ቢያቅታት ንፋስ ስታዜምብኝ
ከአሳ ቀድሞ 'ሚበላሽ ፀዳሏን ስትበትንብኝ
ከረግረግ ጨፌ በጥሼ በጣቷ 'ምታሾፍብኝ
እዩልኝ ልብ አርጉ ሰዎች
በየደፍ በአፀድ በጥጉ ስሜን ቆልላዋለች
ደሞም በውበት ሰክራ ምኑምኔ ትላለች
የልቧን መንፈቅ ከልላ በቀሪው ትጫወታለች
ቁማር መሰላት መዋደድ
የሆነ ስሜት አስይዞ የሆነ ስሜት ደብቆ
ያልሆነ ንዴት መናደድ

ይልቅስ አቅሜን እንዳሻት ቢመስላት የምትዘውረው
እኔስ በቀና ልቤ ልወዳት እየጣርኩ ነው


ሰይፈ ተማም 2010
አትመሪ
ውዴ....በቀረብኩሽ መጠን..
የገላሽ ጠረኑ--የገፅሽ ፍካቱ
የምናብሽ ርቀት--የሀሣብሽ ግዝፈቱ
ባንድነት እብረው ያሸነፉኝ ለታ
ሱባኤ ገብቼ
ስህለት አስገብቼ
እኔ አንቺን ማግኘቴን ያላወቁ ሁሉ
ውበትሽ ማርኲቸው ደጅሽ ይቆማሉ
ስንት እድሜ ከፍዬ- ከልብሽ እንዳደርኩ
ስንት ህልም ሠፍሬ- አንገትሽን እንዳቀፍኩ
ሀቁ ካልገባቸው
"እውነት" እንዳያዩ ውበትሽ ከሆነየጋረደባቸው
እስኪ አትኲኲይ እትመሪላቸው
ወጡን ወጥውጪና እንጀራውን ጋግረሽ
ሣትተጣጠቢ ውጪ ከነ ሊጥሽ
ነጩን ጥበብ ቀሚስ አትልበሽው ይቅር
ጫማም አትጫሚ ሒጂላቸው በ'ግር
ፊትሽም ይጠውልግ ፀጉርሽ አይጎንጎን
እድፍ ይሁንበት አታፅጅው ገላሽን

ይቅር እትመሪ
ይደበቅ ይከለል ውበትሽ አስኩዋሉ
ያኔ...
ገፅሽን አካልሽን የቁዋመጡ ሁሉ
'ጣይ እንዳየው ጤዛ ምኞታቸው ረግፎ ካይንሽ ይርቃሉ

በዚህ ከተስማማን
ከተመቸሽ ላንቺ ከተመቸኝ ለኔ
በመጠውለግሽ ልክ በድምቀትሽ መጠን እምዳይሠፍርሽ
አይኔ
ከሁሉ አስቀድሞ ያላንዳች እኩያ
ያላንዳች አምሣያ
ከከፍታው በላይ አኑሮሻል ልቤ!
እናም እልሻለሁ፦
"ስጋ"ን ላፈቀረ "ገፅ" ላደነቀ መንገደኛ ትውልድ
ፈራሹን ሠጥተነው
እኔና አንቺ ብቻ ነፍሳችን ይዋደድ።.

ዳግም ተካ