ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ጠረንህ አሰረኝ
መአዛ አሰከረኝ
ተንገዳገድኩ ፣
ናፈቅኩህ
እንደ እናት እቅፍ
እንደመንሰፍሰፍ
እንደ መንዘፍዘፍ ፣
እንዲ መሆንን መች ተማርኩት?
ከእውነትህ ስር ነው ገባኝ ያደኩት ::
ከእምነት ወንጌል
ከህይወት ላይ ቃል፣
ይፈሳል ደጅህ
አበጃጀኝ ፣
ሰው አርጎ ሰራኝ
መንገዴን መራኝ ::
ናፍቆት አሰከረኝ
ተንገዳገድኩ
ናፈቀኩህ
እንደ መንሰፍሰፍ
እንደመንዘፍዘፍ
እንዲ መሆንን መቼ ተማርኩት???
መች ለት አወቅኩት ?
ቅፅበት ለዘላለም
ዘላለም ለቅፅበት ምንና ምን ናቸው?
ሳውቅህ አወቅኳቸው ::

©መቅደስ ሞገስ
የያዘች ይመስል
ምድርን በካስማ
ከመንደሩ አንስቶ
እስከ ዳር ከተማ
ያደናንቋታል
ሰው እየተሻማ

እንደደብሩ ማህሌት
ያለችው ሚሰማ
ማማውን ምታስንቅ
ከረባዳው ቆማ

ኧረ ማነሽ ልጅት
የማነሽ ኮረዳ
ያላወቀሽ አለ
ለቀየው እንግዳ
ድንገት ፊቴ ቆመሽ
እንዳትገቢ እዳ

ይሏታል
እንዝርቱን አሹራ
ይሏታል
ፈትላ ያንን ጥጡን
ይሏታል
ለሰራችው ሸማ
ይሏታል
ሸጠላት እርስቱን
ይሏታል
ባፈላችው ቡና
ይሏታል
በጣለችው ጠጅ
ይሏታል
ከሚስቱ አጣላችው
ይሏታል
ቀምሶት አንድ ወዳጅ

እቴጌ እቴጌ
ገብያም አትውጪ
አትምጭ ከቀብሩ
ዕቁቡም ይቅርብሽ
እድር ማህበሩ
ባይንሽ ሰዋይሙትብሽ
አዛኝ ሁኚ ሩሩ
ይላላክልሻል
ጠቅላላ ሰፈሩ

ኤፍሬም ገነነ©
"እንዴት ነው ግን ሳይንስ ተንሰራፋ በተባለበት አካባቢ አሉባልታ እግዜርን፣ ተፈጥሮንና ተጠየቅን የምትዘርረው?

ታዲያ ሰኞ ተከራክረዋቸው ሐሙስ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰለባ ይሆናሉ።

በዚያን ጊዜ ፖለቲካ ይደረጋል እንጂ በመረጃና በጥናት የተደገፈ ሳይንሳዊ ውይይት የለም።

ይፃፋል ይባላል እንጂ የሚረባ አይደለም።

በስነ-ፅሁፍ በኩል የነበረው የደሃነት መጠን አይጣል ነው። በኢኮኖሚክስ፣ በሶሲዎሎጂ እና በአንትሮፖሎጂ በሌሎችም መስኮች እጅግ ሰፊና ጥልቅ የሆነ የጥሬ መረጃ ጉድለት አለ።

አገሪቱ ችግር ቢያጋጥማት የነሲብና የአውቃለሁ ባይነት ውጤቶች ናቸው።

የዋሸሁ ከመሰለሽ ዪኒቨርሲቲ ሄደሽ የተጠናውን የጥናት መረጃ እዪ። ያሉት ጥናት ተብዬዎች እርስ በእርሳቸው ግማሽ እውነት፣ ቅጥፈትና ስህተት እንደ ማሚቶ የሚቀባበሉ እንደሆኑ መገንዘብ ትችያለሽ።

እነዛን መረጃዎችና ከዛም የጠለሉትን ፅንሰ ሀሳቦች ለመፈተሽ አዲስ መረጃ ካመጣሽ ወይም ይኑር ካልሽ ነባሩ ሀሳብ ስለሚፈርስባቸው አይፈልጉሽም።

በስህተታቸው የተዝናኑ ነበሩ።

ያልተስተካከለ መረጃ ከያዙ የባዕድ መፅሀፍት ላይ ሃሳቦችና ቃላት ተለቃቅመው ብዙ ግድፈት ይሰራል። ተሟጋች ጥሬ መረጃ ይዞ ካልቀረበ ሌሎችን መምሰሉ ከአሉባልታ የተለየ አይደለም።

'እንትና የተባለው የዚህ ሀገር ፕሮፌሰር እንትን በተባለ መፅሀፉ ስለ ኢትዮጵያ እንትን አለ' ማለት ምንም ማለት ነው። ከእንትን እና እንትን ብዛት ምን ትጠብቂያለሽ? የተፃፈ አሉባልታ እንጂ።

ስለዚህ አሉባልታ ስለምፈራና የስነ ዕውቀታቸውን መልክዓ ምድር (epistemological landscape) ስለምጠራጠር ለማናቸውም ግድ አልነበረኝም።

***
የስንብት ቀለማት
👍1
They say
a picture is worth a thousand words
But
a word creates thousands of wounds
They say
every picture tells a story
But they don't really know
how every word in a poem is stony
They say
words are powerful
They can create or they can destroy
They don't really know
how pictures create words in our head
how words can picture
what pictures can't capture
...
But in deed,
a picture is worth a thousand words
a word is worth a thousand words
if words were not invaluable

©Seife Temam
Forwarded from LinkUp Addis
Shifta Lounge will host a book launch event on Saturday 27 March 2021. The event will feature book excerpt readings, music and poetic performance by all-female talents. Doors will open at 3:00pm. Entrance is for free but a green dress is a must. @linkupaddis
Forwarded from Poetic Saturdays
ሠላም ሠላም ግጥማዊ ቅዳሜያውያን ወርሃዊውን የጥበብ ድግሳችንን እንዲሁም የ5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችንን የምናከብርበት ፕሮግራማችንን ይዘን መጥተናል!
ቅዳሜ መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በፈንድቃ የባህል ማዕከል ተገናኝተን አብረን እናክብር፡፡
አዲስ በወጣው የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ ምክንያት የታዳሚያችንን ቁጥር ቀድመው ለተገኙ 50 ሰዎች ብቻ ልንገድበው ተገድደናል፡፡
የመግቢያ ዋጋ፡ 100 ብር ብቻ
አዳዲስ እና የራስዎን ፈጠራ ብቻ እንዲያቀርቡ ይመከራል
ለእያንዳንዱ አቅራቢ 5 ደቂቃ ብቻ ቢፈቀድም የፈለገውን ያህል ማቅረብ ይችላል።
ምንም አይነት የቋንቋ እና የይዘት ገደብ የለውም
ምንም አይነት የጥበብ ስራ ይበረታታል
ይምጡና የጥበብ ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ!
*** ጀማሪ እና አዳዲስ ፀሐፊያን ይበረታታሉ! ***
*Do not forget your mask!*
Hi Creative Addis, Poetic Saturday will be on this Saturday, April 3rd, 2021 at Fendika Cultural Center to celebrate our 5th Year Anniversary!
Due to the latest COVID-19 safety guidelines, we are forced to limit our audience to the first 50.
Entrance Fee: 100 Birr

As usual, we will start registration at 2: 00 pm.
Only perform YOUR ORIGINAL work. The audience is there to listen to your truth!
Each performer gets 5 minutes total. You can perform as many times but respect the time limit.
All languages welcome.
Shifta presents Gitem Sitem an open mic circle of fun and poetry.
Happens on every first Wednesday of the month with your hosts Heran and Seife.
We have very simple rules:
1. Sign up online https://forms.gle/oEbMTixhnKu4HKox7 or by the gate prior to the event
2. 5 minute per performer
3. Be respectful to the performers and all beings around you
4. Be you
5. Make sure you follow all the precaution measures for Covid 19

https://www.facebook.com/gitemsitem

ሽፍታ የግጥም ሲጥምን የክፍት መድረክ ክበብ አቀረበላችሁ!
ረቡዕ, መጋቢት 29 ከ 1 ሰዓት ጀመሮ በሽፍታ
ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የቁም ኩምክና፣ ስዕል እና ሌሎችም አዝናኝ የጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ።
ስራችሁን ለማቅረብ ማስፈንጠሪያውን ተጠቅማችሁ በምታገኙት ቅጽ ተመዝገቡ! https://forms.gle/WveKjAsZ5PBx9MVr9
ስንት. . .
***
የእግዜር ጥንተ ስጋት
የሰው ዓይን ትዝብቱ
የራስ ከራስ ማነስ
ኅሊና ትዝብቱ
ኧረ ስንት አለብን
ስንት አለብን ስንቱ።

©ዲበኩሉ ጌታ
Forwarded from Bruh Club
Out now, the Arts Mailing List newsletter – 5th April 2021 https://bit.ly/39CBcJ9

Featuring the beautiful work of Tewodros Bekele https://www.instagram.com/tewodros691/

With so many exciting open calls, competitions, grants etc… there is something for all Ethiopian Animators, Architects, designers, AR & VR designers, Circus practitioners, Dancers, Digital artists, Events & Festival managers, Filmmakers, Graffiti artists, Graphics Designers, Illustrators, Journalists, Multi-media artists, Music Producers, Musicians, Photographers, Poets, Sculptors, Textile Designers, Video Makers, Visual artists, Writers


@artsmailinglist
Please check this👇🏾 out and if you need any help or assistance from Gitem Sitem, please feel free to contact us.
Forwarded from LinkUp Addis
The US Embassy is hosting a youth competition for people of ages between 18-25 to share their personal viewpoints on the interconnectedness of citizen participation, their future and democracy. Participants can submit either a short video or a short poem addressing one of the following: "What I want Ethiopia to be; my contributions to elections; what democracy means to me.
Winners of the contest will be awarded digital devices such as laptops, tablets, mobile devices, etc. Deadline for submission is 03 May 2021.
For more info, visit https://bit.ly/2OnZOhe.
@linkupaddis
Forwarded from LinkUp Addis
Eniy Cinema at Laphto Mall will host a poetry and literature night on Thursday 08 April 2021 titled 'Man Sinager Man Zim Yibel'. The event will feature some of the leading Ethiopian poets and writers including Nebiy Mekonnen, Daniel Kibret and Ephrem Seyoum. Doors will open at 5:30pm. The entrance ticket is ETB 100 and is available at Jaefar Book Shop and Faith Hotel.

Download and enjoy the April edition of LinkUp Addis Magazine: https://bit.ly/31B0Idt @linkupaddis
ተመኘሁ
ጭራፊ እይታ ጠብታ መውደድህን፤
ሽራፊ ፈገግታ ጎዶሎ ልብህን፤
ቀዝቃዛዋን ነፍስህ ከጭጋግ አለምህ፤
ላጠፋው ተመኘሁ።
ነፍስህን ላሞቃት አለምህን ለኮስኩ፤
ፈገግታህ እንዲሞላ ሳቅ ልብህ ላይ ተከልኩ።
ከመውደዴ ጅረት ወዳንተ ፈስሼ
ጠብታ ደረቁን ሁሉን አረስርሼ።
ስመጣ ወዳንተ
ሞልተህ ትፈሳለህ
ከሩቅ ታበራለህ
በቃ ትሞቃለህ!!
ግና
ጠብታነትህን
ኢምንት ነፍስያህን
ጥላሸት መልክህን
ጨለማ አለምህን
ደግሜ አየሁት።
ሙሉ በቀረፅኩት የአንተነት አለም ውስጥ
ጎዶሎነትህን
በግልፅ አስተዋልኩት!!።

©መሁብ ይመር