ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አልባስጥሮስ
Gitem Sitem presents you the marvelous Migbar Siraj and his works along with other outstanding poets.
Poetry, Music, Campfire, Foods and Drinks and so much more.
Please RSVP by sending your full name to gitemsitem@gmail.com or @seifdman on telegram.

ግጥም ሲጥም ልዩ ባለቅኔ የሆነውን ምግባር ሲራጅን ከሌሎች እጹብ ገጣሚያን ጋር ይዛላችሁ መጥታለች!

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

ዝግጅቱን ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እና ቀድመው ቦታ ያስያዙ ሰዎች ብቻ በአካል ይታደሙታል። (መግቢያ አናስከፍልም) ቦታ ለማስያዝ በኢሜይል ወደ gitemsitem@gmail.com ወይም በተሌግራም @seifdman ላይ ሙሉ ስማችሁን እና ስልካችሁን/ የቴሌግራም አድራሻችሁን ላኩልን።


https://goo.gl/maps/EiCpLt2RCoYHLXoK7

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ

https://goo.gl/maps/EiCpLt2RCoYHLXoK7
ለአዳዲስ ከዋክብት ሰማይ ለመሆን ያወጣነውን ጥሪ ተከትሎ ካገኘናችው ምርጥ ገጣሚያን አንዷ - ሮዛ ሽታ (ግሩም ነን መቼም)ን ተዋወቁልን!

#ሮዛሽታ #ግሩምነንመቼም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
[♣️እብን ይወክላል ልብን?♣️]

የመውደድ ገላ መዓዛ
ከአሪቲ ዛላ መዝዛ
ሸተተኝ የማፍቀር ለዛ።
ከአልባጥሮስ፣ ከእጣን፤ ከርቤ
የሰማሁት፤ ተደልቄ እንደ ድቤ
ተሽቀንጥሬ እንደ ፈትል
መሬት ስሜ ልክ እንደትል
ፍቅር ተማገኝ መልኩ
ታየኝ የተዘነጋ ልኩ፡፡
♣️
ኮከብ ከመሬት ተለቅማ
ሰማይ እንደ ጉንጭ ተስማ
እንደ ቃላብ ለፍቅር ተሞ
ድምጽ አውጥቶ እንዳታሞ
'ገዳም ሳይቀረው ገሞ'።
♣️
ልቡን መውደድ አሸተው
ድካሙ ዓይኑን ሸተተው
[የጠጠሮች “ቋ..ቀጭ” ዜማ
በአፍንጫው ጠረን ጽፎ
የብሌኑን ሞራ ገፎ]
ሄደ፤ ሄደ በረረ
ሽታው ግን ዕጹብ ነበረ፡፡

ለ ምግባር ሲራጅ

#ቶማሰአድማሱ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ግጥም ሲጥም አዲስ ተሰጥዖ ፍለጋ ባደረገችው ቅኝት ካገኘቻቸው ምርጥ ገጣሚዎች አንዱ የሆነውን ቃለአብ አባይነህን ተዋወቁልንማ።

#ቃለአብአባይነህ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
ፍርፋሪ ታሪክ
- - - — - - -
"ከጅምሩ ማን ፍጠር አለህ እንዲህ ያለ ነገር? ይሄ ነው ፍርድህ? ዛሬስ አትወርድም፣ አትጽፍም ከግንባሩ ላይ ኃጢያቱን የሚያጽፍ ድፍን የቀዮ ጎረምሳ ተሰልፏል..."
"ተው አርዮስ! ተው! ከፈጣሪ አትጋፋ!...አዋቂ ነው...ተው"
"ድንቄም አዋቂ! ሲታወቅ እንዲህ ከሆነ እውቀት በአፍንጫዬ ይውጣ። አይገርምህም!"
"ለአንዲት ጋለሞታ ፈጣሪህን...ትክዳለህን!"

"ጋለሞታ? ጋለሞታ አልህ?...የት አየህ ስትዘሙት?...የት?...አዘሟች ከሌለ ዘማዊት ትፈጠር ይመስል።እንደወይራ፣እንደቀጋ አትበቅል ዘማዊት..."
"ይወራል።...ድፍን መቂ እሱኑ ነው የሚያወራው"
"እና አመንህ አንተ?"
"ምን አማራጭ ይኖራል? ሰው ተኩኖ።...ሁሉ አምኗል እኔ ማነኝና ሰው ያመነውን አላምን የምለው?"
"አልገባኝም?"
"አይገባህም። አንተ ብቻ ከሰው፣ ከቀየው ተነጥለህ፣ ለዘማዊት ሴት ጥብቅና የሚያስቆምህ ነገር። ብቻህን ከአድባር ትጋጫለህ?...ሴት ጠፋ? ከሸርሙጣ?"
"ዝም በል አንተ!!...ምፅዋ ሸርሙጣ አይደለችም።"
"ነች!"
"አይደለችም! ምፅዋ ሸ...ር...ሙ...ጣ... አይደለችም!! ትሰማኛለህ...አንተ ካላባለግኃት አንዲት ምስኪን ሯጭ ከመሬት ተነስታ ሸርሙጣ አትሆንም።"
"ትጠረጥረኛለህ?"
"አላምንህም"
"አህመድንስ ትጠረጥራለህ? ከእርሳቸው አፍ ነው ቀድሜ የሰማሁት።"
"እሳቸው ቅዱስ ገብርኤል ናቸው? የማልጠረጥራቸው?"
"እና እርሳቸውንም ጠርጥረህ?"
"እንክት! ምፅዋዬ እኮ ናት!"
"በል ወግድልኝ ልሂድበት መንገዴን! እውነትም አሪዎስ!...ያሳደጉህ የእናትህ ጡት ሳይሆን ስምህ እንደሆነ ገና ዛሬ ገባኝ!"
"የምን መንገድ?...የሰው መንገድ አበላሽቶ ...ወዴት?"
"የማን መንገድ ተበላሸ? አንተ ኩሩሩ ወግድልኝ!"
"የምፅዋ። የምስኪኗ...በወሬ ገፍታችሁ የጣላችኋት።...ህልሟ መንገዷ አልነበረም? እ!"
"የምን ህልም አላት ደግሞ ሸርሙጣ? ምን ትሰራበታለች ቢኖራትስ?"
"አንተም አለህ አይደል፤ አይደል እሷ? ሯጭ ነበረች ታውቃለህ።... አቦ ሸማኔ የሚያሳድድ ፍጥነት ነበራት።...የጥንቸል ሳንባ ምታስተፋ ነበረች ይህን አንተም ታውቃለህ....ምን ያረጋል!"
"ጋለሞቶች።"
"አልገለሞተችም።....አንተ ውሻ እንዳልዘነጥልህ በዚህ ከዘራ!"
"ኧረ በህግ...በህግ አምላክ!...ምን ታረግበት ነው እሱ...ኧረ ኡ!...ኡ!...ኧረ በህግ!..."
"ልጄን!...አይኔን!...በማህፀኗ...እንደያዘች...አስኮበለላችኋት...ምፅዋዬን አሸሻችኋት"
"ተው አሪዎስ!...ተው አንተ ከሐዲ!...ባለውለታህን?"
"የት ብዬ ልፈልጋት እሺ አሁን?...ንገረኝ!...እ!..."
"እንካ ቅመስ ይችን ለምፅዋዬ!!...እ!...ይህችን ደግሞ በማህፀኗ ይዛ ለተሰደደችው ልጄ...እንካ!!"
"ኡ!...ኡ!...ኡ!...ኧረ የሰው ያለህ!!!"
"የት ብዬ ነው የምፈልጋት አሁን?...እ!...ምፅዋዬ...የበኩር ልጄን እናት?"

©ምግባር ሲራጅ
ዘንባባ
ከገፅ 132 - 134

#ዘንባባ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
በተለያዩ የግጥም መድረኮች ላይ ተወዳጅ ስራዎቹን የሚያቀርበው ኤሊያስ ሽታሁን የራሱን መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊያደርስ በተቃረበበት ጊዜ በጥዑም ግጥም ዝግጅታችን ላይ የምግበር ሲራጅን ግሩም ግጥሞች በሱ አቀራረብ ሊጋብዛችሁ ተዘጋጅቷል።

#ኤልያስሽታሁን #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
“Feelings along the Sidewalk” is open now!
Find it on the Sidewalk of the Italian Cultural Institute and, online on http://tibebbeadebabay.org

#tba #tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival #artinaddis
Meet one of the poets we've spotted following our call to artists. This emerging poet is ready to share her perspectives and express her self through poetry.

#AdomiaFekede #gitemsitem #poeticsaturdays #migbarsiraj
#አዶሚያፈቀደ #ግጥምሲጥም #ግጣምዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
መልክዐ ሮዝ

ቅዠቴ..
ቀድሞ
ከማይታረም ግዜ መሀል
ራሳችንን ልናስበልጥ
በየጫካው ስንኮበልል
መመለሻው እንዳይጠፋን
ከየሳሩ ከየዛፉ
ጠረንሽን እየቀባን
አልፈን መጣን::
ጉዱ (ተዐምራቱ)
እጣኔዋ
እጣኒቱ::
ካለፍንበት ስመላለስ
ከዚህ ቀደም ከኔ ቀድመሽ
ያለፍሽበት እየቀባሽ
ከዛፍ ከሳሮቹ
ከሀረግ ከእሾሆቹ
ከመሀከላቸው አንድም አልሸበተ
<ፎስት> እንደቀመሳት
ጠበል ጠዲቅ ሁሉ
ወጣት ነው ዘላለም አንቺን ያሸተተ::

©ምግባር ሲራጅ

#ዘንባባ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ተዋወቁልንማ፣ ይህን ጥዑም ግጥም ሰናኝ! ቴዲ ካሳ በግሩም ግጥሞቹ ቆይታችንን ሊያጥም ተዘጋጅቷል።

#ቴዎድሮስካሳ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ምግባርሲራጅ #ጥዑምግጥም
Due to security issues in our city, we are forced to move the event to the 21st of November (next Saturday).

We thank you all for your interest in our event. We hope you understand how the situation is beyond our power and we hope you excuse us.

Please stay tuned to Gitem Sitem's channels for more updates.
ከተማችን ውስጥ ባለው የጸጥታ ስጋት ይተነሳ ዝግጅታችንን ወደሚቀጥለው ሳምንት ልናስተላልፍ ተገደናል።
እስካሁን ላሳያችሁን ተነሳሽነት ሁሉ ሁላችሁንም እያመሰገንን ያለንበት ሁኔታ ከአቅማችን በላይ የሆነና በአገር ደረጃ ካሉ ሁኔታዎች ጋር የተገናኘ መሆኑን ተረድታችሁ ይቅርታችሁን እንደምትቸሩን ተስፋ እናደርጋለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን የግጥም ሲጥም ገጾች የሚያቀብሏችሁ ይሆናል።
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (Seife Temam)
ጸልያለሁ
========
እጸልያለሁ ለሰው ልጅ
በሰንሰለት ላለው እጅ
እጸልያለሁ ታትሬ
ህላዌን ያላወቀ አለም
ፍፃሜን እንዳያይ ዛሬ

እጸልያለሁ ጸሎቴን

ኩታዬን በኮት ስቀይር
ስለፈረሰው ቤቴ
ራቤን በም'ራብ ስሰፍር
ስለተራበው ጉልበቴ
ስሜን በሰም ሳሰፍር
ስለነደደው ውበቴ

ከራሴ ወጥቼ
ፀርሃ አርያም
ቅጥሩን ተጠግቼ
የዓይኖቼን ውሃ
በፍቅር አተንናለሁ
እ-ጸ-ል-ያ-ለ-ሁ
እጸልያለሁ ጸሎቴን
ዕለትን በአለት ሲያቆም ሲመትር
ስለደከመው አያቴ
ግንጥልጣይ ገጥሞ ሲቀምር
ስለተሰዋው አባቴ
ነፍስ ላይ ነፍጥ ሲከምር
ስለጠበበው አጎቴ
ከራሴ ወጥቼ
መንበረ ፀባዖት
ቅጥሩን ተጠግቼ
የወዜን ብልጭልጭ
በእምነት እጠርጋለሁ
እ-ጸ-ል-ያ-ለ-ሁ
እጸልያለሁ ለሰው ልጅ
በሰንሰለት ላለው እጅ
እጁ ለሰንሰለቱ ሳይጠብ
ሰንሰለት እጁላይ ሳይቀልጥ
ህላዌን እንዲያየው አለም
ፍፃሜን ተግቶ ከማለም

ሰይፈ ተማም 2008
በአርትስ tv እንዲሁም በታላላቅ መድረኮች ላይ የምናውቀው ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን አዲስ የ telegram ቻናል ከፍቷል በመቀላቀል ከጥበብ ማዕህድ ይቋደሱ

👇👇👇👇

@Eliasshitahun
@Eliasshitahun
@Eliasshitahun
Elias Shitahun:
ምስጢረ ሰው መሆን ከምንመረምር
እስቲ አንዳንድ ጊዜ ከአሜን እንጀምር።
ድረሰቱን ዜማውን መሰደር አቁመን
በትርጉም ከምንሞት ከሀሳብ አድመን
ሁሉ እንዲቃናልን ከደቡብ ከሰሜን
ሁሉን ገታ አርገን እንጀምር ከአሜን።
ያመንከውን አስስ
አሜንን ፍለጋ ሰው ከተሰደደ
እንደመስቀል ችቦ በአንድ ከነደደ
ጨለማ ይቀናል በብርሀን ዳና
ሰማይ ቀን ይመስላል ሰው ሰማይ ነውና።
ያመንከውን ፈልግ ከቶ አታፍነው
ጭስ ያበረታኻል ቆሻሻ ቢደፍነው
ያመንከውን ፈልግ
ከሰው በታች ቀብሮህ መቻልህን ገድሎህ
ያልታደለ ሰቃይ
ያነሰ ይመስለዋል መሬት እንኳን ጥሎህ።
ሰቃይ እንደዚህ ነው
የአለምን ድውይ ስትፈውስ ሰትሽር
ጠላትህ ይነሳል ማዳንህን ሊሽር።
ችቦህን አጠራቅም ደመራህን ለኩስ
በአላማህ መንን በሰው ህብረት መንኩስ
ጠላትህን ቀማው የመጥላቱን አቅም
መውደድህን አወጋው
መውጋትን አያውቅም።
ከሰቃይህ ብለጥ ከክፋት ብርሀን
እሳት ይወለዳል በስንጥሮች መሀል።
ከስንጥሮች ቅሰም የህይወትን ትርጉም
ተጋግዞ መብራት ነው የሚያባረረው ጉም።
ደግ ዛሬ ያለው ነገውን ያምጣል
ሁሉን ተወውና ክፉን ትናንት ጣል
ተገኘሁኝ ብለህ ዛሬ እንድትዘምር
ከመታሰብ ቀጥል ከመጀመር ጀምር።
ምስጢረ ሰው መሆን ከምንመረምር
እስቲ አንዳንድ ጊዜ ከአሜን እንጀምር።