ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Seifu
የሐውልት ላይ ጽሑፍ
• • • • • ፨•••••••••••

"ጸሐፊው በምን አረፈ?''
ተብላችሁ ብትጠየቁ
ኑሮውን ስትዘክሩ፣

እንዲህ ብላችሁ መስክሩ…

ጸሐፊው ነቢይ ነበረ፣
ብዕሩ ቀለም ተሞልቶ
ልቦናው በሀሳብ ታጭቆ፣
እንዲጽፍ የተፈጠረ።

አንጋሹ ቀቢው በርክቶ፣
ከፍ ከፍ አድራጊው በዝቶ፣
በእብሪት እንደተበተ፣
ጥቂት መስመር እንደጫረ፣

በሆነ መድረክ ግረጌ፣
ጭብጨባ ጨፍልቆት ሞተ።
•••••••••
•••••••••••••
ቴዎድሮስ ጸጋዬ
"ነፍሰጡር ስነንኞች" የግጥም መድብል
ምን አገራረፈን?
ዘመን ፈልፍሎብህ፥
ጅራፍ የጨበጠ፥ ክፉ ተጣማሪ
በተቀኘኸው ልክ፥ ገዳይና ማሪ
መቀበል ያስጠቃል፥ አቀብል አዝማሪ።
..........አቀብል...እንካማ...
.....||ዐይን ሰርግ ሊሄድ፡ ሲኳኳል ቆቡ ስር
.....ማን ይየው የታቹን?
.....ደምቶ ማለቁ ነው፡ አፍንጫ በነስር።||
የሚያዘንቡብህን፥
ስንኞች ወጥረህ፥ በማሲንቆህ ቆዳ
የሚቀዱብህን ፥ አዙረህ ብትቀዳ
ጥያቄ እንደፈራ፥ ሰነፍ አስተማሪ
ምላሹ ጅራፍ ነው፥
አትቀበል ተወው፥ አቀብል አዝማሪ።
............አቀብል... እንካማ
.....||እንደአረፋ ሙክት፡ ልክ እንደዒድ በሬ
.....ሰርክ የሚያሳርደኝ፡ አለመሶበሬ||
የመንደሩ ወግ ነው ፥
ግንድ እየደበቁ፥ ንፋስ መማገሩ
አቀባይ እጅ እንጂ፥
ተሸካሚ ጀርባ፥ የለውም ሀገሩ
ብልጥ...ሁን ... እባክህ
ገንዘብ እንደሌለው አራዳ ቆማሪ
ሳትሰጥ ሳትቀበል፥
አየር ባየር ብላ፥ አቀብል አዝማሪ
............አቀብል... እንካማ
....« በሳቅ መፍረስ የሚል ፡ ፈሊጥስ ነበረን
..... ፈርሶ መሳቅ ደሞ፡ ማነው ያስተማረን?

©ረድኤት አሰፋ
Forwarded from Free talk🤓🙃
Victim #297

I looked at her, I see your reflection in her eyes,
I told myself you found another victim

The flicker of trust that you offer
The promises that you made, cuffed her
The hope that runs through her vain
I felt it,

Your momentarily satisfaction
Your endless need of validation
Your being prisoned her in terms of your condition

She feels obligated to satisfy your vanity
Sadly, the notion about one day you will be hers made her heart aches
Yet she killed parts of her to keep you smiling

Then I saw you, In your eyes there is only illusions of her,You never sure

Even when she's standing wearing red dress, bleeding love in drizzling night
She fall to be enough in your eyes,


@freetalkk
🦋🦋🦋
We need you
And by we, me and you
We need you
Not for me not for you
But for us by the bayou
Lost in life lost in the woods
Craving signs hope in words
Hooked up in lust longing for a fix
Crumbling, Crawling, souls entangled
Not up front or behind
Side by side
We need you
Me and you
To stand still against the wind roaring towards us
Or we can kiss
And forget you and I, if that’s what you please
That is what I please
Us
©️YeGetanehLij
Grand Eliana Hotel will host an exhibition and cartoon book launch titled Funteziya on Friday 04 May 2021. The event will showcase the launch of a cartoon book titled Funteziya by Alex Terefe. Doors will be open the whole day until 7:00pm.

@GitemSitem
የቃል ስፍር

ንፋስ ከብርሃን ይረቃል
ያ'ንተም ቃል!
ከነፍሴ ማሳ ይፀድቃል
የንፋስ መንገድ
የብርሃን ሞገድ
ቃል ተመስሎ
ውበት ተኹሎ
ሲገለጥ በተስፋ አምሳል
ካንተ እኩል ይተካከላል
እምነት ባንተ ይበረታል
ኹሉ በቃልህ ይረታል

እኔም!

©️መንበረማርያም ኅይሉ
መንቢ የሎዛ
Pain augments the depth within my poems
Peace of mind lets my words breathe
I want to keep writing
I must
Somedays I will tell you about my bruises, the tears I can’t cry away, the grief pressing on my chest, and the breaths I hold to punish myself
Other days I will tell you how life is so good with a cup of tea in your hands, love in your heart, yellow before your eyes, sun kisses on your skin, and music in your head
And dear reader,
I don’t mean to betray you by the latter
I will always remain a poet
In peace or in pain.

©️Kalkidan Getnet
Everted

https://www.facebook.com/Everted

https://t.me/Everted
Shifta presents Gitem Sitem
an open mic circle of fun and poetry.
on every first Wednesday of the month with your hosts Heran and Seife.

We have very simple rules:
1. Sign up online https://forms.gle/oEbMTixhnKu4HKox7 or by the gate prior to the event
2. 5 minute per performer
3. Be respectful to the performers and all beings around you
4. Be you
5. Make sure you follow all the precaution measures for Covid 19

https://www.facebook.com/gitemsitem

ሽፍታ የግጥም ሲጥምን የክፍት መድረክ ክበብ አቀረበላችሁ!
ረቡዕ, ግንቦት 25 ከ 1 ሰዓት ጀመሮ በሽፍታ
ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ መጻሕፍት፣ የቁም ኩምክና፣ ስዕል እና ሌሎችም አዝናኝ የጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ።
ስራችሁን ለማቅረብ ማስፈንጠሪያውን ተጠቅማችሁ በምታገኙት ቅጽ ተመዝገቡ! https://forms.gle/WveKjAsZ5PBx9MVr9

https://t.me/GitemSitem
#የመጽሐፍ_ምርቃት
🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊
#የሞት_ጥቁር_ወተት
የግጥም መድበል
በተስፋኹን ከበደ
🎉
ኑ አብረን እንመርቅ
📍
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
🗓
ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ኀሙስ በ11:30
Forwarded from Solitaire
Our dreams are wet contrary to our realities.

To a habit i couldn't left completely
Like talking in darkness
Like Crawling back to a lullaby
Like running to the water
Because sometimes that's how i remember to feel.

And to the things i 'almost' have
Like the chatter of a wind
The enchant of a river
The laughter of a child
I wanted to tell them no,
I'm not nostalgic, I don't have anything to shed for a different time continuum, yet everything for a different space continuum.
#አንተ_ማነህ ?
ከመፍራት የሚሻል መፍትሄ
ከመትረፍ የሚዘል ህላዊ
ከመትረፍ የሚገዝፍ ፍፃሜ
ከመንገድ የማይጠም መንገድ
ከሰው መስማሚያ መውደድ
ከአገር የሚገዝፍ ጥበብ
ታስሳለህ ?
አንተ ማነህ ?
_
ፈጥሮ ጨርሶኻል ወይስ ራስህን ትፈጥራለህ ?
አንተ ማነህ?
ልብህ ምን ይልሃል
ሰው ሰበረህ ? አሻገረህ ?
አፈዘዘ አደመቀ ?
በሰው ተሰራህ ወይስ ፈረስክ ?
በረርኩ ስትል አነስክ
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ? ወዴት ነው የምትሄድ ?
_
አንተ ማነህ
ተደሰተ ሲሉህ ምትነደው
ፈፀመ ሲሉህ ምጀምረው
አፈረሰ ሲሉ ምትገነባ
ፈገገ ሲሉህ ምትባባ
አንተ ማነህ ?
_
ንጉስ ነኝ ባልክ ማግስት
በጥበቃ ከበር ሚመልሱህ
ዙፋንህን ወንበር የሚሉት
አንተ ማነህ ?

ደምና ላብህን እንዲያልፍልህ ብት. ገብር
ዜና የምትሆነው ስት ሰበር
አንተ ማነህ ?

መደዴ እየጠሉ
ከመደዴው አንሶ መኖር
ብዙ ዘርቶ እፍኝ መልቀም
በክብ ጥያቄ መታነቅ
እፍኙንም ማስነጠቅ
የምር ማነህ ?
_
ብትኖር ትጠቅማለህ ?
ብትሞት ታጎላለህ ?
እህል ከመጨረስ
አልጋ ከመከስከስ
ፍራሽ ከማድቀቅ
ድንጋይ ከማሞቅ
ራስ ከመውቀስ
ትዘላለህ ?
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ?
_
_
ያስፈራሃል ይህ ሁሉ ጥያቄ
ያነድሃል____ ይህ ዕድሜ
እደርሳለሁ ያልከው እንኳ ልትደርስ
መታጠፊያው ራሱ የጠፋህ
አንተ



?
_
_
ግንድ ነኝ ብለህ ስትወጣ
____ሲቲክኒ አከልክ ?
የሰፈር ምላስ መሞረጃ
ጥርስ መጎርጎሪያ ሆንክ ?

ማነው የፈጠረህ
ለምን ነው የገጠመ ታውቀዋለህ ?
ምን ያነድሃል ?
ምን ያፈዝሃል
ምን ያቀዝሃል
ምን ያስሮጥሃል .
_
_
ህልም ምንድነው ? ልብ እያፈሰሰ
ሰላም ምንድነው ? ሩቅ ካላስኬደ
ደም ካፋሰሰ ' ጠላት ' ካስለቀሰ

መንገድ ምንድነው ? ወረት ።
ተጓዥ እያዩ መቅረት
ከራስ መራቅ
ከሰው ለመድረስ
"የሆነ ሰው ለመሆን ' ያልሆነውን ማሰስ ?




ማነህ ?
__
በቸከ ቀን
በቸከ ህይወት
ወረቀት የሚያሰኝህ
መፅሐፍ የሚያስገልጥህ
ውስኪ እንደመቅመስ
ሴት ከንፈር እንደመንከስ
ወገብ እንደመጨረስ
በቸከ ህመም
በቸከ ወረቀት የሚያስቸከችክህ
አንተ ማነህ ?
_
የእሳት ግለት
የበረዶ ብርደት
የፍጥረታት መሞት መራባት
መባላት
የእግዜር ዝም ማለት
የሚያስጨንቅህ ?
አንተ ማነህ
ምንድነህ
ወዴት ነው የምትሄደው ?

#1ዱ
©️አንዱ ጌታቸው
Forwarded from LinkUp Addis
Busara Championship is starting on 19 June 2021 at Goethe Institut. The event will mainly feature three games in one srage bringing young and talented players together on one court. The games that will be featured at the event will be Joteni (Foosball), Gebeta and Busara. Training will be provided for those who do not know how to play the games. For more info about the events, go to: https://bit.ly/3v1b5Dv.

Download and enjoy the June 2021 edition of LinkUp Addis: https://bit.ly/34zMpY5. @linkupaddis
ዓለም
'የለም!'
ብትለኝም
እንደው ርዕስ ሆኜ
'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
የት አገኘሽው በሉልኝ
የታል ዱካ ፈለጉ

ምናልባት ስፋቷ ነቅቶ
ምናልባት ንቃቷ ሰፍቶ
አሻራዬ (ash-አርዓያዬ) ተገኝቶ
መንበሬን ያመነች እንደሁ
እንደኖረ መንበር አጥቶ
'አለም የለም ለማለት ማን ነበርሽ አንቺ!' በሉልኝ
በዓለም
ላለም
በሙሉ
የሄድኩበት ላይ አብሩልኝ
እንደው እን'ዳጋጣሚ
እግሬ ያረፈበት ላይ
ይረግጥ እንደሆን ገጣሚ
እንደው እንደ ዕድል ሆኖ
(ክፉ ዕድል)
'መምህር' ይደግመው እንደሁ
የለፈፍኩትን ቃል ዘግኖ

እንዲገለጥለት በፈለገው መጠን
ለስንቱ ተገልጧል እስኪገነጣጠል
ብላችሁ ንገሯት ለዝ'ች ሟርተኛ ዓለም
መኖር ለምትሰፍር ስፍር ለምታኖር
በዘርና ቀለም!
የለም!!!
የለም!!!
እንደውም ምንም አትበሏት
ብጨልምም ብበራባት
አልነበር
'አለው' ለማለት
እንድትነቃ እንጂ ወደ 'ውነት
እንድትቀና እንጂ ከጥመት
የላ የላ ዝም በሏት እኔው ላውራት

ዓለምዬ ዓለም ብርቁ
የቱ ነው የግብርሽ ጥድቁ
እንዳንቺስ ሆኖ ሳይነቁ
መኖር ምንድነው ስንቁ?

ጽልመትሽ ብራ'ን የጠላ
ብርሃንሽ ጽልመት የከላ
'አለ'ምሽ መኖር የፈራ
'የለም'ሽ ተኑሮ ያልጠራ

'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
ከየት ተገኘ ዓለሜ ያለመኖሬስ ፈለጉ
[የዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለ መኖሬስ ፈለጉ
ያ ለመኖሬስ ፈለጉ
ያ ዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለመ ኖሬስ ፈለጉ. . . ]
. . . ዱካዬን ብት'ደብቂም
ባለሽበት ሁሉ አለሁ
መንበሬም ካነበረሽ ነው!
የሚያኖርሽ እንደኖረው
አለም - አለሁ!
ዓለም
አለሁ!
አለማለሁ!

©️ሰይፈ ተማም
#የሞት ጥቁር ወተት
የግጥም መድበል
📚📗📒📕📚
የመጽሐፍ ምርቃት
ኑ አብረን እንመርቅ . . .
🗓
ሰኔ 03/2013 ዓ.ም
ኀሙስ በ11:30 ሰዓት
📍
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
🎙
#የዝግጅት አቅራቢዎች
ገጣሚ ነቢይ መኮንን
ገጣሚ ፍሬዘር አድማሱ
ደራሲ አዜብ ወርቁ
ተዋናይ መስከረም አበራ
ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ
ድምፃዊ ካሥማሰ
🎤
#ግጥም በውዝዋዜ
ገጣሚ ተስፋኹን ከበደ
ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን
#መድረክ መሪ
ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ
🎼
#ሙዚቃ
በኢትዮ ጣዕም የሙዚቃ ባንድ

#አጋዥ_አካላት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አ.ማ
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
አርትስ ቴሌቭዥን
ጃጃው አታሚዎች ኃ.የተ.የግ.ድርጅት
ማፊታ ዲዛይንና ዲኮር
ጃሎ ፒክቸርስ
Forwarded from Bae🎤🎤
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
A night out with a twist on an already unique frequency - angelic musical performances, sweet poetry, and a fascinating live painter. A night like none other full of soulful/expressive/underground vibes.

We can’t wait to see you at FreeSoul

When
Saturday, June 12 @ 7pm

Where
Olympia Heights (unfinished bldg)
Across from Dembel, beside the Deluxe furniture & Awash bank
@Betty_bae