ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
I woke up this morning and figured I'd call you
In case I'm not here tomorrow
I'm hoping that I can borrow a piece of mind
I'm behind on what's really important
My mind is really distorted
I find nothing but trouble in my life
I'm fortunate you believe in a dream
This orphanage we call a ghetto is quite a routine
And last night was just another distraction
Or a reaction of what we consider madness
I know exactly what happened
You ran outside when you heard my brother cry for help
Held him like a newborn baby and made him feel
Like everything was alright
And a fight he tried to put up, but the type
Of bullet that stuck had went against his will ...


Kendrick Lamar - Sing About Me, I'm Dying of Thirst
. . .
ደሞ እንደ መስቀል ወፍ እንደ አደይ አበባ
ህይወት እንደሚያድስ መስከረም ሲጠባ
እናፍቃታለሁ እንደ ህጻን ልጅ
አትሂድብኝ የትም አትውጣ ከደጅ. . .
. . . እንደ ናርዶስ ሽቶ እንደ ፈዋሽ ጸበል
ማነው ያልተመኛት የኔናት የማይል
የትም ዞራ ውላ ስትመለስ ድንገት
ያጣል መሸሸጊያ አይኔ የሚገባበት
ማን ለምን ይላታል ማን አለ ጠያቂ
የቱ ሽማግሌ የትኛው አዋቂ. . .

ሲያምረኝ - ምትናፈቅ
'ጉራ ብቻ'
(በታመነ መንግስቴ)

ያው የማከብረው ወዳጀ መምህር ሀብታሙ አለማየሁ አንድ ማስፈንጠሪያ(Link) ላከልኝ።Egypt Independant የተሰኘ ገፀ ድር ጉራ ተሸክሟል።"ኢትዮጵያ እና ግብፅ ጦርነት ቢገጥሙ ማን ያሸንፋል?" ዓይነት የሰይጣን ንፅፅር ውስጥ ለመግባት ሲንደረደር የአገሩ ርዕሰ ብሔር አብደል ፈታህ አል ሲሲ የአየር ኃይል መኮነኖቻቸውን "ለየትኛውም የአገር ውስጥ ወይም የድንበር ባሻገር ተልዕኮ ተዘጋጁ"እያሉ ማሟሟቃቸውን ወሽክቷል።

ይቀጥልና የግብፁ ውጭ ጉዳይ ምሉክ ሳሚ ሽኩሪ ስለ እኛው አቻቸው አቶ ገዱ ዓረፍተ ነገሮች"ጠብ አጫሪነትና"እና "አበሳጭነት" መናገራቸውን ፅፏል።ከዚያም ከዓለም ዐቀፉ የጦር መሳሪያ ሃይል ድረገፅ አገኘሁት ያለውን የኢትዮጵያና ግብፅ ንፅፅሮሽ ያስቀምጣል።ለአብነት፦

ሀ.የግብፅ ዓለም ዓቀፍ የጦር አቅም ዘጠነኛ ሲሆን የኢትዮጵያ 60ኛ ተብሏል።

ሁ.የግብፅ ዓመታዊ የጦር ኃይል ገንዘብ ድልድል(በጀት) 11.2 ትዕልፊት(ቢሊዮን) ሆኖ የኢትዮጵያው 350 አዕላፍ(ሚሊዮን) ተገምቷል።

ሂ.የግብፅ ወታደሮች ቁጥር 920ሺ ተገምተው የእኛዎቹ 160ሺ ላይ ተቀምጠዋል።

እንግዲህ ነፃነትን ለ2ሺህ ዓመታት ተነፍጋ በቱርክ፣እንግሊዝ፣ሮማ፣ፋርስ፣እና ኢትዮጵያ ስትገዛ በኖረችውና ነፃነትን በማታውቀው አገረ ግብፅ ያለ የሚመስለው 'Egypt Indepndant' የፃፈውን እንመነውና ወደ እኛ ጉዳዮች እንምጣ፦

'ከነገራችን ጋር' የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምሉክ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የያዙት መንገድ አይከፋም።ግብፅን እንደማንፈራትና በተለይ በሁለት እጆቿ ልታፍስ መቃጣቷን መቃወማቸው ያስመሰግናቸዋል።_ ሰውየው ደመ ሞቃት ስለመሆናቸው ራሳቸው ለዘመን መፅሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ውስጥ አንብቤያለሁ።

ቢሆንም ከዘመን አይሽሬው የኢትዮጵያ ላዕከ መንግስት(Diplomat) አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር የሚነፃፀር ብልጠት ያስፈልጋል።አክሊሉ በማስታወሻቸው እንደፃፉልን ኤርትራን ለማስመለስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ረፍት አልባ ሆነው ለህመም ሳይቀር ተዳርገዋል።የዚያኔ ኢትዮጵያን በስም እንኳ በደንብ ከማያውቋት አገራት መሪዎች ጋር በፈጠሩት መልካም ግንኙነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ደግፈው እጅ እንዲያወጡልን አድርገዋቸዋል።

ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ዛሬ "የጥቁር እንቁ" የምንለውን የጋምቤላ ምድር ወደ እናት አገሩ የመለሱት በጥበብ ነው።ኦጋዴንን፣የባቡሩን ባለቤትነት፣ ኢትዮጵያን ራሷን ያስረከቡን በከፍተኛ የተግባቦት ብቃት ነው።ከእነ አቶ ገዱ ይሄ እና ከዚህ በላይ ይጠበቃል።

የእኛ ትውልድ ሃውልት የህዳሴ ግድብ ነው።ግብፅ "ጦርነት" የምትለው 'ጉራ ብቻ' ነው።ምክንያቱም ዘመኑ አይፈቅድማ! የምወደው ነገራተሰብ(ጋዜጠኛ) ዮርዳኖስ አበበ እንደሚለው "በዚህ ዘመን በአንድ ጦርነት የሚመጣን ኪሳራ 20 ዓመት አይመልሰውም።" ጦርነቱ ከሆነም እንዲሁ በጉራ ደረጃ እና የአገር ውስጥ ባንዳዎቻችንን በመመልመል ነው።ስለዚህ ለጊዜው በአጥንት መናከሱን ትተን ወደ ጅቡ መጮህ አለብን።

ጅቡ ብዙ ነው።እነ አሜሪካም የእኛን ጉዳይ ለራሳቸው ይፈልጉታል።ያ ታላቅ ሰው-አክሊሉ ሃብቴ እንደፃፉት"ሁሉም ለየራሱ ጥቅም እንጅ በፖለቲካ 'ጀስቲስ'(ፍትሕ) እንደሌለ የታወቀ ነው።"

በዚህም ተባለ በዚያ እኛ መራብ አንፈልግም።ግዮን ኢትዮጵያን "ይከብ" ዘንድ በአምላኩ ታዝዟል።አሁንም ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ኦጋዴንን ሊነጥቋቸው ለቋመጡ እንግሊዞች"ሳንዋጋና ሳንሸነፍ ልትወስዱት አትችሉም!" እንዳሏቸው እኛም "ሳንዋጋና ሳንሸነፍ የዓባይን ግድብ ውሃ ሙሌት ልትከለክሉን አትችሉም!" ብለናል።

"ጉራ ብቻ'' የለቀቀብኝን ገፀ ድር ማስፈንጠሪያ እነሆ፦https://egyptindependent.com/is-an-egypt-ethiopia-war-an-option-a-comparison-between-the-egyptian-and-ethiopian-armies/
Forwarded from Daily Say by Rob Haile
Naked as we came,
Naked we will go.
No Nation.
No Race.
No Sex.
No Chains.
Liberty's taste so sweet
As there is nothing to hold back
The true self.
No labels.
No expectations.
Oneself and oneself only.

#DailySay
@storyteller_rh
አዲስ ቅርበት

እንደ አዲስ ተዋውቀንበት
አዲስ ሰው የምናውቅበት
በቅርበት የምንረቅበት
ረቅቀን የምንኖርበት
አዲስ መርገም አዲስ በረከት

በእጅ ማንጫው ስንነጣ
ተጣጥበነው የ'ጅን ዕጣ
ቤት ከትመን ሳንወጣ
አዲስ ውረድ አዲስ ውጣ
ዛሬን ኖረን ነገም ይምጣ

እሲቲህ ባንድነት እንስከን
እሲቲ ላንድነት እንዝፈን
እሲቲህ እንግዘፍ በአዲስ ቀን
አዲስ ቅርበት ነው ያደለን
እጅ ከሚያስጥል አስጥሎን
አስተባብሮ 'ሚያረዳዳን

ቅርበት ተው ከቻልክ ቅር እቤት
ታጠቢው እጅሽ ይንጻበት
እንንጻ እንድንጸናበት
እንጽና እንድንጸናበት

ይኸው እጄን ፊት ነሳሁት
ይኸው ፊቴም እጅ ነሳ
የራቁኝን ቀረብኳቸው
የቀበርኩት ፊት ተረሳ
ምን ጉድ ነው አትበሉ ለዚህ
አዲስ መልክ ነው ጭምብሉም
ፈተና መች ችግር ሆኖ
ያው በረከት ነው መርገሙም

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ቀን አለን!

የቆረቆረንን ጠጠር
ተነስተን እናራግፋለን
የዘመመውን ምርኩዝ
አቃንተን እንደገፋለን
ቀን አለን!
እንቆማለን!
የፍጥረቴ
አፈሬ ሆይ...
ቀን አለን!
እንቀናለን...!
ስንቃና...
ስንቀና..
መቆም ቢሰምርልንም
እንመውደቁ አይጥመንም...
እኔ ሆይ...ነይ እንርቀቅ
አንዳችን በሌላችን
አፈር እቅፍ እንውደቅ
.....

ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ማርቆስ_ዘመንበረልዑል
Forwarded from Bereket Adane
Open call by Office of the Prime Minister-Ethiopia


የዚህ ዓመት የ #አረንጓዴዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ወር ሊሞላው ነው። በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማራችሁ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ሁሉ፣ ተደምራችሁ አነቃቂ የ #አረንጓዴዐሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅታችሁ #የጠሚአረንጓዴዐሻራጥሪ በሚል መለያ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለተመረጡት ሥራዎች ባለቤቶች አስደናቂ በረከቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።


I challenge all Ethiopian creatives, film makers, graphic artists, photographers, storytellers, cartoonists, etc to come up with the best short #GreenLegacy videos and share on social media marked #PMGreenLegacyChallenge. A surprise follows for the best productions.
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን ዓለም አቀፍ ውድድሮች መሳተፍ ይፈልጋሉ? በየሳምንቱ የሚለቀቀው የአርት ሜሊንግሊስት ይመልከቱ!!
The Arts Mailing List newsletter – 29th June 2020 is out now https://bit.ly/2YGJGtD With over 100 open calls, competitions, funding and residencies, there is something for every Ethiopian artist/create!!!


This week, we also bring the multi-talented artist Enku Sillasie Yesgat https://www.facebook.com/Enku-sillasie-yesgat-art-works-410394766454671/


In this week’s newsletter, opportunities and stories from @ethiofendika, @BigDreamET, @freelance_ethio, @getz_mag, @loline_mag, @LinkUpAddis, @everythingaddis and so much more


@artsmailinglist
Forwarded from Abiy Haile
Virtual training with 4 sessions in a row organized by: Jot Self-Development Program

Theme: "How to cope up and persist in difficult situation?"

Format: Online(zoom)
📅 July 15 - August 12 2020 G.C

Register for #free using the link below and join the training.

Register 👉 bit.ly/37YPEZW

📌 For more info: +251962033752
Telegram: @jotmedia
Forwarded from Daily Say by Rob Haile
I am afraid.


When you look into my eyes,
I get scared.
I figure you will see,
I am bruised.

I act out and create tension,
You stay away.
It works out as I planned,
You don't look my way.

A small part of me wants to cry to you,
Dreaming of your shoulders.
To list all the wrenching moments,
As the night grows colder.

The nights do grow colder.
I do not let out a peep.
I silently rot in.
With the scars starting to run deep.

I know you do care.
I hope you do.
I have spoken once.
You did not take it as urgently as I wanted you to.
So, I took that as a lesson.
I rather dig this hole further,
See where it lands me.


#DailySay
@storyteller_rh
Forwarded from HAPPY (Ribka Sisay)
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን ዓለም አቀፍ ውድድሮች መሳተፍ ይፈልጋሉ? በየሳምንቱ የሚለቀቀው የአርት ሜሊንግሊስት ይመልከቱ!!

The Arts Mailing List newsletter – 27th July 2020 is out now https://bit.ly/32VRAlp

And this week we bring the work of multi-media artist Tesfahun Getachew

With over 100 open calls, competitions, funding and residencies etc… there is something for every Ethiopian artist/creative to apply for!!!!!

@artsmailinglist