ውዴ
ዝምታሽ ቢጨንቀኝ ቴክስትሽ ቢርቀኝ
ስልኬ ያለልማዱ ብሬን ቢምርልኝ
አፌን አሞጥሙጬ ልነግርሽ ቆረጥኩኝ
እቱ የኔ አበባ....
ዝምታሽ ከባድ ነው ሆድን ያሸብራል
ቀልብንም አርቆ አንጀት ያላውሣል.....
ብዬ እንዳልልሽ.... ብዬ እንዳልልሽ
ቃላት አይገዙ በቂ ስንኝ የለኝ
እኔም ካንቺ የባስኩ ስንኞች የከዱኝ
ብቻ....
ጀማሪ መሆኔ እንዳይነቃብኝ
ኝ ኝ ኝ ..... እያልኩኝ
መግጠሙ ደብሮኝ
የሆዴን ሣልሸና ልተኛ ወሠንኩኝ።
(እባክሽ አደራ እንዳትስቂብኝ.ኝ ኝ ኝ..)
ኖታ
ዝምታሽ ቢጨንቀኝ ቴክስትሽ ቢርቀኝ
ስልኬ ያለልማዱ ብሬን ቢምርልኝ
አፌን አሞጥሙጬ ልነግርሽ ቆረጥኩኝ
እቱ የኔ አበባ....
ዝምታሽ ከባድ ነው ሆድን ያሸብራል
ቀልብንም አርቆ አንጀት ያላውሣል.....
ብዬ እንዳልልሽ.... ብዬ እንዳልልሽ
ቃላት አይገዙ በቂ ስንኝ የለኝ
እኔም ካንቺ የባስኩ ስንኞች የከዱኝ
ብቻ....
ጀማሪ መሆኔ እንዳይነቃብኝ
ኝ ኝ ኝ ..... እያልኩኝ
መግጠሙ ደብሮኝ
የሆዴን ሣልሸና ልተኛ ወሠንኩኝ።
(እባክሽ አደራ እንዳትስቂብኝ.ኝ ኝ ኝ..)
ኖታ
እዬዬ
ከውዶቹ መሃል አንድ ሰው አነሰኝ
ሀዘን ሆዴ ገብቶ እያንሰፈሰፈኝ
ጠቆረብኝ ውስጤ ልቤም ጨላለመ
ያሸከምኩት ተስፋ በአፈር አከተመ
እዬዬ ለራሴ እዬዬ ለሃገሬ
ታናሼ ሲቀድመኝ እኔ ተገትሬ
እዬዬ ለቋሚ ውዱን ለሸኘ ሰው
ከተመረጠማ የአብስራ ድንቅ ነው
ሰይፈ
ከውዶቹ መሃል አንድ ሰው አነሰኝ
ሀዘን ሆዴ ገብቶ እያንሰፈሰፈኝ
ጠቆረብኝ ውስጤ ልቤም ጨላለመ
ያሸከምኩት ተስፋ በአፈር አከተመ
እዬዬ ለራሴ እዬዬ ለሃገሬ
ታናሼ ሲቀድመኝ እኔ ተገትሬ
እዬዬ ለቋሚ ውዱን ለሸኘ ሰው
ከተመረጠማ የአብስራ ድንቅ ነው
ሰይፈ
ግዝት
አድምጡኝ እንጂ አትስሙኝ
በክፋት ጥላቻ በህይወት ገላችሁ
ከነመፈጠሬም በቁሜ ረስታችሁ
የአፈሬን ሳጥን በቅርቡ አይታችሁ
እንዳታለቅሱልኝ ...
ኻላ እንዳላዝንባችሁ
አትክልት አይደለሁ እንባችሁ አይረባኝ
ከሞት አለምልሞ ህይወት አይዘራብኝ
እንዲያው ከንቱ ድካም እንዳይሆንባችሁ
መኖሬን ከድታችሁ ሞቴን ካመናችሁ
ያኔ... በበድኔ ዙሪያ እንዳላይ ከባችሁ
በቁሜ እያለሁ ይኸው ገዘትኳችሁ።
እንዳታለቅሱልኝ...!!!
ኖታ
አድምጡኝ እንጂ አትስሙኝ
በክፋት ጥላቻ በህይወት ገላችሁ
ከነመፈጠሬም በቁሜ ረስታችሁ
የአፈሬን ሳጥን በቅርቡ አይታችሁ
እንዳታለቅሱልኝ ...
ኻላ እንዳላዝንባችሁ
አትክልት አይደለሁ እንባችሁ አይረባኝ
ከሞት አለምልሞ ህይወት አይዘራብኝ
እንዲያው ከንቱ ድካም እንዳይሆንባችሁ
መኖሬን ከድታችሁ ሞቴን ካመናችሁ
ያኔ... በበድኔ ዙሪያ እንዳላይ ከባችሁ
በቁሜ እያለሁ ይኸው ገዘትኳችሁ።
እንዳታለቅሱልኝ...!!!
ኖታ
ሁለት አለሜ
መጀመሪያ ሳይሽ ልቤ ምቱ ጠፋው
ግጥሜ ተበላሸ
ቀለሙ እየሸሸ
መጀመሪያ ሳውቅሽ ሰው አለኝ የሚለው
ቃልሽ ልቤን ወጋ
እንዴት ካንቺ ላውጋ
ክንፍ ያለኝ ይመስልጊዜን መራመጃ
ነገን ካንቺ ከረምኩ የዛሬዬን እንጃ
ጸዳልሽን አየሁ ከጎኔ ሲበራ
የቆዘመ ገጼን በሙቀት ሲጣራ
ደሞም ደስስ እያለ መልሶ ሲያስፈራ
እኔና አንቺ ብቻ ካለንበት ቦታ
ከቦን ያለም ሃዘን ከቦን ያለም ሆታ
ቅጽበታት ደምረን ስናረገው አፍታ
ዱካክ እንዳጠረው እንቅልፍ አልባ ጊዜ
ባንኖ መታ ልቤ ባንቺው ስልት አባዜ
ሁለት አለም ኖረኝ
አንደኛው የንቃት ሌላው የትካዜ
ሰይፈ ተማም 2010
መጀመሪያ ሳይሽ ልቤ ምቱ ጠፋው
ግጥሜ ተበላሸ
ቀለሙ እየሸሸ
መጀመሪያ ሳውቅሽ ሰው አለኝ የሚለው
ቃልሽ ልቤን ወጋ
እንዴት ካንቺ ላውጋ
ክንፍ ያለኝ ይመስልጊዜን መራመጃ
ነገን ካንቺ ከረምኩ የዛሬዬን እንጃ
ጸዳልሽን አየሁ ከጎኔ ሲበራ
የቆዘመ ገጼን በሙቀት ሲጣራ
ደሞም ደስስ እያለ መልሶ ሲያስፈራ
እኔና አንቺ ብቻ ካለንበት ቦታ
ከቦን ያለም ሃዘን ከቦን ያለም ሆታ
ቅጽበታት ደምረን ስናረገው አፍታ
ዱካክ እንዳጠረው እንቅልፍ አልባ ጊዜ
ባንኖ መታ ልቤ ባንቺው ስልት አባዜ
ሁለት አለም ኖረኝ
አንደኛው የንቃት ሌላው የትካዜ
ሰይፈ ተማም 2010
ለመስራት
ለመጨረስስ አልሰራም ለመስራት ልጨርስ እንጂ
ተጨርሶ ሲመረቅ እንደሚታደስ መንገድ
ስካሩ ጠፋ ሲባል መልሶ 'ሚንገዳገድ
እንኳን ተሻለህ ሲሉት እንደሚያቃስት ህመመኛ
ለመጨረስስ አንስራ ለመስራት እንጨርስ እኛ
ሰይፈ ተማም 2010
ለመጨረስስ አልሰራም ለመስራት ልጨርስ እንጂ
ተጨርሶ ሲመረቅ እንደሚታደስ መንገድ
ስካሩ ጠፋ ሲባል መልሶ 'ሚንገዳገድ
እንኳን ተሻለህ ሲሉት እንደሚያቃስት ህመመኛ
ለመጨረስስ አንስራ ለመስራት እንጨርስ እኛ
ሰይፈ ተማም 2010
ከመሬት ነኝ
መሬት አይደል መነሻዬ
መሬት ያጣሁ መሬት ሁኜ
መነሳትን ተጠይፌ
የወደቅኩኝ ተንሳፍፌ
እኔም ራሴ መሬት
ለመብቀያ ያበቀለኝ
ከመሬት ነኝ?
ከምሬት ነኝ?
ከምር የት ነኝ?
ቁንጥር አፈር ዘግኖ በእጁ ካበጃጀኝ
ቁንጽል አንቀጽ ጠቅሶ በእጁ 'ሚያስፈጀኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከመሬትም መሬት
ሲረማመዱብኝ እንቁዬን ደብቄ በቀን እኩለ ሌት
ሲዘንብ እምቦካ የቋጠርኩኝ አለት
ሲያርሱ 'ምበረበር
ሲበትኑ 'ምዘር
የማያዳብረኝ የሰጡኝ ምርጥ ዘር
አለቴን ገድዬ 'ማረገው አፈር
ጨረቃን ጋርጄ ፀሃይ የምሰፍር
ፀሃይ በዛ ብዬ ደሞ ምንጨረጨር
ህዋ ላይ ተጥዬ የማርፍበት የናፈቀኝ
አዎ መሬት ያጣሁ መሬት ነኝ
ቀማሽ ምላስ ሰጥቶ ጣ'ም 'ሚያስቆጥረኝ
ጣፋጭ ስኳር ነስቶ በጨዉ ሲያስመርረኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከምሬትም ምሬት
ወዳጄ ስሞታ ወዳጄ ጣ'ም ሃሞት
የማያጣኝ ከቤት
የማያጣኝ ከሬት
ብሶት የወለደው ብሶ ያንገሸገሸኝ
ጣ'ም ያጣሁ ምሬት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
መሬት ምሬት ምርየት
መሬቱ ሰው አለው
አለው የሰው ኩሩ
'ራሱን እማይነጥል
ከዱሩ ከአፈሩ
ሲጠብቃት ኖሮ
ከሷው ነው አዳሩ
ይኸም ሰው ጨፍግጓል
መረሮታል ጠአሙ
መጣፈጥ ጠፍቶታል
መልኩም ሆነ ስሙ
ለአንድ ቡሃቃ ሊጥ
20 ሺ እያሰሙ
ከምር ወደየት ነው
ከየት ወየት መንገድ
(ከሰከሩም እንኳን)
አይቶ ገምቶ ነው
ኋላ መንገዳገድ
ወይ የሚያቅፉ መስሎ
ትከሻ መላመድ
ወይ እራስን መብላት
ከመሬት መዋደድ
የምን ቆሞ መሄድ
የምን ሄዶ መቆም
በራስ ቤት መታሰር
ቂም ይዞ እንደመፆም
ለመዋደድ ነቅቶ
በፍቅር ነው መሾም
እንዳሹት ከምታሽ
እንደ ደማከሴ
የት እንዳለሁ ሳላውቅ
አድር ይሆን ፈውሼ?
ያለት ስንጣሪ
ከምድር የቀረፀኝ
ቅምሻ ፍርፋሪ
ኮምጥጦ አገረሸኝ
አይኔን አስጨፈነኝ
ኸረ ከምር የት ነኝ?
ታውሮ ሚመራው
መንገዴን ነጠቀኝ
እኔጠፋሁ ልበል
ካለሁስ ወዴት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
... ሆኜ ካለሁበት
ሰይፈ ተማም 2010
መሬት አይደል መነሻዬ
መሬት ያጣሁ መሬት ሁኜ
መነሳትን ተጠይፌ
የወደቅኩኝ ተንሳፍፌ
እኔም ራሴ መሬት
ለመብቀያ ያበቀለኝ
ከመሬት ነኝ?
ከምሬት ነኝ?
ከምር የት ነኝ?
ቁንጥር አፈር ዘግኖ በእጁ ካበጃጀኝ
ቁንጽል አንቀጽ ጠቅሶ በእጁ 'ሚያስፈጀኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከመሬትም መሬት
ሲረማመዱብኝ እንቁዬን ደብቄ በቀን እኩለ ሌት
ሲዘንብ እምቦካ የቋጠርኩኝ አለት
ሲያርሱ 'ምበረበር
ሲበትኑ 'ምዘር
የማያዳብረኝ የሰጡኝ ምርጥ ዘር
አለቴን ገድዬ 'ማረገው አፈር
ጨረቃን ጋርጄ ፀሃይ የምሰፍር
ፀሃይ በዛ ብዬ ደሞ ምንጨረጨር
ህዋ ላይ ተጥዬ የማርፍበት የናፈቀኝ
አዎ መሬት ያጣሁ መሬት ነኝ
ቀማሽ ምላስ ሰጥቶ ጣ'ም 'ሚያስቆጥረኝ
ጣፋጭ ስኳር ነስቶ በጨዉ ሲያስመርረኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከምሬትም ምሬት
ወዳጄ ስሞታ ወዳጄ ጣ'ም ሃሞት
የማያጣኝ ከቤት
የማያጣኝ ከሬት
ብሶት የወለደው ብሶ ያንገሸገሸኝ
ጣ'ም ያጣሁ ምሬት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
መሬት ምሬት ምርየት
መሬቱ ሰው አለው
አለው የሰው ኩሩ
'ራሱን እማይነጥል
ከዱሩ ከአፈሩ
ሲጠብቃት ኖሮ
ከሷው ነው አዳሩ
ይኸም ሰው ጨፍግጓል
መረሮታል ጠአሙ
መጣፈጥ ጠፍቶታል
መልኩም ሆነ ስሙ
ለአንድ ቡሃቃ ሊጥ
20 ሺ እያሰሙ
ከምር ወደየት ነው
ከየት ወየት መንገድ
(ከሰከሩም እንኳን)
አይቶ ገምቶ ነው
ኋላ መንገዳገድ
ወይ የሚያቅፉ መስሎ
ትከሻ መላመድ
ወይ እራስን መብላት
ከመሬት መዋደድ
የምን ቆሞ መሄድ
የምን ሄዶ መቆም
በራስ ቤት መታሰር
ቂም ይዞ እንደመፆም
ለመዋደድ ነቅቶ
በፍቅር ነው መሾም
እንዳሹት ከምታሽ
እንደ ደማከሴ
የት እንዳለሁ ሳላውቅ
አድር ይሆን ፈውሼ?
ያለት ስንጣሪ
ከምድር የቀረፀኝ
ቅምሻ ፍርፋሪ
ኮምጥጦ አገረሸኝ
አይኔን አስጨፈነኝ
ኸረ ከምር የት ነኝ?
ታውሮ ሚመራው
መንገዴን ነጠቀኝ
እኔጠፋሁ ልበል
ካለሁስ ወዴት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
... ሆኜ ካለሁበት
ሰይፈ ተማም 2010
👍1
በጾሙ
ልቤ ጠረጠረ ነገር ነገር አለኝ
ከተኩሎቹ መሃል ፍየል ቢጤ ባገኝ
ስጋዋም ወተቷ መድሃኒት ነው አሉ
ዘምዘም እጠጣለሁ ሲያሻኝ ከጠበሉ
ወይ እታከማለሁ ደሞ በዶክተሩ
ልቤ እንዲጠራልኝ እንዲቀለኝ ቂሙ
እላለሁ ተኩሎቹም አብይን በጾሙ
አብይን በጾሙ አብይን በጾሙ
ሰይፈ ተማም 2010
ልቤ ጠረጠረ ነገር ነገር አለኝ
ከተኩሎቹ መሃል ፍየል ቢጤ ባገኝ
ስጋዋም ወተቷ መድሃኒት ነው አሉ
ዘምዘም እጠጣለሁ ሲያሻኝ ከጠበሉ
ወይ እታከማለሁ ደሞ በዶክተሩ
ልቤ እንዲጠራልኝ እንዲቀለኝ ቂሙ
እላለሁ ተኩሎቹም አብይን በጾሙ
አብይን በጾሙ አብይን በጾሙ
ሰይፈ ተማም 2010
ልወዳት እየጣርኩ ነው
ቁንጅናዋን አይኔ አክብዶት ከልቤ ጋር ከመከረ
ከጉያዋ የፈለቀ እሳት ውስጤን ካኮማተረ
አቅሜን የያዘችው ቢመስላት እንዳሻት የምትዘውረው
በቀና ልብ ተንደርድሬ ልወዳት እየጣርኩ ነው
ከፍታ ቢሰማው ቀልቧ የወጣ መስሎት ከማማ
ወስኜ ነበር ልረሳት ክብሬን እንዳላስቀማ
ዛሬ 'ምማትር ዞሬ ገጿን እማይ አጮልቄ
ልመራት እንጂ ደፍሬ አይደለም ብርሃን ናፍቄ
እዩልኝ ሰዎች ልብ አርጉ
ድብቅ መናፍስት ካሉበት በዐይኖቿ ሲበረግጉ
ከጠረኗ እጣን ወጥቶ ንቦች ሲውረገረጉ
ከአናብርት ቆዳ አብልጠው አዳኞች እሷን ሲወጉ
ልብ አርጉ ሰዎች እዩልኝ
የወፏ ዜማ ቢያቅታት ንፋስ ስታዜምብኝ
ከአሳ ቀድሞ 'ሚበላሽ ፀዳሏን ስትበትንብኝ
ከረግረግ ጨፌ በጥሼ በጣቷ 'ምታሾፍብኝ
እዩልኝ ልብ አርጉ ሰዎች
በየደፍ በአፀድ በጥጉ ስሜን ቆልላዋለች
ደሞም በውበት ሰክራ ምኑምኔ ትላለች
የልቧን መንፈቅ ከልላ በቀሪው ትጫወታለች
ቁማር መሰላት መዋደድ
የሆነ ስሜት አስይዞ የሆነ ስሜት ደብቆ
ያልሆነ ንዴት መናደድ
ይልቅስ አቅሜን እንዳሻት ቢመስላት የምትዘውረው
እኔስ በቀና ልቤ ልወዳት እየጣርኩ ነው
ሰይፈ ተማም 2010
ቁንጅናዋን አይኔ አክብዶት ከልቤ ጋር ከመከረ
ከጉያዋ የፈለቀ እሳት ውስጤን ካኮማተረ
አቅሜን የያዘችው ቢመስላት እንዳሻት የምትዘውረው
በቀና ልብ ተንደርድሬ ልወዳት እየጣርኩ ነው
ከፍታ ቢሰማው ቀልቧ የወጣ መስሎት ከማማ
ወስኜ ነበር ልረሳት ክብሬን እንዳላስቀማ
ዛሬ 'ምማትር ዞሬ ገጿን እማይ አጮልቄ
ልመራት እንጂ ደፍሬ አይደለም ብርሃን ናፍቄ
እዩልኝ ሰዎች ልብ አርጉ
ድብቅ መናፍስት ካሉበት በዐይኖቿ ሲበረግጉ
ከጠረኗ እጣን ወጥቶ ንቦች ሲውረገረጉ
ከአናብርት ቆዳ አብልጠው አዳኞች እሷን ሲወጉ
ልብ አርጉ ሰዎች እዩልኝ
የወፏ ዜማ ቢያቅታት ንፋስ ስታዜምብኝ
ከአሳ ቀድሞ 'ሚበላሽ ፀዳሏን ስትበትንብኝ
ከረግረግ ጨፌ በጥሼ በጣቷ 'ምታሾፍብኝ
እዩልኝ ልብ አርጉ ሰዎች
በየደፍ በአፀድ በጥጉ ስሜን ቆልላዋለች
ደሞም በውበት ሰክራ ምኑምኔ ትላለች
የልቧን መንፈቅ ከልላ በቀሪው ትጫወታለች
ቁማር መሰላት መዋደድ
የሆነ ስሜት አስይዞ የሆነ ስሜት ደብቆ
ያልሆነ ንዴት መናደድ
ይልቅስ አቅሜን እንዳሻት ቢመስላት የምትዘውረው
እኔስ በቀና ልቤ ልወዳት እየጣርኩ ነው
ሰይፈ ተማም 2010
አትመሪ
ውዴ....በቀረብኩሽ መጠን..
የገላሽ ጠረኑ--የገፅሽ ፍካቱ
የምናብሽ ርቀት--የሀሣብሽ ግዝፈቱ
ባንድነት እብረው ያሸነፉኝ ለታ
ሱባኤ ገብቼ
ስህለት አስገብቼ
እኔ አንቺን ማግኘቴን ያላወቁ ሁሉ
ውበትሽ ማርኲቸው ደጅሽ ይቆማሉ
ስንት እድሜ ከፍዬ- ከልብሽ እንዳደርኩ
ስንት ህልም ሠፍሬ- አንገትሽን እንዳቀፍኩ
ሀቁ ካልገባቸው
"እውነት" እንዳያዩ ውበትሽ ከሆነየጋረደባቸው
እስኪ አትኲኲይ እትመሪላቸው
ወጡን ወጥውጪና እንጀራውን ጋግረሽ
ሣትተጣጠቢ ውጪ ከነ ሊጥሽ
ነጩን ጥበብ ቀሚስ አትልበሽው ይቅር
ጫማም አትጫሚ ሒጂላቸው በ'ግር
ፊትሽም ይጠውልግ ፀጉርሽ አይጎንጎን
እድፍ ይሁንበት አታፅጅው ገላሽን
ይቅር እትመሪ
ይደበቅ ይከለል ውበትሽ አስኩዋሉ
ያኔ...
ገፅሽን አካልሽን የቁዋመጡ ሁሉ
'ጣይ እንዳየው ጤዛ ምኞታቸው ረግፎ ካይንሽ ይርቃሉ
በዚህ ከተስማማን
ከተመቸሽ ላንቺ ከተመቸኝ ለኔ
በመጠውለግሽ ልክ በድምቀትሽ መጠን እምዳይሠፍርሽ
አይኔ
ከሁሉ አስቀድሞ ያላንዳች እኩያ
ያላንዳች አምሣያ
ከከፍታው በላይ አኑሮሻል ልቤ!
እናም እልሻለሁ፦
"ስጋ"ን ላፈቀረ "ገፅ" ላደነቀ መንገደኛ ትውልድ
ፈራሹን ሠጥተነው
እኔና አንቺ ብቻ ነፍሳችን ይዋደድ።.
ዳግም ተካ
ውዴ....በቀረብኩሽ መጠን..
የገላሽ ጠረኑ--የገፅሽ ፍካቱ
የምናብሽ ርቀት--የሀሣብሽ ግዝፈቱ
ባንድነት እብረው ያሸነፉኝ ለታ
ሱባኤ ገብቼ
ስህለት አስገብቼ
እኔ አንቺን ማግኘቴን ያላወቁ ሁሉ
ውበትሽ ማርኲቸው ደጅሽ ይቆማሉ
ስንት እድሜ ከፍዬ- ከልብሽ እንዳደርኩ
ስንት ህልም ሠፍሬ- አንገትሽን እንዳቀፍኩ
ሀቁ ካልገባቸው
"እውነት" እንዳያዩ ውበትሽ ከሆነየጋረደባቸው
እስኪ አትኲኲይ እትመሪላቸው
ወጡን ወጥውጪና እንጀራውን ጋግረሽ
ሣትተጣጠቢ ውጪ ከነ ሊጥሽ
ነጩን ጥበብ ቀሚስ አትልበሽው ይቅር
ጫማም አትጫሚ ሒጂላቸው በ'ግር
ፊትሽም ይጠውልግ ፀጉርሽ አይጎንጎን
እድፍ ይሁንበት አታፅጅው ገላሽን
ይቅር እትመሪ
ይደበቅ ይከለል ውበትሽ አስኩዋሉ
ያኔ...
ገፅሽን አካልሽን የቁዋመጡ ሁሉ
'ጣይ እንዳየው ጤዛ ምኞታቸው ረግፎ ካይንሽ ይርቃሉ
በዚህ ከተስማማን
ከተመቸሽ ላንቺ ከተመቸኝ ለኔ
በመጠውለግሽ ልክ በድምቀትሽ መጠን እምዳይሠፍርሽ
አይኔ
ከሁሉ አስቀድሞ ያላንዳች እኩያ
ያላንዳች አምሣያ
ከከፍታው በላይ አኑሮሻል ልቤ!
እናም እልሻለሁ፦
"ስጋ"ን ላፈቀረ "ገፅ" ላደነቀ መንገደኛ ትውልድ
ፈራሹን ሠጥተነው
እኔና አንቺ ብቻ ነፍሳችን ይዋደድ።.
ዳግም ተካ
ድርሻ
ከተቆላው ቡና አሁን ከጠጣነው
የትኛው ፍሬ ይሆን እንደዚህ ያጣመው?
የትኛው ልቃሚ ወደአፈር ተጣለ
የቱ ጋር በስብሶስ በፍግነት ዋለ
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ጋር ዘመደ
የቱ ዛፍ ተቆርጦ የቱ ከሰል ነዶ ጀበናው ተጣደ
ከየትኛው አፈር ጀበናው ተበጀ
የትኛው ሰው ሞቶ አፈሩ ደረጀ
የትኛውን ሰው ነው
ጀበና ነው ብለን ከእሳቱ የጣድነው
ጥኡም ቡና ብለን አሁን የጠጣነው
...
ግን...
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ተቆራኘ
የትኛው ቅንጣት ነው ይህንን የቃኘ
ወዘተ ተብሎ የቱ የት ተገኘ
የቡናስ ገለባ እንዴት ተሰናኘ?
የሰው መሆን አጽናፍ የጭንቅላት ዳሩ
የንዝረት ስብጥር የብርሃን በሩ
የጨረር ጥርቅም በራሳቸው 'ሚያዩ
እነዚህ አይኖች መሀል ሰውነት ተተክሎ
አንዱ ኳስ የሚለው ለሌላው አሎሎ
አንዱ የለቀመውን ሌላው ቡና ብሎ
ተሰጠን ፀጋ ግን እንካችሁ ተብሎ
የመንጻት ምድጃ የስልጣን ረከቦት
የኃይል መቁያ ምጣዱ የበረከት
በጥበብ ተለቅሞ እኩል ከተቆላ
የዶሮአይን ብለው ይጠጡታል ኋላ
የሰው ዓይንማ ፊትለፊቱን እንጂ ውስጡን እረስቷላ
የሰው መሆን አጽናፍ የጭንቅላት ዳሩ
የንዝረት ስብጥር የብርሃን በሩ
የጨረር ፍላጾች በውስጡ እንዳሉ
አያይማ
የቡናው ፍሬዎች መለከት ሲነፉ
ስስ ገለባዎችም ባየር ሲንሳፈፉ
አይሰማማ
በዓይኑ ማየት ትቶ ልቡን ካልቀኛኘ
ሁሉን ፍሬ አክብሮ ካላቆረኛኘ
አይጸድቅማ
ቡና እንኳን ጥሎበት ጥላ ይወዳል አሉ
ምነው ድርሻ አጣን ማኖሪያ ላምሳሉ
ምነው ልብ ያላልነው ፍሬዎች ሲጣሉ
ምነው እሳ ምነው ምነው የማትሉ
ከተቆላው ቡና አሁን ከጠጣነው
የትኛው ፍሬ ይሆን እንደዚህ ያጣመው?
የትኛው ልቃሚ ወደአፈር ተጣለ
የቱ ጋር በስብሶስ በፍግነት ዋለ
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ጋር ዘመደ
የቱ ዛፍ ተቆርጦ የቱ ከሰል ነዶ ጀበናው ተጣደ
ሰይፈ ተማም 2010 -
Neurodiversity at Lebawi
ከተቆላው ቡና አሁን ከጠጣነው
የትኛው ፍሬ ይሆን እንደዚህ ያጣመው?
የትኛው ልቃሚ ወደአፈር ተጣለ
የቱ ጋር በስብሶስ በፍግነት ዋለ
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ጋር ዘመደ
የቱ ዛፍ ተቆርጦ የቱ ከሰል ነዶ ጀበናው ተጣደ
ከየትኛው አፈር ጀበናው ተበጀ
የትኛው ሰው ሞቶ አፈሩ ደረጀ
የትኛውን ሰው ነው
ጀበና ነው ብለን ከእሳቱ የጣድነው
ጥኡም ቡና ብለን አሁን የጠጣነው
...
ግን...
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ተቆራኘ
የትኛው ቅንጣት ነው ይህንን የቃኘ
ወዘተ ተብሎ የቱ የት ተገኘ
የቡናስ ገለባ እንዴት ተሰናኘ?
የሰው መሆን አጽናፍ የጭንቅላት ዳሩ
የንዝረት ስብጥር የብርሃን በሩ
የጨረር ጥርቅም በራሳቸው 'ሚያዩ
እነዚህ አይኖች መሀል ሰውነት ተተክሎ
አንዱ ኳስ የሚለው ለሌላው አሎሎ
አንዱ የለቀመውን ሌላው ቡና ብሎ
ተሰጠን ፀጋ ግን እንካችሁ ተብሎ
የመንጻት ምድጃ የስልጣን ረከቦት
የኃይል መቁያ ምጣዱ የበረከት
በጥበብ ተለቅሞ እኩል ከተቆላ
የዶሮአይን ብለው ይጠጡታል ኋላ
የሰው ዓይንማ ፊትለፊቱን እንጂ ውስጡን እረስቷላ
የሰው መሆን አጽናፍ የጭንቅላት ዳሩ
የንዝረት ስብጥር የብርሃን በሩ
የጨረር ፍላጾች በውስጡ እንዳሉ
አያይማ
የቡናው ፍሬዎች መለከት ሲነፉ
ስስ ገለባዎችም ባየር ሲንሳፈፉ
አይሰማማ
በዓይኑ ማየት ትቶ ልቡን ካልቀኛኘ
ሁሉን ፍሬ አክብሮ ካላቆረኛኘ
አይጸድቅማ
ቡና እንኳን ጥሎበት ጥላ ይወዳል አሉ
ምነው ድርሻ አጣን ማኖሪያ ላምሳሉ
ምነው ልብ ያላልነው ፍሬዎች ሲጣሉ
ምነው እሳ ምነው ምነው የማትሉ
ከተቆላው ቡና አሁን ከጠጣነው
የትኛው ፍሬ ይሆን እንደዚህ ያጣመው?
የትኛው ልቃሚ ወደአፈር ተጣለ
የቱ ጋር በስብሶስ በፍግነት ዋለ
የቱ ምን ለየቱ ምን ምኑ ጋር ዘመደ
የቱ ዛፍ ተቆርጦ የቱ ከሰል ነዶ ጀበናው ተጣደ
ሰይፈ ተማም 2010 -
Neurodiversity at Lebawi
ውባለሜ
----------
አንቺን ማከም
እንዳሰብኩት ዋዛ አይደለም
አንቺ የኔ እኔም ያንቺ
እኔና አንቺም የሁሉ ነን
ሁሉም የኛ እኛም ሁሉን
ብለን ካመን
አምነን ካልን
ያልነውን
ስንሆን
ጥላቻ አይደል ወይም ስስት
'ራሴን ላክም የምታክት
ውባለሜ
በህመምሽ መታመሜ
ጎኔን ይዞኝ በመክሰሜ
አንቺን ማከም
እንዳሰብኩት ዋዛ አልሆነም
ውጋት ቁርጠት ትኩሳትሽ
በኔ ብሶ ታመምኩልሽ
የኔም ህመም ተጨምሮ
ከሚገፋሽ ጣርሽ ጥሮ
ይኧው ጉልበቴ በረከ
ልቤም መኖሬን ተረከ
የራሴን ጉድፍ ላጠራ
የጠፋ አይንሽ ባይበራ
ለቅሶሽን እንኳ ባባራ
እጄን ወደ ዓይኔ ላከ
ሌቱም ሲጠራ ማለዳ
ክብሬን ለአንገትሽ ማክዳ
ስሜን ከብርድ መዳኛ
አቅሜን ልክሽን ማፅኛ
አድርጌ አንቺን ላስታምም
ባልፈውስሽም እንኳ
ህመምሽ በኔ አይብስም...
እራሴን አቅፌ ስሜ
መቋሚያዪን አቅልሜ
ባላድንሽ እንዳያምሽ
'ደርስልሻለሁ አለሜ
ሰይፈ ተማም 2008ድሬ
----------
አንቺን ማከም
እንዳሰብኩት ዋዛ አይደለም
አንቺ የኔ እኔም ያንቺ
እኔና አንቺም የሁሉ ነን
ሁሉም የኛ እኛም ሁሉን
ብለን ካመን
አምነን ካልን
ያልነውን
ስንሆን
ጥላቻ አይደል ወይም ስስት
'ራሴን ላክም የምታክት
ውባለሜ
በህመምሽ መታመሜ
ጎኔን ይዞኝ በመክሰሜ
አንቺን ማከም
እንዳሰብኩት ዋዛ አልሆነም
ውጋት ቁርጠት ትኩሳትሽ
በኔ ብሶ ታመምኩልሽ
የኔም ህመም ተጨምሮ
ከሚገፋሽ ጣርሽ ጥሮ
ይኧው ጉልበቴ በረከ
ልቤም መኖሬን ተረከ
የራሴን ጉድፍ ላጠራ
የጠፋ አይንሽ ባይበራ
ለቅሶሽን እንኳ ባባራ
እጄን ወደ ዓይኔ ላከ
ሌቱም ሲጠራ ማለዳ
ክብሬን ለአንገትሽ ማክዳ
ስሜን ከብርድ መዳኛ
አቅሜን ልክሽን ማፅኛ
አድርጌ አንቺን ላስታምም
ባልፈውስሽም እንኳ
ህመምሽ በኔ አይብስም...
እራሴን አቅፌ ስሜ
መቋሚያዪን አቅልሜ
ባላድንሽ እንዳያምሽ
'ደርስልሻለሁ አለሜ
ሰይፈ ተማም 2008ድሬ
የጸባኦት ጣሪያ
(በ ሰይፈ ተማም)
ከደሜ ደም ተጣብቆ
የልቤን ልብ አርቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛበ ላይ
መጥቆ
ሲፍለቀለቅ
ሲንዠቀዠቅ
ሲያብረቀርቅ
ሲርቅ
ሲመጥቅ
... ሲደባለቅ
አዩትና ይህ ንልዩ
አዩትና ́ከኔ ́በላይ
ካለው በላይ ከበላዩ
አዩትና በእንቅልፍልብ
አዩትና ባሳብ ክልብ
አዩትና . . .
(አይ ሰው ሞኙ
ስምወዳጁ ርዕስ ቀኙ)
. . .
ከደሜ አንጓ ተፈልቅቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ካጥናፍ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛ በላይ መጥቆ
ዘመን አልባ
ቅጽበት አልባ
የማይነጋ የማይጠባ
የማይተጋ የማይገባ
የማይለማ የማይሰባ
የጸጋ ለምድ የክብር ካባ
የንቁ አጸድ የፍቅር አምባ
መሻትን የማይሻ
ምሉዕ የሁሉ ድርሻ
ሰቶም እማይጎድል
ነዶም እማይከስል . . .
ያዩትን ብቻ ́ሚያዩ
ከትውስታ ሳይለዩ
አዩትና ይሄን ልዩ
አዩትና ካ ́ለምጋራ የዘገዩ
አይተው መስሏቸው ያዩ
ጻፍልን አሉኝ ስሙን
ጻፍልን አሉ ማሰሪያ
ጻፍልን አሉ ማጠሪያ
ጻፍልን አሉ መጠሪያ
ስም ያለው ይመስል
የጸባኦት ጣሪያ
(በ ሰይፈ ተማም)
ከደሜ ደም ተጣብቆ
የልቤን ልብ አርቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛበ ላይ
መጥቆ
ሲፍለቀለቅ
ሲንዠቀዠቅ
ሲያብረቀርቅ
ሲርቅ
ሲመጥቅ
... ሲደባለቅ
አዩትና ይህ ንልዩ
አዩትና ́ከኔ ́በላይ
ካለው በላይ ከበላዩ
አዩትና በእንቅልፍልብ
አዩትና ባሳብ ክልብ
አዩትና . . .
(አይ ሰው ሞኙ
ስምወዳጁ ርዕስ ቀኙ)
. . .
ከደሜ አንጓ ተፈልቅቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ካጥናፍ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛ በላይ መጥቆ
ዘመን አልባ
ቅጽበት አልባ
የማይነጋ የማይጠባ
የማይተጋ የማይገባ
የማይለማ የማይሰባ
የጸጋ ለምድ የክብር ካባ
የንቁ አጸድ የፍቅር አምባ
መሻትን የማይሻ
ምሉዕ የሁሉ ድርሻ
ሰቶም እማይጎድል
ነዶም እማይከስል . . .
ያዩትን ብቻ ́ሚያዩ
ከትውስታ ሳይለዩ
አዩትና ይሄን ልዩ
አዩትና ካ ́ለምጋራ የዘገዩ
አይተው መስሏቸው ያዩ
ጻፍልን አሉኝ ስሙን
ጻፍልን አሉ ማሰሪያ
ጻፍልን አሉ ማጠሪያ
ጻፍልን አሉ መጠሪያ
ስም ያለው ይመስል
የጸባኦት ጣሪያ
ፍቅር ወይ ወንበዴ
አንገቴ ላይ ሽፍታ አለ
ልክ እንዳንቺ እየጠፋ የሚወረኝ ብቅ እያለ
የሳምሽኝ ለት ቻፒስቲክሽ ከቆዳዬ እንደታተመ
መኖርሽን ያህል ተስፋ መኖሬ ውስጥ አከረመ
ልነቀሰው ሁሉ ቃጣኝ የከንፈርሽን ቅርጽ አድምቄ
ማስታወሻ እንዲሆነን አሳሳምሽን አድንቄ
መሳም እፈራ ነበር
መሳም እፈራ ነበር
በሱ ነውና ጌትዬው ተሰቅሎ 'ሚቸነከር
ግና መቸንከር ሁሉ
አንድ አይደል እና ውሉ
ለተሳመም ሁላቸው
አንድነት ከየት አላቸው
ፍቅር ተስሞ ተሽጦ ተክዶ ተገርፎ ይደማል
ዝቅ ባረጉት ቁጥር አይሎ ጭራሽ ከፍ ይላል
ስመው ባስያዙት ቁጥር ተሰቅሎ ቤዛ ይሆናል
ማን ያውቃል?
የግራውንስ ወንበዴ ማን አሳልፎ ሰጥቶታል
ነጭ ለብሶ አስጠቁሮታል
የቱ ይሁዳ ስሞታል
ከፍቅር በተቃራኒ በማይመለክ መስቀል
ሳይቤዥ አሰቅሎታል
አንገቴ ላይ ሽፍታ አለ
ልክ እንዳንቺ እየጠፋ የሚወረኝ ብቅ እያለ
ተንጠራርተሽ ተንጠራርተሽ አንገቴ ላይ ስትስሚኝ
ፍቅርን ልሁን ወንበዴ ይሁዳዬ ስትሆኚልኝ??
ሰይፈ ተማም 2010
አንገቴ ላይ ሽፍታ አለ
ልክ እንዳንቺ እየጠፋ የሚወረኝ ብቅ እያለ
የሳምሽኝ ለት ቻፒስቲክሽ ከቆዳዬ እንደታተመ
መኖርሽን ያህል ተስፋ መኖሬ ውስጥ አከረመ
ልነቀሰው ሁሉ ቃጣኝ የከንፈርሽን ቅርጽ አድምቄ
ማስታወሻ እንዲሆነን አሳሳምሽን አድንቄ
መሳም እፈራ ነበር
መሳም እፈራ ነበር
በሱ ነውና ጌትዬው ተሰቅሎ 'ሚቸነከር
ግና መቸንከር ሁሉ
አንድ አይደል እና ውሉ
ለተሳመም ሁላቸው
አንድነት ከየት አላቸው
ፍቅር ተስሞ ተሽጦ ተክዶ ተገርፎ ይደማል
ዝቅ ባረጉት ቁጥር አይሎ ጭራሽ ከፍ ይላል
ስመው ባስያዙት ቁጥር ተሰቅሎ ቤዛ ይሆናል
ማን ያውቃል?
የግራውንስ ወንበዴ ማን አሳልፎ ሰጥቶታል
ነጭ ለብሶ አስጠቁሮታል
የቱ ይሁዳ ስሞታል
ከፍቅር በተቃራኒ በማይመለክ መስቀል
ሳይቤዥ አሰቅሎታል
አንገቴ ላይ ሽፍታ አለ
ልክ እንዳንቺ እየጠፋ የሚወረኝ ብቅ እያለ
ተንጠራርተሽ ተንጠራርተሽ አንገቴ ላይ ስትስሚኝ
ፍቅርን ልሁን ወንበዴ ይሁዳዬ ስትሆኚልኝ??
ሰይፈ ተማም 2010