ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ለ አባባ ተስፋዬ 1
'ዛሬ አበባዎች
የነገ ፍሬዎች'
ብለው ከጠሯቸው ስንቶቹ ረገፉ?
ለሳሎን ጌጥነት ስንቶች ተቀጠፉ?
እርሶስ ፍሬ ሆነው ተዘርተው አለፉ::
#seifetemam
ለአባባ ተስፋዬ 2

ያኔ...

የፕላስቲክ ኮዳ የሞባይል ካርዱ
መንገድ ሳይከመር
መስኮትና ጣሪያው በዲሽ ሳይወረር
አንድ ቲቪ ብቻ ላንድ ሙሉ ሰፈር
አንድ ቲቪ ቻናል ላንድ ሙሉ ሃገር
አንድ ሰው ብቻውን ስንቱን ያስቆም ነበር?

ኋላ ላይ...

እንደ'ውቀት ፍሬ ልጅ ሁሉ እድሜ በላ
እንደ አዳም ባነነ ጩጬ ና ፈልፈላ
ገባው እንደሌሉ አባባ ተስፋዬ
ከስክሪኑ ኋላ
ፎገሩኝ እያለ ተካቸው በሌላ

ከዛም...

ቴሌቭዥኑም ከስቶ እንደእንጀራ ሳሳ
ገብስ ወረረው ፈልቶ የአበባውን ማሳ
ልጅ ባገሩ በዝቶም ልጅ ሁላ ተረሳ
(በአካል ተከስቶም) ለአባባ ተስፋዬ ጠፋ የሚነሳ

ከዛም በኋላ...

ለገዢው መደብ ጦር ተሰለፉ ልጆች
ለአባይ ዘመሩ ጮሁ ለታጋዮች
'ብሔር ብሔረሰቦች'

ከ'ዛ በኋላም በኋላ...

እነዛን ተወዝዋዥ እጆች
እስኪዘክራቸው ታሪክ
እስኪገኝ የአባባ ምትክ
አዋቂው እንደ ልጅ ይጃጃል
ልጅም ይቅበጥ በአዋቂ ልክ
ማንም ለማንም አይነሳ
እራሱን ያክብር ዘመኑ
'1' እና '0'ን ቀምሩ
የ'1' እና '0' ነው ቀኑ
በሉ ልጆች ደህና ሁኑ
ደህና ሁኑ ደህና ሁኑ
#seifetemam
ለማፍቀር ቀጠሮ

ሸትታ 'ምትገለማ
መርቅዛ 'ምትገማ
ወፍፋ ያበደች
ጨርቋን ጥላ የሄደች
ማንነቷን ስታ
ከሆነው ተጣልታ
ካልሆነው ተጣብታ
ያልሆነውን ሽታ
ማስመሰል አብዝታ
በመክሰም ለማበብ
በመግደል ለማከም
በምታደክም አለም
ውዴ አንቺን ልወድሽ
'ሚገባ አይደለም
...
... ... ስለዚህ
...
በናርዶስ ምዓዛሽ የዝች ቅርናት አለም ሽታዋ ከጠፋ
ወይ ሰናይ ፀባይሽ አሽሏት እንደሆን እንዳትቀር ወፍፋ
ማስመሰሏን ከሳ
እራሷን ስትሆነው ደግሞ ተመልሳ
ቀጠሮ ስላለኝ ያንግዜ ልወድሽ
አለሜን አክምያት እንዳይረፍድ ባክሽ
#seifetemam
የገጣችን ታዳሚዎች ሆይ
ከስር በተቀመጠው ማግኛ (link) ከ9500 በላይ ወዳጆች ያሉትን የ ፌስቡክ ገጣችንን ትጎበኙት ዘንድ ተጋብዛችኋል https://www.facebook.com/gitemsitem/
የአለም ሰባኪ

እከዘለዓለመ አለም
ስለሚያኖረው አውርቶ
ከሚያስቀድሰው
የሚያስነውረውን አብዝቶ
በደቂቃ ደቀቀ ሳቱ ባላቸው ስቶ
የሳቱትም ፈረዱ መሳት በሳት በርክቶ
#seifetemam 2008
የማለዳ ፀሎቴ

በቀኝህ አውለኝ ብሎ እንዲፀልይ ሰው
… እኔ ግን ብያለሁ
በየ ደረስኩበት እንደው በየቦታው
ወረፋና ሰልፉ እግሬን ስላዛለው
… እኔ ግን ብያለሁ በግራህ አውለኝ
ግድየለም ግዴለም
ግራውም ያንተው ነው
#seifetemam
#gitemsitem #poetic_saturdays #ግጥም_ሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #seifetemam

ህመሜን ላጣጥም
-----------------------
እስቲ ልንቆራጠጥ ተዉኝ ላቃስትበት
ህመሜን ላጣጥም እስክፈወስበት
እንዳትወጉኝ ማደንዘዣ
እንዳትሰጡኝ ማስታገሻ
በሰፊ አውታር መገናኛ
በብልጭልጭ መሸፈኛ
የዘመን ጎርፍ አግበስብሶ
በከሰተው መከወኛ
ከኔ በላይ ላያማችሁ
ከህመሜ ላይ ሰራርቃችሁ
በሽተኛ ስንኩል ሳለሁ
አታፍጥኑት ሞቴን ካለው
እያላችሁ ጤነኛ ሰው
ልዳን እንጂ አታስታግሱኝ
ተዉኝ ተዉኝ ልንቆራጠጥ
ላተኩሰው ሆዴ ይቁረጥ
እራሴ ይምታ አይኔ ይበጥ
ሰው አድርጉኝ የሚሰማው
ከራሱ ጋር የሚታደም
በሽታዬን ካልተቀማሁ
በህመሜ ነው የምታከም

ሰይፈ ተማም 2009
አንድ ሰው

‘ሜክሲኮ ሜክሲኮ’
ይጣራል ወያላ
ሰባት ሰው ይዞ
ባዶ ወንበርም ይዞ
‘አንድ ሰው የሞላ’
ይህ ታክሲ ሊሞላ ስንት ቀረው ብሎ
ተሳፋሪው አይኔ ይቆጥራል ቀላቅሎ
ወጪውን ከወራጅ ትርፉን አመሳቅሎ
‘አንድ ሰው አንድ ሰው’
ድምጹ እየከረረ
እንደኔ ላለ ሰው ቆንጆ ላፈቀረ
ወይም ለቀጠረ
የጊዜን ግፍ አውቆ
በመሙላት ተሳልቆ
‘ አንድ ሰው አንድ ሰው’
ይሄ ልጅ ምን ነካው
ትመጪ ይመስል ትገቢ ከታክሲው
አንድ ሰው የሚለው
እኔ በበኩሌ
በአንድ ሰው ብቻ የሞላሽ እማቀው
አንድ አንቺን ብቻ ነው
እንጂማ
እንዳንቺ አቀራረት በዚህ ልጅ አጠራር
ይህ ታክሲና ልቤ ባንድ ቢነጻጸር
‘ አንድ ሰው’ ማለቱን ወያላው አይጠላም
ቢገባም ባይገባም
ታክሲውና ልቤ
እንኳንስ ባንድ ሰው በተራው አይሞላም
‘የሞላ የሞላ’
ያልሞላለት ወያላ
ሰው በራሱ ካልተሟላ
እንደምን በሌላ
በጎዶሎ ዘመን
‘የሞላ የሞላ’
ከሞላ አይሄድም
የደከመ ልቤን ይባስ ከሚያደክም
አንድ እማይሞላ ሰው ከታክሲው አጭቆ
አንድ ሰው ይጣራል አንቺ እንዳልሆንሽ አውቆ
‘ኧረ እንሂድ ሹፌር’ ይላል ተሳፋሪ
አንቺን ቀጥሯል እንዴ
መድረሻ ቢስ ሁላ ይህ ሂያጅ እና ቀሪ
ይበሰጫጭ ይዟል በወያላው ጥሪ
‘ሜክሲኮ ሳርቤት ሜክሲኮ ሳርቤት’
ያጎደልሽው ልቤ ከጫናት ምናልባት
ቆንጆ ቀጥርያለሁ አንቺን ልረሳባት
የት? ሳርቤት
የምታነድ ፀሃይ የሚገማ ጫማ
የምታሽካካ ሴት ስልክ ተሸክማ
ምት አልባ ሙዚቃ ጮሆ ‘ማይሰማ
የሚዋጋ ወንበር የአርሴናል አርማ
‘በጣድቋ በቅድስት አርሴማ’
የተዘረጋ እጅ ሲቀበል ሊቀማ
ተላካፊ ጥቅሶች
ቁጥር ወሳጅ ወንዶች
እድል ያዞራቸው እድል አዟሪዎች
በከበቡት ታክሲ እኚህ እና ሌላ
ሞልቶ በማይሞላ በሚያፈስ መኪና
ተጭኜ ከኋላ
‘አንድ ሰው የሞላ’
‘አንድ ሰው የሞላ’
ቀጥሏል ወያላ
ይህ ታክሲ ሊሞላ ስንት ቀረው ብሎ
ተሳፋሪው አይኔ ይቆጥራል ቀላቅሎ
ወጪውን ከወራጅ ትርፉን አመሳቅሎ
ይሄ ልጅ ምን ነካው
ትመጪ ይመስል ትገቢ ከታክሲው
አንድ ሰው እያለ ስንትነው ‘ሚጣራው
ወራጅ ብለሽ ሄደሽ ባዶ ያረግሽው ልቤ
ቆንጆ በተርፍ ይዞ
ሊረሳሽ ተክዞ
ተጠጋጉ ሲባል ስጠጋ ላስጠጋ ብነቃ ከሃሳቤ
በትርፍ የገባሽው ለካ አንቺው ሆነሻል ይኧው ካጠገቤ
በል ወያላ ዝጋው - በልሹፌሩ ንዳው
ገብታለች አንድ ሰው
አታዩአቱም እንዴ ብቻዋን ስትሞላው

ሰይፈ ተማም
ጥር 2009 (poetic saturdays)
1
መስመር ቢጤ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መጻፊያ ለጎመ ወረቀት ቀደደ
ስራ ገቡ መሰል መብራት አሁን ሄደ
ሻማም እንዳልገዛ ዋጋው ተንጋደደ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ወር አጭር ርቀት ተቀይሯል ለካ
የምገባበት በር በአከራይ ተንኳኳ
ጋሽ አያሌው ናቸው
ከደጄ ቆመዋል እንደደብር ዋርካ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መዝሙር ግዙኝ የሚል ዘፈን አቋረጠኝ
ስብከትም መሰለኝ ንቀትም መሰለኝ
ውስጤን እንዴት ልስማ ውጭው እያመመኝ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ከጎረቤታችን ይሰማል ኡኡታ
በመኪና አደጋ አንዲት ወጣት ሙታ
አወይ አንቺ ኑሮ አወይ አንቺ ሕይወት
ማሽከርከር መሽከርከር እንዲሁ እንደዘበት

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
እናቴን መሳይ ሴት ምስል እያሳዩ
እነ ዜና አንባቢ እነ አስመሳዩ
ያን ባዶ ማጀቷን ውሸት ይሞላሉ
ጠገበች፣ አገሳች ምናምን እያሉ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ይረብሻል ከጎን የሚሰማው ስድብ
የሚሰማው ሁከት
አንደኛው አግብቶ አንደኛው ገብቶበት
ሁለቱም ይጮሃል ደጋግሞ ለመርሳት
የኳስን፣ የኑሮን፣ የፍቅርን ክብነት

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መከረኛ ስልኬ ይጮሃል ደጋግሞ
‘ውጣ እንውጣ’‘ሚል ሰው ውስጡ ተሸክሞ
ጀመረው እንግዲህ ሊያስነካካኝ ምስሉን
ቧልትና ለገጣ ያደባባይ ስጡን
ቲርኪሚርኪ፣ እንቶ ፈንቶ፣ አተካራ
መፈስበኪያው፣ ማሞጥሞጫና በግተራ

መስመር ቢጤ ነገር ብዬ ልጽፍልሽ …
ብዕሬን ተቀማሁ በዥጉርጉር ለባሽ
አንቺም እንዳ’ገሬ ቦለቲካ ሁነሽ

ሰይፈ ተማም ፪፼፰6
የጎጇችን ተስፋ

ውዴ ይቺ ጎጆ ምንነክቷታል እሳ
አንዱን አንጠራርታ አንዱን አስጎንብሳ
ባንድ ወገን ደራርቃ ባንዱ ጋር በስብሳ
አንድ አይኗን ጎልጉላ አንዱን አጨናብሳ
ባልሞቀ ገል ጠብሳ
በባዶ አንጀት ምሳ
ምነው ይች ጎጆ ምንነክቷታል እሳ
ውዴ እኛ ነን ወይ
ሳርክዳኑን ስናይ
እንደከሳ በሬ የቁም ጎድን ጥብሱ
የግድግዳው ምርግ ወጨፎ አለቅልቆት
ጨፈቃና አግዳሚ ፈጠው ሲታዩበት
እኛ ነን ወይ ውዴ የኛ ነወይ ጥፋት
ማገሩን ስንደግፍ የአግዳሚው መግፋት
ጣራውን ስንደፍን ወለሉ መጨቅየት
መቀመጫ ጥግም አጣን
ማረፊያ መደብም ነሳን
መቆምም አልሆን አለን
ውዴ ይሁን ግዴለም የደረሰብንን
እንደመቻል ካልን
ግና ካንቺ ጉያ ያለች የኛ ተስፋ
እንደምንድን ይሆን ደርሳ ምትፋፋ
ነዳ የማትጠፋ
ጠፍታ የማትከፋ
ከፍታ የማትሰፋ
ሰፍታ የማትገፋ
እንደምንድን እንደምን ተጽፋ
የተስፋችን ቁልል እኛው ላይ ተንዶ
የረፈደው ንጋት ጽልመት እጁን ሰድዶ
ይቺን ጎጆ ሲንጥ ማገሩን አንጋድዶ
ደምሽና ደሜ የቋጠሯት ስንኝ
ማንይሆን አጣርቶ አንብቧት ሚገኝ

ሰይፈ ተማም 2007
...እንዲቀለኝ

ከታደልሽው ጎልቶ
የሚጎልሽ ሁሉ በታየኝ በርክቶ
አንቺ መንግስት ሁነሽ እኔ ተቃዋሚ
ስተትሽን ጥፋትሽን ጉዳትሽን ለቃሚ
ምናለ ባረገኝ
የሰማዩ ሰሚ
እንደዚህ ከምገኝ
ቴሌቭዥን መስዬ
ጥጋብ ‘ሚያወራ ርሃብ እየታዬ
እንደዚህ ከምገኝ
መስዬ አቃጣሪ
ደንድነሻል የሚል ሳለሽ ስንጣሪ
ሆኜ ቀባጣሪ
ጠፍቶ ፍርፋሪ
‘ምንገድ ነው ያማራት’
መንገድ መንገድ አላት
ወዘተ … ወዘታት..

ልማታዊ አፍቃሪ ብለሽ ላትሸልሚኝ
ዘወትር ሳሞግስሽ ስክብሽ ከሚያመኝ
በላዬ ደርጅተሽ አባል ከሚያረገኝ
ከታደልሽው ጎልቶ
የሚጎልሽ ሁሉ በርክቶ በታየኝ

ሰይፈ ተማም
መብላት እና መሽናት
መንገድ ላይ ሲሸና ምንም ያልመሰለው
መንገድ ላይ አይበላም እያለ ‘ነውር ነው’
ብላችሁ በዚህ ሰው አትዘባበቱ
ይኑር እንደራሱ ወይም እንደ አያቱ
የሚያባላ ሞልቶ የሚበላው ግን ብርቅ በሆነበት ሃገር
የዳቦ ባይ ልጆች እሞሉበት መንገድ
እጅ የሚዘረጋው ለመቀበል ብቻ እየሆነ እያደር
እየበሉ መሄድ እንዴት አይነወር?
አይገባውም ለሱ የተራበ ነዳይ በሞላው ጎዳና
ዳቦ እየገመጡ መጓዝ ይሉት ዝና
የህጻን ጨዋታ እንቁልልጭ አይነት አሮጌ ዝመና
መንገድ ላይ ሲሸናም ምንም ያልመሰለው
እሱና መንግ ስቱ በመራራቃቸው
የሚሰሩት መንገድ መስሎት ለራሳቸው
መንገድ ላይ ሲሸና ምንም ያልመሰለው
መንገድ ላይ አይበላም እያለ ‘ነውር ነው’
ብላችሁ በዚህ ሰው አትዘባበቱ
ለብቻ አይበላም ደንቡ ነው ከጥንቱ
ሰው ሞልቶ በሚያፈስ በዚህ አውራ ጎዳና
ጉርሻ ለመቋደስ ኪሱ አይችልምና
እያየም ለማለፍ ሆዱ አይችልምና
ርሃቡን ውጦ ምናል ቢያቀና
ሲያሻው እየተፋ ሲያሻው እየሸና
መቼም እዚህ ሰፈር ማሕበር ቢበዛም
እንብላ ነው እንጂ እንሽና አይባልም
መንገድ ላይ ሲሸና ምንም ያልመሰለው
መንገድ ላይ አይበላም እያለ ‘ነውር ነው’
ብላችሁ በዚህ ሰው አትዘኑ ከቶ
እንጀራ ነው ስራው የሚያበላው በልቶ
ቆሞ እንኳን አይበላም እንኳን መንገድ ወቶ
ሃሳቡን በልሣን በፅሁፍ መፈክር
ባ’ንደበት ነፃነት መንገድ ላይ ከማስፈር
በሽንት መፃፍ ነው እያራሱ አፈር
ከሁሉም ከሁሉ
ከመሰሎቹ ጋር ተባብረው ሲሸኑ
ቆርቆሮዎች ዝገው መንገዶች ቢገሙ
የበላትን ነጥቆ ሳይወረውር ሽታው
የኑሮ ብሶቱን በመሽኛው አነባው
ብለን እንለፈው?
አ - ስ - ለ - ቀ - ሰ - ው
ሰይፈ ተማም 2008
👍1
የተዉሶ ኑሮ
ይቺን አካል እና አንዲቷን 'ራሴ
አሰባጥራ ይዛ በተሰጣት ሃገር በተሰጣት ግዜ
መልሽ እስክትባል ትኖራለች ነፍሴ
እኔ...
ይችን አካል ይዤ ከዝች 'ራሴ ጋር
ከኋላ እየመራሁ ከከብቶቼ 'ምማር
ከሜዳ የወረድኩ ግጦሽ ይሉት ሃገር
የፈጣሪው ምሱል ያው እረኛ ነገር
ሜዳው...
የግጦሹም ሜዳ ሳር አልባ መላጣ
'ሚያጎርሰው የለው 'ሚያለብሰው ያጣ
የሚያደነቃቅፍ አባጣ ጎርባጣ
በተውሶ ክምር እራሱን ያሳጣ
ክምሩ...
ቢመዙት ሜዳው ላይ አይገኝም ስሩ
ፕላስቲክ ነው ውስጡ አይሆንም ለአየሩ
አይሆንም ለአፈሩ
ከብቶች ሆይ ጠርጥሩ
ጠይቁ መርምሩ
የተውሶ ድርቆሽ ከየት ይሆን ዘሩ?
ነፍሴ...
ይቺን አካል እና አንዲቷን 'ራሴ
አሰባጥራ ይዛ በተሰጣት ሃገር በተሰጣት ግዜ
በተውሶ ኑሮ ትጓዛለች ነፍሴ
#seifetemam አሁን
አትምጪልኝ
ስጠራሽ አትምጪ አታግኚኝ ጭራሽ
መንገድም ከጀመርሽ እንደውም ተመለሽ
ስታገኚኝማ
አይንሽን ሳይማ
ያመመኝ ድኖ ነው ህመሜ 'ሚያገረሽ
#seifetemam አሁን
እባክዎ ግጥሞን ያጋሩን @SeifesBot የሚለውን መንገድ በመጠቀም ያድርሱን በጥራት የተቀዱ እንዲሁም በአማርኛ ሆሄያት የተተየቡ ግጥሞችን እንጋራ እናጋራ ።
Forwarded from ቶኔቶር
# ወፍእናማለዳ
እንኳን ችግኙ ÷ሰዎች የተከሉት
ሥር ይዝ ነበረ ÷ አዕዋፋት የዘሩት፣
ዘንድሮ ግን ወፎች ÷ እንኳንስ ሊዘሩ
ናፍቆኛል ማለዳ ÷ መስማት ሲዘምሩ፡፡
ወፎች ከማለዳ በምን ተቃቃሩ?!
ፅልመቱ ሲገፈፍ አንዳላበሰሩ፣
ማዜም ተስኗቸው ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት ወዴትስ በረሩ?!
ምንጭ = ሀ-ሞትየግጥሞች ስብስብ ኄኖክ ስጦታው
:
መጀመሪያ:እንደ:ሁለት:ነጥብ
በየሃሳቤ:መሃል
በየቃሌ:መሃል
ትገኚ:ነበረ
ዛሬ:ጊዜ:ሄዶ ሁሉም ተቀየረ
የኔ ሁለት ነጥብ ክፍተት ሆኖ ቀረ
#seifetemam
የመቆም ዑደት

የቅድም አያቴን አጽም ከአፈር አውጥተው
ቀጥ ብሎ መሄድን በሷ እንደጀመርነው
ይነግሩኛል ደፍረው
...እንደዚህ እያሉ
ከጥንቱ ጥንት ፊት ሰው ዝንጀሮ ሳለ
ዝንጀሮ ሰው ሁኖ መቆም ሰለጠነ
ለሱም ምልክቷ
ሙዝየም አኑረው ይቹትና አጥንቷ
ይህንን አምኜ ለእንግዳ ስናገር
ለመጣ ለሄደው ለኦባማ ሳይቀር
ቀድመን እንደሞቅነው የመቆምን ጀምበር
...ደሞ ከመንገዱ
ወይዘሪት ድንቄ እና እትዬ አረገዱ
ሸክም አጉብጧቸው 'በ' ን ሰርተው ሲሄዱ
እኔ ደሞ እላለሁ
ቀድመን እንደቆምን ቀድመን የወደቅነው
እኛው እንደጀመርን እኛው ልንጨርሰው
#seifetemam #አሁን
ወዳጄን ምን ነካው
ከመንጋው መንጋጋ ፈልቅቆ እየወጣ
ተነጥሎም ሲቆም አጀቡን እያጣ
ለሞቀው ገበያ ምሽቱ ሲነጋ
እራሱን አሹሎ የሚሆን መንጋጋ
ለሌላኛው መንጋ
መሾሉስ ባልከፋ
መሳሉስ ባልከፋ
ወጀብ የፈጠረው ባጀብ እንዳይጠፋ
ወዳጄን ጥሩልኝ እናውራ በወጉ
ከመንጋው ቢጠፋ አይሸጥም በጉ

ሰይፈ ተማም 2008
ቡሄ በሉ
ከ ሰይፈ ተማም
=======
ቡሄ የልጆች በዓል ነው። ልጅ እያለን ትዝ ይለኛል ከነ ሰይድ ጋራ ሆያሆዬ ስንጨፍር - እነ ጋሽ ጃፈር ቤት ሁሉ ብር ይሰጠናል እንጂ ተባረን አናውቅም።ሃገሪቷ ውስጥ የፈጠራ ችሎታ ማነሱን ከሚያመላክቱ ነገሮች አንዱ (ከዚህ ፅሁፍ ውጪ ማለት ነው)አዲስአባ ውስጥ እንዳሉ ታሪካዊ ህንፃዎች ያልታደሱት የሆያሆዬ ግጥሞች ናቸው።በቀን የሶስት ወይም የአራት ታክሲ ገቢ የሚያስገባ ልማታዊ ልጥጥ ሱቅ በር ላይ" እዛ ማዶ አንድ ካልሲእዚህ ማዶ አንድ ካልሲየዚህ ቤት ጌታ ባለታክሲ"ይህን ሲባል በየቀኑ እየተጋጨ እና በሹፌሩ ሰበብ እየታሰረ አማሮት የሸጠው ታክሲ አይኑ ላይ ድቅን ሲል የሆያሆዬ ባንዱን በንዴት ያፈራርሰዋል ልማታዊ ልጥጡ ይህን ሲያደርግ ያየ ለሃገርናባህል ተቆርቅሪ ነኝ ባይ አልፎ ሂያጅ በእርሱ የልጅነት ዘመን የተገጠሙ ቡሄ በሉ ግጥሞችን በውስጡ 'ሆ' እያለ በመስማት ላይ ሳለ ልማታዊ ልጥጡን ለባህል መጥፋት አንዱ ተጠያቂ አርጎ ኮንኖ ማስቲካውን ይለጥጣል።የግድ በየማዶው አንድ ነገር እንዲያሰፍር የተፈረደበት ቡሄበሉ ግጥም እንደምንም ብሎ ሌላ ማዶ ይቀጥላል...በሬ ላይ የቆሙትን ሶስት ሆያሆዬያን አዲስ ግጥም ያላቸው እንደሆን ጠየኳቸው ደሞዛቸው እንደ ግጥማቸው አሪፍነት እንደሚያድግም ነገርኳቸው"እዛ ማዶ አንድ ኮምፒተር" አሉ በወኔ እኔም ዘመኑን የመሰለ እንደ ቀበሌ ነው ወረዳ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ሊሰሩ ነው ብዬ ስጠብቅ"እዚ ማዶ አንድ ኮምፒተርየዚህ ቤት ጌታ ሊሄድ ነው አሜሪካን" ያቺን የሳንቲም አንድ ብር ከማግኘታቸው በፊት በሆዴ ያልኩትን ፊቴ ላይ ሳያዩ አይቀርም እኔም 'እድሜ ልኬን የሞከርኩት ዲቪ ለማስተዛዘኛ ኤምባሲው ጋር እንኳን አድርሶኝ አያውቅም' ነበር ያልኩት። ልጆቹ ከሄዱ በኋላ ሳስበው ግን በዚች ከልጥጦች ልጥጥነት፣ ከጠባቦች ጠባብነት፣ ከሙሰኞች ሙሰኝነት እና ከመሳሰሉት ውጭ ነገሮች ወይ በበጎ በማይለዋወጡበት ወይ ማንነትን የሚገልፁቱ ከዘመኑ ጋር በማይቀጥሉበት ሃገር እየኖሩ ምን ፍጠሩ ሊባሉ ኖሯል? እስኪ አስቡት ሁለት ወጣት ባልና ሚስት ያዩ ልጆች"እዛ ማዶ አንድ አሞራአዚ ማዶ ሌላ አሞራየኔማ እንትና ዛራና ቻንድራ" ቢሉ... የአገልግሎት ግዜ ያለፈባቸው የቡሄ ግጥሞች ተጠቃሚው ጋር እንዳይደርሱ ተመልክቶ የማያውቀው የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - አንዳንድ የአዱስ አበባ ነዋሪዎች ሳይሆኑ እኔ ነኝ ያልኩት። ለዚህም ጎረቤቴ ብርሃኑ ላይ የተገጠመውን ማየት በቂ ነው።"እዛ ማዶ አንድ ብር እዚ ማዶ አንድ ብርየዚ ቤት ጌታ ባለባቡር"ከውስጥ የነበረው ብሬ ይህ ጊዜው ያለፈበት ግጥም አቅለሽልሾት "የዚህ ቤት ጌታ ኢሃዲግ ነው አሏቹ?" ብሎ ልጆቹ ላይ አስታውኮ ይህንን ሲል የሰማው አዋቂ ያለ እንደሆን ዙሪያውን በፍጥነት ገለማምጦ በሩን ጠርቅሞት ገባ። እኔም አዳዲስ እና ነባር እንዲሁም ሪሚክስ የተደረጉ ስራዎችን የሚያ ቀርቡ አባላት ያሉት የሆያሆዬ ባንድ በምናቤ አቋቋምኩለት...እዛ ማዶ የላም ወተት(እንዴ የወተት ላም ነች የላም ወተት? ወይስ የለም ወተት? ቆይ እስኪ እዚ ማዶ ይድገሙትእዚ ማዶ የላም ወተትየኔማ ብሬ አይዘውም አተትኢሽሽ አሁን ይሄ ሟርት ነው ሙገሳ?... እዛ ማዶ አንድ ዶሮእዚ ማዶ አንድ ዶሮየኔማ ብሬ ቴዲ አፍሮ(ኧረ ሳያፍር ነው አሪፍ...ደሞ ሊያሳስሩን ነው እንዴ..)እዛ ማዶ አንድ ጠመኔ'ዝምበል!' አለ ብሬ በንዴት'ኧረ አሪፍ አዲስ ግጥም ነው' የባንዱ መሪ ነበር።ብሬም እጁን እያወናጨፈ 'በቃ በቃ ኔ በምትባል ፊደል የሚገጥም ምንም ደህና ነገር የለም' አለ። ... ብሬ ደሞ ያበዛዋል ገና ለገና ወ*ኔ ሊሉ ነው ብሎ...


ቡሄ
2008