ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እኔ እና አንቺ

አንቺ ማለት ጸሃይ፡ እኔ ጨረቃዋን
ባንቺ ብርሃን የምፈካ፡ ባንቺ መጥፋት የምባክን
አንቺ ሙሉ አለም፥ እኔ ትንሽ ድንኳን


ኢብራሂም አብዱ

@Ibrocr7
ጊዜ
በሰኮንዶች ድምር በደቂቃ መሄድ
በሰአታት ማለፍ በቀናቶች መንጎድ
በወራት መተካት በአመታቶች መክነፍ
በጊዜ ሽቅድድም በወቅታቶች ማለፍ
አካልም ይደክማል ደጋፊውን ይሻል
በወጣትነቱ የዘራውን ያጭዳል
ባሳለፈው ትላንት ጊዜ ፈራጅ ሁኖ ዛሬ ላይ ይቀጣል።

እምነት

@Enku41
የይሁዳ ከንፈር

ስለ አንተና እኔ
ትንቢት ባይፃፍም ነብይ ባይናገር
ልትሄድ መምጣትህን ልቤ ነግሮኝ ነበር

አንተ ይሁዳ ሆነህ
እኔ ሆኜ አምላክ

ባላንጣህ ባይገዛኝ በ"ዲናር" ባትሸጠኝ
በመጨረሻ እራት በመሳም ሸኘኸኝ...

በምህረት
ሐምሌ /2013ዓ .ም

@mihretengida
.................ፀ*ፀ*ቴ*
አዎን ፀፀቴ ነህ ንስሀ ያስገባኸኝ
ካምላኬ አጣልተህ ካምላኬ ያስታረከኝ
ጥፋቴን አልወቅሰው መርቶኛል ወደ
እውነት
ተመርጫለሁኝ ለትልቁ ደስታ በትንሹ
ክፋት

@Mekdiyemariyam
!?!
እርምጃችን ሁሉ ታንፆ በስጋት
መራቅ ለመጠጋት
ባዶ ተስፍ መጋት
ጀንበርን መናፈቅ እየሸሹ ንጋት
ምን ይሉት ነው ደግሞ?
ለመድረስ መጓጓት እርምጃን አቁሞ

✍️ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )

@Tufaw_muhe
ሠው ምንድን ነው

ታስበው ዘንድ ብሎ መዝሙር እንደፃፈው
ትመረምረው ዘንድ ብሎ እንደቀጠለው
እኔም ልጠይቅህ የሠማይ ፈጣሪ
የብርሃናት አባት የምድርም ቀማሪ፤
እድል ፈንታው ፈቅዶ ሞትን የሸለምከው
ይሄ ያንተ አምሣል፤ ጌታ ''ሠው'' ምንድን ነው?


26/11/13
ገጣሚ : ዳዊት:ጥዑማይ

@faberfortunae
፠ሰመመን፠

ሲቃ በሚንጠው በጠቆረ ሰማይ
በዋይታ እርይታ በስቃይ ላይ ስቃይ
በትዝታ ጭሰት ጭስ በሌለው ንዳድ
በብቸኝነት ውስጥ በባይተዋር ጉድጓድ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፋቅርን ተሸክሜ
በቀቢፀ ተስፋ ላይቀለኝ ደክሜ
አለሁ!!
አለሁ እንዳለሁኝ ሞቼም አገግሜ፡፡

✍️መሊኩ [ MAJNUN ]

@Bufal
ኑ !ወደ ነፃነት እንንጎድ
እፍ እያልን
በጭስ እንባ ሳናባክን
ኑ !ለነገ እንንደድ
ኑ።

(ኤደን ሙሉነህ)

@Oritethe
መሪ ቃል

ባይሆን እሮጣለሁ፥
በዘመን ሜዳ ላይ፥ በሰው የመሆን መም፤
ባይሆን አሸንፌ፥
አውለበልባለሁ፥ የልቤን ባንዲራ፥ የ'ኔነቴን ቀለም።
ካልሆነ ግን...
ለመሮጥ የሚሆን፥ ቢያንሰኝ እንኳ አቅም፤
ሯጩን ላለመጥለፍ፥ መሙ ላይ አልወድቅም።
......የዘመኔ ምስል.......
ጉልበት ሳይዝል፤ ልብ ደከመ
ስጋ አብቦ ፤ ነፍስ ቆዘመ
በምጥ መሀል፤ ባለች ፈገግታ
ስንቱ ታለለ ፤ ህይወት ተረት'ታ. ..!!
(ነብዩ.ብ)
ቤት የለኝም

ያም ሰፈር የነሱ ይሄም የእነንትና
የትጋ ቤቴን ልስራ ከማን ልጠጋና
ዘር አልቆጥር ነገር የፈጣሪ ልጅ ነኝ
እንግዲ እኔ አልሰራም ቤቴን ራሱ ይስጠኝ🙏

ያሬድ.የ

@Yjaredy
ከትርምስ መሀል ከኖረ ፀጥታ
በክፉ ቀን መሀል ከበዛ ዝምታ
ያንን ነዉ መተርጎም አንድም ለአንድምታ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita21
1
የእሽቅድድም ህይወት

ግራን አስቀድሞ ቀኝን ለማስቀረት

አንድ አካልን ጥሎ በአንዱ መንኳተት

ሙሉነቱን ጥሎ በግማሽ እየለፋ

በግማሽ አካሉ ሰውን እየገፋ


ቀኙን ማዶ ጥሎ ግራውን እየሣበ
በአንድ አካሉ ማራቶን ያሰበ


@blessedloner
ለመደስኮሩማ ስብከት ለመስበኩ
በወርች ሱባኤ ፍቅርን ለማምለኩ
መምህር መች ሽቶኝ ለወሬ ሽንገላው እኔው መቼ አነስኩ
የቸገረኝ ቢኖር የጠፋኝ ያጠረኝ መፍትሄ ብልሀቱ
የአክስቴን ገዳይ ቆስሎ ከተኛበት ደግፎ ማንሳቱ
በቆሎ ተዘርቶ ኩርንችት ማፍራቱ


@Mahlet_Be
👍1
ትናንት ትዝ እንዳይለኝ- ከራሴ ጋ ማልኩኝ

ትናንትን ስረሳ- ለዛሬም አልኖርኩኝ

ካላየሁዋት የነገ ፀሐይ ተወዳጀሁ

እምነትን ይዤ ለተስፋ ደገስሁ

ከዛማ... በተከራየሁት የጊዜ ሰሌዳ
እኔ ሆንኩኝና የራሴ አለቃ፣ ቀጠሮን ቀጠርኩኝ

ነገ ዛሬ ሲሆን ደሞ ላባርረው

አዲስ ቅዠት ልቃዥ፣ የፈረደበትን መልሼ ልቀጥረው


@Mtesfaye7
.......የሞኝ ኑዛዜ......

ፈውስማ አለፈኝ፣ ምክኒያት ደንታን አልፎ
ተቅበዝባዥ አረገኝ፣ ከፍርሃት እብደት ተርፎ
ሃሳቤ ራስ ስቶ፣ ንግግሬ በዝቶ
ይገላምጠኛል፣ እውነቴ ተብቶ
.
ውብ ብያለሁና፣ ደማቋ ደመራ
ጭልም የሆንሽውን፣ የግሃነም ጮራ።


-ኖኔም
መንታ ፍልስፍና....

የሚንከራተተው ያ'ዳም ዘር በሙሉ:
ሲዳፋ ሲቃና ሲዋትት መዋሉ:
የመፈጠሩን ቅድ ሊደፍን ነው አሉ።



@NikoTheGreat
ወዲህም
ካየሽ ፈሶ ደም
ወዲያም
ካየሽ ፈሶ ደም
ሌላው ሌላው ቢቀር
"እኔን"ንን ለማለት ፤ አፍሽ አይሎገም
።።።።።።።።።።።።።።።፡።።።

ሳሙኤል አለሙ

@Samuelalemuu
መልካም ዜና ለሱ ሀዘኔን ላልካሰኝ
ሳላለቅስ የቻልኩት ለ"ምነው?" ሆድባሰኝ
ስወጣ ጠንካራ ተደብቆ አልቃሻ
(ተብረክርኮም መቆም፤ቢዝልም ትከሻ)
ሲፈሩት ይደፍራል ሃዘን እና ውሻ!


@Guadyeee
"ህይወት....🤔 ጢባ ጢቤ..."

ከፍታ ላይ 'ምታወጣ
አንዲት ቅጠል ጥላ ትታ!
አልያም ደ'ሞ የምትጥል
ትንሽ ድልን አስገኝታ!!
ወይም ደሞ..የለገመች...
ከፍ ላትል ላትረታ
ለሞከሯት.. ጠዋት ማታ!!!

@ZionismT
👍1