ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ለግጥም ሲጥም የቴሌግራም ቤተሰቦች በልዩነት የተዘጋጀ የአጭር ግጥም ውድድር!!!

ወደ ዳሞቻ ተራራ የሚደረግ ጉዞን የሚያሸልም

ደንብ እና ሁኔታዎች
———————
1. ተወዳዳሪዎች የቴሌግራም ቻናላችን ተከታይ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተወዳዳሪዎች ግጥማቸውን እራሳቸው በቀጥታ በቴሌግራም ወደ @seifetemam እስከ ሐሙስ ለሊት 6 ሰዓት ብቻ መላክ ይኖርባቸዋል።

3. ተወዳዳሪዎች ከ 18 ዓመት በላይ መሆን አለባቸው።

4. ግጥሙ በማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ መሆን ሲችል ከ8 መስመር ያልበለጠ መሆን አለበት።

5. የተወዳዳሪዎቹ ግጥም በቻናሉ ከተለጠፈበት ሰዓት አንስቶ እስከ አርብ 6 ሰዓት (ከቀኑ) በብዙዎች የተወደደው ግጥም አሸናፊ ይሆናል።

መልካም ዕድል!

#ግጥምሲጥም #ዳሞቻ #ማትሪፕ #ጉዞ
A poetry contest for Gitem Sitem's telegram family!

With a chance to win a hiking trip to Damocha!

Terms and Conditions
———————
1. The contestant must be a member/follower of our channel.

2. The pieces should be submitted by contestants via telegram to @seifetemam until Thursday midnight.

3. Only those who are 18 years old and above are eligible.

4. There is no specific theme or topic for the contest but it should not be longer than 8 lines.

5. Poems with most likes until Mid day Friday will be the winner.

Good Luck!

#gitemsitem #damocha #ma_trip #hiking
😫ችግር😩
ችግር ይበርታ እና ይቸግር ጠንክሮ
ስልጣኔም አይዘግይ÷አያብዛ ቀጠሮ
ችግር ፈቺ ትውልድ ነገ እንዲኖረን
ችግርን ማግነን ነው ዛሬ የሚያስፈልገን🤔🤪
✍️ህሊና

@Hilina70
ኅልቆ - ሸለፈት
-------------------
የሚገለማ ~ ስጋ ታቅፌ
በምን ብልኃት ~ ልኑር አርፌ
ጥሎብኝ ቁልፈት ~ ክፉ ሸለፈት
ከላዬ ሰፍፎ ~ ልክ እንደ ገፈት
ዛሬ ብቆርጠው ~ ነገ ሊመዘዝ
ስንቴ ልቀንጠብ ~ ስንቴስ ልገረዝ?

#ዮናታን

@yonii_boss
የትም ቦታ ይጣለኝ
አደባባይ መሀል ቁና ሙሉ ቅማል ስቀምል ያውለኝ
መሪ ምርኩዝ ይንሳኝ
አውላላ ሜዳ ላይ ገደል ገባሁ እያልሁ ስደናበር ልገኝ
በጠራራ ጠሀይ ሚፋጅ አስፓልት ላይ እንደ እህል ልሰጣ
ዶፍ እየዘነበ መሸሸጊያ ልጣ
ታድያ እንዲህ ሲያደርገኝ አትሁኚ ጎኔ
አብረሺኝ ከሌለሽ ገሀነም ራሱ ገነቴ ነው ለኔ

@Fullof_memory
ጥላሸት በጥብጣ ድርብ መርፌ ይዛ፣
ህመሜን እንድችል በአረቄ አደንዝዛ፤
ድዴን ትወቅራለች ፥ ጉራማይሌ ጥርሴን፣
እንጃ ከዚህ ኋላ ፥ እህልም መቅመሴን።
ፈገግታ እየቆጠብኩ ፥ እኖራለሁ እንጂ ፣
እንዲህ ነው 'ሚያደርገኝ ጥለሽኝ ስትሄጂ ።
ጥርሴን ተነቅሼ ፥ ለሳቅ ለጨዋታ ፣
እንኳንስ ከንፈሬ ፥ ግንባሬ አይፈታ።

አስካለ ልቅና

@AskuAn
ቃና : ዘ : ገሊላ_..

በጎደለ : ቀኔ : የሞላውን : ውሀ
ሲያቅረኝ : ለመንኩት : እንዲሆን : አምሀ
እሱም : ቃሌን : ሰምቶ : ወይን : አደረገልኝ
ቀድቼ : ጠጥቼ : ጥማትን : : ሰከርኩኝ
_በል: እንግዲህ_
.....
አገባለሁ : ብዬ : የጠራሁት : ሚዜ : ተሞሽሯልና
ወይኑን : ውሀ : አርግልኝ : ስትመለስ : ቃና...
/***/
ናታን ኤርምያስ

@UniqueDY
እኔ እና አንቺ

አንቺ ማለት ጸሃይ፡ እኔ ጨረቃዋን
ባንቺ ብርሃን የምፈካ፡ ባንቺ መጥፋት የምባክን
አንቺ ሙሉ አለም፥ እኔ ትንሽ ድንኳን


ኢብራሂም አብዱ

@Ibrocr7
ጊዜ
በሰኮንዶች ድምር በደቂቃ መሄድ
በሰአታት ማለፍ በቀናቶች መንጎድ
በወራት መተካት በአመታቶች መክነፍ
በጊዜ ሽቅድድም በወቅታቶች ማለፍ
አካልም ይደክማል ደጋፊውን ይሻል
በወጣትነቱ የዘራውን ያጭዳል
ባሳለፈው ትላንት ጊዜ ፈራጅ ሁኖ ዛሬ ላይ ይቀጣል።

እምነት

@Enku41
የይሁዳ ከንፈር

ስለ አንተና እኔ
ትንቢት ባይፃፍም ነብይ ባይናገር
ልትሄድ መምጣትህን ልቤ ነግሮኝ ነበር

አንተ ይሁዳ ሆነህ
እኔ ሆኜ አምላክ

ባላንጣህ ባይገዛኝ በ"ዲናር" ባትሸጠኝ
በመጨረሻ እራት በመሳም ሸኘኸኝ...

በምህረት
ሐምሌ /2013ዓ .ም

@mihretengida
.................ፀ*ፀ*ቴ*
አዎን ፀፀቴ ነህ ንስሀ ያስገባኸኝ
ካምላኬ አጣልተህ ካምላኬ ያስታረከኝ
ጥፋቴን አልወቅሰው መርቶኛል ወደ
እውነት
ተመርጫለሁኝ ለትልቁ ደስታ በትንሹ
ክፋት

@Mekdiyemariyam
!?!
እርምጃችን ሁሉ ታንፆ በስጋት
መራቅ ለመጠጋት
ባዶ ተስፍ መጋት
ጀንበርን መናፈቅ እየሸሹ ንጋት
ምን ይሉት ነው ደግሞ?
ለመድረስ መጓጓት እርምጃን አቁሞ

✍️ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )

@Tufaw_muhe
ሠው ምንድን ነው

ታስበው ዘንድ ብሎ መዝሙር እንደፃፈው
ትመረምረው ዘንድ ብሎ እንደቀጠለው
እኔም ልጠይቅህ የሠማይ ፈጣሪ
የብርሃናት አባት የምድርም ቀማሪ፤
እድል ፈንታው ፈቅዶ ሞትን የሸለምከው
ይሄ ያንተ አምሣል፤ ጌታ ''ሠው'' ምንድን ነው?


26/11/13
ገጣሚ : ዳዊት:ጥዑማይ

@faberfortunae
፠ሰመመን፠

ሲቃ በሚንጠው በጠቆረ ሰማይ
በዋይታ እርይታ በስቃይ ላይ ስቃይ
በትዝታ ጭሰት ጭስ በሌለው ንዳድ
በብቸኝነት ውስጥ በባይተዋር ጉድጓድ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፋቅርን ተሸክሜ
በቀቢፀ ተስፋ ላይቀለኝ ደክሜ
አለሁ!!
አለሁ እንዳለሁኝ ሞቼም አገግሜ፡፡

✍️መሊኩ [ MAJNUN ]

@Bufal
ኑ !ወደ ነፃነት እንንጎድ
እፍ እያልን
በጭስ እንባ ሳናባክን
ኑ !ለነገ እንንደድ
ኑ።

(ኤደን ሙሉነህ)

@Oritethe
መሪ ቃል

ባይሆን እሮጣለሁ፥
በዘመን ሜዳ ላይ፥ በሰው የመሆን መም፤
ባይሆን አሸንፌ፥
አውለበልባለሁ፥ የልቤን ባንዲራ፥ የ'ኔነቴን ቀለም።
ካልሆነ ግን...
ለመሮጥ የሚሆን፥ ቢያንሰኝ እንኳ አቅም፤
ሯጩን ላለመጥለፍ፥ መሙ ላይ አልወድቅም።
......የዘመኔ ምስል.......
ጉልበት ሳይዝል፤ ልብ ደከመ
ስጋ አብቦ ፤ ነፍስ ቆዘመ
በምጥ መሀል፤ ባለች ፈገግታ
ስንቱ ታለለ ፤ ህይወት ተረት'ታ. ..!!
(ነብዩ.ብ)
ቤት የለኝም

ያም ሰፈር የነሱ ይሄም የእነንትና
የትጋ ቤቴን ልስራ ከማን ልጠጋና
ዘር አልቆጥር ነገር የፈጣሪ ልጅ ነኝ
እንግዲ እኔ አልሰራም ቤቴን ራሱ ይስጠኝ🙏

ያሬድ.የ

@Yjaredy
ከትርምስ መሀል ከኖረ ፀጥታ
በክፉ ቀን መሀል ከበዛ ዝምታ
ያንን ነዉ መተርጎም አንድም ለአንድምታ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita21
1