ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Poetic Saturdays
ሠላም ሠላም ግጥማዊ ቅዳሜያውያን ወርሃዊውን የጥበብ ድግሳችንን ይዘን ብቅ ብለናል!
ከረጅም ጊዜ መነፋፈቅ በኋላ ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በፈንድቃ የባህል ማዕከል በአካል ተገናኝተን ናፍቆታችንን እንወጣ ዘንድ ደግሰናል፡፡
በአካል መገኘት አይችሉም? እንግዲያውስ በዙም ይቀላቀሉና!
ሊንኩም ይኸው! https://us02web.zoom.us/j/71147805916
እንደተለመደው ከ8 ሰዓት ጀምሮ ምዝገባችንን እንጀምራለን፡፡

አዳዲስ እና የራስዎን ፈጠራ ብቻ እንዲያቀርቡ ይመከራል
ለእያንዳንዱ አቅራቢ 5 ደቂቃ ብቻ ቢፈቀድም የፈለገውን ያህል ማቅረብ ይችላል።
ምንም አይነት የቋንቋ እና የይዘት ገደብ የለውም
ምንም አይነት የጥበብ ስራ ይበረታታል
ይምጡና የጥበብ ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ!
*** ጀማሪ እና አዳዲስ ፀሐፊያን ይበረታታሉ! ***
*Do not forget your mask!*
Hi Creative Addis, Poetic Saturday will be on this Saturday, March 6th, 2021 at Fendika Cultural Center after a long break from physical gatherings.
Can’t make it in person? Then join us via Zoom!
https://us02web.zoom.us/j/71147805916
ነጩ ፈረስ ማነው?

ከአድዋ ጦር ማግስት
በቆሰለ አርበኛ የተማረከ ሰው
እልፍኝ ውስጥ ሆኖ እንደዚህ ጠየቀ…
"ሲወጋ፣ሲያዋጋ፣ሲያጠቃን የነበር
ነጩ ፈረስ የታል?"
ይሄ …ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?
ነጩ ፈረስማ?!
ጦርነት ስትለፍፍ ፣ ድንበር ስትገፋ
መሬት ስትቆፍር ፣ ዱካ ስታሰፋ
ይቅርብህ እያለ ምክር ያቀረበው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ? ያ ነው!
ነጩ ፈረስማ!?
አይገባውም ብለህ ፣ አልተማረም ብለህ
እንደ ስፔን
ፖርቹጋል እንግሊዝ ተመኝተህ
አፍሪቃ ምድር ላይ ግዛት ልያዝ ብለህ
ሰውነቱን ንቀህ
በጥቁረቱ ስቀህ
በብረት ካቴና አስረህ ያደማኸው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ! ነው!
ነጩ ፈረስማ!?
ከኤርትራ ምድር መቀሌ አምባላጌ፣
ማን አለብኝ ብለህ
ስትገፋ ስትወርረው አይገባውም ብለህ
ውጫሌ ምድር ላይ
በቃላት ውስጥ መርዝ ለውሰህ ሰጥተኸው
እውነቱን
ተርጉሞ "እምምቢ" ያለህ ሰው ነው!!
ነጩ ፈረስ የታልል?
ነጩ ፈረስ የታልል??
ይሄ ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል??
ነጩ ፈረስማ!
ያንተን ስልጡን ሀገር
የሰለጠነን ሰው የዘመነውን ጦር ፣
የታጠቀን አረር
መትረየስ ሳይፈራ ፣ መድፉን ቁብ ሳይሰጠው
እምቢ ላገር ብሎ የተዋጋህ ሰው ነው!!
ነጩ ፈረስማ?!
ነጩ ፈረስማ!?.
ተደፈርኩኝ ብሎ ከሰሜን፣ደቡብ ጫፍ
ምዕራብ ምስራቅ ነቅሎ
የከፋ ዘመኑን ፣ የሆድ ስሞታውን
ተመደፈር በታች አቅልሎ አሳንሶ
ግማሹ በፀሎት ጨፌውን ነስንሶ
ግማሹ በወኔ ጎፈሬውን ነቅሶ
እንደ አንበሳ አግስቶ ፣
እንደ ነብር ዝቶ
በምታ ነጋሪት ሁሉም በአንድ ከቶ
አድዋ ምድር ላይ በጦር በጎራዴ የተጋፈጠህ ሰው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!!
ነጩ ፈረስ የታል??!
ነጩ ፈረስ የታል!??
ይኼ… ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?!
ነጩ ፈረስማ?!
የጣይቱን ምክር ያባ መላን መላ
እሺ ብሎ ሰምቶ በልቡ እያብላላ
የእቴጌዋን ምክር
ትዕዛዝ አክብሮ
የምትጠጣውን ምንጭ ከብቦ ቆጣጥሮ
"ውሃ ውሃ" ያሰኘህ ደንቆሮ ነው ያልከው.
አላወቅህም እንጂ
ነጩ ፈረስ ያ! ነው!!
ነጩ ፈረስማ…
ነጩ ፈረስማ!!?
እምነት በልቡ አስሮ
አንድነት አክብሮ
ፈጣሪውን ሰምቶ
ከራሱ ጋር ታርቆ
ጦርና ጎራዴ ባጭር ባጭር ታጥቆ
"ሆ…"ብሎ ሲመጣ "ኦ…"ብለህ ተኩሰህ
ሀገር ትኑር ባለ … ሀገር ትኑር ባለ
ሀገሩ ላይ ገድለህ
እሳት የሚተፋ ባሩዱ ሲያልቅብህ
በቀደመው ጥይት ቆስሎ የማረከህ
ደሙ እየፈሰሰ ውሃ ጠጣ ያለህ
አይገባውም ብለህ ንቀህ የደፈርከው
ንቀቱን ዋጥጥ አርጎ አንተን የማረከዉ
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነዉ
ነጩ ፈረስማ
መቀሌ አምባላጌ ዶግ አመድ አድርጎህ
በአድዋ ተራሮች
እፍረት አከናንቦህ
ባቆሰልከዉ ጀግና እፍረት እጅ ሰጥተህ
ማተብ ባታከብርም ማተብ እያሳየህ
እልፍኝ አስገብቶ አብልቶ ያጠጣህ
ሮምን የጣለ ዓለም ያከበረዉ…
የጥቁር ህዝብ ኩራት መመኪያ የሆነው
ለማረከው ግብር
ጥሎ ያጠገበው
የአድዋው ጀግና የቴዎድሮስ ልጁ
የዬሃንስ ወንድም የጣይቱ ባሏ
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያልከው
የጥቁር ህዝብ ኩራት ንጉስ ምኒሊክ ነው!!
ነጩ ፈረስ ማን ነዉ ???

©ሰለሞን ሳህለ
ተጎናበስኩ
ለክብሩ በጉልበቴ ምድር እየሳምኩ
ሰገድጉ
የነፍሴን አዳፋ በቃሉ አጠብኩ
አሰላመትኩ
የሁለት አገር ሰው አንድ እኔን አሳከልኩ
አከልኩ መሆንህን
አከልኩ ጉድለቴን
ጉድ የሆነ ዕለቴን

#ጁመዓ (ጅመት)
©ባንችአየሁ አሰፋ
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter – 15th March 2021 – is out now https://bit.ly/3tdZpN7

Featuring Superno a film by Abel Mekasha https://www.youtube.com/watch?v=aZOCdiR63rk

With so many exciting open calls, competitions, grants etc… there is something for all Ethiopian Animators, Architects, designers, AR & VR designers, Circus practitioners, Dancers, Digital artists, Events & Festival managers, Filmmakers, Graffiti artists, Graphics Designers, Illustrators, Journalists, Multi-media artists, Music Producers, Musicians, Photographers, Poets, Sculptors, Textile Designers, Video Makers, Visual artists, Writers

@artsmailinglist
Forwarded from ሁለተኛ
The amazing Andu Getachew at ጠላ አለ.

Come by this Saturday at selo craft tella to witness this talent.
Have a tella or two while you're there And enjoy board games with your friends.

@AndugetachewDnd
@huletegna
አንጎራጉራለሁ ለነፍሴ
እስቅበታለሁ ለጥርሴ
ነፍስ መክተሚያ አለው ሲሽትበት
ውበት ያጠምዳል እተገኘበት
አይንም ማረፊያውን ይሻገራል
ኮከብ አድማሱን ይማትራል ::
ለሁሉም አለው መሆን
ዝምታዬን ምን ይሁን !

©መቅደስ ሞገስ
The organizers send their apologies and will inform you about the new date, stay tuned
Forwarded from ሁለተኛ
Hey guys
We are sorry to inform you that the ጠላ አለ series tomorrow have been postponed to a later date.

Please stay tuned @huletegna
Forwarded from Bruh Club
Calling all Ethiopian artists: travel from Addis to Jinka for 10 days in May 2021 all-expenses paid and meet, connect, learn, exchange, aspire and empower with those residing in the towns we travel through. Astrobus 2021

www.bruhclub.com deadline is 12th April 2021

@artsmailinglist
ጠረንህ አሰረኝ
መአዛ አሰከረኝ
ተንገዳገድኩ ፣
ናፈቅኩህ
እንደ እናት እቅፍ
እንደመንሰፍሰፍ
እንደ መንዘፍዘፍ ፣
እንዲ መሆንን መች ተማርኩት?
ከእውነትህ ስር ነው ገባኝ ያደኩት ::
ከእምነት ወንጌል
ከህይወት ላይ ቃል፣
ይፈሳል ደጅህ
አበጃጀኝ ፣
ሰው አርጎ ሰራኝ
መንገዴን መራኝ ::
ናፍቆት አሰከረኝ
ተንገዳገድኩ
ናፈቀኩህ
እንደ መንሰፍሰፍ
እንደመንዘፍዘፍ
እንዲ መሆንን መቼ ተማርኩት???
መች ለት አወቅኩት ?
ቅፅበት ለዘላለም
ዘላለም ለቅፅበት ምንና ምን ናቸው?
ሳውቅህ አወቅኳቸው ::

©መቅደስ ሞገስ
የያዘች ይመስል
ምድርን በካስማ
ከመንደሩ አንስቶ
እስከ ዳር ከተማ
ያደናንቋታል
ሰው እየተሻማ

እንደደብሩ ማህሌት
ያለችው ሚሰማ
ማማውን ምታስንቅ
ከረባዳው ቆማ

ኧረ ማነሽ ልጅት
የማነሽ ኮረዳ
ያላወቀሽ አለ
ለቀየው እንግዳ
ድንገት ፊቴ ቆመሽ
እንዳትገቢ እዳ

ይሏታል
እንዝርቱን አሹራ
ይሏታል
ፈትላ ያንን ጥጡን
ይሏታል
ለሰራችው ሸማ
ይሏታል
ሸጠላት እርስቱን
ይሏታል
ባፈላችው ቡና
ይሏታል
በጣለችው ጠጅ
ይሏታል
ከሚስቱ አጣላችው
ይሏታል
ቀምሶት አንድ ወዳጅ

እቴጌ እቴጌ
ገብያም አትውጪ
አትምጭ ከቀብሩ
ዕቁቡም ይቅርብሽ
እድር ማህበሩ
ባይንሽ ሰዋይሙትብሽ
አዛኝ ሁኚ ሩሩ
ይላላክልሻል
ጠቅላላ ሰፈሩ

ኤፍሬም ገነነ©
"እንዴት ነው ግን ሳይንስ ተንሰራፋ በተባለበት አካባቢ አሉባልታ እግዜርን፣ ተፈጥሮንና ተጠየቅን የምትዘርረው?

ታዲያ ሰኞ ተከራክረዋቸው ሐሙስ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰለባ ይሆናሉ።

በዚያን ጊዜ ፖለቲካ ይደረጋል እንጂ በመረጃና በጥናት የተደገፈ ሳይንሳዊ ውይይት የለም።

ይፃፋል ይባላል እንጂ የሚረባ አይደለም።

በስነ-ፅሁፍ በኩል የነበረው የደሃነት መጠን አይጣል ነው። በኢኮኖሚክስ፣ በሶሲዎሎጂ እና በአንትሮፖሎጂ በሌሎችም መስኮች እጅግ ሰፊና ጥልቅ የሆነ የጥሬ መረጃ ጉድለት አለ።

አገሪቱ ችግር ቢያጋጥማት የነሲብና የአውቃለሁ ባይነት ውጤቶች ናቸው።

የዋሸሁ ከመሰለሽ ዪኒቨርሲቲ ሄደሽ የተጠናውን የጥናት መረጃ እዪ። ያሉት ጥናት ተብዬዎች እርስ በእርሳቸው ግማሽ እውነት፣ ቅጥፈትና ስህተት እንደ ማሚቶ የሚቀባበሉ እንደሆኑ መገንዘብ ትችያለሽ።

እነዛን መረጃዎችና ከዛም የጠለሉትን ፅንሰ ሀሳቦች ለመፈተሽ አዲስ መረጃ ካመጣሽ ወይም ይኑር ካልሽ ነባሩ ሀሳብ ስለሚፈርስባቸው አይፈልጉሽም።

በስህተታቸው የተዝናኑ ነበሩ።

ያልተስተካከለ መረጃ ከያዙ የባዕድ መፅሀፍት ላይ ሃሳቦችና ቃላት ተለቃቅመው ብዙ ግድፈት ይሰራል። ተሟጋች ጥሬ መረጃ ይዞ ካልቀረበ ሌሎችን መምሰሉ ከአሉባልታ የተለየ አይደለም።

'እንትና የተባለው የዚህ ሀገር ፕሮፌሰር እንትን በተባለ መፅሀፉ ስለ ኢትዮጵያ እንትን አለ' ማለት ምንም ማለት ነው። ከእንትን እና እንትን ብዛት ምን ትጠብቂያለሽ? የተፃፈ አሉባልታ እንጂ።

ስለዚህ አሉባልታ ስለምፈራና የስነ ዕውቀታቸውን መልክዓ ምድር (epistemological landscape) ስለምጠራጠር ለማናቸውም ግድ አልነበረኝም።

***
የስንብት ቀለማት
👍1
They say
a picture is worth a thousand words
But
a word creates thousands of wounds
They say
every picture tells a story
But they don't really know
how every word in a poem is stony
They say
words are powerful
They can create or they can destroy
They don't really know
how pictures create words in our head
how words can picture
what pictures can't capture
...
But in deed,
a picture is worth a thousand words
a word is worth a thousand words
if words were not invaluable

©Seife Temam