ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Marumbo is a spoken word artist and poet, whose poetry is deeply rooted in the understanding of Culture, Life, Love and God. He draws deeply from life’s experiences and his observations to create well-meaning and relatable poetry that not only entertains but also educates and raises awareness for the struggles and issues of daily life. These attributes were showcased in an array of contexts in his debut EP Broken Keys and later in a poem titled Poetry in Africa more recently in an EP named ‘Conversations of a broken and mended heart’
He has featured at Lake of Stars, Likoma Festival, Tumaini Festival and Ufulu festival to name a few.

Good luck Malawi!

https://www.facebook.com/1719463041680780/posts/2630974210529654/

#marumbo_sichinga #Malawi #AfricanCupofSlamPoetry #CASP #PoeticSaturdays #poetry #poetryslam #poetrylovers #artinaddis
#AddisAbeba #JulyNovember2021
Forwarded from Poetic Saturdays
Come join Poetic Saturdays at GUAC-ON in Hayahulet this coming Saturday, July 10 2021!

https://www.facebook.com/guaconaddis

Entrance: 100 ETB (includes free Arada)

Please note that this event is 21 and over only.

As usual, we will start registration at 2: 00 pm.
Only perform YOUR ORIGINAL work. The audience is there to listen to your truth!
Each performer gets 5 minutes total. You can perform as many times but respect the time limit.
All languages welcome.
All performance art forms welcome!
We are excited our audiences and honored our performing family is growing. So come by and witness the amazing talents brewing in our city.
Tell a friend!
ዛሬ ለግርምት (ሰርፕራይዝ) የሽፍታው Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም ላይ የሚገኙ በዚህ ዓመት መጽሐፍ ያሳተሙ 3 ገጣሚያን /አጣሚያን/።
የሶስቱንም ስም በትክክል ለመለሱ የመጀመሪያ 4 ሰዎች እያንዳንዳቸው የገጣሚያኑን መጽሐፍት የሚሸለሙ ይሆናል።

በነገራችሁ ላይ የመግብያ ባናስከፍልም መጽሐፍ እንድትገዙ ልንጨቀጭቃችሁ እንችላለን።

PS: We love you
ዳሪክ ጥበባት

ቀለም 🎨

እሁድ ሐምሌ 11/2013ዓ/ም
ከቀኑ 9:00 ጀምሮ
በበቀለ ሞላ ሆቴል አዳማ
አረተኛው የግጥም ሲጥም ነጻና ክፍት መድረክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን 👇🏾ይመስል ነበር።
መኖር

ሲገፉህ ተገፍተህ
ሲያገኙ ሲረሡህ
ስታገኝ ሲመጡ አንድ ያለህን ሠጥተህ።!
ሀዘን ለቅሷቸውን ወደ አን እያጋቡ አንተን ሲያስለቅሡ
ሀዘናቸው ወስዶህ ቀና ሳትል አንተ ሀሴት ነው ለነሡ።
ላጣ ለተጎዳ
ላገኘ ከበርቴ በዲናሩ ብዛት ለሚበላ ፍዳ
ለሁሉም ሠው ሆነህ
ያለህን ትልቁን ክቡር ጊዜ ሠጥተህ
ምንም እንደማይሠጥ እንደ ንፉግ ታይተህ
ማንም ካንተ ሳይሆን አንተ ለሠው ሆነህ
ከማንም ሳጠብቅ ሁሌም እየሠጠህ
መኖር በመኖር ታስተምረኛለህ።
እንዲህ ቃል የሚሆን ነፍስ ያለው አንድ እውነት
እንኳን ካጠገብህ ከየትስ ይገኛል ቢፈለግ ካለበት።
ፈልጎ አለመድከም አግኝቶ አለመርካት
ያው የልብን መኖር ያው የልብን መንካት።!!!
መኖር ነው አንተነት
መኖር ነው እኔነት።!!!!

©️ተስፋልደት በለጠ

https://t.me/GitemSitem
የግጥም መጽሐፍ ምረቃ

ርእስ፦ ርእስ የለውም
ገጣሚ፦ ኤልያስ ሽታሁን

በጥዑም ግጥሞቹ እና ግሩም ለዛ ባለው አቀራረቡ በርካታ መድረኮች ላይ የምታውቁትና የምትወዱት ኤልያስ ሽታኹን 'ርእስ የለውም' በሚል ርእስ የመጀመሪያ መጽሐፉን ለንባብ አብቅቷል።

ቦታ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር
ቀን፦ ሐምሌ 5
ሰዓት፦ 11 ሰዓት

አዘጋጅ፦ ሰምና ወርቅ

#ኤልያስ_ሽታኹን #ርእስ_የለውም #ሰምናወርቅ

https://t.me/GitemSitem
ቀድሼ ላግባሽ

እምነ በሃ ቅድስት ቤተክርስቲያን
,.... ወስዕልት በእንቆጳዝዮን
በሚለው ቃል ዜማ ስርአት መልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ:
ተንስኡ እያልኩኝ በቅድስቱ ስፍራ
በቀኖናው ድርስት ከእግዜሩ ጋር ላውራ
በሚፈተትበት የቁርባኑ መና
ከልቤ ላመስግን የግሌ ሁኚና
የልቤ ህዋሶች በእንግዳ ስሜት
በፍሰሐ ሰክረው በተመስጦ ስሌት
በምስጋና ድምፀት የማወጣው ዜማ
የጠለቀ እንዲሆን ከሰማይ ደመና
ነጠላ አጣፍተሽ አክሊሉንም ደፍተሽ
ህግሽን ጠብቀሽ ክብርን ተጎናፅፈሽ
ካባውን ደርበን በእምነት ኪዳን ጥላ
በፈገግታ ልይሽ የግሌ ሁኚና

የኔታ የሰጡኝ የወንጌሉ በፍታ
ጠንክሮ እንዲፀና ፍፁም ሳይረታ
በግዕዝ ባራራይ ስርአት መልሼ
'እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!
የህይወቴን ምስጢር የኑሮዬን ድርሳን
ልቤን ገልጩልሽ እያዜምኩኝ ምልጣን
በክርስትናሽ ስም ፀሎትን አድርሼ
የእለቱን ምስባክ ስንክሳር ከልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!

የተላለፍኩትን የኃጢአት ደዌ
በንስሐ ስሽር በገሐድ ነነዌ
የፈጣሪ ምሕረት ላንቺም እንዲመጣ
በተክሊል ሱባዔ ከበደሌ ልንጣ
አዎ የኔ መውደድ አንቺም ተለመኚ
ገነትም ቀላል ናት ብቻ ከኔ ሁኚ!
አንድም ለኔ ፅናት አንድም ላንቺ ጸጋ
ቃልሽን ሸልሚኝ ልቤ ባንቺ ይርጋ።
ውዴ
ስብሐት ለአብ ብዬ ሠራዊት ዘልቄ
በሐሴት ሰክሬ በደስታ ጠልቄ
ተክህኖ ለብሼ ስርአት መልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!


©️ዳዊት ጥዑማይ
@jawithpoetdeva
2/9/2013

https://t.me/GitemSitem
Forwarded from ኩነት - Kunet
Live Painting & Poetry Night

Gojo Bar presents you a live painting and poetry night along with other entertainments. The show will be hosted by Gitem Sitem's co-host Seife Temam.

Saturday, July 17
7PM - 8PM

Hill Bottom Recreation Center

Entrance fee is ETB 100.

#July_17_21 https://t.me/Kunet_Sitem

#Gojo_Bar #poetry #livepainting #gitemsitem #seifetemam #Hill_bottom
አዝኛለሁ…
በልፋቴ በድካሜ ባቆየሁት
ሳቃችንን‐ ተንከርፍፎ ስላየሁት!
አዝኛለሁ…
ለተዝካሩ ለሙሾው ድንኳን ተክሎ እንዳይወጣ
ዕድሜያችን‐የኩርፊያ እንኳን ትዝታ ቢያጣ።
የደስታ የፈገግታ አሻራ ባናስቀር ደርሰን
እንዴት
በባዶ እንዲያው ዝም ብሎ ያለ እድሜው፣ እድሜ ያፍርሰን!

አዝኛለሁ…
ቀና ችን‐ቀን ሳለ ሳይዳምን ፀሐይ ባይወጣበት
እንደሌላው እለት ወዝ ስለታጣበት።
ፀሐይ ያጣ ተብሎ ቀን አይሰረዝም
እድሜ ላይ ይጫናል ታሪክ እንዲያስረዝም።

ሕይወታችን‐ድግሱ ውብ ነበር
እንኳን ቁም ነገሩ ዋዛና ለበጣው
አዝኛለሁ…
ከተነሳንበት ተመልሰን ሄደን ፈልገን ስናጣው።

©️ያዴል ትዕዛዙ