ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እምወድሽ

ለምን ሳልል በፊት አንቺን ማለት ቀድሞ
ያርበተብተኛል ልብሽ ልቤን ስሞ
የፊቴ ላይ ከንፈር ጉንጭሽ ላይ ይገኛል
ገጽሽን ተሳልሞ ካልተሳልኩ ይለኛል

የተንጠፈጠፈች ጭላጭ ቀናነቴ
የፍቅር ርጋፊ ይዛ በአከላቴ
ታላውሰኛለች አንቺን አንቺን ብላ
ቃል ቸግሯት ደሞ ከወደድኩሽ ሌላ

ለምን እንዳትይኝ እኔስ መች አውቄ
እንዲሁ ልውደድሽ ወይ ምክኒያት አርቅቄ

እምወድሽ
ተፈርዶ ነው ከላይ እንደ ትእዛዛቱ
እንደሰለጠኑ እንደብርሃናቱ
እንደጨረቃዋ እንደ ፀሃይቱ
'ይውደድሽ' ብሎ ነው የቃልም ቃላቱ

ቀን ዳምኖ ባይፈካ ቢያጥረው ወገግታ
አይኔን ቢጋርደው የልቤ ወለምታ
ከሰፌዶች መሃል የሰበዝ እይታ
የገጽሽ ብርሃን ነው አቅሜን ያበረታ

እምወድሽ
አንድ ሰበዝ ቀልማ ተሰፍታ በጥበብ
ነጠላነት ትታ ልታስውብ ስትከብ
እንዴት ዝም ልላት አስችሎኝ ልሸበብ
ለስንደዶነቴ ሰበዜን እማልክብ

ለምን ሳልል በፊት እንዴት ሳልል በፊት
እንደቤቴ እያለሁ አንቺም እንዳንቺ ቤት
ከሚያመሳስለን የሚለየን በዝቶም
የልብሽን መግቢያ አላጣውም ከቶ

እምወድሽ
እንደ እናቴ ጉርሻ ባልውጥሽ ደስታዬ
እንደ ጥሜ መቁረጥ ቅጽበተ ትንሳኤ
ድንገት እንዳገኙት እንደረሱት ገንዘብ
በአሳ እንደተሞላ የነ ጴጥሮስ መረብ
እንደ ልጅነት ሳቅ እንደ አባሮሽ እስር
እንደ እፉዬ ገላ የአሮጊት ፈስ ጭምር

ለምን እንዳትይኝ እኔስ መች አውቄ
እንዲሁ ልውደድሽ ወይ ምክኒያት አርቅቄ

እንዲያ እነደተሰማኝ በ'እንደ' አስቤ
እንዲሁስ አልወድሽ እግዜር አይደል ልቤ

ሰይፈ ተማም 2010
...እስካሁን...
ሀሳቤን ስሆነው ሀሳቤ ሲሆነኝ
እንደ ሀሳቤ ልሆን ማሰብ ሲያሳስበኝ
ሀሳብ ኖረኝ እንጂ መች ሀሳቤን ኖርኩኝ

ሰይፈ ተማም 2010
ጸልያለሁ
========
እጸልያለሁ ለሰው ልጅ
በሰንሰለት ላለው እጅ
እጸልያለሁ ታትሬ
ህላዌን ያላወቀ አለም
ፍፃሜን እንዳያይ ዛሬ

እጸልያለሁ ጸሎቴን

ኩታዬን በኮት ስቀይር
ስለፈረሰው ቤቴ
ራቤን በም'ራብ ስሰፍር
ስለተራበው ጉልበቴ
ስሜን በሰም ሳሰፍር
ስለነደደው ውበቴ

ከራሴ ወጥቼ
ፀርሃ አርያም
ቅጥሩን ተጠግቼ
የዓይኖቼን ውሃ
በፍቅር አተንናለሁ
እ-ጸ-ል-ያ-ለ-ሁ
እጸልያለሁ ጸሎቴን
ዕለትን በአለት ሲያቆም ሲመትር
ስለደከመው አያቴ
ግንጥልጣይ ገጥሞ ሲቀምር
ስለተሰዋው አባቴ
ነፍስ ላይ ነፍጥ ሲከምር
ስለጠበበው አጎቴ
ከራሴ ወጥቼ
መንበረ ፀባዖት
ቅጥሩን ተጠግቼ
የወዜን ብልጭልጭ
በእምነት እጠርጋለሁ
እ-ጸ-ል-ያ-ለ-ሁ
እጸልያለሁ ለሰው ልጅ
በሰንሰለት ላለው እጅ
እጁ ለሰንሰለቱ ሳይጠብ
ሰንሰለት እጁላይ ሳይቀልጥ
ህላዌን እንዲያየው አለም
ፍፃሜን ተግቶ ከማለም

ሰይፈ ተማም 2008
የንብ ሰነፍ

ጥዝዝዝዝ...ጥዝጥዝ
አርጋኝ ስትከንፍ
ንጹህ ስትጠየፍ
ዝንብ ናት እያልኩኝ ንብ አካሏን ስገድፍ
ለካስ አላት ማሩ ለካስ አላት ሰፈፍ
ደም ቀስማ የሰራችው አበባ ስትነድፍ

ሰይፈ ተማም
ባነደድሽው ክሰል እያረግሽ እፍ እርግብ
እፍ እርግብ እርግብግብ
... ... አነስተኛ ነፋስ
ገጽ አየዳሰሰ እሳት የሚለውሰ
ከካርቶኑ ቅዳጅ ከእጅሽ ውዝዋዜ
የሚወጣ ዜማ የምቱ አባዜ
እኔን አደንዝዞ እንዳፈዛዘዘኝ
እሳትሽ ነደደ በቆሎሽ ፈነዳ
ልቤ ግን ከሰለ እሳት ሆኖት ዕዳ
ስበት

ልብሽ ቢጠራኝ ነው ልቤን አሳከከኝ
መንገድ ብትጀምሪ ስትመጪ ታወቀኝ
እንደበጋ መሬት ውስጤ መሰንጠቁ
የስክነትን ለዛ ድንገት መነጠቁ
ተነሳሽ ማለትነው ልትመጪ እየወጣሽ
ወደኔ ነው ታክሲ አዋክቦ 'ሚያመጣሽ
መግነጢሳም ልብሽ ሲቀርበኝ አውቃለሁ
ሳቢውን ይስባል እኔም ስመጣ'ለሁ

ሰይፈ ተማም 2011
ናፍቆትሽ

የቀዘቀዘ ልብ የተደፋ ወተት
የጨበረ ጸጉር ያዘነበለ አንገት
የተሰበረ ገል ያልተቆላ ቡና
የታረደ ዶሮ የሸተተ ቡላ
ሞልቶ ያልሞላ ታክሲ የሌለው ወያላ

ጨረቃ ስትስቅ ጥርሰሽ ይታየኛል ግልጥልጥ እያለ
ትናፍቂኛለሽ ደግሜ ስስምሽ ለአይኔ እየተሳለ
በቀዘቀዘ ልብ ግድም እማይለው ሰው ለመውደድ ሲሻ
ሁሉን አስበርዶ እያንቀጠቀጠ 'ሚፈልግ መሸሻ
ጉራንጉር አይምሮ ከመጪ ሂያጂዋ አንቺን የሚፈልግ
'ለምን' ሲል ጠያቂ ከመልሱ መልሶ ጥያቄ 'ሚመርግ
ከደረቴ መሃል ፀሀይሽ ሲጠፋ ክረምት ሆኖ 'ሚያዘንብ
እንደተራራ ጫፍ እንዳላበው ቢራ የቀዘቀዘ ልብ

በጠራ ሰማይ ላይ ጥጥ መሳይ ደመና ሳቋ ነው እያለ
ትናፍቂኛለሽ ደግሜ ስስምሽ ለአይኔ እየተሳለ
የተደፋ ወተት ከታቹ ከንፈርሽ ስትስቂ የወጣ
ትዝታውን መዝዞ ቀልቤን የሚቀጣ
ጣቴ እየለኮሰ የጥርሴ ላይ ብልዝ እንደ እከክ ሰፋ
የጣድኩት ገንፍሎ በአሳር ያነደድኩት እሳቴን አጠፋ
ከከንፈሬ ቀርቶ የመሳቂያሽ ቅርጹ በነከስሽኝ ድንገት
የማይሳም ከንፈር 'ማይታፈስ ሃሳብ የተደፋ ወተት

የቀዘቀዘ ልብ የተደፋ ወተት
የጨበረ ጸጉር ያዘነበለ አንገት
የተሰበረ ገል ያልተቆላ ቡና
የታረደ ዶሮ የሸተተ ቡላ
ሞልቶ ያልሞላ ታክሲ የሌለው ወያላ

የሚሸረብ ዞማ መዳፍሽ ያወዛው እያቀማጠለ
ትናፍቂኛለሽ
ጣቴ ሲንቀዠቀዥ
አናቴ መሃል ላይ አንቺን እየሳለ
የጨበረ ጸጉር የተንጨፋረረ የሚነካው ያጣ
ይኸው ካንቺ ወዲህ ባለው አስተዳደር ሰንደቅ ሆኖ ወጣ
ጫፍ ጫፉ ይቋጫል ይኸው እለት እለት
የመቆረጫው ልክ የጣትሽ መለኪያው ጣቴ ቢጠፋበት
ጉራንጉር አይምሮን በሸፈነው አናት የተከመረ ዱር
ናፍቆት የሚያቃጥር የጨበረ ጸጉር

ወዳጁን በስስት የሚያይ ታማኝ ውሻ ከፊቴ እየታየኝ
ያለቃል ሳወጋሽ ላ'ይኔ እየተሳለ ትናፍቂኛለሽ
ያዘነበለ አንገት እንደመሬት ዛቢያ ወዳንቺ ያጋደለ
በትዝታ ቅኝት ክራሩ ሲገረፍ አብሮ ያዘነበለ
አንቺን ፈላጊ አይኖች
ድምጽሽ የጠማቸው ዲሽ መሳይ ጆሮዎች
አነፈናፊ አፍንጫ ከአደይ ከቅጠሉ ጠረንሽን 'ሚያሸት
በናፍቆት ተመዝዞ ያዘነበለ አንገት

ምንም አትጠይቂኝ
የተሰበረ ገል ያልተቆላ ቡና
የታረደ ዶሮ የሸተተ ቡላ
ሞልቶ ያልሞላ ታክሲ የሌለው ወያላ
ምንድናቸው ብለሽ ምንም አትጠይቂኝ
ሁሉም ልቤ ናቸው ሁሉም እራሴ ነኝ

ሰይፈ ተማም 2011
ስፈራ ስፈራ
የሃሳቤን አጥር
ያጠረኝን ቅጥር
የቅጥሩን ጌታ
ስፈራ ቆይቼ አፌ እንደተፈታ
የምለው ሳላጣ
የፈራሁት 'ሰሚ' ሆኖት ሰላረፈው
አሁን አይሰሜውን ህዝብ ፈርቻለሁ


ሰይፈ ተማም 2011
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter - 11th March 2019 is out now,
featuring @Royalphotography22, Fekat Circus, @behagerlij, Habesha Animation, Fano Creatives, Association of Ethiopian Architects, Designlab ETH, Everted, Artistic Ethiopia, Art in Addis, Zoma Museum - https://bit.ly/2Ho5ZvO We hope you enjoy!!
የኋላ የኋላ

የታሰረን መምታት
የወደቀን መግፋት
ጀግንነት ነው ወይ
ከሌለው መቀማት
ጦስ ይሆን የለም ወይ
የመቱት ሲፈታ ሲበቅል የገፉት
ሰብል እኮ ይሆናል ዘርን ሲበትኑት

ሰይፈ ተማም 2010
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5.pdf
3.2 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል with over 20 opportunities for you to explore!!! https://bit.ly/2Ve5RHs
This week featuring @michaelfelleke, Beza Hailu Lemma, Ethiopian Records. የኢትዮጵያ ልጅ, Yefikir Design, @kunjina_ltd, Gobeze, Seife Temam, Ayni's, @melkam74, @LinkUpAddis, Contemporary Nights
Forwarded from Bruh Club
ውድ አርቲስቶቻችን፣
የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2
Featuring @Mykeyliyew, @BigDreamEt, @melkam74, @habeshawian, @Sabegnn and so much more
Forwarded from SABEGN
Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before
Forwarded from Bruh Club
The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.ly/2Mji35E
This week we feature Awell Kedir Afro Fair Fest, Gebeya Talent, @BigDreamET, Addis Foto Fest (AFF), Addis Insight, BAM Ethiopia, Awtar Multimedia, LinkUp Addis, Betty G., Startup Ethiopia, @talktolife and so much more
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6.pdf
4.3 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6

💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!!
https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls, competitions, residencies etc for the Ethiopian creative practitioner. So do apply!!!!!!

This week featuring visual artist @Mesfinarts

Book-worm, @Freelance_ethio, @LinkUpAddis, @BiGDreamET and so much more