ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
[ አዲስ ንጋት ]
:
ቀስ
ቀስ
ቀስ ቀስ
ሄድ መለስ
እጥፍ ዘርጋ ሰበር ሰካ፣
በውዴታ
አንቺን ዕይ‘ት አንቺን ነካ፣
አመድ ገፄ
በ ፀዳልሽ እስኪፈካ፡፡

ፍክት
እርክት
ደስታን ንክት

ደግሞ
አንዴ ቆም
ከመወዝወዝ
ከመናናጥ ለአፍታ እርፍ፤
ዝለታሙን
መታከቴን ጥልት እንትፍ፤
ከእርፍታ አፀድ
ከእፎይ ዛፍሽ ብርታት ቅጥፍ፡፡

ቅጥፍ
ቅጥፍ
እርፍ
እርፍ

እርግፍ፣
እርግፍ የክፉን ግፍ፡፡

እንትፍ
እንትፍ
ብርታት ሲገኝ
ዝለትን ጣል ብሎ ሀክ እንትፍ፡፡

ደግሞ እንዳዲስ
ላ‘ዲስ ማረፍ
ሄድ መጣ ወረድ ወጣ፣
ድብርታሙ ድባቴዬ
በሀሴት ጅራፍ እስኪቀጣ፣
ለእርካታዬ
አዲስ ንጋት
አዲስ ፀሐይ እስክትወጣ፡፡

ዕልም
ዕልም
በራስ መንደር በራስ ዓለም፣
ንጋት ማየት ነገን ማለም፡፡

ዕይት
ቅኝት
ልይት
በአዲስ ዕለት
ፅልመት ገድሎ
ንጋት ወልዶ ተስፋን መሳብ፣
ከፍ ካለው
ከከፍ እርካብ ከመንፈስ ካብ፣
ተስፋ አግኝቶ
ዛሬን ዐይቶ ነገ እንዲሳብ…!!

©️ዳግም ሔራን
ኤልያስ ሽታኹን
*     *      *     *     *
አሳቢያን
ፍቅር የለም ባይ ናቸው
በቃ እኔ አላስብም
"አፈቀርኹላቸው"
ፈላስፎች
የተጋባን ሁሉ
"ዘይትና ውኃን
እሳትና ብረት
ይመስላሉ" 
አሉ፡፡
አፍቃሪያን ደሞ
"ዘይትና ውኃም
እሳትም ብረትም
ተዋህዶ አይተናል
በዕውቀት ለሚኖር ይህ እንዴት ይገባል?"
(ብለናል)
ፈላስፋ ሰልፍ ወጣ
ፊሀፊ ሰልፍ ወጣ
አሳቢ ሰልፍ ወጣ
"ፍቅር የለም" በሚል መፈክር  ሸክፎ
አፍቃሪ ግን የለም ከሚስቱ  ተቃቅፎ፡፡


*     *      *    *      *       *     *     *    *
(ኤልያስ ግን የለም ከሚስቱ ተቃቅፎ)
Forwarded from LinkUp Addis
We are opening up our platform for content creators!
If you think you are a skilled writer and if you have blog articles you have written on social commentary, fashion, lifestyle, entertainment, music, films, etx. submit them via our email linkupaddis@gmail.com or submit them to @linkupaddisofficial.
If they meet our editorial guidelines, we will put them up on our website and our other platforms. @linkupaddis
We perish as if we were never here.
May be now
May be later...
Nobody knows.
And the one thing we often do
Is die for a better cause.

We build up a lot just to let it go
We learn too much gibbrish
And spend the rest of our lives trying to unlearn it.

It's all a process of leaving behind and growing apart.

I, am growing apart from myself.
[After all the greatest war fought is, between man and himself.]

We Perish as If we never existed.
And we let go of those who leave
As if, we never notice them missing

We kill and dance,
We die and chant...
We smile as we perish.
It all lies on finding a purpopse..
A purpose, after achieving one.
A purpose after a purpose.
A purpose deconstractimg the first one..
Unlearning everything.

We live to draw lines and then spend time widening them
Or erasing the lines and limit ourselves with excessive freedom.

We let go of what we've been seeking desperately.

[If you ask me,
I would never die for anything,
I don't even get to live well for my self.

And to be honest death is overrated,
Cause the bravest thing you could do is live.]

We perish and be forgotten
In the roads of existence
We are walking towards Nothingness.

And knowing that might make see something,
Like all we can do is
Just live life for the sole purpose of living.

We perish and we know.
So we smile through it
Cause the bravest thing we could do,
Is live.

#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#To_the_oblivion
Follow us on Instagram! Username: gitemsitem
https://www.instagram.com/gitemsitem?r=nametag
እኔስ ንግር የለኝ ታሪክም አልሻ
ትንሽ ስፍራን እንጂ ከአለም መሸሻ
አሜን ለአርምሞ
አሜን ለምናኔ
አሜን ለደናግል
አሜን ለመነጠል
አሜን ደግሞ ለቃል
ሰማይ ለዘረጋ
ለለበሰ ስጋ
አሜን ደግሞ ለሰው
በፍሬ ለሳተ
በምርጫ ለሞተ
አሜን ለሴቲቱ
ከእባብ ለተጣላች
አሜን ለመሀፀኟ
ጌታን ለወለደች
አሜን ለመልአክቱ
በነጋ በጠባ ለሚላላኩቱ
አሜን ደግሞ ለእኔ
መሀል ለተገኘሁ
ከግራ ያለውን ከቀኝ ለምዳኘው
አሜን ፈጣሪ ነው

©️Feben Fancho
2
ሰባተኛውን የክፍት መድረክ ክበብ ይዘንላችሁ መጥናል!
እሮብ 12 ሰዓት ሽፍታ ብትገኙ እስከ 12:30 እንመዘግብና በሰዓታችን እንጀምራለን። መድረኩን በእናንተ ድጋፍ ለማስቀጠል ስንል የምናስከፍላችሁ 50 ብር ብቻ ነው።
እስክትስቂልኝ ነው

(አስቱ)

…ፈገግታሽ ነው እንጂ
አኩርፎ የኖረውን ሰውነት ያፈካው፤
ጨዋታሽ ነው እንጂ
ታስሮ የከረመውን አንደበት የነካው

ቁልምጫሽ ነው እንጂ
አልያዝ ያለውን ስሜን ያ_(አስታወሰኝ)፤
ደግነትሽ እንጂ
ሞልቶ ያስተረፈኝ ኪሴን የቀደሰኝ

ምን አለኝ ከ ኩርፊያሽ- ምናለኝ ከቁጣሽ፤
ጠልቼሽ አደለም
እስክትበርጅልኝ ነው እስክትስቂ ልጣሽ

የክፋት ጎመራ ውስጤ ሲንበለበል፤
በዘምዘም ብነከር በፀበል ብፀበል
.
አለቅህ ያለውን
አልተውህ ያለውን
.
ፀባይሽ አደል ወይ ደርሶ ያላቀቀኝ፤
ታዲያ ግፍ አይሆንም
ካንቺ ሌላ ባዜም ካንቺ ሌላ ብቀኝ!
……
ምንአለኝ ከኩርፊያሽ _ምናለኝ ከቁጣሽ፤
ሌላ አምሮኝ አደለም
እስክትስቂልኝ ነው እስክትበርጂ ልጣሽ

ያቀልድሽ ነው እንጂ
ከደነዘዝኩበት ኮርኩሮ ያሳቀኝ፤
ትንፋሽሽ ነው እንጂ
ያንዘፈዘፈውን አካሌን ያሞቀኝ

…መቸም ታውቂዋለሽ
ድንጉጥ ነው መንፈሴ ፈሪ ነው ልቤ እንደው፤
ታዲያ እንዴት አድርጌ
ቁጣሽን ልልመደው ኩርፊያሽን ላብርደው!?
…………
……
ምናለኝ ከኩርፊያሽ _ምንአለኝ ከ ቁጣሽ
ጠልቼሽ አደለም
እስክትበርጂልኝ ነው እስክትሰክኚ ልጣሽ።

©️አስቱ
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንዲህ ድንቅ የሆነ የመላኩ፣ የአስቱ እና ኪሩቤል ጥምረት አምልጧችሁ ነበር!

የዩቲውብ ቤታችንንም ሰብስክራይብ በማድረግ ግቡና ቤተኛ ሁኑ👇🏾

https://youtu.be/9hKHLSCJ6sI
ሰላም ወዳጆች

አዲስ ነገር እያመጣንላችሁ ነው! ኢንስታግራም ላይ ያልተቀላቀላችሁን ብዙ ሊያመልጣችሁ ይችላል፣ አብዛኛውንም እዛ ላይ እናካሂደዋለን።

በዚህ አዲስ ነገር ከምናካትታቸው ነገሮች አንዱ የሳምንቱን ግጥም መምረጥ ነውና በተለይም በዚህ በሶሻል ሚድያው ላይ ብዙዎች ጋር በመድረስ የበለጠ ተጽዕኖ መፍጠር የቸለ፣ የቆየም ሆነ የቅርብ ሆኖ ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተገጣጥሞ መነጋገሪያ የሆነ፣ በርካታ የግጥም ወዳጆች የተቀባበሉት ወይም በብዙዎች የተጠቆምነውን ግጥም የሳምንቱ ግጥም ብለን ልናጋራ ተዘጋጅተናልና እንግዲህ አግዙን። እስቲ እንደ ማሟሟቂያ ያለፈውን ሳምንት አስባችሁ የሳምንቱ ግጥም የምትሉትን ጠቁሙንማ።

https://www.instagram.com/gitemsitem/
ጥቅምት 5 የፊታችን አርብ ከ11 ጀምሮ
"ቃል ና ሀሳብ" የስነ-ፅሁፍ ምሽት
ቦሌ ሚካኤል ከሩዋንዳ ኤምባሲ ዝቅ ብሎ ታክሲ ማውረጃው ጋር
"ጓዳ ስጋ ቤት"..በገጣሚያን እና ደመቅ ባለ ልዩ ዝግጅት ይጠብቃችኋል ።
ለበለጠ መረጃ
0987367513

@gitemsitem
Forwarded from ኩነት - Kunet
BlueSpace is hosting the second edition of Arif Poetic Night, a night of poetry performances on Wednesday 13 October 2021. Doors will open at 6:00pm. This event does not have entrance fee. @linkupaddis
ጥቅምት 5 የፊታችን አርብ ከ11 ጀምሮ
"ቃል ና ሀሳብ" የስነ-ፅሁፍ ምሽት
ቦሌ ሚካኤል ከሩዋንዳ ኤምባሲ ዝቅ ብሎ ታክሲ ማውረጃው ጋር
"ጓዳ ስጋ ቤት"..በገጣሚያን እና ደመቅ ባለ ልዩ ዝግጅት ይጠብቃችኋል ።
ለበለጠ መረጃ
0987367513

@Gitem_Sitem
@gitemsitem
1👍1
Forwarded from LinkUp Addis
Tune in to LinkUp Addis's Instagram page starting Monday 18 October 2021 and join our live shows every evening.
We will be livestreaming LinkUp Addis's original shows live on Instagram.
@linkupaddis
« ያልተመለሰ አንጓ ..!
---

መቃብሩን አቀፍኩ ፣ ሳምኩት መቃብሩን
መለየትን አየኹ ፣ አየኹ የሞት በሩን
አየኹ የሞት ጥላ ፣ አየኹ የሞት ጉዝጓዝ
አንቺን ተከናንቦ ፣ ሣቅ ወደ'ኔ ሲጓዝ ።

ለሚል ታካች ገላ...!

አፈር አንከባሎ ፣ ወደ ሞት ቁልቁለት
አፈር ሰውነትን ፣ አፈር ኹን ያለ ዕለት
«ተው» የማይባል ሞት ፣ ቁም የማይባል ቀን
በእንባ ስንጠብቀው
በሣግ ስንጠብቀው ፣ በሣቅ ሰነጠቀን ።

አጀብ ነው አንቺዬ..!

ሕይወት ‟ግብረ - መልኩ” ፣ ካንቺ መለያየት
የመኖር ‟ጣር - ልኩ” ፣ ካንቺ መወያየት
ተወዲያ ተወዲህ ፣ ቁሞ መተያየት
እንደ ገሳ ግምጃ ፣ እንደ ቀትር ጀንበር
አልገለጥ አለ
መኖር ማለት ኹሉ ፣ መሞት እንደ ነበር ።

አልገለጥ አለ
በቀን በሸፈነው
በጋረደው መዝገብ ፣ በሸሸገው በኩል
ፈጣሪው 'ራሱ
እስከ'ሚሆን ድረስ ፣ ሞት ከሚለው እኩል ።

©️ሶሎሞን ሽፈራው

@GitemSitem
👍2
Forwarded from አድማስ Book Delivery (Mele😋)
አታንብብ
ምክንያቱም
ማንበብ ጥርጣሬን ይፈጥራል እምነትን ይሸረሽራል (ያላወቅነው በተገለጠልን ቁጥር የማናቀው እንደሚሰፋ ስለምንረዳ የያዝነውን መጠራጠር እንጀምራለን)

ምክንያቱም
ማንበብ ያፈላስፋል (የ 'ለምን' ጥያቄን ይደረድራል)

ምክንያቱም
ማንበብ ያሳብዳል(...)

ምክንያቱም
ማንበብ ከማህበረሰብ ያስገልላል...

ምክንያቱም
ማንበብ ከሃይማኖት አስተምህሮ ያቃቅራል (ስታነብ የበለጠ ማወቅ ስለምትፈልግ በማመን የሚታለፉ ረቂቅ ሃሳቦችን በጥልቀት ለማወቅ በሚደረግ ትግል የእምነት ሚዛን ይዛኘፋል ለዚህም ነው ያወቁ ያነበቡ ሰዎች ለኑፋቂ ወይም ለክህደት የተጋለጡ የሚሆኑት)

ዝም ብለህ አንብብ!

ቢያንስ ጥያቄህ ምክንያታዊ እንዲሆንና የማይወላወል የፀና አቋም እንዲኖርህ ንባብን ምርጫህ አድርግ!
ከንባብ ለመራቅህ ምክንያት አትደርድር🙌

ማንበብ የሚፈልጉት መጽሐፍ ካለ ያናግሩን ቅርብ ከሆኑ በአካል ራቅ ካሉ በፖስታ ቤት ያሉበት እናደርሳለን!
ለስምንተኛው ክፍት መድረካችን የሚቀርበውን አዘጋጃችሁ?
ብታቀርቡ በደስታ ብትታደሙም በአክብሮት እንቀበላችኋለን - እናንተ ብቻ ኑልን!

የፊታችን ረቡዕ 12 ሰዓት ላይ ምዝገባ እንጀምርና ልክ 12:30 ሲሆን እስከ 2:30 የሚቆየው ዝግጅታችን ይጀምራል

ሐያት ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ሽፍታ Shifta እንተያይ

@PoeticSaturdays @aradaet

@LinkUpAddis @Ramapicture

@FebenFancho @SeifeTemam @Mcholmes


#gitemsitem #LinkUpAddis #PoeticSaturdays #feben_fancho #Arada #Shifta #Poetry #artinaddis #poetrylovers