ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ውበትን መገዘት

ከፊቷ ፀዳል ላይ ጥላ ዐይኑን ጥሎ
እድሜ ጅምር ማድያት ከመልኳ ላይ ስሎ
ዘመኗ በክንዷ ደርሶ እያሸለበ
ጊዜ ደም ግባቷን ገልጦ እያነበበ ::
ውበቷን ልትገዝት ትነሳለች ፎቶ . . .
የሳር መንገድ ወገብ ይቀራል በፎቶ
ተውርጋራጊ ዳሌ ይታተማል ጎልቶ ::

ፎቶ አንሺው ጨነቀው ፣
ያልተኖረ ዘመን የሚል የአኳሏን ቃል
ከምን ላይ ያስቀምጠው ::

©መቅደስ ሞጎስ

https://t.me/GitemSitem

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
በተረፈ ቀን ላይ በተረፈ ሠዐት እንዲህ አስባለሁ:(የሰማይ አዳም(በዘፍጥረት) እውሩ አሟራ, ወይስ ወፏ?)
ወፏ
መቼ ነው ክረምቷ?
እህል ምትዘራበት
መቼ ነው መኸሯ
የምትወቃበት?
መቼ ነው ፀደዯ
የምታርምበት?
እንጃ!
ወፍ እህል በላ ናት?
ይደናገረኛል..
እሺ ወፍ ለሰማይ ስንተኛ ልጁ ናት?
ዝሪ እጨጂ ብሎ ማይቆነጥጣት
ለምን ነው ፏላይ ልጅ አድርጎ ያሳደጋት?
ሰማይ ሆይ!
ምን በዘፍጥረትህ ከምድር ብትቀድምም
አሰትሮ ማኖር፡ ልጅ አስተዳደግን
ከታናሽህ ምድር ለምን አትማርም?

©ሳምራዊት ውለታው

https://t.me/GitemSitem

@gitmnlemadmet

#ሳምራዊት_ውለታው #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
ፈጣሪ

ታረቀን
ታረቀን
ታረቀን ይሉሀል
ቀን ወጥቶ የራቁህ
ቀን ወጥቶ ይሹሀል
ይሁን እርቀ ሰላም
ይሁን ታረቃቸው
ቀን የወጣ ዕለት ነው አንተም
የራቅሀቸው

©ባንችአየሁ አሰፋ

https://t.me/GitemSitem

#ባንች_አሰፋ (ባንች) #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
Untitled one
While her bower eyes cry
In the middle of dark day
She weaves by the long day
She whisper to the blue sky
With the powerful word
But in her night the pain was obvious and clear
Her shadow was scare and fear
Not a single air was full of joy, Rather
The magic was visible in her tear
All her hope was inside the air
The sparkle day was off and gone
To the far and far away kingdom that won’t be visible to bee seen in trode❤️

May/2020
©Tina
https://t.me/joinchat/AAAAAEwq0Pmw61GSm7UoKQ

https://t.me/GitemSitem

#Tina’sview #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
ኑ ጭቃ እናቡካ ይባላሉ

የተለያዩ ባለእጆች ያበጇቸውን የእጅ ስራዎቻቸውን ይዘው መጥተው እንዲሸጡ፣ በሌላ እንዲለውጡ ወይም እንዲገዙ እንዲሁም አዳዲስ ባለእጆችን እንዲያበረታቱ ልዩ የባለእጆች ኩነት አዘጋጅተዋል።

ታህሳስ 17 እና 18 በሚገርም ቅናሽ ለገና በዓል ማስታወሻ እና ስጦታ የሚሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶችን ሸምቱ ሲሉ ጋብዘዋችኋል።
Forwarded from Poetic Saturdays
ሠላም ሠላም ጤና ይስጥልን ፣ ቅዳሜ ታሕሳስ 24 ቀን 2013 (ከቀኑ 10:00 ጀምሮ) የመስመር ላይ (ኦንላይን) ግጥማዊ ቅዳሜ እናስተናግዳለን! ይህ ምናባዊ የጥበብ መድረክ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው።
"ዙም" ላይ ይቀላቀሉ ወይም በፌስቡክ ቀጥታ ይመልከቱን! ለማንበብ ፍላጎት ካለዎት አስቀድመው በውስጥ መስመር መልዕክት በመላክ ያሳውቁን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ያለ ቋንቋ፣እድሜ እና ርዕስ ገደብ አምስት ደቂቃ ይኖርዎታል። እዚያው እንገናኝ!
https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)
Hey everyone, this Saturday, January 2nd at 4pm, we will host online Poetic Saturdays! Virtual Poetry is open to everyone. Call in and join by Zoom or watch live on Facebook! If you're interested in reading, let us know beforehand or, if you join in on Zoom, send us a private message. As always, you'll have five minutes and we encourage all languages, all ages, and all topics. See you there!
https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)
የክፉ ሰው ምላስ*

ምሰሶው ተማግዶ ጎጆኣችን ነደደ
ውበት ትዝታው ላይ ፍም ሳት ወረደ
ጢሱ በአይን ሞላ ነበርን ሸፈነው
አሁን የቆምንበት ጥላሸት አመድ ነው ፡፡
ብለን ተክዘን ሳል
ካመዱ ላይ ቆመን
አንድ እውነት ገረመን
አንድ ሀቅ አመመን
እዚህ እኛ እውነት ላይ
እፍቅራችን ሞት ላይ
ነፋስ ስራው በዛ
ከአመዱ ቆንጥሮ ሰው ፊት እየነዛ ! ! !

©መቅደስ ሞገስ

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Cork Cellar Wine Bar in partnership with Uncle Don Authentic Jamaican Jerk BBQ invites you to join us to Celebrate Kwanzaa from December 26-January 1. Happy Kwanzaa 🎊🎉

Poets invited!

https://t.me/GitemSitem
"የዮሴፍ ሰቦቃ አስደናቂ ሥዕሎች ከዕይታ ሳይወርዱ እንድታይዋቸው እጠቁማለሁ" ሲል ሰይፉ ወርቁ በ ጠብታ ማር - ጣፋጭ ሃሳቦች ግሩፑ ግብዣውን አቅርቧል!

ፈንዲቃ ካዛንቺስ በማንኛውም ሰዐት ከቀን እስከ ምሽት በሚመቻችሁ ሰዐት ሄዳችሁ ጎብኙት!


https://t.me/GitemSitem
https://www.nebeb.com/
እናንብብ፣ እንወያይ፣ ነፃ እንውጣ። lets read, let's discuss, let's get liberated.
|የተመኟት|
[በዜማ]
አ....ት..ራ....ወጡ
ከ...ትግል.. ውጡ
ተዓ`ምሯን አድምጡ
(ያገኟት... «አ...ሜን»)
|የተመኟት|
[በዜማ]
ሙት አታስታሙ
በድን አትሳሙ
መጥታለች ቁሙ
ተዓምሯን ስሙ።
(ያገኟት... «አ...ሜን»)
[[የተኛት]]
|በሹክሹክታ|
ከሽ... ኮሽ...
ከሽ..ከሽ...
ሿሿ... ሿሻ... ሻሻ
ደረት ማንከሽከሻ
ተንጋሎ እሚቆላ
ቡናማ ገላዋ
ባርያ ያደርገኛል፡ ጌትነትም ብሻ።
ደረት ማንከሽከሻ...
ቡናዋን ታቅፎ
በእሳት ላንቃ መሃል፡ ግራ ቀኝ ይሰግራል
ጠረኗ እየጤሰ፡ እንኳንስ ጎረቤት፥ መላዕክት ይጠራል
( ሚኻኤል ና ቡና ጠጣ!)
ከከከሽ... ከከከሽ
ከሰማይ ተልከሽ...
በእኩለ ሌሊት... በተክሌ ዝማሜ
ስንጋደድ ስትቆሚ... ስትንጋደጅ ቆሜ
ከጉልበቴ ቀድሞ እያጠረኝ እድሜ
ከምኔው ፃይ ወጣች? መንጋት "አፈር ድሜ!"
ከሽሽ...ሻ... ከሸሽ...ሻ
ደረት ማንከሽከሻ
ቡናዋ እህል ውሃ... ነፍስ መመለሻ...
ራብ ራብ ቢለኝ... ቢታጠፍ አንጀቴ
አካሌ ጎጆዋ... ገላዋ ማጀቴ
ብዬ ወደ እሳቷ ... እጄን መዘርጋቴ
ከዛ መፈጀቴ...
ይህች... የፍል ውሃ.. ይህች ትኩስ እህል
ጣዕሟን አልደርስበት፡
መልኳም ይርቀኛል፡መፋጀቷን ባኽል?!
ብረት ምጣድ ደረት
ቡናዋን ታቅፎ
በእሳት ላንቃ መሃል፡ ይተረማመሳል
ጠረኗ እየጤሰ፥ ሰማይ ላይ ይደርሳል
የስንት መ'ላክ ናላ፡ በአምሮት ይፈርሳል?
( ገብርኤል ና ቡና ጠጣ!)
ብረት ምጣድ ደረት
የሚጋፍ በወረት
ቡና የመሰለ ሰማያዊ መና
ያሳርር ጀመረ መቁላቱ ቀረና...
እሳት መልክ ይሰራል
ለቅጽበት ያዘሉት፡ ጀርባ ላይ ይቀራል
ለጌጥ የተኳሉት ተነቅሶ ይኖራል
ታዲያ ማን ይፈራል?
ከፍሬሽ ተተፋሽ.. ያረረውን ደፋሁ
ከማንከሽከሻዬ፡ እስክትወጪ ለፋሁ
አጠፋሪስ ቡናሽ፡
ቀልቤን አቦነነው፡ አቅሌን ስቼ ጠፋሁ።
አትውረጂ ልልሽ፡ ከየት ይምጣ ልሳን?
ግርጅፉን ሰውዬ፡
ጡትሽ ያደርገኛል፡ አንድ ፍሬ ህፃን
እያብረቀረቀ፡
ቆዳሽ ድንግዝግዙን፡ ሲያጠፋው አይቼ
ቢቀላቀልብኝ፡
ቀድቼ ሰጠሁት፡
ተጣለ ያሉትን፡ መላዕክ ጠርቼ
(ሳጥናኤል ና ቡና ጠጣ)
ረካሁ
ያጣሁትን ተካሁ
ከሞት እስከፍቅር፡
ያለውን ርቀት፡ በከንፈሬ ለካሁ
በስተገላሽ በኩል፡
ባንድ ሌት መላክም፡ ሰይጣንንም ነካሁ
ምን ቀረ ከእንግዲህ?
ምኞት ወዲያ ማዶ፡ እጣፈንታ ወዲህ
ምን በጀን ከእንግዲህ?
መላኩን ካወደው፡ ሰይጣኑን ከጠራ
ከሌቱ ቡናችን፡ ትውስታ እንቁጠራ!
ከማንከሽከሻው ላይ፡ ትዝታ እንቆንጥራ
ልክ እንደዛች ሌሊት፥
ይች ዘልዛላ ህይወት፡ እድሜዋ ይጠ`ራ!
(ትዝታ ና ቡና ጠጣ )

©ረድኤት አሰፋ