ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
@rophnan 's
My Generation concert in collaboration with Gitem Sitem brought you Expression II

Music, live painting, open mic, selected performances and the anticipated poetry slam contest

A poetry fest where we will be crowning a My Gen poetry slam champion

Entrance: 100 Birr only

የሮፍናን የኔ ትውልድ ኮንሰርት ከግጥም ሲጥም ጋር በመሆን የከሰተላችሁ 'ምድር ቅንን. . . ' የተሰኘው ለሁለተኛ ጊዜ የምናቀርበው መሰናዶ ጥር 3 ከቀኑ 10:30 እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት ቦሌ ሞኤንኮ አጠገብ በሚገኘው ሽፍታ

ሙዚቃ፣ ዳሰሳ፣ ክፍት መድረክ፣ የተመረጡ ገጣሚያንና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የግጥም ግጥሚያ

መግቢያ:- 100 ብር ብቻ

#Rophnan #IIIVIIX #MyGen #universalmusic #poetrylovers #poetry #artinaddis #heransyoga #poetic_saturdays #expression #poetryslam #slam #slampoetry #openmic #music #gitemsitem
👍3
Our own gitem sitem is at Zoya representing poetry

Come and join us!
📅 :- January 21st
📍 :- Greek club
🕔 :- 4PM

Share our event poster on your story and tag our page and a friend to be among the first 10 people who will win a giveaway

PS: Contact us to get discounted tickets to Zoya

እዚህም ግጥምን ወክለናል ፤ ተገኙ ተዝናኑ !
#zoyaaddis #linkupaddis #gitemsitem
👇🏾Spot where we will be, share it on your IG story, tag us and win a chance to get a free ticket to the event
👍2
Forwarded from LinkUp Addis
👍2
Forwarded from Seifu
#እባካችሁ_ለቢኒ__እንድረስለት!!
BINI ቢኒን እዚህ መንደር የምታውቁት እና ስለ #Poetic_Saturdays ፖኤቲክ ሳተርዴይስ (#ግጥማዊ_ቅዳሜ) የጥበብ ምሽትን በአካልም ሆነ በኦንላይን የታደማችሁ፣ እንዲሁም ለሰዎች ፈጥናችሁ የምትራሩ ሁሉ ደጋጎች ሁሉ #ስለ_ቸርነታችሁ_ትለመናላችሁ!!!

ለብዙዎቻችን መሰባሰቢያ የነበረውንና በፈንዲቃ የባህል ማዕከል ሲዘጋጅ የነበረውን የጥበብ ምሽት ሲያስተባብርና ደፋ ቀና ብሎ ሲያገለግል የነበረው ባለብሩህ ፈገግታው እና ትሁቱ ወንድማችን ቢኒ ከ"#ብሬይን_ቲዩመር" ጋር እየታገለ ይገኛል። ... በአገር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ቀዶ ጥገና የተደረገለት ቢሆንም፣ ... በፍጥነት ወደ ሕንድ አገር ሄዶ መታከም ይኖርበታል!!!...

• ፈጣሪ ጨርሶ እንዲምረው በጸሎታችሁ አግዙት! አቅማችሁ የፈቀደውን በሁለት ወዳጆቻችን ስም በተክፈተው በቀጣዩ አካዉንት እርዱ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000529173435

ከአገር ውጭ ያላችሁ ወዳጆች በክሪስ አማካኝነት በተከፈተው የgofundme አካዉንት እገዛችሁን አድርጉ።

https://gofund.me/da6fcd7f
👍6
ከ ጥቂት እረፍት በኋላ የሽፍታዋ ግጥም ሲጥም ወደ መድረክ ተመልሳለች ፤ በ አድዋ ዋዜማ ጀግንነት ፣ ነፃነት፣ ጥቁርነት፣ ሠውነት ዙርያ ያጠነጠኑ ግጥሞችን፣ሙዚቃዎችን እና ሌሎች የጥበብ ስራዎችን ከእናንተው እናደምጣለን ::


ከመግቢያው የሚገኘው ሙሉ ገቢ ወንድማችን ለሆነው ለ "ግጥማዊ ቅዳሜው" ቢኒ የህክምና ወጪ የሚውል ይሆናል ::


📅 ረቡዕ:- የካቲት 22

🕐 12:30 ይጀምራል

💳 100ብር ብቻ

📍ሽፍታ ሬስቶራንት :- ቦሌ ከ ሞኢንኮ ከፍ ብሎ ከ ዘሃብ ሆቴል ፊት ለፊት

#shifta #gitemsitem #poetic_Saturdays #kirunfuddigitals #heransyoga #linkup_addis #hibreqal #poetrylovers
1👍1
Forwarded from Event Addis Media
ግጥም ሲጥም!

ትኩረቱን የአድዋ ድል በዓል ላይ ያደረገው ወራሃዊው "ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ዛሬ  ረቡዕ የካቲት 22 2014 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ሽፍታ ሬስቶራንት ይካሄዳል። 12:30 ሲልም ይጀምራል ተብሏል።

መግቢያው 100 ሲሆን ከመግቢያው የሚገኘው ገቢ ሙሉበሙሉ ለቢኒ ህክምና እንደሚውል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1
👍21
Forwarded from LinkUp Addis
After a short break, Gitem Sitem is returning for an Adwa Edition. Poems, music and other works of art focused on bravery, blackness, freedom and humanity can be presented. This event is taking place tomorrow Wednesday 1 March 2023 at Shifta.

All proceedings of the event go to help pay the medical bills of Bini.
@linkupaddis
1👍1
Forwarded from 📚📖 ከመጻሕፍት አንደበት 📖 📚 (Ãbdü "Muslim vacation is Fisebililah")
አድዋ ያልገባው
(ተጻፈ በ ሰይፈ ተማም)

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
የአድዋ ጀግኖች የተዋደቁለት
ይመስለው ይሆናል ለሱ ለመጨመር አንዲት የ'ረፍት ለት
ካላንደር የዘጋት አንዲት 24 ሰዓት

«እፎይ ስራ የለም
አቦ ክላስ የለም አድዋ ነው ዛሬ
ፊልሜን መኮምኮም ነው እግሬን አጣምሬ
ጣል ያንን አትበሉኝ አልጥልም ደፍሬ»

እንዴት ያል ነገር ነው?
ለዚህ ነበር እንዴ
እነ አባ ቃኘው ያነሱት ጎራዴ?

ጣልያንን ጥለን አነ አንቶኔሊን
እነ አልቤርቶኒ እነ ማንፍሬዲኒ
ሽቅብ የሚጓዙት ደሞ እነ አልፔኒ
ጠቅላይ ጦር አዛዡ ዋናው ባራቲየሪ
ይህን ሁሉ ጥልያን
ጥለን ጣጥለን
ኳስ እያየን አለን
(እነማንን? እነባላቶሊን ጥቁሩን ጣልያን)

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
የአድዋ ጀግኖች የተዋደቁለት
ይመስለው ቢሆንስ እንደው ከንቱ ልፋት
ስልጣኔን መግፋት

(ከዚህ ስልጣኔ ምኒልክ የታየው
የናት፣ የርስት እና የዕምነት መነጠቅ ነው።)
ታካች ሰው ምንግዜም ልፍስፍስ ነውና
ሂወት አልባ ዝመና
የሰነፍ ፍልስፍና
የወቅቱ ሰዎች መብት
አርነት፣ ግዕዝ፣ ነጻነት
በድህነት ታክተን
ሰሞነኛ ብቻ አይተን
በማያልም ህልማችን
ወቀስን ጀግናችንን
ሚዛናችንም ስቶ
በህንጻ በዳስ ሲለካ
የነጻነት ኩራትስ እንዴት በገንዘብ ይለካ?
የዘመናዊነት ጤዛነት
ላይናችን እስኪታያት
ባሉታ የታሸ የጥልያን ልገሳ
አንዳች ሳያስቀምጥ
ያለንን ሁላ ሊያነሳ?
ለዚህ ነበር አንበሳው ከያለበት የተነሳ
እንደመብረቅ እያገሳ

ግን አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
የአድዋጀግኖች የተዋደቁለት
ምን ይገርማል ከቶ ባይገባው ነጻነት
አላየውምና ተነጥቆ በጉልበት

አንዳንድ ግዜኮ
የውሃንም ጠዓም
ይቻላል ማጣጣም
ጠላም ውሃ ነበር በጌሾ ቢቆጣም
አዲሱ ኢትዮጵያዊ ነጻነትን እንዲያውቅ
ላንዲት ጀምበር ብቻ ውብ ሃገሩን መንጠቅ
ያኔ አያስችለውም ይህ የጀግና ውላጅ
ከጠላቱም አልፎ አለምንስ ቢፈጅ
ፈዞ ቢታይ ዛሬ - ልቡ
ያድዋ ግማጅ

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
አገሩን ከሰጠ በእጅአዙር አዙሮ
ባለፋ ምኒልክ ከተራራው ጓሮ

አባ ዳኘው የልጅልጅ ልጅ ልጁን ቢያየው
ዘራፍብሎ የሚሸሸው
ኢትዮጵያዊነት ሲጎድለው
ኳስ ና ፊልም ሲያፈዘው
ምን ይል ይሆን ማየት ቢችል ያድዋው ጀግና አባ ቃኘው?
ምን ይል ይሆን ሰራዊቱ
ምንትል ይሆን እናቲቱ
ምንትል ይሆን ምድሪቱ
ምንይል ይሆን ሰማይቱ
ኧረ ምን ትል ይሆን ጣይቱ
መጋደሉ መዋጋቱ
ከረፍት ቀን የዘለለ
ሆኖ ካልታየ ውጤቱ
ለዘመነኛ ወጣቱ
ምንትል ይሆን ብርሃነ ኢትዮጵያ
ጠሃይቷ ጣይቱ?
ተጠየቅ አንተ ዘረ ብርቱ

ባመጣልህ ተሽከርካሪ
ከስንቱ ጋር ሲነታረክ
ስትዋከብ ስትገጭ ቢያይክ
ምንይልክ ይሆን ምኒልክ?
መገናኛን ቢያስብልክ
ዛሬ ይዘህ በኪስክ
ቦሌ ሆነህ ንፋስ ስልክ
ስትቀጥፍበት ቢያይክ
ምንይልክ ይሆን ምኒልክ?
ቢኖር ምን ይላል ዛዲያ
የሴጣን ስራነው ሲሉኝ
በሰማሁ ከማለት ወዲያ
ላለበሰህ ነጻ መንፈስ
ወቀሳህን ብታደርስ
ያኔነው እምዬ ሚያለቅስ

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ቢመስለው ምናልባት ይህ አድዋ ማለት
እንደነ መቅደላ የጦርነት ፍጅት
የመድፍ ጋጋታ የሙታን ክምችት
የተራራ ርችት
ቢመስለው ምናልባት
አድዋን እራሷን ለምን አንጠይቃት

የአድዋ ተራሮች
እኩይ ሃሳብ
እንደባብ ሲሳብ
ከውጫሌ ካብ
ደሞም
የኢትዮጵያ መንፈስ
አትረብሹኝ ብሎ ሲፈስ
ሲውተረተር ሲገሰግስ
ሲንደረደር ሲገማምስ
ሲግተለተል ሲደማምስ
ሲንቦለቦል ሲያተራምስ
ወዲአ ላይ ሲርመሰመስ

ኢጣልያ ባገሩ ላይ ሲያምርበት
ባየ ግዜ
የቸኮለ በሌጣው
ያልቸኮለ በኮርቻው
እየተሰካ እየፎከረ እየተንደቀደቀ ገባበት

የአድዋ ተራሮች ላፍታ ልሳን ቢኖራቹ
ከዚህ ውጪ የምትሉን ስንት ጉድ ነው ያያቹ?

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
የአድዋ ጀግኖች የተወደቁለት
ምስጢሩ የገባው ለት
ቢመስለውም እንኳ ለሱ ለመጨመር
አንዲት የ'ረፍት ለት
ካላንደር የዘጋት አንዲት 24 ሰዓት
እያመሰገነ እፎይ እያለ ነው በነጻነት ኩራት
ሃገሩን ሚያያት
ያኔ ይንደላቀቅ ይረፍ እግሩን ሰቅሎ
ይሴብህ እያለ ለዓድዋው ውሎ

@Arthabesha
@Arthabesha
👆👆👆👆👆👆
👍54🔥1
THE ART OF BEING HUMAN | ሰው የመሆን ጥበብ
በ ቡድን የተዘጋጀ የጥበብ ኤግዚቢሽን

ተዘጋጀ :- በ '23 art studio and teyem art center'
መቼ :- አርብ ከ መጋቢት 8 - ሰኞ መጋቢት 11
የት :- @SABEGN ቦሌ አትላስ ከ ሳፋየር አዲስ ፊት ለፊት
የኛዋ ግጥም ሲጥም በ ቦታው ትገኛለች ፣ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ትመራለች፣ ክፍት መድረክ አለን ፣ ከመሃላችን የሚያቀነቅኑም ይኖራሉ ::


#SABEGN #GitemSitem
1