ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.72K subscribers
879 photos
57 videos
20 files
413 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ጥንብ አንሳ

በዘመነ ጥንባት ሰው ከሰው ተሻትቶ በረከሰበቱ
ብዙኃን አሉና ሰውነታቸው ውስጥ ሞተው የሸተቱ
ወይ ልብህን አንፃ ሙታኑን ቀስቅሳ
ወይ ሆድህን ሙላ ሁንና ጥንብአንሳ

@seifetemam #seifetemam
👍1
እሺ እንዴትናችሁልኝ? አዲሱ አመት አያያዙ የተመቻችሁ ይመስላል ። የግጥም ውድድራችን ተጀምሯል እስከ እሁድ አስር ሰዓት ይቆያል ። ግጥማችሁን በ @Seifdman አድርሱኝ ። ከመሳተፍ ማንበብን የምትመርጡ ከሆነ ለ 👍 እንዲሁም ለ 👎 በመምረጥ አሸናፊ ግጥሞችን እንለይ ። በድምጽ የተቀዱም ካሉ እቀበላለሁ ። መልካም ውድድር ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በዚህ አመት ደግሞ ሌላ ውድድር አዘጋጅቼላችኋለሁ በማንኛውም ርዕስ ላይ የተጻፈ የራሳችሁ ግጥም ። format: ርዕስ ፣ ግጥም ፣ የጸሃፊ ስም መልካም ዕድል!!! ልብ በሉ ተሸላሚ የሚሆነው በብዙ ሰው የተወደደው ብቻ ሳይሆን የ 👎 ምልክት የተሰጠውም ጭምር ነው ። ለመላክ @seifetemam የሚለውን በመጠቀም በቀጥታ አድርሱኝ ። በድጋሚ መልካም በዓል!!!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ተወዳዳሪዬ ፍሰሐ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቋል ።
40 ልብ

አይ እታባ ...
እንዴት ቀለድሽ ባክሽ
ሆድ ሆዴን ቢበላው ይመጣል ማለትሽ
አልታይህ ቢለኝ የያኔው ተረትሽ
አልጨበጥ ቢለኝ የፊተኛው ተስፋሽ
ይኸው እታባዬ ...... ቧልተኛ ነሽ አልኩሽ

ቁጥር እንደው አያፍር .....

ደንደሱን አስፍቶ ደሞ እያጠበበ፤ ይከንፋል... ይበራል
ሺዘጠኙን በቅጡ ሳንኖር፤ ፪ሺ ሠፍቶ ያተራምሰናል
እሱ ምን አለበት..... እንዳባይ ይነጉዳል...
እኔ አለሁ እዚ በሀሳብ የምርድ
አርባዬን ቀርጥፌ አፋሽ የሆንኩ አመድ

እና እታባዬ.....

የታል ታድያ ያ ልብ የነገርሽኝ ቀድሞ
በ40 ዘመኔ የማገኘው ቆሞ... (አልያም ተጋድሞ)
ከብትንትን ኑሮ የሚገላግለኝ
ከ40 ልብ ህይወት የሚያሰናብተኝ

የታለ እታባ?? ... የታለ??...
👆👆👆👆👆 writer...ናትናኤል "አብራራው G12"
ውዴ
ዝምታሽ ቢጨንቀኝ ቴክስትሽ ቢርቀኝ
ስልኬ ያለልማዱ ብሬን ቢምርልኝ
አፌን አሞጥሙጬ ልነግርሽ ቆረጥኩኝ

እቱ የኔ አበባ....

ዝምታሽ ከባድ ነው ሆድን ያሸብራል
ቀልብንም አርቆ አንጀት ያላውሣል.....

ብዬ እንዳልልሽ.... ብዬ እንዳልልሽ

ቃላት አይገዙ በቂ ስንኝ የለኝ
እኔም ካንቺ የባስኩ ስንኞች የከዱኝ

ብቻ....

ጀማሪ መሆኔ እንዳይነቃብኝ
ኝ ኝ ኝ ..... እያልኩኝ
መግጠሙ ደብሮኝ
የሆዴን ሣልሸና ልተኛ ወሠንኩኝ።
(እባክሽ አደራ እንዳትስቂብኝ.ኝ ኝ ኝ..)
ኖታ
እዬዬ

ከውዶቹ መሃል አንድ ሰው አነሰኝ
ሀዘን ሆዴ ገብቶ እያንሰፈሰፈኝ
ጠቆረብኝ ውስጤ ልቤም ጨላለመ
ያሸከምኩት ተስፋ በአፈር አከተመ
እዬዬ ለራሴ እዬዬ ለሃገሬ
ታናሼ ሲቀድመኝ እኔ ተገትሬ
እዬዬ ለቋሚ ውዱን ለሸኘ ሰው
ከተመረጠማ የአብስራ ድንቅ ነው

ሰይፈ
ግዝት
አድምጡኝ እንጂ አትስሙኝ

በክፋት ጥላቻ በህይወት ገላችሁ
ከነመፈጠሬም በቁሜ ረስታችሁ
የአፈሬን ሳጥን በቅርቡ አይታችሁ
እንዳታለቅሱልኝ ...
ኻላ እንዳላዝንባችሁ
አትክልት አይደለሁ እንባችሁ አይረባኝ
ከሞት አለምልሞ ህይወት አይዘራብኝ
እንዲያው ከንቱ ድካም እንዳይሆንባችሁ
መኖሬን ከድታችሁ ሞቴን ካመናችሁ
ያኔ... በበድኔ ዙሪያ እንዳላይ ከባችሁ
በቁሜ እያለሁ ይኸው ገዘትኳችሁ።
እንዳታለቅሱልኝ...!!!
ኖታ
👍1
ሁለት አለሜ

መጀመሪያ ሳይሽ ልቤ ምቱ ጠፋው
ግጥሜ ተበላሸ
ቀለሙ እየሸሸ
መጀመሪያ ሳውቅሽ ሰው አለኝ የሚለው
ቃልሽ ልቤን ወጋ
እንዴት ካንቺ ላውጋ

ክንፍ ያለኝ ይመስልጊዜን መራመጃ
ነገን ካንቺ ከረምኩ የዛሬዬን እንጃ
ጸዳልሽን አየሁ ከጎኔ ሲበራ
የቆዘመ ገጼን በሙቀት ሲጣራ
ደሞም ደስስ እያለ መልሶ ሲያስፈራ
እኔና አንቺ ብቻ ካለንበት ቦታ
ከቦን ያለም ሃዘን ከቦን ያለም ሆታ
ቅጽበታት ደምረን ስናረገው አፍታ
ዱካክ እንዳጠረው እንቅልፍ አልባ ጊዜ
ባንኖ መታ ልቤ ባንቺው ስልት አባዜ
ሁለት አለም ኖረኝ
አንደኛው የንቃት ሌላው የትካዜ

ሰይፈ ተማም 2010
ለመስራት

ለመጨረስስ አልሰራም ለመስራት ልጨርስ እንጂ
ተጨርሶ ሲመረቅ እንደሚታደስ መንገድ
ስካሩ ጠፋ ሲባል መልሶ 'ሚንገዳገድ
እንኳን ተሻለህ ሲሉት እንደሚያቃስት ህመመኛ
ለመጨረስስ አንስራ ለመስራት እንጨርስ እኛ

ሰይፈ ተማም 2010
ከመሬት ነኝ

መሬት አይደል መነሻዬ
መሬት ያጣሁ መሬት ሁኜ
መነሳትን ተጠይፌ
የወደቅኩኝ ተንሳፍፌ
እኔም ራሴ መሬት
ለመብቀያ ያበቀለኝ
ከመሬት ነኝ?
ከምሬት ነኝ?
ከምር የት ነኝ?

ቁንጥር አፈር ዘግኖ በእጁ ካበጃጀኝ
ቁንጽል አንቀጽ ጠቅሶ በእጁ 'ሚያስፈጀኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከመሬትም መሬት
ሲረማመዱብኝ እንቁዬን ደብቄ በቀን እኩለ ሌት
ሲዘንብ እምቦካ የቋጠርኩኝ አለት
ሲያርሱ 'ምበረበር
ሲበትኑ 'ምዘር
የማያዳብረኝ የሰጡኝ ምርጥ ዘር
አለቴን ገድዬ 'ማረገው አፈር
ጨረቃን ጋርጄ ፀሃይ የምሰፍር
ፀሃይ በዛ ብዬ ደሞ ምንጨረጨር
ህዋ ላይ ተጥዬ የማርፍበት የናፈቀኝ
አዎ መሬት ያጣሁ መሬት ነኝ

ቀማሽ ምላስ ሰጥቶ ጣ'ም 'ሚያስቆጥረኝ
ጣፋጭ ስኳር ነስቶ በጨዉ ሲያስመርረኝ
መሆኔ አይደለም ወይ ከምሬትም ምሬት
ወዳጄ ስሞታ ወዳጄ ጣ'ም ሃሞት
የማያጣኝ ከቤት
የማያጣኝ ከሬት

ብሶት የወለደው ብሶ ያንገሸገሸኝ
ጣ'ም ያጣሁ ምሬት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት

መሬት ምሬት ምርየት

መሬቱ ሰው አለው
አለው የሰው ኩሩ
'ራሱን እማይነጥል
ከዱሩ ከአፈሩ
ሲጠብቃት ኖሮ
ከሷው ነው አዳሩ
ይኸም ሰው ጨፍግጓል
መረሮታል ጠአሙ
መጣፈጥ ጠፍቶታል
መልኩም ሆነ ስሙ
ለአንድ ቡሃቃ ሊጥ
20 ሺ እያሰሙ
ከምር ወደየት ነው
ከየት ወየት መንገድ
(ከሰከሩም እንኳን)
አይቶ ገምቶ ነው
ኋላ መንገዳገድ
ወይ የሚያቅፉ መስሎ
ትከሻ መላመድ
ወይ እራስን መብላት
ከመሬት መዋደድ
የምን ቆሞ መሄድ
የምን ሄዶ መቆም
በራስ ቤት መታሰር
ቂም ይዞ እንደመፆም
ለመዋደድ ነቅቶ
በፍቅር ነው መሾም
እንዳሹት ከምታሽ
እንደ ደማከሴ
የት እንዳለሁ ሳላውቅ
አድር ይሆን ፈውሼ?

ያለት ስንጣሪ
ከምድር የቀረፀኝ
ቅምሻ ፍርፋሪ
ኮምጥጦ አገረሸኝ
አይኔን አስጨፈነኝ
ኸረ ከምር የት ነኝ?

ታውሮ ሚመራው
መንገዴን ነጠቀኝ
እኔጠፋሁ ልበል
ካለሁስ ወዴት ነኝ
አገር ማለት መሬት
አገር ማለት ምሬት
አገር ማለት እኔ
ተምታቶብኝ ድንገት
... ሆኜ ካለሁበት

ሰይፈ ተማም 2010
👍1
በጾሙ

ልቤ ጠረጠረ ነገር ነገር አለኝ
ከተኩሎቹ መሃል ፍየል ቢጤ ባገኝ
ስጋዋም ወተቷ መድሃኒት ነው አሉ
ዘምዘም እጠጣለሁ ሲያሻኝ ከጠበሉ
ወይ እታከማለሁ ደሞ በዶክተሩ
ልቤ እንዲጠራልኝ እንዲቀለኝ ቂሙ
እላለሁ ተኩሎቹም አብይን በጾሙ
አብይን በጾሙ አብይን በጾሙ

ሰይፈ ተማም 2010