ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አትምጪልኝ
ስጠራሽ አትምጪ አታግኚኝ ጭራሽ
መንገድም ከጀመርሽ እንደውም ተመለሽ
ስታገኚኝማ
አይንሽን ሳይማ
ያመመኝ ድኖ ነው ህመሜ 'ሚያገረሽ
#seifetemam አሁን
እባክዎ ግጥሞን ያጋሩን @SeifesBot የሚለውን መንገድ በመጠቀም ያድርሱን በጥራት የተቀዱ እንዲሁም በአማርኛ ሆሄያት የተተየቡ ግጥሞችን እንጋራ እናጋራ ።
Forwarded from ቶኔቶር
# ወፍእናማለዳ
እንኳን ችግኙ ÷ሰዎች የተከሉት
ሥር ይዝ ነበረ ÷ አዕዋፋት የዘሩት፣
ዘንድሮ ግን ወፎች ÷ እንኳንስ ሊዘሩ
ናፍቆኛል ማለዳ ÷ መስማት ሲዘምሩ፡፡
ወፎች ከማለዳ በምን ተቃቃሩ?!
ፅልመቱ ሲገፈፍ አንዳላበሰሩ፣
ማዜም ተስኗቸው ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት ወዴትስ በረሩ?!
ምንጭ = ሀ-ሞትየግጥሞች ስብስብ ኄኖክ ስጦታው
:
መጀመሪያ:እንደ:ሁለት:ነጥብ
በየሃሳቤ:መሃል
በየቃሌ:መሃል
ትገኚ:ነበረ
ዛሬ:ጊዜ:ሄዶ ሁሉም ተቀየረ
የኔ ሁለት ነጥብ ክፍተት ሆኖ ቀረ
#seifetemam
የመቆም ዑደት

የቅድም አያቴን አጽም ከአፈር አውጥተው
ቀጥ ብሎ መሄድን በሷ እንደጀመርነው
ይነግሩኛል ደፍረው
...እንደዚህ እያሉ
ከጥንቱ ጥንት ፊት ሰው ዝንጀሮ ሳለ
ዝንጀሮ ሰው ሁኖ መቆም ሰለጠነ
ለሱም ምልክቷ
ሙዝየም አኑረው ይቹትና አጥንቷ
ይህንን አምኜ ለእንግዳ ስናገር
ለመጣ ለሄደው ለኦባማ ሳይቀር
ቀድመን እንደሞቅነው የመቆምን ጀምበር
...ደሞ ከመንገዱ
ወይዘሪት ድንቄ እና እትዬ አረገዱ
ሸክም አጉብጧቸው 'በ' ን ሰርተው ሲሄዱ
እኔ ደሞ እላለሁ
ቀድመን እንደቆምን ቀድመን የወደቅነው
እኛው እንደጀመርን እኛው ልንጨርሰው
#seifetemam #አሁን
ወዳጄን ምን ነካው
ከመንጋው መንጋጋ ፈልቅቆ እየወጣ
ተነጥሎም ሲቆም አጀቡን እያጣ
ለሞቀው ገበያ ምሽቱ ሲነጋ
እራሱን አሹሎ የሚሆን መንጋጋ
ለሌላኛው መንጋ
መሾሉስ ባልከፋ
መሳሉስ ባልከፋ
ወጀብ የፈጠረው ባጀብ እንዳይጠፋ
ወዳጄን ጥሩልኝ እናውራ በወጉ
ከመንጋው ቢጠፋ አይሸጥም በጉ

ሰይፈ ተማም 2008
ቡሄ በሉ
ከ ሰይፈ ተማም
=======
ቡሄ የልጆች በዓል ነው። ልጅ እያለን ትዝ ይለኛል ከነ ሰይድ ጋራ ሆያሆዬ ስንጨፍር - እነ ጋሽ ጃፈር ቤት ሁሉ ብር ይሰጠናል እንጂ ተባረን አናውቅም።ሃገሪቷ ውስጥ የፈጠራ ችሎታ ማነሱን ከሚያመላክቱ ነገሮች አንዱ (ከዚህ ፅሁፍ ውጪ ማለት ነው)አዲስአባ ውስጥ እንዳሉ ታሪካዊ ህንፃዎች ያልታደሱት የሆያሆዬ ግጥሞች ናቸው።በቀን የሶስት ወይም የአራት ታክሲ ገቢ የሚያስገባ ልማታዊ ልጥጥ ሱቅ በር ላይ" እዛ ማዶ አንድ ካልሲእዚህ ማዶ አንድ ካልሲየዚህ ቤት ጌታ ባለታክሲ"ይህን ሲባል በየቀኑ እየተጋጨ እና በሹፌሩ ሰበብ እየታሰረ አማሮት የሸጠው ታክሲ አይኑ ላይ ድቅን ሲል የሆያሆዬ ባንዱን በንዴት ያፈራርሰዋል ልማታዊ ልጥጡ ይህን ሲያደርግ ያየ ለሃገርናባህል ተቆርቅሪ ነኝ ባይ አልፎ ሂያጅ በእርሱ የልጅነት ዘመን የተገጠሙ ቡሄ በሉ ግጥሞችን በውስጡ 'ሆ' እያለ በመስማት ላይ ሳለ ልማታዊ ልጥጡን ለባህል መጥፋት አንዱ ተጠያቂ አርጎ ኮንኖ ማስቲካውን ይለጥጣል።የግድ በየማዶው አንድ ነገር እንዲያሰፍር የተፈረደበት ቡሄበሉ ግጥም እንደምንም ብሎ ሌላ ማዶ ይቀጥላል...በሬ ላይ የቆሙትን ሶስት ሆያሆዬያን አዲስ ግጥም ያላቸው እንደሆን ጠየኳቸው ደሞዛቸው እንደ ግጥማቸው አሪፍነት እንደሚያድግም ነገርኳቸው"እዛ ማዶ አንድ ኮምፒተር" አሉ በወኔ እኔም ዘመኑን የመሰለ እንደ ቀበሌ ነው ወረዳ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ሊሰሩ ነው ብዬ ስጠብቅ"እዚ ማዶ አንድ ኮምፒተርየዚህ ቤት ጌታ ሊሄድ ነው አሜሪካን" ያቺን የሳንቲም አንድ ብር ከማግኘታቸው በፊት በሆዴ ያልኩትን ፊቴ ላይ ሳያዩ አይቀርም እኔም 'እድሜ ልኬን የሞከርኩት ዲቪ ለማስተዛዘኛ ኤምባሲው ጋር እንኳን አድርሶኝ አያውቅም' ነበር ያልኩት። ልጆቹ ከሄዱ በኋላ ሳስበው ግን በዚች ከልጥጦች ልጥጥነት፣ ከጠባቦች ጠባብነት፣ ከሙሰኞች ሙሰኝነት እና ከመሳሰሉት ውጭ ነገሮች ወይ በበጎ በማይለዋወጡበት ወይ ማንነትን የሚገልፁቱ ከዘመኑ ጋር በማይቀጥሉበት ሃገር እየኖሩ ምን ፍጠሩ ሊባሉ ኖሯል? እስኪ አስቡት ሁለት ወጣት ባልና ሚስት ያዩ ልጆች"እዛ ማዶ አንድ አሞራአዚ ማዶ ሌላ አሞራየኔማ እንትና ዛራና ቻንድራ" ቢሉ... የአገልግሎት ግዜ ያለፈባቸው የቡሄ ግጥሞች ተጠቃሚው ጋር እንዳይደርሱ ተመልክቶ የማያውቀው የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - አንዳንድ የአዱስ አበባ ነዋሪዎች ሳይሆኑ እኔ ነኝ ያልኩት። ለዚህም ጎረቤቴ ብርሃኑ ላይ የተገጠመውን ማየት በቂ ነው።"እዛ ማዶ አንድ ብር እዚ ማዶ አንድ ብርየዚ ቤት ጌታ ባለባቡር"ከውስጥ የነበረው ብሬ ይህ ጊዜው ያለፈበት ግጥም አቅለሽልሾት "የዚህ ቤት ጌታ ኢሃዲግ ነው አሏቹ?" ብሎ ልጆቹ ላይ አስታውኮ ይህንን ሲል የሰማው አዋቂ ያለ እንደሆን ዙሪያውን በፍጥነት ገለማምጦ በሩን ጠርቅሞት ገባ። እኔም አዳዲስ እና ነባር እንዲሁም ሪሚክስ የተደረጉ ስራዎችን የሚያ ቀርቡ አባላት ያሉት የሆያሆዬ ባንድ በምናቤ አቋቋምኩለት...እዛ ማዶ የላም ወተት(እንዴ የወተት ላም ነች የላም ወተት? ወይስ የለም ወተት? ቆይ እስኪ እዚ ማዶ ይድገሙትእዚ ማዶ የላም ወተትየኔማ ብሬ አይዘውም አተትኢሽሽ አሁን ይሄ ሟርት ነው ሙገሳ?... እዛ ማዶ አንድ ዶሮእዚ ማዶ አንድ ዶሮየኔማ ብሬ ቴዲ አፍሮ(ኧረ ሳያፍር ነው አሪፍ...ደሞ ሊያሳስሩን ነው እንዴ..)እዛ ማዶ አንድ ጠመኔ'ዝምበል!' አለ ብሬ በንዴት'ኧረ አሪፍ አዲስ ግጥም ነው' የባንዱ መሪ ነበር።ብሬም እጁን እያወናጨፈ 'በቃ በቃ ኔ በምትባል ፊደል የሚገጥም ምንም ደህና ነገር የለም' አለ። ... ብሬ ደሞ ያበዛዋል ገና ለገና ወ*ኔ ሊሉ ነው ብሎ...


ቡሄ
2008
የረሳሁት እኔ...

የዘነበው ዝናብ ካለሽበት ሃገር
ከጉንጬ ተንኖ ነው ናፍቆቴን ሊናገር
የነፈሰው ንፋስ ፊትሽን ‘ሚዳስስ
‘ኡፍ’ ያልኩት ትንፋሽ ነው ጭንቀቴ ሲባባስ
ያለሽበት ቦታ ምሽቱ ‘ማይመሸው
በሰቀቀን ሃሳብ
ያንቺን መምጣት ሳስብ
የኔቀን አጥሮ ነው
...
የሄድንበት መንገድ አንገትሽን ከእጄ
እጅሽ ከወገቤ
ልብሽን በልቤ
ፍቅርሽን አጥምጄ
ያረፍንበት ጥላ ካንደበት እርቀን አይኖችሽን ሳነብ
በመኖርሽ ስቄ በመኖሬ ስቀሽ ሃሴት ስንመገብ
በጠራራ ፀሃይ እንደምሽት መስለን
ደሞ በምሽቱ እንደፀሃይ ደምቀን
ተጓዥ መንገደኛው ካይን ያውጣቹ እያለ ከአይኑ ሲከተን
‘ባይኑ ሲከተለን
ጎርፍ ጭቃ ቁሩን መኖርሽ አስኪዶ
መኖሬም ወበቁን ንዳዱን አብርዶ
እኛ ዘንድ ተውበው ካፊያ ዶፍ በረዶ
ይህን እና ሌላ ካንቺ ጋር የሄዱ እየመላለሱ
የረሳሁት እኔን የማልረሳሽ አንቺን እየቀሰቀሱ
ማንኔተን ነቅሰው ፍቅር ነህ እያሉ እኔን አስታወሱ

#seifetemam #የረሳሁትእኔ
👍1
ለህይወትህ ዋጋ አትስጥ

ከዋጋም በላይ ነች
Priceless እንዲል ነጭ
ከምትወደው ሁሉ ነፍስህን አስበልጥ
ከፍ እንድታደርጋት ለህይወትህ ዋጋ አትስጥ
#seifetemam 2006 #ለህይወትህ_ዋጋ_አትስጥ
ቀለበቱ

ዋለ አሉኝ ከጣትሽ ገድሎ ከሚያስውበው
ሊለኝ ፈለገና አንተ የልቧ ነህ እሱማ የጣቷ ነው

#seifetemam
አቋራጭ

የኔን መጥፎ 'ሚሻ መሆኑን እያየሁ
እንዴት እንደራሴ ጠላቴን ልውደደው
… ይልቅስ…
ከቃሉ እንዳልወጣ እንዳይቀየመኝ
እራሴን ጠልቼ ጠላቴን ባልወደው
አቋራጭ መሰለኝ

ሰይፈ ተማም 2004
#seifetemam #አቋራጭ
ምርጫ
====
ቤት ሥራ ፤ ተፈንከት
ምርጫው የራስህ ነው ድንጋይ ሲወረወር
አናትህን ስትባል ግንባር እየሰጠህ ሕይወትህን ማማረር?
ወይ እየጠራረብህ በልክ እየሰተርህ ግንብህን ማበጀት አጥርህን መደርደር

#የጌታነህ_ልጅ
ነሐሴ 2009
ባንቺ መንቃት

ፈዝዘሃል አትበሉኝ ነቅቻለሁ በጣም
ከዓይኔ 'ሚገባ የሚታይ ሰው ባጣም
ስለሷ አስባለሁ እጅጉን ታትሬ
መኖሯን ለከርሞ ማደሯን ለዛሬ

#seifetemam
ሃሞተ ቢስ ጀግና

ዛሬ አዲስ አባ ውስጥ
ብዙ ሰው መሮታል
አፉ ሬት ሆኖታል
የሚጠጣው ድራፍት
መሪር እንደጅኑ
እንደጠላው ሁሉ
የሚበላውም ጫት
መሪር እንደኑሮ
የሚጣፍጥ መርሮ
ይህን ጀግና ትውልድ
እንደው በለበጣ
ሃሞተ ቢስ አሉት
ሃሞት እየበላ
ሃሞት እየጠጣ

#seifetemam
Forwarded from ቶኔቶር
ውዴ ፦
እንደኔ ያለ አፍቃሪ
እንደኔ ያለ ፈሪ
ቃላት ካፉ ጠፍቶ
ሚናገረው አጥቶ
ለፍቅር እጁን ሰጥቶ
ጉልበት ተቀምቶ
ስርሽ ተጎልቶ
ዐይን ዐይንሽን ሲያይ
ቀናት በጊዜ ቦይ ዘመን ሆነው አለፉ
ጨረቃና ፀሐይ በቀን ተቃቀፉ።
አጠገቤ እያለሽ ከዘመናት ርቀሽ
ጠፈር ሆነሽ ሰማይ
ምስልሽን ስጠብቅ አንጋጥጬ ወደላይ
ቀኑን አጨልመው ጉዳቸው እንዳይታይ
ከንፈር ይጋራሉ ጨረቃና ፀሐይ።

@TONETOR
@TONETOR
@TONETOR
ፍቅርና ደሞዝ

ስራ ተቀጥሬ ከዋክብት ቆጠራ
እጅግ አደከመኝ እንዴት ብዬ ልስራ
ቆጥሬ ቆጥሬ እየተምታታብኝ
አልሰራህም ብለው ደሞዝ ከለከሉኝ
ስራዬ ፍቅር ነው ከዋክብት ውበቷ
ደሞዜም እሷው ነች በጄየገባች ለታ
(ለ...)
ሰይፈ ተማም 1996
ድምጽ፣ ሽታ፣ ጣዕም

ምስኪኑ ሰአሊ በወጠረው ሸራ
የሳላት ጉራንጉር የሳላት መንደሯ
ድምጽ የላትም ጭራሽ
ምኗም አይሰማም
ድምጽ ቀለም ሆኖ ከሸራው ላይ የለም
እነማማ እንትና ሰውን ሲቦጭቁ
እነ ጋሽ እከሌ አዳልጧቸው ሲወድቁ
ወይዘሮ እከሊት ጠበል ሲጠድቁ
የተሰማው ሁሉ የለም ከቀለሙ
የተጠጣው አቦል ከየት አለ ጣ'ሙ
ከየት አለ ሽታው የቡናው የጣኑ
ድምጽ ሽታ ጣዕም
በቀለም አይወጡም
በብሩሽ አይሰፍሩም

ወይስ
አይን የለም እነዚን ለማስፈር ከሸራ
አይን የለም እኒህን ለማየት ከሸራ
ምስኪኑ ሰዓሊ የሳላት መንደሯ
ስንቱን እንዳወጣች ስንቱን ነገር ቀብራ

ወይም
ድምጽ ሽታ ጣዕም ከዚህ ሰፈር የሉም
አይሰሙ አይሸቱ ጨርሶም አይጥሙም
እንደድሮ አይደሉም
ወይም...

ወይም ይጮሃሉ
ወይም የገማሉ
ወይም ይመርራሉ

ድምጽ ሽታ ጣዕም ኑሮነን እያሉ
ባለመሳል መስመር ሁሌ እየተሳሉ

#seifetemam #ድምጽሽታጣዕም
ለአከራዬ ልጅ

መብራት የጠፋ ለት ሻማ ስታበሪ
ጥላሽን አየሁት ልብስ ስትቀይሪ
ልብስ የምታጥቢም ለት ጨምረሽ ከሳፋ
(መብራትስ ሁሌ ይሂድ ውሃ ግን አትጥፋ)
ጦረኞቹን አየሁ ሲሉ ቀና ደፋ
ቀና ደፋ እያልኩኝ ስሰራ የምታይ
እንዳያልፍብኝ ነው የናትሽ ቤት ኪራይ
ቤት ኪራይ ፍለጋ ጊቢያችሁ ስመጣ
አንቺን ብዬ ከፈልኩ ቤቱስ አያዋጣ
አያዋጣም ከቶ 'ማይከለል መስኮት የማይዘጋ በር
እናትሽ ሲወጡ ካልመጣሽ በስተቀር


#seifetemam #አሁን
@seifetemam @seifetemam
አቻ

ቃላት ሳታረቁ
ነገር ሳታደቁ
ያላቻ ጋብቻ
ይቅር ብሎ ብቻ
አቻ ደሃ አጥተን
ይኸው ቆመን ቀረን

ሰይፈ ተማም
2007
#seifetemam
🤩1