ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ስፈራ ስፈራ
የሃሳቤን አጥር
ያጠረኝን ቅጥር
የቅጥሩን ጌታ
ስፈራ ቆይቼ አፌ እንደተፈታ
የምለው ሳላጣ
የፈራሁት 'ሰሚ' ሆኖት ሰላረፈው
አሁን አይሰሜውን ህዝብ ፈርቻለሁ


ሰይፈ ተማም 2011
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter - 11th March 2019 is out now,
featuring @Royalphotography22, Fekat Circus, @behagerlij, Habesha Animation, Fano Creatives, Association of Ethiopian Architects, Designlab ETH, Everted, Artistic Ethiopia, Art in Addis, Zoma Museum - https://bit.ly/2Ho5ZvO We hope you enjoy!!
የኋላ የኋላ

የታሰረን መምታት
የወደቀን መግፋት
ጀግንነት ነው ወይ
ከሌለው መቀማት
ጦስ ይሆን የለም ወይ
የመቱት ሲፈታ ሲበቅል የገፉት
ሰብል እኮ ይሆናል ዘርን ሲበትኑት

ሰይፈ ተማም 2010
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5.pdf
3.2 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል with over 20 opportunities for you to explore!!! https://bit.ly/2Ve5RHs
This week featuring @michaelfelleke, Beza Hailu Lemma, Ethiopian Records. የኢትዮጵያ ልጅ, Yefikir Design, @kunjina_ltd, Gobeze, Seife Temam, Ayni's, @melkam74, @LinkUpAddis, Contemporary Nights
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን፣
የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2
Featuring @Mykeyliyew, @BigDreamEt, @melkam74, @habeshawian, @Sabegnn and so much more
Forwarded from SABEGN
Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before
Forwarded from Bruh Club
The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.ly/2Mji35E
This week we feature Awell Kedir Afro Fair Fest, Gebeya Talent, @BigDreamET, Addis Foto Fest (AFF), Addis Insight, BAM Ethiopia, Awtar Multimedia, LinkUp Addis, Betty G., Startup Ethiopia, @talktolife and so much more
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6.pdf
4.3 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6

💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!!
https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls, competitions, residencies etc for the Ethiopian creative practitioner. So do apply!!!!!!

This week featuring visual artist @Mesfinarts

Book-worm, @Freelance_ethio, @LinkUpAddis, @BiGDreamET and so much more
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7.pdf
3.5 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰
ጽደቅ እንደ ችግኝ አፍላ እንደ ሾላ
ከአለም ደጉን ወስደህ መልካም ፍሬ ዝራ
ዘለአለም ለመኖር አሁንን አትፍራ
ሰይፈ ተማም 2011
እግዜሩ ፈርሟል!

©በታመነ መንግስቴ

እሱ ጥበበኛው፡
አንችን ለማሳመር
እንዳይሆኑ ሆኖ፡
የማይደክመው ደክሟል!

እና ከዚያ ወዲህ፡
ከአንች የበለጠች
የውበት ማሳያ
ላይፈጥር ፈርሟል፡፡
ታመነ መንግስቴ ውቤ, [03.09.19 11:36]
[Forwarded from አዲስ ጉራማይሌ (ታመነ መንግስቴ ውቤ)]
አብዮት

©በታመነ መንግስቴ

ቅጠል እያኘከ
ኒያላ አቦነነ!
በወሲብ ነደደ
በኳስ ሱስ አበደ ፣
እያልኩኝ አልፅፍም
ትውልዴ ተነነ፡፡

ሌላ ሌላ አሠኘኝ
በአብዮት ዋዜማ፡
ልብ አረስርስ ግጥም
ተስፋ ያለው ዜማ፡፡

ዘንድሮ
የጫት ማሳው ደርቆ
ሲተከል በርበሬ
አድዋ ሲያዘምር
የባሌ ገበሬ፡
ዋሽንግተን ሲናኝ
የኢትዮጵያ ዝና
ዕንደ ህልም ዕነደ ህልም
ይታየኛልና!!!

መልካም የጳጉሜን መሻገሪያ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት፡፡

ነሃሴ 28/ 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ
ተጀነት አለት ስር የፈለቀች ግጥም
•••፨••• ........ሰ.ወ.አ....
•፨•••፨•••፨•••፨•••••፨•••፨•••፨•••፨•
ተጀነት አለት ስር - የፈለቁ ግጥሞች
ጥም እየፈወሱ -የሚያስጠሙ ጥሞች
...
ተጀነት አለት ስር - የፈለቀች ግጥም
ጥም እየፈወሰች - የምታስጠማ ጥም
..
ታንቺ ወዲያ ዜማ - ታንቺ ወዲያ ቅኔ
ስትስሚኝ ለፈለፍኩ - ቃላት ሆንኩኝ እኔ
...
ማሪቱ ለገሠ በቁም ቀረች ቀልጣ
አስቴር 'እግዞ!' አለች
ድምጥሽን አድምጣ
ውብ ቅኔሽ ቀንቅኖት
የአያ ሙሌ ቅኔ - በፀፀት ተቀጣ
እንኳንም ሼክስፒር አማርኛ አልቻለ
ቀሽም ግጥሞቹን ይረግም ነበረ!
...
ታድያ እኔ መናኛሽ - በከንፈርሽ ጉልበት
ወዝ ወንዝ አፈለቅሁኝ - ተገረጣሁበት
...
ስታዜሚ አዚም - ክንፉ ተሰበረ
በቅኔሽ ተመቶ - ጁሃን ደነበረ
ድምጥሽ ነው ያነሳኝ፤
ሰባራ አጥንቴ ውስጥ፣መቅኒ እየፈጠረ
...
እናንት ጅል ገጣሞች፣
አታስቆንጁ ሥንኝ - ግጥም አትኳሉ
ተሷ ቃል አያምርም - የተጣፈው ሁሉ
...
አንቺ የልቤ ወይን - የመንፈሴ ስካር
ካልተደበቅሽለት፣
ይኮስሳል ውበት፤
መልኩን ያጣል ማማር!
....
ይቅር አትድገሚኝ - የከንፈርሽን ጠበል
አፌን እየከለስኩ - እሰይ እሰይ ልበል!

እንኳን ተደግሜ - የእንጆሪሽን ጉርሻ
አንዱንም ጠንቶብኛል - እየሆነ ግርሻ
መኖርም አልሻ
መሞትም አልሻ
አፍሽ ዳር ያድርገው - የአፌን መጨረሻ!
...
ተጀነት አለት ስር - የፈለቅሽው ግጥም
ጥሜን እየቆረጥሽ - አነደድሺኝ በጥም
..........
•••]ሰይፉ ወርቁ.አ[•••
እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቻችን!
በአሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሽልማት አለን:- አሁን የያዝነው ዓመት ዘመነ ምን ይባላል?
በ 12ሰዓታት ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ለሰጡን የመጀመሪያ 3 ሰዎች የዐየር ሰዓት ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።