ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ስቆሽሽ በጊዜ እንቅልፍ የጣላችሁ
ምነው ዛሬ ደርሶ ፊንፊን ያላችሁ
ነገ ዛሬ
ዛሬ ሲቻል ለነገ አልኩ
ነገም ደርሶ ነገን አከልኩ
ከነገወዲያም ደሞ መቶ
ነገ ሊባል ሰበብ ሞልቶ
ነገ ሲባል ተጎትቶ
በነ ነገ ነገር ተወግቶ
ባንዱ ነገ ውስጥ ተካቶ
እቅድ ተገኘ ሞቶ
እምጽ አምጵጽ
#seifetemam
ግጥም ሲጥም:
ቀና ልብ
ያልቀጠረውን ሰው ናፍቆ የሚጠብቅ
በውድቅት ለሊት ጨረቃን የሚሞቅ
ካለም ብርሃናት ላይ ወዳጁን የሚስል
በወደደው መጠን መውደዱን 'ሚያክል
በደም እና በ'ምነት በተስፋ የጸና
ልብስ ይኸውልሽ በፍቅር የቀና
#seifetemam
እውነቱን ልንገርሽ
(በ ሰይፈ ተማም)
እውነቱን ልንገርሽ
ከራሴ አስበልጬ አንቺን የምወደው
እያለሽ ናፋቂ
እየሄድሽ አድናቂ
ተራግመሽ መራቂ
ልቤን ብጠላ ነው
እውነቱን ልንገርሽ
ከራሴ አስበልጬ አንቺን እምወድሽ
ከፋት ብሎ ሚያምጥ
ሳቀች ብሎ ሚያገጥ
ኖረሽ የማይወዛ
ሄደሽ የማይከሳ
ሆኜ ብገኝልሽ
አንቺን የምወደው አብልጬ ከራሴ
አይንሽን ለማየት ጨረር እማይፈራ
አለሽበት ሊደርስ መንገድ ሚሰራ
ጣትሽን ለመንካት ጣቱን ሚሰዋ
ቃልሽን ለመስማት መናኝ እስከ ህዋ
የሆነው አካሌን ብትጠላው ነፍሴ
ከማንም አብልጬ አንቺን የወደድኩኝ
የወደድሽው ሁሉ...
በፍቅር አሳቦ
ቅናትን ሰብስቦ
ቢያስጨንቀኝ ከቦ
(አንቺን ከማስበለጥ) አማራጭ አጣሁኝ
ህዳር ፳፬፣ ፪፼፯ ዓም
#seifetemam
ወዳጄ
ጠጥቶ ጠጥቶ ጠጥቶ
ውሃም ይሁን ጠላ ተግቶ ተግቶ
ግድግዳ ይጠጋል
አጥር ይደገፋል ጀርባ ለሰው ሰጥቶ
አጥር ስር ማስለቀስ ህቅም እንኳን ሳይለው
ሊከልል ይጥራል
የሰውነቱ አካል ሆኖበት ማፈሪያው

(ጋሼ Seife ...አስለቃሽህ ወዳጅህን ጠምጄዋለሁ ዛሬ)
የጌታነህ ልጅ
ሐምሌ 22, 2009
ያልቃሽ አዋጅ

በዚህ ፊት አምላኪ በበዛበት አለም

ፊት እንደመቧጠጥ ታላቅ ግድፈት የለም
#ፍሰሃ
እጅ-አዙር
አዬ አጤው ቴዎድሮስ እጅግ ተታለለ
በነጭ መያዝን ውርደት እንዳላለ
ልቡን አጀገነ ያችን ጥይት ሊውጥ
በማን ተሰራና በ'ጁ ያለው ሽጉጥ
#seifetemam
ግጥምጥም
የሰበራችሁትን እገጥማለሁ ብዬ
ያጣመማችሁትን አቀናለሁ ብዬ
እኔው ተሰብሬ እኔው ተጣምሜ
ማቅናቴም መግጠሜ
በማዝመም ማዝገሜ
አወይ ግጥም ጥሜ
#seifetemam
ዋጋ የለሽም
ምክንያቴን ሁሌም ተረጂው
ቢለይብሽም መንገዴ
ተመን የለኝም ላንቺ
ከቶም አልልሽ ውዴ
በዚች ኮተታም አለም
ኦና ቤቴን ካሻሽም
ውድነት ቢያረክስሽ እንጂ
አንቺስ ዋጋ የለሽም
#seifetemam
መስታወተ ጓደኛ
ጓደኛ ሲሆን መስታወት
'ራስን 'ሚያሳይ ሲያዩት
አንዳ'ንዱ ግን ይለያል
የ'ራሱን ምስል ሲያሳዩት
ጓደኛዬ ይህ ነው ይላል
#seifetemam
ለ አባባ ተስፋዬ 1
'ዛሬ አበባዎች
የነገ ፍሬዎች'
ብለው ከጠሯቸው ስንቶቹ ረገፉ?
ለሳሎን ጌጥነት ስንቶች ተቀጠፉ?
እርሶስ ፍሬ ሆነው ተዘርተው አለፉ::
#seifetemam
ለአባባ ተስፋዬ 2

ያኔ...

የፕላስቲክ ኮዳ የሞባይል ካርዱ
መንገድ ሳይከመር
መስኮትና ጣሪያው በዲሽ ሳይወረር
አንድ ቲቪ ብቻ ላንድ ሙሉ ሰፈር
አንድ ቲቪ ቻናል ላንድ ሙሉ ሃገር
አንድ ሰው ብቻውን ስንቱን ያስቆም ነበር?

ኋላ ላይ...

እንደ'ውቀት ፍሬ ልጅ ሁሉ እድሜ በላ
እንደ አዳም ባነነ ጩጬ ና ፈልፈላ
ገባው እንደሌሉ አባባ ተስፋዬ
ከስክሪኑ ኋላ
ፎገሩኝ እያለ ተካቸው በሌላ

ከዛም...

ቴሌቭዥኑም ከስቶ እንደእንጀራ ሳሳ
ገብስ ወረረው ፈልቶ የአበባውን ማሳ
ልጅ ባገሩ በዝቶም ልጅ ሁላ ተረሳ
(በአካል ተከስቶም) ለአባባ ተስፋዬ ጠፋ የሚነሳ

ከዛም በኋላ...

ለገዢው መደብ ጦር ተሰለፉ ልጆች
ለአባይ ዘመሩ ጮሁ ለታጋዮች
'ብሔር ብሔረሰቦች'

ከ'ዛ በኋላም በኋላ...

እነዛን ተወዝዋዥ እጆች
እስኪዘክራቸው ታሪክ
እስኪገኝ የአባባ ምትክ
አዋቂው እንደ ልጅ ይጃጃል
ልጅም ይቅበጥ በአዋቂ ልክ
ማንም ለማንም አይነሳ
እራሱን ያክብር ዘመኑ
'1' እና '0'ን ቀምሩ
የ'1' እና '0' ነው ቀኑ
በሉ ልጆች ደህና ሁኑ
ደህና ሁኑ ደህና ሁኑ
#seifetemam
ለማፍቀር ቀጠሮ

ሸትታ 'ምትገለማ
መርቅዛ 'ምትገማ
ወፍፋ ያበደች
ጨርቋን ጥላ የሄደች
ማንነቷን ስታ
ከሆነው ተጣልታ
ካልሆነው ተጣብታ
ያልሆነውን ሽታ
ማስመሰል አብዝታ
በመክሰም ለማበብ
በመግደል ለማከም
በምታደክም አለም
ውዴ አንቺን ልወድሽ
'ሚገባ አይደለም
...
... ... ስለዚህ
...
በናርዶስ ምዓዛሽ የዝች ቅርናት አለም ሽታዋ ከጠፋ
ወይ ሰናይ ፀባይሽ አሽሏት እንደሆን እንዳትቀር ወፍፋ
ማስመሰሏን ከሳ
እራሷን ስትሆነው ደግሞ ተመልሳ
ቀጠሮ ስላለኝ ያንግዜ ልወድሽ
አለሜን አክምያት እንዳይረፍድ ባክሽ
#seifetemam
የገጣችን ታዳሚዎች ሆይ
ከስር በተቀመጠው ማግኛ (link) ከ9500 በላይ ወዳጆች ያሉትን የ ፌስቡክ ገጣችንን ትጎበኙት ዘንድ ተጋብዛችኋል https://www.facebook.com/gitemsitem/
የአለም ሰባኪ

እከዘለዓለመ አለም
ስለሚያኖረው አውርቶ
ከሚያስቀድሰው
የሚያስነውረውን አብዝቶ
በደቂቃ ደቀቀ ሳቱ ባላቸው ስቶ
የሳቱትም ፈረዱ መሳት በሳት በርክቶ
#seifetemam 2008
የማለዳ ፀሎቴ

በቀኝህ አውለኝ ብሎ እንዲፀልይ ሰው
… እኔ ግን ብያለሁ
በየ ደረስኩበት እንደው በየቦታው
ወረፋና ሰልፉ እግሬን ስላዛለው
… እኔ ግን ብያለሁ በግራህ አውለኝ
ግድየለም ግዴለም
ግራውም ያንተው ነው
#seifetemam
#gitemsitem #poetic_saturdays #ግጥም_ሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #seifetemam

ህመሜን ላጣጥም
-----------------------
እስቲ ልንቆራጠጥ ተዉኝ ላቃስትበት
ህመሜን ላጣጥም እስክፈወስበት
እንዳትወጉኝ ማደንዘዣ
እንዳትሰጡኝ ማስታገሻ
በሰፊ አውታር መገናኛ
በብልጭልጭ መሸፈኛ
የዘመን ጎርፍ አግበስብሶ
በከሰተው መከወኛ
ከኔ በላይ ላያማችሁ
ከህመሜ ላይ ሰራርቃችሁ
በሽተኛ ስንኩል ሳለሁ
አታፍጥኑት ሞቴን ካለው
እያላችሁ ጤነኛ ሰው
ልዳን እንጂ አታስታግሱኝ
ተዉኝ ተዉኝ ልንቆራጠጥ
ላተኩሰው ሆዴ ይቁረጥ
እራሴ ይምታ አይኔ ይበጥ
ሰው አድርጉኝ የሚሰማው
ከራሱ ጋር የሚታደም
በሽታዬን ካልተቀማሁ
በህመሜ ነው የምታከም

ሰይፈ ተማም 2009
አንድ ሰው

‘ሜክሲኮ ሜክሲኮ’
ይጣራል ወያላ
ሰባት ሰው ይዞ
ባዶ ወንበርም ይዞ
‘አንድ ሰው የሞላ’
ይህ ታክሲ ሊሞላ ስንት ቀረው ብሎ
ተሳፋሪው አይኔ ይቆጥራል ቀላቅሎ
ወጪውን ከወራጅ ትርፉን አመሳቅሎ
‘አንድ ሰው አንድ ሰው’
ድምጹ እየከረረ
እንደኔ ላለ ሰው ቆንጆ ላፈቀረ
ወይም ለቀጠረ
የጊዜን ግፍ አውቆ
በመሙላት ተሳልቆ
‘ አንድ ሰው አንድ ሰው’
ይሄ ልጅ ምን ነካው
ትመጪ ይመስል ትገቢ ከታክሲው
አንድ ሰው የሚለው
እኔ በበኩሌ
በአንድ ሰው ብቻ የሞላሽ እማቀው
አንድ አንቺን ብቻ ነው
እንጂማ
እንዳንቺ አቀራረት በዚህ ልጅ አጠራር
ይህ ታክሲና ልቤ ባንድ ቢነጻጸር
‘ አንድ ሰው’ ማለቱን ወያላው አይጠላም
ቢገባም ባይገባም
ታክሲውና ልቤ
እንኳንስ ባንድ ሰው በተራው አይሞላም
‘የሞላ የሞላ’
ያልሞላለት ወያላ
ሰው በራሱ ካልተሟላ
እንደምን በሌላ
በጎዶሎ ዘመን
‘የሞላ የሞላ’
ከሞላ አይሄድም
የደከመ ልቤን ይባስ ከሚያደክም
አንድ እማይሞላ ሰው ከታክሲው አጭቆ
አንድ ሰው ይጣራል አንቺ እንዳልሆንሽ አውቆ
‘ኧረ እንሂድ ሹፌር’ ይላል ተሳፋሪ
አንቺን ቀጥሯል እንዴ
መድረሻ ቢስ ሁላ ይህ ሂያጅ እና ቀሪ
ይበሰጫጭ ይዟል በወያላው ጥሪ
‘ሜክሲኮ ሳርቤት ሜክሲኮ ሳርቤት’
ያጎደልሽው ልቤ ከጫናት ምናልባት
ቆንጆ ቀጥርያለሁ አንቺን ልረሳባት
የት? ሳርቤት
የምታነድ ፀሃይ የሚገማ ጫማ
የምታሽካካ ሴት ስልክ ተሸክማ
ምት አልባ ሙዚቃ ጮሆ ‘ማይሰማ
የሚዋጋ ወንበር የአርሴናል አርማ
‘በጣድቋ በቅድስት አርሴማ’
የተዘረጋ እጅ ሲቀበል ሊቀማ
ተላካፊ ጥቅሶች
ቁጥር ወሳጅ ወንዶች
እድል ያዞራቸው እድል አዟሪዎች
በከበቡት ታክሲ እኚህ እና ሌላ
ሞልቶ በማይሞላ በሚያፈስ መኪና
ተጭኜ ከኋላ
‘አንድ ሰው የሞላ’
‘አንድ ሰው የሞላ’
ቀጥሏል ወያላ
ይህ ታክሲ ሊሞላ ስንት ቀረው ብሎ
ተሳፋሪው አይኔ ይቆጥራል ቀላቅሎ
ወጪውን ከወራጅ ትርፉን አመሳቅሎ
ይሄ ልጅ ምን ነካው
ትመጪ ይመስል ትገቢ ከታክሲው
አንድ ሰው እያለ ስንትነው ‘ሚጣራው
ወራጅ ብለሽ ሄደሽ ባዶ ያረግሽው ልቤ
ቆንጆ በተርፍ ይዞ
ሊረሳሽ ተክዞ
ተጠጋጉ ሲባል ስጠጋ ላስጠጋ ብነቃ ከሃሳቤ
በትርፍ የገባሽው ለካ አንቺው ሆነሻል ይኧው ካጠገቤ
በል ወያላ ዝጋው - በልሹፌሩ ንዳው
ገብታለች አንድ ሰው
አታዩአቱም እንዴ ብቻዋን ስትሞላው

ሰይፈ ተማም
ጥር 2009 (poetic saturdays)
1
መስመር ቢጤ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መጻፊያ ለጎመ ወረቀት ቀደደ
ስራ ገቡ መሰል መብራት አሁን ሄደ
ሻማም እንዳልገዛ ዋጋው ተንጋደደ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ወር አጭር ርቀት ተቀይሯል ለካ
የምገባበት በር በአከራይ ተንኳኳ
ጋሽ አያሌው ናቸው
ከደጄ ቆመዋል እንደደብር ዋርካ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መዝሙር ግዙኝ የሚል ዘፈን አቋረጠኝ
ስብከትም መሰለኝ ንቀትም መሰለኝ
ውስጤን እንዴት ልስማ ውጭው እያመመኝ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ከጎረቤታችን ይሰማል ኡኡታ
በመኪና አደጋ አንዲት ወጣት ሙታ
አወይ አንቺ ኑሮ አወይ አንቺ ሕይወት
ማሽከርከር መሽከርከር እንዲሁ እንደዘበት

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
እናቴን መሳይ ሴት ምስል እያሳዩ
እነ ዜና አንባቢ እነ አስመሳዩ
ያን ባዶ ማጀቷን ውሸት ይሞላሉ
ጠገበች፣ አገሳች ምናምን እያሉ

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
ይረብሻል ከጎን የሚሰማው ስድብ
የሚሰማው ሁከት
አንደኛው አግብቶ አንደኛው ገብቶበት
ሁለቱም ይጮሃል ደጋግሞ ለመርሳት
የኳስን፣ የኑሮን፣ የፍቅርን ክብነት

መስመር ቢጤ ነገር ልጽፍልሽ ብዬ …
መከረኛ ስልኬ ይጮሃል ደጋግሞ
‘ውጣ እንውጣ’‘ሚል ሰው ውስጡ ተሸክሞ
ጀመረው እንግዲህ ሊያስነካካኝ ምስሉን
ቧልትና ለገጣ ያደባባይ ስጡን
ቲርኪሚርኪ፣ እንቶ ፈንቶ፣ አተካራ
መፈስበኪያው፣ ማሞጥሞጫና በግተራ

መስመር ቢጤ ነገር ብዬ ልጽፍልሽ …
ብዕሬን ተቀማሁ በዥጉርጉር ለባሽ
አንቺም እንዳ’ገሬ ቦለቲካ ሁነሽ

ሰይፈ ተማም ፪፼፰6
የጎጇችን ተስፋ

ውዴ ይቺ ጎጆ ምንነክቷታል እሳ
አንዱን አንጠራርታ አንዱን አስጎንብሳ
ባንድ ወገን ደራርቃ ባንዱ ጋር በስብሳ
አንድ አይኗን ጎልጉላ አንዱን አጨናብሳ
ባልሞቀ ገል ጠብሳ
በባዶ አንጀት ምሳ
ምነው ይች ጎጆ ምንነክቷታል እሳ
ውዴ እኛ ነን ወይ
ሳርክዳኑን ስናይ
እንደከሳ በሬ የቁም ጎድን ጥብሱ
የግድግዳው ምርግ ወጨፎ አለቅልቆት
ጨፈቃና አግዳሚ ፈጠው ሲታዩበት
እኛ ነን ወይ ውዴ የኛ ነወይ ጥፋት
ማገሩን ስንደግፍ የአግዳሚው መግፋት
ጣራውን ስንደፍን ወለሉ መጨቅየት
መቀመጫ ጥግም አጣን
ማረፊያ መደብም ነሳን
መቆምም አልሆን አለን
ውዴ ይሁን ግዴለም የደረሰብንን
እንደመቻል ካልን
ግና ካንቺ ጉያ ያለች የኛ ተስፋ
እንደምንድን ይሆን ደርሳ ምትፋፋ
ነዳ የማትጠፋ
ጠፍታ የማትከፋ
ከፍታ የማትሰፋ
ሰፍታ የማትገፋ
እንደምንድን እንደምን ተጽፋ
የተስፋችን ቁልል እኛው ላይ ተንዶ
የረፈደው ንጋት ጽልመት እጁን ሰድዶ
ይቺን ጎጆ ሲንጥ ማገሩን አንጋድዶ
ደምሽና ደሜ የቋጠሯት ስንኝ
ማንይሆን አጣርቶ አንብቧት ሚገኝ

ሰይፈ ተማም 2007