ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Can we grow together?
Grow to be strong enough to let me put my hands on the places you are hurting and to trust you enough to see me angry and sad and resentful.

Can we grow together?
Grow to be wise enough not to poke each other's wound and worse the pain but instead heal them slowly and wholly.

Can we grow together?
Grow to find absolute freedom in our world. Grow free from every thing we were molded into believing against our will, grow free from all restraints,
Free from rules,
Free from society,
Free from life,
Free from death,
Hell! Even grow free from time for it is one hell of a bitch.

Can we grow together?
Grow in love.
I didn't say fall darling because everything that falls gets broken and we're left with only few healthy tendons, we can't afford to be hurt again.

Can we grow in love together?

Wordgasm
Words I cum

Talk to me @PoeticMind_bot
https://t.me/Wordgasm
👍1
(Inspired by Goethe's "the drop of nectar")

I make things of, sweet flavor
But my sweetness is yours
It would have been selfish to keep you all for my self,
I wanted to share you to the world!

መዋቲያን መሐል
ለጣ'ም የተፈጠርን ኢመውታን
አላቂ ላይ የተጣልን ጅምሮች

በየቀኑ ከመውደድ ሕይወት
ከመውደድ ሞት ልንሰራ
እየወደቅን ልናሰራራ
ዘፍጥረታችን
ቀስሞ ተቀምሶ መብነን

ቀፎዬን ለቅቄ ስመጣ
ከመኖርሽ ጣዕም ስቀምስ
መኖሬን አዲስ ቃና ዘለቀው

ብቼዬን ልወድሽ ብትበዢ
ቢከብደኝ ጣዕምሽን መሸከም
ለዓለም ሁሉ ባጋራሁሽ
ዓለም ሁሉ ቢወድልኝ ብዬ ተመኘሁ!

I let you pollinate
And you wilted.

ለካ
እጅ ያልነካት ጽጌ
ዐይን ይሰብራታል
ብትበረክቺልኝ ብዬ
ያጋራሁት ዓለም
ቀጥፎ መቃብሬ ላይ አኖረሽ

ካንቺ ቀስሜ ያጣፈጥኩት ሕይወት
ከነለዛው ተረስቷል
የታመምንለትን ውበት
ሕመማችንን ሳይቀር
ሕመሜ ቢሽር ያለ ይታከምበታል

ከበላዬ ካረፈ አለት ላይ ቀይ ጽጌ
እንቡጥ ቀይ
ከበላይዋ ቢራቢሮ
ከጣዕሟ የሚጋሩ መዋቲያን

የታባቱ ሕይወት
አንዳንዴ በርረን ከማንጨርሰው መንገድ
ለቀሰማ አረፍ ብለን
ከክንፋችን ብርሃን እየተፋን
ስናስበው
ሞት የላቀ ጣዕም አለው።
ከበተንነው ቅንጣት መሐል
ሕይወት ሲያብብ አይቻለሁ!

መዋቲ ዓለም ውለታ ቢስ ነው
ያለመንካት
አይቶ ነገሮ ሕልም ይሰብራል

ደጃፉ ላይ
ለዐይኑ ረሃብ
ለዐይኑ ጥም የተከላትን ጽጌ
በተከለበት እጁ ይቀጥፋል!
👇🏾
👍5🤩2
ከዚህ ከመዋቲው መሐል
አዲስ ዓለም አዲስ ሕይወት
ከሕይወት ሰፈፍ ወለላ ደግሞ አዲስ ሞት

ግን የታባቱ ሕይወት
አንዳንዴ በርረን ከማንጨርሰው መንገድ
ለቀሰማ አረፍ ብለን
ከክንፋችን ብርሃን እየተፋን
ስናስበው
ሞት የላቀ ጣዕም አለው።
ከበተንነው ቅንጣት መሐል
ሕይወት ሲያብብ አይቻለሁ!

I make things of, sweet flavor
But my sweetness is yours

[As simple a thing as admiring
Can shift the world
And the hand that breaks us
Is the hand that we hold

From the ashes,
Comes a new birth
And of sweetness of birth
Another death]

©Markos
4👍2🔥2
Here is the July edition of Gitem Sitem's Open Mic Circle of Fun and Poetry at @shiftafoods for you all to warm up in this rainy season!

Entrance: 50 ETB
Sign up: 6pm
Show starts at 6:30 pm

ሰኔ ሊገባደድ ባለበት የወሩ የመጨረሻ ረቡዕ ላይ ሽፍታ ጎራ ብላችሁ የግጥም ሲጥም ክፍት መድረክ ጋር ግጥም እንድትሞቁ ተጋብዛችኋል!

መግቢያ 50ብር ብቻ
12 ሰዓት ላይ የሚያቀርቡ ሰዎችን እየመዘገብን ልክ 12:30 ሲሆን ዝግጅታችን ይጀመራል።


https://t.me/GitemSitem
2👍1
Forwarded from Event Addis Media
የመጽሐፍ ምርቃት!

የገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ (አስቱ) "ወደ ነገን ሒያጅ ነኝና" መጽሐፍ ምርቃትዐዐ የፊታችን ሰኔ 28 (ማክሰኞ) ከ11:30 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ይመረቃል።


https://t.me/EventAddis1
👍2
ቀኑ ፥ መሸት መሸት
ጀምበር ፥ ሸሸት ሸሸት

ምሽቱም ጽልመት - እንደወለደ
ሻማ ብለኩስ፥
አልቆመም በእግሩ ፤ ተንገዳገደ።

አንስቼ ባ'ፍጢም - ብዘቀዝቀው፥
እንባውን ቁልቁል - አንዠቀዠቀው።

ከፈሰሰው ጋር፥
ተጣብቆ ሲደርቅ - ባለበት ፀና!
በእንባው የቆመ - አይወድቅምና።

©ሚካኤል ምናሴ

https://www.facebook.com/micky.minassie
8👍1🔥1
Join us Saturday evening 6-8PM @ Malaika African Grill for a Pan African Open Mic session with Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም

As usual we kick off with movement to break the ice & release the butterflies by Heran's Yoga followed by Heran's Poetry.

We have an English line-up with poems & songs for the first 1/2 & prepare to be surprised with Open Mic in any language & any format for the second half of the program.

Malaika African Grill provides the space, the drinks & finger foods, barbecue, grill & vegan options.

Also will there be African-made design bags by ደግ ፳፯ ፋውንዴሽን - Deug 27 Foundation and African clothing for sale.
👍1
Confession

Taker of life, murderer i
Stifled an infant
That would've grown
Grown up to fly
From flower to flower
As a butterfly
Beautiful forever
For more bloom yet
To please my eye

On a leaf of mint
Was a tiny caterpillar
i didn't see
That i dipped …
.
. . into hot tea
.
Oh, shame on me!

©Roman Tewolde

https://www.facebook.com/profile.php?id=1009126277
3👍1
Forwarded from Woini Creatives
Get ready for an exciting challenge launch #7daysfidelchallenge starting from July 16-22 rules will be posted tomorrow.
Stay tuned!!
.
.
.
.
.
#7daysfidelchallenge
#fidelchallenge
#funwithfidel
#fidelwithwoini
#illustration
#typographydesign
👍1
Forwarded from Woini Creatives
Fidel Scavenger Hunt

@Woinicreatives got an exciting community challenge for all challange lovers out there.

The Game is simple. We will announce the Fidel of the day (Amharic letter of the day) and whenever You find that letter through your day, we want you to take a picture of it sent it to @woinicreatives.

And also use #funwithfidel whenever you post. So that we won't miss it 😉

Whoever did it for 7 days consecutively and has more likes, wins amazing prices 🥳 Easy right??

3 Winners will be selected. Winners will get one of @woinicreatives Arts,Tshirt or Coasters on July 23.

So who is ready??? 😁

Stay tuned for Day 1 competition on Saturday July 16th.

For more info, check out @woinicreatives

#Funwithfidel
#woinicreatives
Forwarded from Everted (Kalkidan Everted)
Somedays
It takes my soul a number of existence
A number of lives
Within her
The old lady with a woven past around her neck
Within him
The young boy drunk in youth
Within it
A wasted dream
Within God himself
In flesh trying to fit into the skin of man

And
Somedays
It takes closing my eyes
Taking off all that skin and flesh

And there
I find myself
A pure energy

Until I have to be human again
እሸሻለሁ! ከብዙ ነገር....

ከሞት እሸሻለሁ። መኖር ያስበረግገኛል።
ከማጣት እሸሻለሁ። ማግኘትን እሸሻለሁ።  እሷን እሸሻለሁ። ከእሷ መለየትን እሸሻለሁ።
አካል ለበስ ፍርሃት ነኝ። በመፈለግና ባለመፈለግ መሐል ሰፋሪ ነኝ። ምናልባትም መሸሽን መኖር ብዬ የያዝሁ.... ጉዞዬ ክብ መሆኑን አልታዘበውም። የምሸሸውን ዞሬ ከፊቴ ሲመራኝ አገኘዋለሁ። ወደሽሽቴ ጉያ ሮጣለሁ።
--------------------------------
የገፋሁት ገላዋ ከሩቅ ውልብልታው ይታየኛል። የሚታየኝ ጀርባዋ ይሁን ፊቷ አላውቅም። እየሄደች ይሁን እየመጣች እንጃ ..... ብቻ አያታለሁ። እርግጠኛ የምሆነው እሷነቷ ላይ ብቻ ነው። በፋናዋ የምለያት ናት።
ዝም ብዬ ሚራዧን እታዘባለሁ። ሌላ አይነት ሽሽት፤ ዝምታ! ስሜት አልባ መታዘብ። ፋናዋ ይቀርበኛል። በዝምታ ርቀዋለሁ። ይርቀኛል በዝምታ አቀርበዋለሁ። 
-------------------------------
የሽሽት ሥጋዊ ገጽታ ነኝ።
እሸሻለሁ!
ፖለቲካ ያንገሸግሸኛል። ።ኮሚዩኒዝም ሆነ ካፒታሊዝም ከኮረዳ እቅፍ ይልቃሉ? ከጠይም ሳቅ ይገዝፋሉ? የጥርሷ መገለጥ ከአብዮት ፍንዳታ በላይ ብርሃን ይፈልቅበታል። ከእዚህች ልጅ ፍቅር የሚበልጥ ሪቮሉሽን አለ? እንጃ... መጽሐፍቱ ከቨር ላይ ያለው ራሰ በራው ሠውዬ ያ ኢሊች ሌኒን የሚሉት ይህቺን የግራ ፖለቲካ ያልተጠመቀች ሣቅ ርዕዮተ ዓለሟ የሆነች ጠይም ሴት አያውቃትም።

ወደምንቀው ፖለቲካ በሽሽቴ ተጠለፌ እወድቃለሁ። ለማንቋሸሽ በማነባቸው ቀያይ እና ቡላማ የኮሚኒስት መጻሕፍት የጭቆና ተንታኝ እሆናለሁ። ግን አይነግሩኝም አየህ የድሃ ሀገር ፖለቲካ መሠረቱ ጭቆና እንደሆነ...! ከቨራቸውን አሳምረው ሽታቸው ወርቅ የሆነ እነዛ መጻሕፍት በምሸሸው ነገር እየተሳብሁ እንደሆነ... መፈለጌን እና አለመፈለጌን እያስተሳሰሩ ዳያሌቲክስ ቅብርጥሶ በሚል ትብታብ ሥር አሰማምረው ሲጽፉልኝ ይሄን አይነግሩኝም። ግን እንደነሱ ዳያሌክቲክስ ብናወራ እውነትም የምሸሸውን እየተከተልሁ ነው።
---------------------------------
እየሄደች እንደሆነ አስብና ልቤ ይፈራል። ልቤን እንዲሸኛት ስልከው አብሮ ይቀራል። የቁራ መላክተኛ ነው። ይዘሽ ነይ እንድላት ታክቲክ መሆኑ ነው። እንዴት ሠው በአንድ ገላ ሁለት ይሆናል! ትንሽዬ የራሴ ዳያሌክት ፈጠርሁ ማለት አይደል?
እያየኋት ይህቺን በውል የማትታየኝን ፊት ትሁን ጀርባ ፌርዌል እሰድላታለሁ።

Bella Ciao!
ደህና ሁኝ ውቢት!
----------------------------------------
መሸሼ አይቆምም!
ሕዝብ መሆን እሸሻለሁ። መቆዘም ወደሚመርጥ ባለትልልቅ ቡትሌ ድራፍት እና የፈረንጅ ካቲካላ ቤት እደበቃለሁ። ሶበር ሆኜ ያራቅሁትን ሕዝብነት ከእኔን መሰል ድንጉጥ ግለኞች ጋር ተቀላቅዬ የጠርሙስ ማሕበር እፈጥራለሁ።
ሌላ ሕዝብ!

ቺርስ! ግጭ! ስለፍርሃት እንጠጣ።
---------------------------------------
እሩቅ የማያት ፋና ምናልባትም ታክቷት የቆመች፤ ያቀፍኋት። ያቀፈችኝ። እሷ! የእስከለመይቴው ፍላጎቴ የዘለዓለም ሽሽቴ እየሄደች ነው! 
ብጠየቅ እንዳላጣት ነው የተውኋት ብዬ እዋሻለሁ።
ምናልባት ልክ እሆን ይሆናል። ዞሮ መሞት ካልቀረ አይነት ይህቺን ዕድሜ የሚሏትን ጳጉሜ ታህል ዘመኔን ባለመኖር መግፋት....! ተስፋን መጣል!

ፋናዋ አይንቀሳቀስም። ፊቴን አዙሬ ብራመድ እየሄደች የማያትን እየመጣች እንደማገኛት ከመንገዴ አውቃለሁ። የክብ ተጽዕኖ አለብኝ!
----------------------------
እሰናበታታለሁ!
ደህና ሁኚ ውቢት!
በምሸሸው እቅፍ እወድቃለሁ
መኖሬ ስለሞት እንሆነ አውቃለሁ

የማይቀር ሽሽቴ ሲወስደኝ
ከተራራው አናት ላይ በአበቦች እቅፍ ቅበሪኝ

ደህና ሁኚ ውቢት!
ተረኞች በዚያ የሚልፉ
ወደሚሸሹት ሚጣደፉ

ወጪ ወራጁ ሁሉ አበባውን እያስተዋሉ
መውደቄን ውብ ነው ይላሉ

እዪልኝ ይህንን ክቤን ፈርሶ ሌላ ክብ ሲሰራ
የምሸሸውን ሞት ሞቼ የምሸሸው ሕይወት ሲዘ'ራ።

Bella Ciao!

Cheers! ስለመሸሽ!
👍42
የሽፍታውን አስራስድተኛ ክፍት መድረክ በመታደም፣ በማቅረብ፣ በአጋርነት እንዲሁም የምንሸልማቸው መጽሐፍት በመስጠት ያጣማችሁልን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ!

ከጊዜም ከቦታም እንዲሁም ከቅርጽ አንጻር የሚመቻችሁን መርጣችሁ የምትታደሙባቸውን ልዩ ልዩ አይነት መድረኮች ይዘን በቅርቡ በተለያዩ መልኮች የተላያዩ ቦታዎች ላይ እንከሰታለንና እንድትከታተሉን ይሁን።

Big thanks to those who attend, performed at and supported our 16th Open Mic night at Shifta.

Stay tuned to our channel and pages for more updates on our upcoming events crafted in different ways for you choose the one that suits you in terms of format, time or location.
11👍1