ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Effortless (Bluu)
Fate isn't exclusively mine,
Like everyone here I gotta wait in line,
Fate doesn't happen to me,
Stumbling along the lines of fear and boldness,
I happen to it,
Fate isn't biased,
"Resigning to my fate" is hoax,
Fate is where you decide to go,
Fate is who you decide to be,
Fate isn't exclusively yours,
One fate wasn't designated for you,
Fate doesn't happen to you,
Along the lines of taking chances,
You happen to it,
"Accepting your fate" is a hoax,
Nothing is given,
With fate, we're always taking,
Not what is predeterminedly ours,
Not what has been written and left to the dust,
With fate, we're always taking,
Taking segments to draw our own line.
@cannotthinkofstgcool
ምታት ምታት አለኝ፤ እራስ እራሴን
ከፍ ዝቅ አረገኝ፤ አንጀት አንጀቴን

ዞር ዞር እላለው፤ እንደነኩት መሪ
ጎንበስ ጎንበስ እኔው፤ ደርሶ እንደአፋሪ

ቅልሽልሽ ቅልሽልሽ ፤ ቂም እንዳረገዘ
ድንብርብር ድንብርብርብር፤ ሰርቆ እንደተያዘ

መሀል አየት ፤ ጥግ ለየት
ድንገት ፍክት፤ ወድያው ጥፍት

ደሞ ልስልስ፤ ከዚያ ውል'ፍት
አይቶ ክስስ፤ ሰምቶ ምልስ

አውቆ መርሳት፤ ጥሎ ማንሳት
ይህን መንካት ፤ ያን ማንኳኳት

ትቶ መተው፤ ቂሎ ማቄል
ስሎ ማሾል፤ ስቶ ማ'ሴት

እንዲህ እንዲያ፤ እንዲያ እንዲህ
እዚህ እዚያ ፤ እዚያ እዚህ

እኔን ያደርገኛል፤ እኔ አደርገዋለው
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ዛሬ
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ርብቃ ሲሳይ @Ribki
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #ርብቃ_ሲሳይ
ከጥያቄሽ ሁሉ እኔን ደስ የሚለኝ
"ትወደኛለህ ወይ"? ብለሽ ስጠይቂኝ
አዉ እወድሻለሁ አዉ እወድሻለሁ
ጠይቂኝ ግዴለም
አንድ ሺ አመት መሉ
አዎ'ወድሻለሁ ብልሽ አይደከመኝም
:
:
:
ከጥያቄሽ ሁሉ እኔን የሚጨንቀኝ
ቃል የሚቸግረኝ
"እንደምን?" ስትይኝ
እንደምን ልበልሽ
እንደ ፅጌረዳ?
እሱ'ኮ ውበቱ ነው እስኪፈነዳ
እንደምን ልበልሽ እንዳደይ አበባ
ባመት እንደሚታይ መስከረም ሲጠባ
የለም የለም
እንደሱም አይደለም
ከምሽት ጨረቃ ከማለዳ ፀሀይ ትደምቂያለሽ በጣም
ያለም ውዱ ሽቶ የገላሽን ጠረን ፈፅሞ አይወክልም
የምወደው ሁሉ ምን በቃል ቢሞሸር አንቺን አያክልም
እርግጥ ነው የቤተስኪያን ዜማ
ቅዳሴ ስሰማ ልቤ ይሸፍታል
ላንቺ ያለኝ ስሜት ግን ከዚህም ይለያል
እባክሽ የኔ አለም
ሰማይና ምድር እንደሚያልፉ እያወቅሽ
እንደምን አትበይኝ እንደምን ልበልሽ
ምንም ስለሌለ ላንቺ "እንደ" የምለው
አንቺን የምወድሽ አንዳንቺ ብቻ ነው

ዳግም ተካ
#ግጥምሲጥም #ዳግም_ተካ
Bibliographic information

Title Together in a Sudden Strangeness: America's Poets Respond to the Pandemic
Editor Alice Quinn
Publisher Knopf Doubleday Publishing Group, 2020
ISBN 0593318714, 9780593318713
Length 208 pages

https://bit.ly/2N8CbVT
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
የኤቶዮጵ መጽሐፍ ደራሲ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ እና ሌሎች አስራስድስት ወጣትና አንጋፋ ደራሲያን በሕብረት ሆነው በጉራማይሌ የአጻጻፍ ስልት በብዕር ቅባት አእምሯችሁን ሊያዋዙ ይኸው ሰብሰብ ብለው " አቦል " በተሰኘ ዳጎስ ባለ ድርሳን መጥተዋል ::

የአብሮነት ውልድ ልጃቸውን " አቦል " ብለው ጠርተውታል፡፡


ያንብቡት ::

ለቴልግራም @jafbok
ለዌብሳይታችን www.jaferbooks.com

መገኛ :- ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Power of Art: Performance and Collaborative Expressions

Art isn't just for aesthetics. They say that it is art together with science that allows a society to move forward by asking stronger questions. This time, we are seeing art in its core as a powerful means of starting dialogue and communication. We hope you enjoy tonight’s conversations. And don’t forget to message us your questions and feedback.

Special thanks to Mulugeta Gebrekidan, Va-bene, and John Herman for making this session possible.

Openly share your individual views and opinions. The session has been recorded and streamed live and due to the depth of the topics, this session will not be suitable for children. Watch the full conversation on Facebook by clicking here: facebook.com/Tibeb2020/videos/1135392696830915/

Copyright/photo credits - pIAR [Perforcraze INTERNATIONAL ARTIST RESIDENCY]
Forwarded from HAPPY (Ribka Sisay)
____ልቤ_____

የሰላምን ፡ ጣዕም ፡ እረሳው: ልቤም ፡ አመፃን ፡ ወደደች፤
የእረፍትን ፡መልክ ፡ ዘነጋው: ነፍሴም ፡ ረብሻን ፡ ፈለገች።
___________________
ህሊናዬ ፡ ግን ፡ ይለኛል : ይህ ፡ መንገድ ፡ ያንቺ ፡ አይደለም፤
አይኔ ደግሞ ፡ ይፈልጋል: ያያል ፡ ግን ፡ ሚታይ ፡ የለም፤
___________________
ልቤ ፡ አመፃን ፡ ወደደች ፡ ማን ፡ ይልቃል ፡ ከጉልበቷ፤
ነፍሴም ፡ ረብሻን ፡ ፈለገች ፡ማን ፡ ይልቃል ፡ ከልኬቷ፤
_________________
የሚገስፅ ፡ የሚመልስ ፡ የሚወቅስ ፡የሚያቃና፤
የተቻለው ፡ የሚቻለው ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡የለምና፤
የፈሰሰ ፡ የእንባ ፡ ሳቅ ፤
የሚመስል ፡ የሀዘን ፡ስላቅ፤
የቆሰለ ፡ የፈውስ ደም፤
የሚመስል ፡ድኖ የሚያም፤
የተደበቀውን ፡ሚስጥሬን፤
እንድታውቀው ፡መሰበሬን፤
ምነግርበት ፡ ቃል ፡የለኝም፤
ቃል ፡ ባወጣም፡ አታምነኝም።
_______________
ታውቀኝ ፡ እንደው፡ፊቴን ፡ አልፈህ ፡ ተመልከተኝ፤
ታዝን ፡ እንደው ፡ ሳቄን ፡ትተህ ልቤን እየኝ።
_______________
ልቤ፡ አመፃን ፡ ወደደች፤
ነብሴም ፡ ረብሻን ፡ ፈለገች፤
የሚወቅስ ፡ የሚያቃና ፤
ካንተ ፡ በቀር ፡ የለምና፤
ፈገግታዬን ፡ ሳቄን ፡ ትተህ፤
ተመልከታት ፡ ልቤን ፡ መተህ።
____________________
እኔ ርብቃ ሲሳይ በሰኔ እሮብ 10 ቀን ፃፍኩኝ😁@beyoubegoodbehappy
Rap is a complex mix of
influences, including
elements of speech , prose,
poetry, and song . Learn to
rap by listening to the
masters, learning rhythms,
and practicing your own
lyrics. There are no
shortcuts, and you won't
sound like Kendrick Lamar
overnight – but if you put in
the hard work, you'll be
rewarded.

https://www.facebook.com/Ethio-Rap-Game-ERG-481719268940791/?ref=page_internal
I woke up this morning and figured I'd call you
In case I'm not here tomorrow
I'm hoping that I can borrow a piece of mind
I'm behind on what's really important
My mind is really distorted
I find nothing but trouble in my life
I'm fortunate you believe in a dream
This orphanage we call a ghetto is quite a routine
And last night was just another distraction
Or a reaction of what we consider madness
I know exactly what happened
You ran outside when you heard my brother cry for help
Held him like a newborn baby and made him feel
Like everything was alright
And a fight he tried to put up, but the type
Of bullet that stuck had went against his will ...


Kendrick Lamar - Sing About Me, I'm Dying of Thirst
. . .
ደሞ እንደ መስቀል ወፍ እንደ አደይ አበባ
ህይወት እንደሚያድስ መስከረም ሲጠባ
እናፍቃታለሁ እንደ ህጻን ልጅ
አትሂድብኝ የትም አትውጣ ከደጅ. . .
. . . እንደ ናርዶስ ሽቶ እንደ ፈዋሽ ጸበል
ማነው ያልተመኛት የኔናት የማይል
የትም ዞራ ውላ ስትመለስ ድንገት
ያጣል መሸሸጊያ አይኔ የሚገባበት
ማን ለምን ይላታል ማን አለ ጠያቂ
የቱ ሽማግሌ የትኛው አዋቂ. . .

ሲያምረኝ - ምትናፈቅ
'ጉራ ብቻ'
(በታመነ መንግስቴ)

ያው የማከብረው ወዳጀ መምህር ሀብታሙ አለማየሁ አንድ ማስፈንጠሪያ(Link) ላከልኝ።Egypt Independant የተሰኘ ገፀ ድር ጉራ ተሸክሟል።"ኢትዮጵያ እና ግብፅ ጦርነት ቢገጥሙ ማን ያሸንፋል?" ዓይነት የሰይጣን ንፅፅር ውስጥ ለመግባት ሲንደረደር የአገሩ ርዕሰ ብሔር አብደል ፈታህ አል ሲሲ የአየር ኃይል መኮነኖቻቸውን "ለየትኛውም የአገር ውስጥ ወይም የድንበር ባሻገር ተልዕኮ ተዘጋጁ"እያሉ ማሟሟቃቸውን ወሽክቷል።

ይቀጥልና የግብፁ ውጭ ጉዳይ ምሉክ ሳሚ ሽኩሪ ስለ እኛው አቻቸው አቶ ገዱ ዓረፍተ ነገሮች"ጠብ አጫሪነትና"እና "አበሳጭነት" መናገራቸውን ፅፏል።ከዚያም ከዓለም ዐቀፉ የጦር መሳሪያ ሃይል ድረገፅ አገኘሁት ያለውን የኢትዮጵያና ግብፅ ንፅፅሮሽ ያስቀምጣል።ለአብነት፦

ሀ.የግብፅ ዓለም ዓቀፍ የጦር አቅም ዘጠነኛ ሲሆን የኢትዮጵያ 60ኛ ተብሏል።

ሁ.የግብፅ ዓመታዊ የጦር ኃይል ገንዘብ ድልድል(በጀት) 11.2 ትዕልፊት(ቢሊዮን) ሆኖ የኢትዮጵያው 350 አዕላፍ(ሚሊዮን) ተገምቷል።

ሂ.የግብፅ ወታደሮች ቁጥር 920ሺ ተገምተው የእኛዎቹ 160ሺ ላይ ተቀምጠዋል።

እንግዲህ ነፃነትን ለ2ሺህ ዓመታት ተነፍጋ በቱርክ፣እንግሊዝ፣ሮማ፣ፋርስ፣እና ኢትዮጵያ ስትገዛ በኖረችውና ነፃነትን በማታውቀው አገረ ግብፅ ያለ የሚመስለው 'Egypt Indepndant' የፃፈውን እንመነውና ወደ እኛ ጉዳዮች እንምጣ፦

'ከነገራችን ጋር' የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምሉክ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የያዙት መንገድ አይከፋም።ግብፅን እንደማንፈራትና በተለይ በሁለት እጆቿ ልታፍስ መቃጣቷን መቃወማቸው ያስመሰግናቸዋል።_ ሰውየው ደመ ሞቃት ስለመሆናቸው ራሳቸው ለዘመን መፅሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ውስጥ አንብቤያለሁ።

ቢሆንም ከዘመን አይሽሬው የኢትዮጵያ ላዕከ መንግስት(Diplomat) አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር የሚነፃፀር ብልጠት ያስፈልጋል።አክሊሉ በማስታወሻቸው እንደፃፉልን ኤርትራን ለማስመለስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ረፍት አልባ ሆነው ለህመም ሳይቀር ተዳርገዋል።የዚያኔ ኢትዮጵያን በስም እንኳ በደንብ ከማያውቋት አገራት መሪዎች ጋር በፈጠሩት መልካም ግንኙነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ደግፈው እጅ እንዲያወጡልን አድርገዋቸዋል።

ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ዛሬ "የጥቁር እንቁ" የምንለውን የጋምቤላ ምድር ወደ እናት አገሩ የመለሱት በጥበብ ነው።ኦጋዴንን፣የባቡሩን ባለቤትነት፣ ኢትዮጵያን ራሷን ያስረከቡን በከፍተኛ የተግባቦት ብቃት ነው።ከእነ አቶ ገዱ ይሄ እና ከዚህ በላይ ይጠበቃል።

የእኛ ትውልድ ሃውልት የህዳሴ ግድብ ነው።ግብፅ "ጦርነት" የምትለው 'ጉራ ብቻ' ነው።ምክንያቱም ዘመኑ አይፈቅድማ! የምወደው ነገራተሰብ(ጋዜጠኛ) ዮርዳኖስ አበበ እንደሚለው "በዚህ ዘመን በአንድ ጦርነት የሚመጣን ኪሳራ 20 ዓመት አይመልሰውም።" ጦርነቱ ከሆነም እንዲሁ በጉራ ደረጃ እና የአገር ውስጥ ባንዳዎቻችንን በመመልመል ነው።ስለዚህ ለጊዜው በአጥንት መናከሱን ትተን ወደ ጅቡ መጮህ አለብን።

ጅቡ ብዙ ነው።እነ አሜሪካም የእኛን ጉዳይ ለራሳቸው ይፈልጉታል።ያ ታላቅ ሰው-አክሊሉ ሃብቴ እንደፃፉት"ሁሉም ለየራሱ ጥቅም እንጅ በፖለቲካ 'ጀስቲስ'(ፍትሕ) እንደሌለ የታወቀ ነው።"

በዚህም ተባለ በዚያ እኛ መራብ አንፈልግም።ግዮን ኢትዮጵያን "ይከብ" ዘንድ በአምላኩ ታዝዟል።አሁንም ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ኦጋዴንን ሊነጥቋቸው ለቋመጡ እንግሊዞች"ሳንዋጋና ሳንሸነፍ ልትወስዱት አትችሉም!" እንዳሏቸው እኛም "ሳንዋጋና ሳንሸነፍ የዓባይን ግድብ ውሃ ሙሌት ልትከለክሉን አትችሉም!" ብለናል።

"ጉራ ብቻ'' የለቀቀብኝን ገፀ ድር ማስፈንጠሪያ እነሆ፦https://egyptindependent.com/is-an-egypt-ethiopia-war-an-option-a-comparison-between-the-egyptian-and-ethiopian-armies/
Forwarded from Daily Say by Rob Haile
Naked as we came,
Naked we will go.
No Nation.
No Race.
No Sex.
No Chains.
Liberty's taste so sweet
As there is nothing to hold back
The true self.
No labels.
No expectations.
Oneself and oneself only.

#DailySay
@storyteller_rh
አዲስ ቅርበት

እንደ አዲስ ተዋውቀንበት
አዲስ ሰው የምናውቅበት
በቅርበት የምንረቅበት
ረቅቀን የምንኖርበት
አዲስ መርገም አዲስ በረከት

በእጅ ማንጫው ስንነጣ
ተጣጥበነው የ'ጅን ዕጣ
ቤት ከትመን ሳንወጣ
አዲስ ውረድ አዲስ ውጣ
ዛሬን ኖረን ነገም ይምጣ

እሲቲህ ባንድነት እንስከን
እሲቲ ላንድነት እንዝፈን
እሲቲህ እንግዘፍ በአዲስ ቀን
አዲስ ቅርበት ነው ያደለን
እጅ ከሚያስጥል አስጥሎን
አስተባብሮ 'ሚያረዳዳን

ቅርበት ተው ከቻልክ ቅር እቤት
ታጠቢው እጅሽ ይንጻበት
እንንጻ እንድንጸናበት
እንጽና እንድንጸናበት

ይኸው እጄን ፊት ነሳሁት
ይኸው ፊቴም እጅ ነሳ
የራቁኝን ቀረብኳቸው
የቀበርኩት ፊት ተረሳ
ምን ጉድ ነው አትበሉ ለዚህ
አዲስ መልክ ነው ጭምብሉም
ፈተና መች ችግር ሆኖ
ያው በረከት ነው መርገሙም

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ቀን አለን!

የቆረቆረንን ጠጠር
ተነስተን እናራግፋለን
የዘመመውን ምርኩዝ
አቃንተን እንደገፋለን
ቀን አለን!
እንቆማለን!
የፍጥረቴ
አፈሬ ሆይ...
ቀን አለን!
እንቀናለን...!
ስንቃና...
ስንቀና..
መቆም ቢሰምርልንም
እንመውደቁ አይጥመንም...
እኔ ሆይ...ነይ እንርቀቅ
አንዳችን በሌላችን
አፈር እቅፍ እንውደቅ
.....

ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ማርቆስ_ዘመንበረልዑል
Forwarded from Bereket Adane
Open call by Office of the Prime Minister-Ethiopia


የዚህ ዓመት የ #አረንጓዴዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ወር ሊሞላው ነው። በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማራችሁ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ሁሉ፣ ተደምራችሁ አነቃቂ የ #አረንጓዴዐሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅታችሁ #የጠሚአረንጓዴዐሻራጥሪ በሚል መለያ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለተመረጡት ሥራዎች ባለቤቶች አስደናቂ በረከቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።


I challenge all Ethiopian creatives, film makers, graphic artists, photographers, storytellers, cartoonists, etc to come up with the best short #GreenLegacy videos and share on social media marked #PMGreenLegacyChallenge. A surprise follows for the best productions.
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን ዓለም አቀፍ ውድድሮች መሳተፍ ይፈልጋሉ? በየሳምንቱ የሚለቀቀው የአርት ሜሊንግሊስት ይመልከቱ!!
The Arts Mailing List newsletter – 29th June 2020 is out now https://bit.ly/2YGJGtD With over 100 open calls, competitions, funding and residencies, there is something for every Ethiopian artist/create!!!


This week, we also bring the multi-talented artist Enku Sillasie Yesgat https://www.facebook.com/Enku-sillasie-yesgat-art-works-410394766454671/


In this week’s newsletter, opportunities and stories from @ethiofendika, @BigDreamET, @freelance_ethio, @getz_mag, @loline_mag, @LinkUpAddis, @everythingaddis and so much more


@artsmailinglist