ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from LinkUp Addis
Gitmawi Kidame (Poetic Saturday) will take place at Fendika Cultural Center and online on Saturday 06 February 2021 from 2:00pm to 5:00pm. @linkupaddis
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
እነሆ
:
:
:

" ሰው ፍቅር ናፍቆት"

#በገበያ_ላይ_ዋለ!!
Join and share…………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
እኔ ...?
ስንዝር ታህል
ከፍ ብዬ ከምድር
መኖር ከቻልኩ ...
የውነት-የውነት የምር
ይህን ነኝ ..ያንንም
ክፉውን ..ደጉንም
--------
ከጀምበር ጀምበር ስዝዘል
ከደም-ስር ስር የምውል
ቕርብ ያልለሁ
ደሞ ሩቅም
መኻን የሆንኩ
የወልለድኩም
--------
(ከሞት) የመርረርኩ ርግማን
(ከህይወት) የጣፈጥኩት ምርቃት
ማርያም ድንግሊቷ
ደሞ ...ዘምማዊቷ
------
ከዘላለም ቀድሜ የነብበርኩ
ጨቅላ ቦቀቅላ አሁን የተወለድኩ
ከሳቅም ሳቅ ከጥርስ ያልወድደቅኩ
ከእንባም እንባ ግት ሆኜ ያልታበስኩ
ቆሜ ልሸና ግንብ (በብልቴ) የተደግገፍኩ
ያላጠባ ጡቴን በጨርቅ የሰበስብኩ
-------
ቅስናዬ ከመስጂድ
ሸኽናዬ ከቤተ ክርስቶስ
ያፈጀሁ ያረጅጀሁ ...
ዕለት ዕለት ስታድደስ
-------
በሲዖል ለም አፈር የተበጀሁ
በጀነት እሳት የተፈጅጀሁ
ከድቅድቅ ጨለማ የምቀብጥ
የብርሃናት ልዑክ እሳት የማምጥ
-------
አምላክነት ...
ልኬ አይሆንም
ሰውነትም ...
ከኔ አይገጥምም
ጽድቅ እና ኩነኔ
ተጠይያቂ ጥያቄ
ማን ነኝ፣ ምን ነኝ'ኔ ...
?

©ዳዊት ካሳ
የ እሳት ራት

እኔ የ ምወደው እሱ እሳት ይወዳል
ከ አጥንቴ ማግዶ ከደሜ አርከፍክፎ
ሰርክ ያቀጣጥላል
ፍም እሳት
ፍርሀት
እኔ እሳት ያስፈራኛል
አጥንቴ ሲማገድ ካለው ህመም በላይ
ደሜ ሲርከፈከፍ ካለው ስቃይ በላይ
እሳት ያስፈራኛል
የፈጣሪን ምስጢር በግልጥ ያወራኛል
ከምድር ከርስ ውስጥ የተቀበረውን
ካልፈነዳሁ እያለ ሚገነፍለውን
ጎመራ ይመስለኛል
ሲኦል ይታየኛል
የፈጣሪን ቁጣ
ሰዶም ወይ ጎመራ
የ ኤልያስን መስዋዕት
ጥልቅ ዘልቆ ሲበላ
ከገነት ደጅ ላይ እየተገላበጠ
ሰውን ከፈጣሪ ስላቆራረጠ
እሳት ያስፈራኛል
እሳት ነውር አያውቅም
ይሉኝታ አይዘውም
ይፋጃል
ያነዳል
ከነደደው እሳት ትንሽ ኩስታሪ
ከንፈሬ ላይ አረፈች
ወጣሁ ከፈጣሪ
ራቅኩ ከ አማልክቱ
ታላላቅ ሚስጥራት ስለተከፈቱ
የቃዬን መስዋዕት
የበአል ነቢያት ያነደዱት እሳት
ሞትን የተሳፈረ ሰረገላ ይመስላል
በሀሩር ሲያነዱት የብርድ መድሀኒቱ
ወበቅን ይወልዳል
ከደም ወዝ ቀላቅሎ መሲህ ያስጨንቃል
ማይታለፍ ፅዋ ለ አምላክ ይቀዳል
የፅድቅ ጥያቄን ፍርድን ይመሰላል
እኔ የምወደው እሱ እሳት ይወዳል
ከ አጥንቴ ማግዶ ከደሜ አርከፍክፎ
ሰርክ ያቀጣጥላል
ጠራኝ....
ፍቅር እና እሳትን እያመዛዘንኩኝ
አንድ ሁለት እርምጃ ወደ እሳት ቀረብኩኝ
ጉዴ
የጨለመን ምስጢር
የሰውነቴን ውስጠት
ያልተረጎምኩትን የመላዕክት ልሳን
ገሀድ የገለጠ የእሳት ብርሀን
ገላዬ ላይ አረፈ
ነፍሴ ተገረፈ
ሌላ ሚስጥር ወጣ
በ እርሱ የፍርድ ወንበር
ከ እሳት ፍርሀት በላይ
ለ እሱ ያለኝ ፍቅር

©Feben Fancho
Jan van Huysum, Vase of flowers, Galleria Palatina
This Face
(Face this Face/Vase Face to Face)

I usually don’t smile or laugh a lot
I may seem shy and in fact, I am
But you won’t believe that
Because unlike plastic smiles
I wear a plastic seriousness
But deep down
My heart cries
For those poor souls by the road sides
For those lucky riches with no souls
For the couples without love
For the pretty girls who feel nothing without make ups
And for all the delusion around us all
But behind this face,
This face, that always looks frowned
Nervous, sad, dejected,
Disgusted or downhearted
This face that faces terror, fear and anxiety
Happiness, bliss and spontaneity
All at the same time may be
And with the same look may be
Yes, behind this face
There is a vase of flowers
That makes me feel handsome
Like I’m the painting by Huysum
If you put another look on my face,
Just know that you’re breaking that vase
And make sure I approve of it
And make sure you replace it
with something better
if there is any …
Yes, I am sensitive but I usually don’t smile or laugh or cry a lot
This straight face tells that I am straight
Nothing less nothing more
May be there is something wrong with my world
Or my facial nerves
But this face,
Is not the face I was born with
Because at this phase,
This face starts wrinkling
And I give face with this faith
That I won’t be shaking or rumbling
But to save face,
I would shout out that this face
Has nothing to do with you
I don’t care whether you like it or not
But if you do, kiss it
If not, just ignore it
Let it frown, let it go straight, just let it be
For this face is a face that belongs to me
I deal with it!
. . . And yes, behind this face
There is a vase of flowers
That makes me feel handsome
And on this vase,
there is your reflection
So deal with it!

(and this face is no ፌዝ)
#seifetemam
Forwarded from The Hub: World of Creators
Rock
(Mahder Addis)

He is my rock that I lay my back onto,
He is my sheild who gets struck by a raining arrow,
While he is bleeding I can sleep in sound despite his sorrow.
I can smell his stench of sweat through his shirt,
I can feel him shivering in the cold of midnight.
Yet...
I am warm,
I am asleep,
I am safe.
He encapsulates me with his love,
His strained eyes, his shaking arm fighting to let me stay in his embrace.
An unconditonal love, wants nothing in return,
His bones chime their own music that keeps me calm with sound of the rain.
My rock, father...
My armor,
My ray of sunshine in dusk's call.
I know this is nothing but words flying,
But its what i could do with all my trying...
To thank,
My heavenly father who got me you of all this existance.
To pray,
And wish you all the years earth offers.
However dreadful it may be,
All is perfect with you, staying by my side.



go to thehub.linkupaddis.com for more
አድዋ የእሳት ልሣን

የጀግናዎች የወኔ ቅስም
የጨቋኞች የውርደት ስም
የጭቆና አርካሽ መድኅን
የባርነት ቁስል እንዲድን
አድዋ የነፃነት አፍ!
የሰውነት ልኬት አጥናፍ!!..

©ሠይፈ ወርቅ
#አድዋ_የእሳት_ልሣን
I saw a falling star today
.
It was Black
No, No, it’s White
Or,
was it gray? 🤔
.
I saw your face in the middle
As it went down in a downhill
I was tempted!
Heavens know,
I was tempted to save us both
From the crash that could end all
I was tempted
.
Hope you’ll survive!

©YeGetanehLij
#YeGetanehLij
አሸንፈናል....ግን ይርበናል?
(ሦስት ተከታታይ ክፍል ያለው ህመም)
ክፍል-፩
:
:
ዘመን የየራሱ 'ማይግሬን' አለበት፡፡ ትውልድ የየራሱ ሽባነት አለው፡፡ የሁሉም 'አሁን' ምንጭ 'ትናንት' ነው፡፡

ትናንታችን ውስብስብ ነው ለማለት አሁንን ማየት በቂ ነው፡፡ በየጦርነቱ በየምሽጉ ድል የሚቀናን ህዝቦች ለመሆናችን ምስክር አያሻንም፡፡

አድዋን ለማክበር በየአመቱ ወደ ፒያሳ ከሚወጡት ወገን ነኝ (ወይም ነበርኩኝ)::

ወደ እንጦጦ ወደንጉሱ ቤት እሄዳለሁ፡፡
በፀሀይ
በረሀብ
በድካም፡፡
(ልብ በሉልኝ የድል ቀን ነው)

የገጠር ቤት እያየሁ፡፡ ውሃ መብራት በቅጡ የሌለበት የሀገሬን ጎጆ እየታዘብኩ፡፡ ደግነት ያለው ያገሬው ሰው ልቡ ልተለወጠም፡፡ ኑሮውም አልተለወጠም፡፡ የአድዋ ጦርነት ጊዜ በነበረበት ድህነት አለ፡፡

ጥያቄ፡- ያሸነፍናቸው ይጠግባሉ
ያሸነፍናቸው በመኪና ነው የሚንደላቀቁት ያውም በነፍስ ወከፍ ገቢ፡፡ እኛስ?

ለዛ ነው ትውልዱ መንገድ ላይ ከነኮተቱ እንደቀረ ቤት ተከራይ ላጤ የተደናበረው፡፡ ዕቃ አለው ከትናንት የተረፈው ታሪክ ውርስ ግን ለሱም ለተረፈውም የሚሆን መጠጊያ የለውም፡፡ የተረፈው ነገር ከምን አዳነው?

ማሸነፋችን ከምን አዳነን?
ከምን?

ከማንነት ዝቅጠት?
ከእርስ በእርስ ጦርነት?
ከመናናቅ?
ከሙስና?
ከችግር ከችጋር?
በራስ ከማፈር?
ከምን?
:
:
በሀቅ መሞገት ያለብን የራሳችን የውስጣችን ጠብ ላይ ነን፡፡ (Inetrnal conflict ) ይሉታል፡፡

ኩራት ራት ሆኖብን ካልሆነ በየመንገዱ የወደቀው ነፍስ ብዛት
የአሮጊቶች እንባ
ዓለምን በመዳፉ የሰራ ፈጣሪ ማደሪያው ታቦቱ ቀኑ ለመለመኛ መዳፍ ሲጠሩ
የ13 አመት ጀምሮ ያሉ ሴቶች ሴተኛአዳሪ መሆናቸው
በሞራልም
በመንፈስም
በአካልም
ወድቀን ሳለን .....አሸንፈን የሚለው ቃል መፈክር ብቻ ይሆንበታል ለትውልዱ፡፡

ይመራል፡፡ ግን ሀቅ ነው፡፡

አሸንፈናል .....ግን ይርበናል::

ያሸነፍናቸው ....የት ናቸው?
ትንሽ ቀዳዳ
ገላዬን ወዳ
በቤቴ ሽንቁር ቀጫጫ ፀሐይ
የብርሀን መስመር በፅልመት ሚታይ
ብትወረውረው ንጋት ጠብቃ
እየቆረጠ የቤቴን ማገር የቤቴን ጭቃ
ከቤቴ ገባ
የተኛው እኔ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡
ውበት ነው ፀሀይ
ሙቀት ነው ፀሀይ
ንዳድ ነው ፀሀይ
የሚያጣጥመው ስለሚለያይ፡፡

©ብሩክ ኮርሳዊ
Forwarded from The Hub: World of Creators
Here is a cool poem shared by Mahder Addis on The Hub. Check out thehub.linkupaddis.com to read the full poem.
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
Motif's poetry slam and music night
📅 March 13th, 2021 4pm
📍 MA restaurant behind sheger
🙏 @Johntravoltawannabe

The day of the anticipated poetry slam and music night has been postponed to march 13th.

Entrance fee- 150 birr only(must bring the ticket with you)
For tickets contact
@Lelasams
@Superdifficult
@eventsethiopia
Forwarded from LinkUp Addis
Shifta will host a special movie screening event night on Adwa Day. Doors will open at 7:00pm. @linkupaddis