ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from ኩነት - Kunet
Live Painting & Poetry Night

Gojo Bar presents you a live painting and poetry night along with other entertainments. The show will be hosted by Gitem Sitem's co-host Seife Temam.

Saturday, July 17
7PM - 8PM

Hill Bottom Recreation Center

Entrance fee is ETB 100.

#July_17_21 https://t.me/Kunet_Sitem

#Gojo_Bar #poetry #livepainting #gitemsitem #seifetemam #Hill_bottom
አዝኛለሁ…
በልፋቴ በድካሜ ባቆየሁት
ሳቃችንን‐ ተንከርፍፎ ስላየሁት!
አዝኛለሁ…
ለተዝካሩ ለሙሾው ድንኳን ተክሎ እንዳይወጣ
ዕድሜያችን‐የኩርፊያ እንኳን ትዝታ ቢያጣ።
የደስታ የፈገግታ አሻራ ባናስቀር ደርሰን
እንዴት
በባዶ እንዲያው ዝም ብሎ ያለ እድሜው፣ እድሜ ያፍርሰን!

አዝኛለሁ…
ቀና ችን‐ቀን ሳለ ሳይዳምን ፀሐይ ባይወጣበት
እንደሌላው እለት ወዝ ስለታጣበት።
ፀሐይ ያጣ ተብሎ ቀን አይሰረዝም
እድሜ ላይ ይጫናል ታሪክ እንዲያስረዝም።

ሕይወታችን‐ድግሱ ውብ ነበር
እንኳን ቁም ነገሩ ዋዛና ለበጣው
አዝኛለሁ…
ከተነሳንበት ተመልሰን ሄደን ፈልገን ስናጣው።

©️ያዴል ትዕዛዙ
Forwarded from Poetic Saturdays
ሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ የመጀመሪያ ዙር ከሰኞ ሐምሌ 12 እስከ ቅዳሜ ሐምሌ 17 ድረስ በኦንላይን ይካሔዳል።

ሀገራችንም በድንቅ ልጃችን "ሰይፈ ተማም" ትወከላለች!

#CASP #CupOfAfricanSlamPoetry #CASP2021 #CASPEthiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የመክፈቻው ቀን ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡

የ33 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮኖች ይሳተፉበታል፡፡

ከነገ ጀምሮ የሚጀምረው ውድድር ቅደም ተከተል ምድብም ዕጣ ወጥቶ ነበር፡፡

ሻምፒዮናችን Seife Temam 9 ሀገራት ባሉበት የመጨረሻው ቀን ምድብ የደረሰው ሲሆን የመጀመሪያ ውድድሩን አርብ ዕለት ያደርጋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ፣ ሞሮኮ ፣ ሞዛምቢክ ፣ ኬፕቬርድ ፣ ማዳጋስካር ፣ ማላዊ ፣ ኒጀር እና ቡሩንዲ በዚህ ምድብ ይገኛሉ፡፡

ቻድ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ላይ አሸናፊ ሻምፒዮን የነበረው እና በሞት ያጣነው ሴኔጋላዊው አልፋሩቅ ም ታስቦ ነበር፡፡
________
ውድድሩ ነገ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡ በፌስቡክ ቀጥታ በመግባት እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡

በአካል መገኘት የምንችል ደግሞ ቀጥታ ስርጭታችንን ከሽፍታ ነውና የምናደርገው ብቅ ብላችሁ ደመቅ ደመቅ እናድርገው!

Coupe d'Afrique de Slam poésie, CASP Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም #casp2021 #CaspEthiopia #slampoetry #Africa #Ethiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የ ሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ በሁለተኛ ቀን ምሽቱ በመጀመሪያ ምድብ የሚገኙ ሀገራት ተወካዮች ተፋልመውበት ተጠናቅቋል፡፡
በውጤቱም
Diaw Fall - ከ ሞሪታኒያ 🇲🇷- በ 70.2 ነጥብ 1ኛ ደረጃ
DJ Huba - ከ አንጎላ🇦🇴 - በ 64.5 ነጥብ 2ኛ ደረጃ
Bokon - ከ ቶጎ 🇹🇬 - በ 63 ነጥብ - 3ኛ ደረጃ
Aladin - ከ ጋቦን 🇬🇦- በ61 ነጥብ (ከ80) 4ኛ ደረጃ ን

በማግኘት ቅዳሜ ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ግጥሚያ ያለፉ የመጀመሪያዎቹ 4 ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
----------------
ነገ ማክሰኞ ሐምሌ 13 በተመሳሳይ ሰዓት (ማታ 2፡00) በሚቀጥለው ውድድር የመጀመሪያው ዙር ሁለተኛ ምድብ ሀገራት ተወካዮች ይፋለማሉ፡፡

በዚህ ምድብ ናይጄሪያ ፣ ቻድ ፣ ሞሪሺየስ ፣ ኬንያ ፣ ሴኔጋል ፣ ካሜሩን ፣ ጋና እና ጊኒ ቢሳው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሀገራት ያላቸውን ረጅም የግጥም ግጥሚያ ልምድ እና ባህል (poetry slam culture) ስናይ … ነገ ጠንከር ያለ ውድድር የሚታይበት ምሽት እንደሚሆን እንጠብቃለን!

በፌስቡክ ቀጥታ በመግባት ውድድሩን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!
#casp2021 #CaspEthiopia #slampoetry #Africa #Ethiopia Coupe d'Afrique de Slam poésie, CASP
Forwarded from Poetic Saturdays
በሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ምድብ ግጥሚያ ዓርብ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ከምሽቱ 130 ጀምሮ መተላለፍ ይጀምራል፡፡

በሽፍታ ሬስቶራንት ሰብሰብ ብለን ሻምፒዮናችን ሰይፈ ተማምን በመጀመሪያ የውድድር ተሳትፎው እንደግፈው!

The final group of the first round matches of the second edition of the African Cup of slam poetry happens on Friday, July 23, 2013 at 1:30pm.

Join us at Shifta Restaurant for a watch party, as our champion Seife Temam performs his first performance of the competition.

#CASP2021 #CASPEthiopia #SlamPoetry #Africa #Ethiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ ሁለተኛ ዙር ውድድር ቅዳሜ ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከ 9፡00 ጀምሮ በኦንላይን ይካሄዳል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከየምድቦቻቸው ያሸነፉ አራት ሀገራት … በአጠቃላይ 16 ሀገራት በዚህ ዙር ይፋለማሉ!

እስታሁን 12 ሀገራትን ለይተን አውቀናል፡፡ ቀሪዎቹን አራት ሀገራት (ኢትዮጵያ ከምትወዳደርበት ምድብ) ዓርብ ላይ እናውቃለን፡፡

በ GUAC-ON ሬስቶራንት ደመቅ አድርገን እንጠብቃችኋለን! ብቅ ብቅ በሉና አበረን እንከታተል፡

The second round of the African Cup of Slam Poetry Competition will be held online on Saturday, July 24, 2013 starting at 3፡00 pm.

Four countries from each group on the first round, 16 countries will battle in this second round!

So far, we have 12 countries secured their spot on this round. The remaining four will be identified on Friday at the final group of the first rounds.

Join us at GUAC-ON for a viewing party and closing celebration of the virtual rounds of the second edition of the African Cup of Slam Poetry!

#CASP2021 #CASPEthiopia #SlamPoetry #Africa #Ethiopia
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
ክረምት እና ንባብ
📅 ሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 10 2013
📍 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ ኢክላስ ህንፃ
🙏 Siti

አዘጋጁ ዋልያ ኢቨንት ሲሆን የዝግጅቱ መሪ ቃል "ንባብና ክረምት" ነው።


የመጻህፍት አውደርእዩ ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 10 በሚቆይበት ጊዜ የተለያዩ መሪ ቃሉን የሚያጎሉ ዝግጅቶች በእያንዳንዱ ምሽቶች ሲካሄዱ ዋና ዋናዎቹም የሚከተሉት ናቸው
_ቁጥራቸው ከአስር በላይ የሆኑ ነባርና አዳዲስ ደራስያን መጽሐፎቻቸውን ያስመርቃሉ።

እንደ ደራሲ ሐይለመለኮት መዋእል ያሉ አንጋፋ ጀራስያን ልምዶቻቸውን ያካፍላሉ።
ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ከአንባብያን የተለገሰውን መጻሕፍት ለተለያዩ ገጠርና ከተማ ለሚገኙ አስር መጻሕፍት ቤቶች ያስረክባል።
ግጥሞች ለአባይ በሚል ርእስ ልዩ የስነጽሑፍ ምሽት ይደረጋል። በዚህ ዝግጅት ከነባር ገጣምያን መካከል የባለቅኔ ጸጋዬ ገብረመድሕንና ነሰይፉ መታፈርያ ፍሬው ግጥሞች አሁን ካሉት ደግሞ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራና አንዱአለም አባተ (ያጸደ ልጅ) ይሳተፉበታል።

ከቀናት መሃከል በአንዱ ወጣቱ ደራሲና የፍልስፍና ሰው መሐመድ ቡርሐን ዲስ
@eventsethiopia
Forwarded from Everted (Kalkidan Everted)
Yes, that.
Those days
You know,
Where your lungs feels like a solitary confinement with four people in it breathing over your shoulder
You know,
Where your eyes are sensitive to light,
Any light
Light coming from your phone, the window, fluorescent tubes, smiles and kind hearts
You know,
Where you can taste the rust against the weathering gears in your brain
Where you hear others calling out your name but you have to blink hard a couple of times
To make sure whether you’re falling asleep or if it’s really coming from across your table
You know,
Where you don’t want to get out of the taxi
In fact, you didn’t want to get in, in the first place
In fact, you wanted to stay in
In your room
your bed
your mind
your dream
your skin
You know,
.
.
.
Don’t you?