ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እሰይ ሰውነት ገነነ
(ከሰይፈ ተማም)

ምስጋና፣ ውዳሴ፣ አርምሞ
ነፍስ በስጋ ተስሞ
ዓለም ምድሩ ቀሊል ሆነ
እሰይ ሰውነት ገነነ

ቅድስና ውስጡ እንዳለ
የሰው አይምሮ ባነነ
በአንዲት ቅጽበት እልፍ ሃሳብን
እንደጭስ እያቦነነ

መከልከልን እንኳን ለሰው
ለ'ግዜር እምቢ ያልን አመጸኛ
በቅጠል ሳንጽፍ አንሞትም
የአለም ምድሩን መዳኛ
የሳር ቅጠሉን አዱኛ

የዳመናውን ጥጥ ዳመጥን
ሰማይ አልጋችን ሆነ
ምድርን እደጊ ብለን
እንትፍ ያልንባት ዘነበ
በነጠላ ቆመን እንኳ
እኛ ብሎ ለማለት ልባችን መቼ ቦዘነ
እሰይ ሰውነት ገነነ

የዳመጥነው ተፈተለ
በውብ ተሸመነ
አማረ
በጠላት ያልወደቀ ገላ
ይኸው በጥለት ዘመነ
እሰይ ሰውነት ገነነ

እሰይ ሰውነት ገነነ
ነፍሱን ተግባባት ስጋ
'ራሱን መጠየፍ ሰጋ
ማብቀል ሆነ ያሁን ጸጋ
በጸደቀው ደምቆ ረካ
ባጸደቀው ጸድቆ ፈካ
ሰውም ከሰው ተሰካካ

እሰይ ሰውነት ሰላ
ገዘፈ ከአካል ከገላ
ተኖረ በቅጡ ሞልቶ
ተሰማ ኦባንግ ሜቶ
ተተነፈሰ ጻድቅ ቃል
እሰይ ሰው መግደል ሞቷል
እሰይ ሰውነት ገኗል

በአንዲት ቅጽበት እልፍ ሃሳብን
እንደጭስ እያቦነነ
የሰው አይምሮ ባነነ
ቅድስና ውስጡ እንዳለ

ምስጋና፣ ውዳሴ፣ አርምሞ
ነፍስ በስጋ ተስሞ
ዓለም ምድሩ ቀሊል ሆነ
እሰይ ሰውነት ገነነ

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ 2012

@seifetemam
My random thoughts in three minutes

By: Biniyam G (Bini_x)


My random thoughts in three minutes
I put on my glasses and see the world with the scratches,
Living in the despair of my innocence,bleeding parts all fixed with plastic patches
Reality is fucked cause everybody can have their own
Playin for the throne, it's like die trying or get that crown
Crashing capitalism is freedom, for some
All the fairness needed, to grow and to triump
Illusions are what dreams have become
Niggas wishing if the pain at least makes them stronger
Thoughts that hit you at midnight when you are sober
It's crazy what happens when you spit the truth
When you call it like it is, when you skip the sooth
It will be 8:00pm and you will be alone in the city
Thinkig, What you know being too less in a way
I tell you, It's just enough if it gets you through the day
For all the wisdom you gain, there is a greater price to pay
If I have to compare how I live with how I am.
How I feel with the climb?
I don't need anything to numb the pain I gotta feel it
I ain't scared of being hurt but when I can I gotta curve shit
Just teach your heart how to be patient
Death is on the high way and if it's late,
it wont be too late.
Stop waiting another day to make the changes you need
If you fuck it's to make a different breed
See now, Tough guilt weighs heavy on my heart
It's like I sinned in ways that are different
Easy to make promises, especially when you are drunk
For your self, Not necessarily for another skunk
Witness your ship as it sunk
On the side,
Nigga with a six pack,
But lost the fat,
Dissolved in alcohol,
That is protocol,
Of the mist,
Life is a gift, strapped with a broken soul
Standards defined for,
fabricated truth taking toll
Last breath being stalled
But still everyone is a know it all
So now...
Thinking I am used to, people leaving me
Used to, having less friends than enemies
Most times,
They tell me the devil is in the details
I ignore those
As it is, I am the architect of my soul
So I put my chest in, head up
And see beyond all
Even though the faults are what are too close
Perfection and forgiveness, I choose both
Reality pinches me, but i fail to respond
Maybe The Highs and lows it's got to be a rhythm
I don't wanna join, and still I aint got to beat them
Been called a narcissist,
Been called inconsiderate,
Below what they anticipate,
Probably end up alone, if I keep going with this pace,
My generation, is controlled over who we must love and hate
It's not what you put in but karma, luck and fate
No pride but for money, power and estate
And when you can hardly relate?
You probably insane, it's you that they resent
As long as you can't pretend, its impossible to blend
Dehna neh endet nesh, is the kind of wisdom to trend
Gotta be open minded or open minded people judge you instead!

@Machiavellixx #Bini_X #poeticsaturdays #ግጥምሲጥም
Forwarded from ከሀ-ፐ
   አንዳንዴ መፅሀፍት በጣም ተጋኖ ይወራላቸዋል። ነገር ግን ገዝተን ወይም ተውሰን ስናነባቸው እንደጠበቅነው ሳይሆኑ ይቀራሉ። የእሱባለው አበራ ንጉሴ "ትዝታሽ ፡ ለእኔ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ"  የተሰኘው መፅሀፍ ከነዚህ መፅሀፍት ፍፁም ይለያል። ይህ መፅሀፍ ተጀምሮ እስኪያልቅ በእያንዳነዱ ገፅ ብዙ ነገሮችን ይዳስሳል።
 የመፅሀፉ ደራሲ እሱባለው አፃፃፉ እፁብ ድንቅ የሚያስል ነው ። አንዴ የሚነበብ መፅሀፍ ብቻ ሳይሆን ተደግሞ እንዲነበብ አድርጎ ነው የፃፈው ።
  ግን እንደ ማኪያቶ ባያንስ ደስ ይል ነበር ። ለነገሩ ማኪያቶ ስላነሰ አይደል የጣፈጠው እረ እንደውም መፅሀፉ እንኳንም አነሰ ።
 ለአንበብያን እንዲያነቡ ከሚጋብዛቸው መፅሀፍ አንዱ ሆኖ አግኝቼዋለሁና . . . . .መልካም ንባባ!!!!
በምን ሃሳብ?
በሚሞናደለው በሚሞዳሞደው
ጎረምሳውን ሁሉ አንገቱን ባስቀጨው
መዳፌን ቸብ አርገሽ ልቤን የሰቀልሽው
ምን ልሁን ብለሽነው?

ደሞ ሲያወሩብሽ የሰፈር ሰው ሁሉ
ተነኳኮሰቸው ለከፈችው አሉ
በአንዱ እያየሽኝ አንዱ መራገቡ😉
ምን ማለትሽ እንደው አይኖችሽ ያውቃሉ

. . . ምን አስበሽ ነው ግን?

ቆነጀሁኝ ብሎ እግር ማደናበር
ተኩያለሁ ብሎ አይን ማቀዣበር
ወገብ አለኝ ብሎ ቅስሞች መሰባበር
አለንጋ አለኝ ብሎ ሰው በጣት ማባረር

ምን አስበሽ ነው ግን ምን አስበሽ ነበር?

በፈገግታሽ ግለት ወደ አፍሽ መጣራት
በከንፈርሽ ቅንጦት መሳምን ማስመኘት
ጀላቲ ባረገኝ ምላስሽን ብበርዳት
ጥርስሽን ታክኬ ጣዕሜን ብትመጫት
ምን አስቤ ነው ግን?🤔

ተራራሽን አየሁ አካል ማንቀጥቀጫ
ለፓርቲ 🕺 ይመቻል ያወጡት መግለጫ
ወዮ ከምን ገባሁ🙆🙆 እንጃልኝ እኔንጃ
ይኸው ስቆም አለሁ ላንቺ መቀመጫ

ምን አስቤ ነው ግን?

ከገላሽ የጣፍሽው ጎትተሽ አይኖቼን
መዳፌን ቸብ አርገሽ የሰቀልሽው ልቤን
የምትነካኪው በጸጉርሽ ታጦቼን
በአምስተኛው አፍሽ የምትበዪው አፌን

ምን አስበሽ ነው ግን?🤔

የምታቃስችው በርሜል 🛢 እንደገፋ
የምተነፍሰው ባሉን 🎈 እንደነፋ
ላብ አደሮች ሆነን ሰርክ የምንለፋ😥
ለምንረሳሳው ለምንጠፋፋ
ምን አስበን ነው ግን?🤷

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም
Forwarded from Seifu
Forwarded from Betsi Dems
Forwarded from Kelela Guides
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአማርኛ፡ በአፋን ኦሮሞ፡ በትግርኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች በመጪው ሳምንት፥ በሶማሊኛና በአፋርኛ ደግሞ በቀጣዮቹ ሳንምታት ማግኘት ይቻላል።

ማህበራዊ ደረ-ገጾቻችን በመከታተል እነዚህንና ሌሎችንም ይዘቶች መከታተል ትችላላችሁ 😊

#KelelaGuides #ከለላ
Now there she goes again, the dopest Ethiopian
And now the world around me be gets moving in slow motion
When-ever she happens to walk by - why does the apple of my eye
Overlook and disregard my feelings no matter how much I try?
Wait, no, I did not really pursue my little princess with persistence
And I was so low-key that she was unaware of my existence..."

Fatlip on The Pharcyde’s “Passin’ Me By” (Verse 4)

#gitemsitem #ግጥምሲጥም #Rapሲጥም
https://t.me/seifetemam
… The scene of a crime every night at the show
The fiend of a rhyme on the mic that you know
It's only one capable, breaks-the unbreakable
Melodie unmakable, pattern unescapable,
A horn if want the style I posses
I bless the child, the earth, the gods and bomb the rest
For those that envy a MC it can be
Hazardous to your health so be friendly
A matter of life and death, just like a Etch-a-sketch
Shake 'till your clear, make it disappear, make the next
After the ceremony, let the rhyme rest in peace
If not, my soul'll release! …

Rakim - Lyrics of Fury
#gitemsitem #ግጥምሲጥም #Rapሲጥም
https://t.me/seifetemam
Forwarded from Kelela Guides
ከለላ ለልጆች ምን ምን አካታለች?

ከለላ ልጆች መምሪያን በዚህ ሳምንት አጠናቀን እስከምናካፍላችሁ በውስጧ ምን ምን እንደያዘች እናሳያችሁ! ☺️

ምዕራፍ አንድ በአጠቃላይ ስለልጆች ወሲባዊ ጥቃት ታስዳስሰናለች። ከትርጉም አንስቶ፡ አጥቂዎቹ ምን አይነት ሰዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ፣ ልጆች ጥቃት ከደረሰባቸው ሊያሳይዋቸው የሚችሉዋቸው ምልክቶች፣ በረጅም ግዜ ያለው ጉዳትና የመሳሰሉትን ታስተምረናለች።

ምዕራፍ ሁለት ደግሞ ስለመከላከል ታስተምረናለች። በተለያዩ የዕድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ልጆች ባህሪያቸው ምን ይመስላል? እንዴት ማስተማር እንችላለን? ማስተማርስ ያለብንስ ምንድን ነው? ልዩ ጥበቃና እንክብካቢ የሚያስፈልጋቸው ልጆችንስ እንዴት እናስተምር? የሚሉትን ትመልስልናለች።

ምዕራፍ ሶስት ደግሞ ጥቃቶች ከተፈጸሙ ምን ማድረግ አለብን? ልጆቻችንን እንዴት እናናግራቸው? እራስችንን እንዴት እናረጋጋ? ምን አይነት የህክምናና የህግ ክትትል ማድረግ እንችላለን? ከነዚህ ክትትሎች ውስጥስ ምን መጠበቅ አለብን? የሚሉ መልሶችንና ሌሎችንም እናያለን።

#KelelaGuides #ከለላ
Forwarded from ተረኛው ብእር (Betsi Dems)
~የፍም ቅንጦት~
በእልልታ ዘመን
ቀርቶ ለመኮነን
የእቅፉ ደስታ
ያልነጠፈ እርካታ
በጥጉ በመስኩ
ለይቶ በመልኩ
ተንዠርግጎ ነበር
ከአለሙ ቀንበር
ተሹሞ በክብር

በከልታማ እይታ
ተፈርዶ በኮታ
ከአላፊ ጓዳ
ተሰማ አጓዳ

ቢያነካካበት ዝንብ
ተረብሾ ከልብ
በጭንቅ ሰረገላ
ውበቱ ሲጉላላ
ስማልኝ አንተዬ
ተከተለ ወዬ
ርዕሱንም ባታውቅ
ከቶ እንዳትሳቀቅ
ባዩ ሲያባብለው
ከፍላት መለሰው

በዛሬ ተጭኖ
ነገውን ተማምኖ
ገፅ እያላተመ
አመድ ተቀመመ

በጣረሞት ጊዜ
ተረስቶ አባዜ
ሲሄድበት ሚዜ
ዝንቦቹንም ረሳ
አንበሳ እያገሳ
ወርቂቷን ሊበሳ
የባሰውን ሲለብስ
ለመጣለት ቅልስ
የለውምና መልስ
እንደምን ይቀስቀስ

ግና ተጨነቀ
ፊት እንዳረቀቀ
ላደጋው አይደለም
ለማጡም አላለም
ዘልቆ ስላልገባ
የረመጡ ካባ
አምጡልኝ እያለ
ሰሚ ስለሌለ
በምሬት ዘለለ
ከቂል እያበረ
መኖርን ቀበረ

በ እ.እ
ልብ በሉ ስራዎቻችሁ በድምጽ ወይም በጽሁፍ መላክ የሚችሉ ሲሆን የውድድሩ ርዕሰ ጉዳዮች የሆኑት የአረንጓዴ አሻራ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ብዝሃ ህይወት ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው።
Forwarded from Getz_mag
“Everyone who has a platform should use it to create spark social conversation. It’s not an obligation, but an ethical responsibility.” - Henok Girma https://bit.ly/Getzmag-Issue9