ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from LinkUp Addis
Join the conversation this evening!
Power of Art: Performance and Collaborative Expressions
Event Format: Online (Zoom)
Event Date: 11 June 2020 at 6:00pm
Hosted by Goethe-Institut Addis Abeba
Event Link: https://bit.ly/2Ap8RaM
Part of Tibeb Online

Make sure to download and enjoy the June 2020 edition of LinkUp Addis digital magazine: https://bit.ly/2Mg68CO #linkupaddis #eventsinAddis #EthiopianCulture
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .)…»
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (S e i f e - T e m a m)
አበቦቹ

ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች
የብራ አለም ሰዎች
የንጹህ አገር ዜጎች
ለሃሴት አፎቱ
ለፍቅርም ቤቱ
ውበት ምልክቱ
. . . ትናንሽ አበቦች. . .
እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ
እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ
ውስጠትን ሰርሳሪ
በውበት አሳሪ. . .

እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ
እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ
ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ

(ለልጆቻችን. . .)
#seifetemam
@seifetemam
Forwarded from Getz_mag
We are happy to announce that you can now find all our previous articles and magazine issues on our website www.getzmag.com
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
የዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ " ሰበዝ " የተሰኘው ዐዲሱ መጽሐፍ በሳምንት ውስጥ ስድሳ ሺህ ቅጂ ታትሞ ነው ለንባብ ገበያ የቀረበው ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

ለቴሌግራም - @jafbok
ለዌብሳይታችን - www.jaferbooks.com


መገኛችን :- ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
ጌትዬ በማርያም - 1

"ጌትዬ በማርያም!" አለችኝ
የደረቀ ስንጥቅ እጇን - ወዳይኔ ጫፍ ሰንዝራ
የተዝረከረከ ያ ቆንጅዬ ልጇን በእጆቿ ጠፍራ
''ጌትዬ'' አለችኝ አንዱን ምስኪን ባርያ

መንገድ የጠፋበት መሄጃውን 'ማያቅ
ሰው አገኘሁ ብላ የሚያበራ ድቅድቅ
መች አወቀች እሷ የስልኬን ውስጥ ድብቅ
እየተከተለች ትለምነኛለች ይቺ የኔው ቢጤ
መንገድ ያከነፈኝ ሁል ጊዜ መጤ
መንፈግ ያስኮፈሰኝ - ጌታ የጠማው ለት የሆንኩኝ ኮምጣጤ
እኔ ደባብቄው አፍኜው እያለሁ ሁሉንም በውስጤ

በእናትየው ስም ለምና - በልጅየው ስም ጠራችኝ
''ጌትዬ በማርያም በማርያም'' አለችኝ
ማርያምና ልጇ ማናለ ቢራሩ
ለሷ እንድደርስላት ለኔ ቢለመኑ ?

'ማርያም ትስጥልኝ' ልበላት ወይስ ልጇን ልጥራ
አላህ ይስጥሽ ልበል ወይስ ኪሴን ላጥራ
ጌታ ተብላለች ልቤ እንዴት አትፈራ
ይች የምርያም ወዳጅ እኔን ጌታ ብላ

ጌትዬዋ ሆንኩኝ ባስረገዛት ወንዱ
የበላይዋ ሆንኩኝ ጠቦባት መንገዱ
እኔስ ጨልሞብኝ ጠፍቶብኛል ገዱ
አለብኝ ቀጠሮ በ'ለት ሃያ አንዱ

የምድሩን ህግ የናቀ የሳምዩን ላያከብር
እንደ ክቡር ዳኛው ልንገራት እንደምን
መጥሪያ ተቀብዬ እንደምሄድ ችሎት
እንዳለብኝ እስር

መንገዴን ሰርዤ ከኮንትራት ታክሲ
በሚኒባስ ልግባ እንድሰጣት ሳንቲ
ወይስ ሚኒባሱ ይቅርና ከቶ
በባሱ ታጭቄ ልስጣት አንድ መቶ
በእግር ብጓዘው አልደርስም ከችሎት
ወይ ጌትዬ መባል ጌታው የረሳን ለት!
Black church services, murderers, Arabs serving burgers
As cats with gold permanents, move they bags as herbalists
The dirt isn’t just fertile, it’s people working and earning this
The curb getters go where the cash flow and the current is
It’s so hot that niggas burn to live
The furnace is, where the money moving, the determined live
We talk shit, play lotto, and buy German beers
It’s so black packed with action that’s affirmative
The corners

Common
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .)…»
"Let's take a trip but not of the physical Sense of direction on a kid who's artistical
Through a gallery of thoughts, of course it's dope
Pay it tough like the name on my rope
Watch it be weary instead of steppin' wit the boys
A musical massacre of inadequate noise
By the new authority 'cause of majority
Of peers who hear will award superiority
To those who know you knew now it's inevitable
I laid the track and it's simple unforgettable..."

The D.O.C. - "Portrait of a Masterpiece" (Verse 1)
". . . ፎጋሪና ፎካሪስ መሃልስ አንድ ፊደል ነው
ልዩነት የሚያመመጣው ሁለቱም ግን ለወግ ነው
ትልቅነት የጎደለው ውሃ ውስጥ መስመጥ ባይቻልም
ያንሳፍፋልም እንጂ አገር አያቋርጥም
እውነት አልዋጥ ያለው ትውልድስ ምን ላይ ያተኩራል. . .

. . . የዛሬ ሰው ሲጠማውስ ቁምነገሩም በልኩ
ፊትለፊት 'ሚናገር 'ሚያወጣውስ ከልቡ
ልብ መርጫለሁ እኔም ይቅርብኝም ስኬት
ከመቶ አጨብጫቢም አንድ ወዳጅን በልክ. . . "

ፓምፋሎን
Forwarded from ከTsenat Magazine
ከTsenatMagazine_RebelEdition2020.pdf
4.8 MB
Rebel Edition

ከTsenatMagazine_Rebel2020

Stay safe out there, better yet stay home 🖤

@KeTsenatMagazine
Forwarded from RasJany Muzik
መስከረም አይሆን ፀደይ ከሌለው አደይ፣
ሰኔም ካለዝናብ ሰኔ ነው አትበይ ፣
እኔም አንቺን ላፍታ ያጣው እንደሆን፣
ቀኑም ቀን አይሆንም እኔም እኔ አልሆን።
Anchihoye One of Ethiopias only Music Scale Mixed with Reggae Track number 2 from the Book Selamta New Sound! #rasjanyethiopia #Anchihoye #reggae #awtar #loveformusic
Forwarded from Zellan Creative and Cultural Centre
If you are interested, please let us know who you are, what project you are working on and how long you would like to use the space. You can DM us on Facebook/Instagram (@zellancreatives) with your links or email us on info@zellan.art We will let you know the availability upon scheduling. Please be aware that we expect everyone to respect WHO recommendations on preventing the spread of COVID-19.

ዘላን የፈጠራ እና የባህል ማዕከል የልምምድ ቦታ ለሚፈልጉ ሙዚቀኞች፣ ለሰዓሊዎች ክፍል/ ግቢ እንዲሁም ለአዳዲ ስራዎች አምሮአቸውን ለሚያዘጋጁ የፈጠራ ባለሙያዎች ቦታውን በነፃ እንዲጠቀሙበት ይጋብዛል።
ፍላጎት ካሎት ማንነትዎን፣ የሚሰሩበትን የስራ ዕቅድ እና ቦታውን ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም እንደሚፈልጉ ማህበራዊ ገፆቻችንን እና info@zellan.art በመጠቀም መልዕልት ይላኩልን።
ክፍት የሆኑ ቀኖችን እናሳውቆታለን።
የዓለም የጤና ድርጅት ያወጣውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረጎን አይዘንጉ::
Meet the Amazing Ethiopian Poet, Liyou Libsekal.

Liyou's poetry explores themes of home, identity and displacement. Liyou's chapbook, Bearing Heavy Things, is included in the African Poetry Book Fund's New Generation African Poets series. Her work has been included in Missing Slate Magazine, Badilisha Poetry and Cordite Poetry Review. Libsekal is winner of the 2014 Brunel University African Poetry Prize.

(https://en.wikipedia.org/wiki/Liyou_Libsekal)

Known for her incredibly powerful poetry and social activism, Liyou Libsekal has made a profound impact on people through her inclusive writing. Libsekal is a contemporary African poet who spent her early years traveling around East Africa with her family, before moving to the states to attend George Washington University. This period in her life is when she discovered her love for writing, and channeled much of her observations and frustrations about the sharp contrasts between Africans and Americans into her poetry. https://beyondthesinglestory.wordpress.co
Agar (By Liyou Libsekal)

I remember a yellow scarf fashioned every which way and beautiful bones that peaked at the cheeks.

Mounted proud “young mother” in eyes mourning a daughter left behind

Families don’t speak of shame and hindsight lives in layers.

She was pieces of you strolling tall, slender and curved but you were with me as she cocooned and rolled and stretched. Always in a flowered dress, always drenched in fate

you sit, a lakeside lullaby a picture of youth then, and forever and forever I gnaw on whether you knew near the end

but with age as authority, we lived in darkness why expect more in death?

My anger lives in layers un-abandoned, if only for my sake.


https://www.ethiobeauty.com/article/ethiopian-poet-liyou-libsekal-wins-the-2014-african-poetry-prize
ቴዎድሮስ ካሳ

በጥልቀት ወደ ግጥሙ ባህር ያደላል ። በእርሱ ስራዎች ዉስጥ መንፈሳዊ ልዕልናዎች ጎልተዉ ይወጣሉ ። ዉበት ፣ እምነት ፣ እዉነት ፣ ፍቅር እና የፈጣሪ ሁለንታ አፅንኦት ተሰጥቷቸዉ ይዳሰሳሉ ። ግጥሞቹ የማንንም ቤት ባይዳስሱ ይወዳል ፥ ይልቁኑ በራሳቸዉ ቁመት የደረሱበትን አሻግረዉ እንዲያዩ ይለቃቸዋል ።

ተወልዶ ያደገዉ ደሴ ነዉ ። ግጥም ዉስጥ ጠልቆ የገባዉ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እያለ ነዉ ። ዩኒቨርሲቲዉ ሳይኾን እድሜየ ነዉ እሳት ዉስጥ የገባዉ ባይ ነዉ ። አዲስአበባ ከመጣ በኃላም በብዙ መዉጣት ባይፈልግም በ ግጥማዊት ቅዳሜ ( poetic Saturday ) @poeticsaturday አንዳንድ ስራዎቹን አቅርቧል ። አሁን ላይ አዲስ የግጥም ቤት ለመስራት እየሰራ ይገኛል ።

ስራዎቹን በፌስቡክ ገፁ ( ቴዎድሮስ ካሳ ) ላይ መከታተል ይቻላል ።
ለባይተዋር ክንፎች
(ከቴዎድሮስ ካሳ)

አያልቅም ቅዠቱ ደርዝ አለዉ ሌሊቱ
ለአንድ ባለቅኔ
መኖር ሁለት ነዉ ሁለት ክዋኔ
አንድ
የፀሀይ ነበልባል የፀሀይ ወጋገን
ከተቀመጠበት ደርሳ እንደምትልሰዉ
እንደምትዳስሰዉ
ረዥም ቀሚሷን እንደሚዳስሳት
በነበልባል ቃሉ ቅኔ እያለበሳት ።

ሁለት
ጠልፋ ከምስታስቀር የናፍቆት ኩሬ ላይ
በመዳፏ ጨልፎ
ሁልጊዜ መጠጣት ህመሙን ቢያብሰዉ
ወደ ጥልቁ ባህር ጠልቆ እንደገባ ሰዉ
የፀሀይን ነጠብጣብ አይችልም መጠጣት
ይንጠራራል እንጅ አንድ'ዜ ሊዉጣት ።
ውስጥ አገር

የተቀደደ አገር ሲጥፉት ቢጋፋ
ድንብርብሩ ድንበር እያደር ባይሰፋ
ባቆመችህ ቦታ እግርህን ደግፋ
ደረትህን ገልብጠህ
ወደልብህ ዙረህ
ጥሩአንባህን ንፋ

ህዋስ ሳለህ ስውር ኗሪ ደቂቅ ፍጡር
ምንነትህ እንኳን ለዓለም ላንተም ምስጢር
ዛፍ አይደለህ አትነቀል
ወይ መልሰህ አትተከል
ከስንቱ ጋር በስንቱ አጀብ
‘ምትታጀብ
ከስንቱ ጋር ለስንቱ አጀብ
‘ምታጅብ
ስንት ለሊት ስንት መዓልት ስንትስ ዘመን
ካለ ትዕይንትህ ‘ምትተውን

‘አገሬ መሬት ነው ወንዝና ተራራ
አገሬ ባህል ነው ምግብና ጭፈራ
አገሬ ሰዉ ነው ኦሮሞና አማራ’
ከማንም ሳትወግን
ማንንም ሳትጠራ ማንንም ሳትፈራ
ይቻልህ እንደሆን ከቆምክባት ቦታ
አገርህን ስራ

ከምትመታው ልብህ አንድ የደም ጠብታ
ከመዋደድ ፀጋም ቆንጥረህ በእርጋታ
ሰላም አፀድ መሃል ውስጥህ አኑራታ
በክብር በሞገስ ሰንደቅህን ተክለህ
ከአይምሮ ባርነት ሰዉን ነፃ አውጥተህ
ከዓለም ሰመመን ሁሉን ቃል አንቅተህ
ባልጠፋ ሸማኔ ባልቸገረ ፈታይ ድሪቶን አትስፋ
ኑር እንጂ አብርተህ

የተቀደደ አገር ሲጥፉት ቢጋፋ
ድንብርብሩ ድንበር እያደር ባይሰፋ
ባቆመችህ ቦታ እግርህን ደግፋ
ደረትህን ገልብጠህ
ወደልብህ ዙረህ
መለከትህን ንፋ
‘ማንነህ?’ ሲልህ ያኔ ሰው ሞኙ ወገኔ
ስም አማኝ ዘመዴ
እኔ ማለት አንተው እራስህ ነኝ ብለህ
ንገረው በዘዴ

ሰይፈ ተማም 2009
Forwarded from Effortless (Bluu)
Fate isn't exclusively mine,
Like everyone here I gotta wait in line,
Fate doesn't happen to me,
Stumbling along the lines of fear and boldness,
I happen to it,
Fate isn't biased,
"Resigning to my fate" is hoax,
Fate is where you decide to go,
Fate is who you decide to be,
Fate isn't exclusively yours,
One fate wasn't designated for you,
Fate doesn't happen to you,
Along the lines of taking chances,
You happen to it,
"Accepting your fate" is a hoax,
Nothing is given,
With fate, we're always taking,
Not what is predeterminedly ours,
Not what has been written and left to the dust,
With fate, we're always taking,
Taking segments to draw our own line.
@cannotthinkofstgcool
ምታት ምታት አለኝ፤ እራስ እራሴን
ከፍ ዝቅ አረገኝ፤ አንጀት አንጀቴን

ዞር ዞር እላለው፤ እንደነኩት መሪ
ጎንበስ ጎንበስ እኔው፤ ደርሶ እንደአፋሪ

ቅልሽልሽ ቅልሽልሽ ፤ ቂም እንዳረገዘ
ድንብርብር ድንብርብርብር፤ ሰርቆ እንደተያዘ

መሀል አየት ፤ ጥግ ለየት
ድንገት ፍክት፤ ወድያው ጥፍት

ደሞ ልስልስ፤ ከዚያ ውል'ፍት
አይቶ ክስስ፤ ሰምቶ ምልስ

አውቆ መርሳት፤ ጥሎ ማንሳት
ይህን መንካት ፤ ያን ማንኳኳት

ትቶ መተው፤ ቂሎ ማቄል
ስሎ ማሾል፤ ስቶ ማ'ሴት

እንዲህ እንዲያ፤ እንዲያ እንዲህ
እዚህ እዚያ ፤ እዚያ እዚህ

እኔን ያደርገኛል፤ እኔ አደርገዋለው
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ዛሬ
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ርብቃ ሲሳይ @Ribki
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #ርብቃ_ሲሳይ