ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
@etenatawol @seifu_worku @ The Horn of Africa International Poetry Festival

Ethiopia is well represented! And we have three of the Ethiopians including our Headline Poet, Andu Getachew with us at Gitem Sitem 2 this Saturday
Gitem Sitem is running perfectly
Forwarded from Ateriraአጤሪራ (Kirubel Atnafu)
Old Aterira, new page 🙂
በአንዳንድ የአጋች ታጋች ድራማች ምክንያት የቀድሞ የፌስቡክ ፔጃችንን ለመቀየር ተገደናል። የቀድሞ ገፅ ላይ ተልከው ነገርግን እትም16 ላይ ያልተካተተላችሁ ቤተሰቦቻችን በአዲሱ ገፅ ወይም እዚሁ ቴሌግራም ላይ (0925749956 ወይም 0911619673) በድጋሜ ብትልኩልን እትም 17 ላይ ለማካተት እንችላላን።
አዲሱ ገፃችን፡
facebook.com/AteriraDigital
እንዲሁም፡
twitter.com/aterira
instagram.com/aterira_digital
ላይ ይከተሉን።
ለአጤሪራ ይፃፉ... አጤሪራን ያንብቡ... አጤሪራን ለወዳጆ ያጋሩ!
ሁለተኛው የ Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም ግጥም ሲጥም ፪ አንዱ እና ስራዎቹን እየዘከረች በአጃቢ አጣሚዎቹ ዲበኩሉ ጌታ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ እቴናት አወል፣ ወንድማገኝ (የኔ አለም) ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ፍጹም አበራ፣ ሳምራዊት ውለታው እና ሰይፈ ተማም

እንዲሁም ምግባር ሲራጅ፣ ቶማስ አድማሱ፣ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል እና ሌሎችም ጥማና ተጣጥማ አልፋላች።

ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant ለመልካም መስተንግዶዋችሁ እና ቤታችንን ስላበጃችሁልን ተመስገኑልን!

https://t.me/seifetemam

የቀጣዩ 'ራስ' ማን እንደሚሆን ገምቱ

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetry #poetrylovers
ውበትን መገዘት

ከፊቷ ፀዳል ላይ ጥላ ዐይኑን ጥሎ
እድሜ ጅምር ማድያት ከመልኳ ላይ ስሎ
ዘመኗ በክንዷ ደርሶ እያሸለበ
ጊዜ ደም ግባቷን ገልጦ እያነበበ ::
ውበቷን ልትገዝት ትነሳለች ፎቶ . . .
የሳር መንገድ ወገብ ይቀራል በፎቶ
ተውርጋራጊ ዳሌ ይታተማል ጎልቶ ::

ፎቶ አንሺው ጨነቀው ፣
ያልተኖረ ዘመን የሚል የአኳሏን ቃል
ከምን ላይ ያስቀምጠው ::

©መቅደስ ሞጎስ

https://t.me/GitemSitem

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
በተረፈ ቀን ላይ በተረፈ ሠዐት እንዲህ አስባለሁ:(የሰማይ አዳም(በዘፍጥረት) እውሩ አሟራ, ወይስ ወፏ?)
ወፏ
መቼ ነው ክረምቷ?
እህል ምትዘራበት
መቼ ነው መኸሯ
የምትወቃበት?
መቼ ነው ፀደዯ
የምታርምበት?
እንጃ!
ወፍ እህል በላ ናት?
ይደናገረኛል..
እሺ ወፍ ለሰማይ ስንተኛ ልጁ ናት?
ዝሪ እጨጂ ብሎ ማይቆነጥጣት
ለምን ነው ፏላይ ልጅ አድርጎ ያሳደጋት?
ሰማይ ሆይ!
ምን በዘፍጥረትህ ከምድር ብትቀድምም
አሰትሮ ማኖር፡ ልጅ አስተዳደግን
ከታናሽህ ምድር ለምን አትማርም?

©ሳምራዊት ውለታው

https://t.me/GitemSitem

@gitmnlemadmet

#ሳምራዊት_ውለታው #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
ፈጣሪ

ታረቀን
ታረቀን
ታረቀን ይሉሀል
ቀን ወጥቶ የራቁህ
ቀን ወጥቶ ይሹሀል
ይሁን እርቀ ሰላም
ይሁን ታረቃቸው
ቀን የወጣ ዕለት ነው አንተም
የራቅሀቸው

©ባንችአየሁ አሰፋ

https://t.me/GitemSitem

#ባንች_አሰፋ (ባንች) #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis