ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
የቱ ጋር?
(ቶማስ አድማሱ)

ከአድዋ በፊት ያው ከድሉም ኋላ
ላንድ የዝና ታሪክ ላንድ የጋራ ጥላ
እንዴት ታጣ መላ?
እንደ ሰው ወደታች ያወረደን ማነው?
ከአድዋ ኋላ የቱ ጋር ነው የቆምነው?
*
እጃችን ማሸነፍ ረስቶ
ልባችን ወኔ ተነስቶ
ነፍሳችን ሃቅ እውነት ስቶ!
በካቻምና ታሪክ ዜማ
ልብ ባይን ሲደማ።
እዚያ ጋር ነው የቆምን እግር በእግር ሲወጋ?
ባንዲራ ላብ ማበስ ትቶ እግር ጠልፎ ሲያዋጋ፡፡
አያምም??
/ያማል/
ጎን ላይ እንደመወጋት
ተሰቅሎ በችንካር ቅጣት
ሆምጣጤ ከከርቤ ቅንጣት
ከሰፍነግ ላይ እንደመጋት፡፡
እሳት ላይ እንደቆመ እግር
እንደ ሰፋ የአራሽ ድግር
ያሸነፉት ሲያሸንፍ የጣሉት መልሶ ሲጥል
ሲያቃጥል!!!
*
“መንገዳችን ያሳዝናል”
የምንሄደው ያሰጋናል
አሁን ደሞ እንዲህ ሆነናል
/እንዲህ/
ይሁዳን እያሞገሱ ከዮሐንስ ጋር መጣለት
እዚህ በርባንን መስደብ በዚያ በኩል መስቀል መጥላት
በጉን ወዶ ተንከባክቦ ምን ይሉታል መጠየፍ ላት??
***
የጣልናቸው እየጣሉን
ያዘልናቸው እየጠሉን
እውነት?
አፈር አፈርን በላ?
ድንጋይ ድንጋይ ላይ ሰላ?
የቱ ጋር ነው የቆምን ከአድዋ ኋላ??

#ቶማስአድማሱ #ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ግጥማዊቅዳሜ
#ThomasAdmasu #tba #tibebbeqdebabay #digitalartfestival #artinaddis #gitemsitem
Forwarded from ጥበብ (dooxbot)
የጦቢያ ትንሳኤ

ምንድነው ማንባቱ ዕንባህን መዘርገፍ
ጠላትህ ሲጋልብ እንደማለት ዘራፍ
ከቶ አይችልምና መሞቱ ሊያባባህ
ሸልል ፎክር እና ስደደው አርቀህ
ግርማህን አሳየው ዝናርህን ታጥቀህ
ሰማይ ሆይ አድምጠኝ ስማኝ አስተውለህ
ከጷግሜ በኋላ ዝናብ ነው ጠላትህ
ወዝህን ማድረቂያ መርዛማ ነው ዕንባህ።
ፀሀይም አትሞኝ አትበይ አልወጣም
ቀንሽን ብሪበት ድመቂበት በጣም
ባክሽን ጦቢያዬ ልብሽን አይክፋው
አብቅቷል ወጀቡ የፀደይ ነው ተራው።
ደዌውን ሊያጠፋ ፌጦው ተፈትፍቷል
የእናቶችም አንጀት ለፀሎት ተፈቷል
ልጆች ሽክ ብለዋል አምረዋል በእጅጉ
አባቶች ባርከዋል ተሰውቷል በጉ።
ዕድልሽ ይታደል ደስታሽም ይደሰት
ችግርሽ ይቸገር ሞትሽ ቀድሞሽ ይሙት
እንደ አሸዋ ውሀ በኖ ተኖ ይጥፋ
ምድርሽ በአደይ እና በፍቅርሽ ይሰፋ
በአዲስ አመት መንበር በነገ ድልድይ ላይ
የፍቅር አክሊልን ደፍተሽ በላይሽ ላይ
ደምቀሽ ፈክተሽ ይታይ
መአዛሽ ይታወድ ከርቤሽ ያረስርሰን
በአዲስ እኛ አንኑር አሮጌውን ትተን።


ተፃፈ በ ግሩም ነን መቼም(ሮዛ)

የመለያ ቁጥር - ET-068

Like and join @eshidigital
@tibeb_drawing_and_poem
መንገደኛ
(ሰይፈ ተማም)

ከደመናት ቅድስናን የምቀዳ
በጉንዳን መስመር ‘ምቀና
በልቤም በ’ግሬም ‘ማቀና
ረቂቅ የመንገድ ጀግና

ከየትም ወዴት ያልመጣሁ
ካለመኖር ውስጥ ኖሬ - ከመኖር መዝገብ የታጣሁ
መጣህብኝ ባይ የሌለኝ
መንገድ ነኝ - መንገደኛ ነኝ

ካልነበረውም ወደ ነበረው መጥቼ
ያልነበረውም ሲነብር አይቼ
እርጥበት ላይ ትኩሳትን
እርኩሰት ላይ ምርቃትን
እርግበት ላይ ክርራትን
እየበተንኩ የማቀና
በጉንዳን መስመር ‘ምቀና
ረቂቅ የመንገድ ጀግና
መ ን ገ ደ ኛ

በቅድስናም ሆነ በፍልስፍና ‘ምነጉድ
‘ሚያመጣ ‘ሚወስደኝ መንገድ
የሆንኩት ሁሉ ቢሰፈር
ቢመጣ ቢሄድ ቢቀመር
ቢለካ በሰፈር ባገር
ቢመተር በቀለም በዘር
ስዘረፍ ቅኔ ወርቅ አሰር
ስታሰር ስንኝ ምቋጠር
ስቋጠርም ስንቅ ‘ምካፈል
ስካፈል አሸዋ ‘ምገረፍ
ስገረፍ ቅኝት ‘ምካረር
ንዝረት ነኝ ያውታር በገና
በጉንዳን መስመር ‘ምቀና
በልቤም በ'ግሬም 'ማቀና
ረቂቅ የመንገድ ጀግና
መ ን ገ ደ ኛ

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ግጥማዊቅዳሜ
#seifetemam #gitemsitem #poeticsaturdays #tba #tibeb2020 #tibebbeadebabay #digitalartfestival #artinaddis
Forwarded from Bruh Club
በመጪው ጥቅምት 2013 በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያውያን የፈጠራ እና የጥበብ ባለሙያዎች ብቻ ነጻ የስልጠና ፕሮግራም ለማዘጋጀት አቅደናል፡:

o በየትኞች ርዕሶች ላይ ብናተኩር ይሻላል ብለው ያስባሉ? o እርሶ የበለጠ ይጠቅማል ብለው የሚያስቡትን ርዕስ ይምረጡ፡፡ o ከዚያም ደግሞ እኛ በተሰጠው ድምጽ መሰረት የስልጠናውን መርሃ ግብር እናሰናዳለን:: እናመሰግናልን::
Final Results
9%
የገንቢ ግምገማ እና ግብረመልስ ልውውጥ ጠቀሜታ
48%
በጥልቀት የማሰብ እና የማገናዘብ ክህሎት
16%
የጥበብ ውድድሮቸ፤፤ ምንድናቸው? እንዴት ነው ምንጠቀምባቸው?
34%
ውጤታማ የስራ ትስስር
15%
የደንበኞች አገልግሎቶች
22%
ጥራት እና ዋጋ ለጥበብ ስራዎች
11%
የጥበብ ስራዎቻችንን ልዩነት ማንጸባረቅ
10%
የስነጥበብ የስራ ማህደር፤፤ ምንድን ነዉ፤ ጥቅሙስ እና አዘገጃጀቱስ?
27%
የውጤታማ ጥናትና ምርምር ክህሎት
18%
የማህበራዊ ትስስር አዉታሮችያላቸው ጠቀሜታ
እኔና መስከረም

ጉድን አስቀድሞ በጠባው መስከረም
መልሶ ሊሰለች ያልናፈቀ የለም
እንደ ዘማች ፋኖ ሜዳው አጎፍሮ
በአደይ ጥርሱ ሲስቅ በመላጣው አፍሮ
በዛ ባዶ ደብተር ስም እንኳን በሌለው
ስምሽን አየሸጎጥኩ ሜዳውን ስስለው
የእፉዬዋን ገላ ጆሮሽ ላይ ስሽጠው
የአምናው ትዝ እያኝ
መስከረም ናፈቀኝ

ሸተተኝ ጠረኑ የምሳቃው አይነት
ዶሮና አጥንቱ ተባብረው የሞሉት
ታየኝ ሌላ ክፍል ወስደው ሊለጥፉት
ታወቀኝ ከዴስኬ ስምሽን እንዳጠፉት

ምን ያረጋል ክረምት ምንያረጋል ብርዱ
ፈገግታሽ የላቸው ካርታና ገመዱ
ሽልጦና አርጩሜ
ታላቅ ፊልም ድጋሚ
ድጋሚው ድጋሚ

አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከበጋው ግፋችን የምንማርበት

... የክረምት ትምህርት...

በአይኔ ለወደድኩሽ ሌላ ደርቤበት
ላንቺ የቀለድኩት ቲቲን እያሳቃት
ሳሩም አደገብን ሊደብቀን ሻተ
ጭቃው አዳለጠን ዋንጫችን ወለቀ
ይህ አሮጌ ደብተር ገጹ መጀመሪያ
ስምሽ ተስሎበት ከሜዳው ሳር ጉያ
የክረምቱን ሳልስል የክረምቱን ሳልፅፍ
ነሐሴ መጣና ጿሚ ሆኜው እርፍ

አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከአዘቦት ግፋችን የምንማርበት

... የሰንበት ትምህርት...

ነጠላ አጣፍቼ ሳንቲም እያጋኘሁ
120ን ትቼ ቤተስኪያን ተገኘሁ
ይቺ ህይወት ናታ ወስዳ ያሳለመችኝ
ደጀ ሰላም ጠርታ ደሞ እያሳመችኝ
ደሞ የቆረበች ለት አፏን ነጠላ አምቆ
ያለችኝንም አልሰማሁ ከንፈሯ ካይኔ እርቆ
ደብተሬም የመዝሙር እንጂ የውዳሴያት ማህደር
በራጅ ላስቲክ ያሸኳት ቢሳልም ሰማዕት ነበር

መስከረም አትምጣ አትጥባ ግዴለም
ደብተሬ በላስቲክ ገና አልተሸፈነም
አይኔ አይኖቿን ሊያይ ድፍረት አላገኘም
ቀለም ጨርሻለሁ አበባ መሳያ
ቀለም ጨርሻለሁ ግጥም ማሳመሪያ
በቀረች ብያለሁ አበባ አየሽ ባዯ
🎤
አበባ አየሽ ወይ - የወር
አበባ አየሽ ወይ - የወር

የሷን አበባ ለወር የኔን ለዓመት አርገህ
ወዲያው ለሚያረጅ ነገር አታምጣ ቀኑን አድሰህ
... ክፍላችንን ለይተህ

አንተም ቀንህ አልፎ
ጊዜህ ተንጠፍጥፎ
እንዳልነበር ውሉ የሚለየን የለም
ዘመን ሲወነጨፍ ሌላ ሚሊኒየም
ብዙ ጉድ ሰምተናል ና ጥባ ግዴለም
ና ግባ መስከረም

አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
ለፀሀይ ቀርቤ ማውጋቱም ናፍቆኛል
ልቃጠል ልንደደው የጉድ ቀን ባይነጋም
ብርድ እያሳበቡ ሰለቸኝ መስከርም
ናፈቀኝ መስከረም
ምንቸቱን ቀይረው
መቼቱን ቀይረው
ለአዲስ ቀን አልሰጋም
ለአዲስ ቀን አልሰጋም

ሰይፈ ተማም 2010

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
እኔ ፀሐይ

እሰይ አደይ ፈነዳች፤
የመስከረም ፀሐይ ወጣች፤
አበባየሁ አሉ ልጆች፤
አበባ ያልያዙ እጆች፤
በምርቃት ሊወለዱ 30 እና 60 ጥጆች፤
ቀልዬ ከሶሪት ላባ፤
ካባቴ ገቦ ወጥቼ ከናቴ ማ'ጸን ስገባ፤
ይኸው መስከረም ጠባ።
እልል አበብሽ ብዬ
ለምለም አደይ ነቅዬ፤
እንግጫሽ አበባ፤አበባየሽ ለምለም
የመስከረም ጸሐይ ወጣች
ከእንዲህ ነጎድጓድ መፍራት በሰማይ ማማረር የለም።
በክረምት ጠል ርሶ፤ ሊመጣ ጸደይ ያማረ፤
በምርቃት ወንድ ሊሰጥ በሴት አካል ወንድ አደረ።
አበባ ነኝ እኔ አበባ
ከአድማስ ፀሐይ ሳትገባ
መታፈር በከንፈር ያልኩ ጥርሴ መንታ የሚያነባ
ቢጫነት በሆዴ ያለ ልቤ መዓት የሚያደባ፤
አበባ ነኝ እኔ አበባ።
ለወደድኩት የዓይን ጥም
ከካህን ማስር ምፈታ ከደብተራ ምጠመጥም
የጠላሁት የሚሰጥም
ለተናቀ ረባዳ
ለተከበረ ሰው ሜዳ።
አበባ ነኝ እኔ አበባ።
እሰይ አደይ ፈነዳች፤ ይኸው ጳጉሜ ከነዳች።
ከሰማይ ምንም ሳይጎድል ከመሬት ሳይጨምር አንዳች።
(ቶ)በምን አገባኝ ፍካሬ አክናፌን ስዘረጋጋ
(ማ) ነህ ብሎ ለሚያዛጋ
(ስ)ብዬ አፉን የማሲዝ የማልፈጥን የማልረጋ።
መሬት ቢጫ ስትለብስ። የአምናን መከራ አልፌ
እልል የምል ችቦ ወገብ ተደግፌ
ለከርሞ ትልሜን ለፍፌ
የሚል ግጥም ሳሰናዳ
እሰይ አደይ ፈነዳ::

#ቶማስአድማሱ #ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ግጥማዊቅዳሜ
#ThomasAdmasu #tba #tibebbeqdebabay #digitalartfestival #artinaddis #gitemsitem
Forwarded from Poetic Saturdays
May the new year brings us more joy, peace, unity and creativity!!

Happy new year everyone

#tba #tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival #artinaddis
የአንች ሆዬ ቅኝት ዜማ
ሞገዱን ሁሉ አዳረሠ
ተራራው በአደይ አጌጠ
መስኩ ውበት ለበሠ
ሀገሬ ፌሽታ ደገሰች
አዲስ ዓመት ነገሠ

ሠናይ አዲስ ዓመት!!!
2013 ዓ.ም
#አሜን #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #አዲስዓመት
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
ይህችን ጣፋጭ ግጥም ከግጥም ሲጥም ያጣጥሙልን
የግጥም ሲጥም አባል ከሆነው ቶማስ አድማሱ

እኔ ፀሐይ

እሰይ አደይ ፈነዳች፤
የመስከረም ፀሐይ ወጣች፤
አበባየሁ አሉ ልጆች፤
አበባ ያልያዙ እጆች፤
በምርቃት ሊወለዱ 30 እና 60 ጥጆች፤
ቀልዬ ከሶሪት ላባ፤
ካባቴ ገቦ ወጥቼ ከናቴ ማ'ጸን ስገባ፤
ይኸው መስከረም ጠባ።
እልል አበብሽ ብዬ
ለምለም አደይ ነቅዬ፤
እንግጫሽ አበባ፤አበባየሽ ለምለም
የመስከረም ጸሐይ ወጣች
ከእንዲህ ነጎድጓድ መፍራት በሰማይ ማማረር የለም።
በክረምት ጠል ርሶ፤ ሊመጣ ጸደይ ያማረ፤
በምርቃት ወንድ ሊሰጥ በሴት አካል ወንድ አደረ።
አበባ ነኝ እኔ አበባ
ከአድማስ ፀሐይ ሳትገባ
መታፈር በከንፈር ያልኩ ጥርሴ መንታ የሚያነባ
ቢጫነት በሆዴ ያለ ልቤ መዓት የሚያደባ፤
አበባ ነኝ እኔ አበባ።
ለወደድኩት የዓይን ጥም
ከካህን ማስር ምፈታ ከደብተራ ምጠመጥም
የጠላሁት የሚሰጥም
ለተናቀ ረባዳ
ለተከበረ ሰው ሜዳ።
አበባ ነኝ እኔ አበባ።
እሰይ አደይ ፈነዳች፤ ይኸው ጳጉሜ ከነዳች።
ከሰማይ ምንም ሳይጎድል ከመሬት ሳይጨምር አንዳች።
(ቶ)በምን አገባኝ ፍካሬ አክናፌን ስዘረጋጋ
(ማ) ነህ ብሎ ለሚያዛጋ
(ስ)ብዬ አፉን የማሲዝ የማልፈጥን የማልረጋ።
መሬት ቢጫ ስትለብስ። የአምናን መከራ አልፌ
እልል የምል ችቦ ወገብ ተደግፌ
ለከርሞ ትልሜን ለፍፌ
የሚል ግጥም ሳሰናዳ
እሰይ አደይ ፈነዳ::

#gitemsitem #tibebbeadebabay #tba

ይከታተሉን
ቴሌግራም: t.me/Tibeb_Be_Adebabay

ፌስቡክ: facebook.com/Tibeb2020

ትዊተር: twitter.com/TibebBe

ዮቲዩብ: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag

ዌብሳይት: tibebbeadebabay.org
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
To all the creatives and artists out there!!
Wherever you are Whoever you are, you can submit your artworks here. Read the details 👇👇

Are you interested in being part of this vibrant festival with the title “Who am I” and the subtitle “Telling Migrating stories"? You are not obliged to align to the the theme and subtitle but if you have your work on these subjects, you are most welcomed!

Click here and submit your works: https://forms.gle/81kfRSqyFyyZ2CJB7

Follow us:
Telegram: t.me/Tibeb_Be_Adebabay

Facebook Page: facebook.com/Tibeb2020

Twitter: twitter.com/TibebBe

YouTube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag

Website: http://tibebbeadebabay.org

#tba #tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival #artinaddis
Forwarded from Bruh Club
OUT NOW: The Arts Mailing List newsletter – 14th Sep 2020 https://bit.ly/3ircAFr

This week featuring the striking work of photographer Jehoiada Degu https://www.instagram.com/jehoiada9/

Click on the above link to find this week’s list of national and international open calls, competitions, funding and residencies etc… for you to apply to and so much more!!

@artsmailinglist
Who am I?

(Oladeji Olowajooba-
Nigeria)

So, when they ask
Who are you?
I want to say
I am as volatile and random as water
I change just as the wind
sways the leaves of the trees
Most days,
My mind is never made up
just as the fly, who loves to perch
on everything.
While on some days, I am picky.
So, when they ask
Who are you?
I can't fit myself in a box
and present that to you as a Christmas present
cause I am the whole store.
All I want to say is 'I am who I am'.
No definitions nor precisions
just infinite discovery.

#Oladeji #gitemsitem #tba #tba2020
Word in My Head
(Seife Temam)
-----------------------
Words just pop out in my head
It feels like they’re made of words’ bed
A tree with leaves of words
Unknown stem and known buds
Unknown branches and known Shreds
And under the sheds
These words of bed
Words I like words I hate
Strange words in lovers’ gate
Making love, giving birth
Reaching orgasm
With immature cum
Word!
Words unsaid
Words untamed
Thoughts of weird words
In the wrong cage
Words get chained
And they just pop out here in my head
My head catches them
While having sex
Tried to film it
The high definition?
No, that takes up space
… space itself
Is a burial place
For dead words left unsaid
Or, is it?
Is it not a space?
For them to be
Like the one in my head
That makes the tree
That makes the leaves leave,
Gives them soil
For them to decay
So that their part, can still stay
So that they’re not led astray
Feeding the tree they belong to
I wish I could say a word or two

I feel like an unused condom
That got thrown
While she’s on period
Left with desire on this sexing bed
That’s how I am
When it’s all words that pop in my head

#seifetemam #poeticsaturdays #gitem_sitem #tibebbeadebabay #tba #Tibeb2020 #artinaddis #digitalartfestival
"አሜን" በሉ!
(ሰይፉ ወርቁ)

° ° °........
ፀሐይ ባለበት ሁሉ፣
የትም "ጥላዎች" አሉ፤
የሚያለቅሱ ድፍርስ ዐይኖች፣
ድፍርስ ብርሃን ያያሉ!
•••
ግርዶሾቹ ምን ቢያይሉ፣
አማኞች "አሜን" ይላሉ!
ፀሐይ በሣቀች ጊዜ፣
ደመናዎች ይቀልጣሉ!
••
አማኞች "አሜን" ይላሉ፤
አሜን ያሉ ይሥቃሉ፤
የኮኮብን ትልቅነት፣
በግርዶሾች ልክ ያውቃሉ!
°°° ....

#ሠይፈ__ወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #tba #tibebbeadebabay #tibeb2020 #artinaddis #digitalartfestival
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Check out this stunning mural Hallucination by Efrata Birhanu from @Addis Street Art

Efrata says "We all had imagination as kids, it was our playground in our minds .we were doctors, movie starts, engineers and so on.... But when we grow up and got to the point where we crossed the line between imagination and hallucination people called us psychotic, but we were just men,

We were pushed out of this world by situations too tough. This life became so hard for us to deal with , so it forced us to create a world in our minds and migrate to a hope of better reality that we can only hear , see and feel."
If you find this mural, take a picture and post it with the hashtags #tba #tibebbeadebabay #addisstreetart Or send it to us and join in the art festival.

Follow us:
Telegram: t.me/Tibeb_Be_Adebabay

Facebook Page: facebook.com/Tibeb2020

Twitter: twitter.com/TibebBe

YouTube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag

Website: http://tibebbeadebabay.org