ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሁለት የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባላት ኮብልለው ፋኖን ተቀላቀሉ::

የአብይ አህመድ ስርዓትን የተቀዋወሙ ሁለት የመከላከያ አባላት ለአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀ/አሳምነው ኮርሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ክ/ጦር በመቄት እጃቸውን ሰጥተዋል።

በክፍለ ጦሩ ህግ ክ/ኃላፊ አርበኛ አንደበት በየነ አቀባበል የተደረገላቸው የ65ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ የመከላከያ አባላት ለፋኖ እጅ መስጠታቸው እና በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው አብዛኛው ሰራዊት በስርዓቱ እኩይ ተግባር እንደተማረረም ገልፀዋል። የመከላከያ አባላቱ በግድ ተጋፎ የገባው ሰራዊት እየፈረሰ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ለመቀላቀል እንደወሰነም ገልፀዋል።

የሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ክ/ጦር አዛዥ ኮማንዶ አማን ጎበዜ አሁንም በአፓርታይዱ ስርዓት ውስጥ ሆነው የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፉ ላሉ አካላት ከፋሽስቱ ወንበር አስጠባቂነት ወጥተው ወደ ትክክለኛው የፋኖ ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 14/2018 ዓ.ም
🙏1
የግንባር መረጃዎች - አፋብን ታላላቅ ውሳኔዎች አሳለፈ | በመርሳ 100% ስኬታማ የRPG ጥቃት | የዲያስፖራው ማህበረሰብ የደስታ መግለጫ
👍1
ሰበር የድል ዜና

የአገዛዙ  የብልጽግና  ሰራዊት /እራሱን ጥምር ብሎ የሚጠራው  የአብይ ምስለኔ  በኮረማሽ ንዑስ ወረዳ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሰምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር ስር ያለችው ሰላምሰው ሻለቃ ላይ በምትንቀሳቀስበት አካባቢ ከበባ ለመፈፀም ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።

የእግዚአብሔር  አብ የንግስ ክብረ በአልን አስመልክቶ በ13/05/18 የህዝብ ክብር በዓል በሚያከብሩበት የንግሥ ቦታ የዘወትር ክህደቱንና ሀገር በጥባጭነቱን ለመፈፀም ቢሞክርም በኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በሻለቃ 3(ሰላም ሰው) በተደረገበት ከፍተኛ ፊልሚያና ትንቅንቅ የንግሥ በአሉን ፋኖዎች ማሥከበር ችለዋል።

በዚህ አውደ ውጊያ አልሳካለት ሲል በ14/5/2018 በቀጥታ ከቱለፋ እና ከሀገረማሪያም ወረዳ  ያለ የሌለ የሚሊሻና የመከላከያ ምንጣፍ ጎታች  ሀይሉን አግበስብሶ  ከንዑስ ወረዳ ከሆነው ከሰም ኮረማሽ በእምዬ ሚኒሊክ የጦር ግምጃ ቤት ካምፕ ያለውን ጦር ጭምር በማሰለፍ በ3 ግንባር ማለትም በወይን አምባ, በሸረርና በሰወሥት አምባ የጦር ግንባሮች ወረራውን አድርጎ በሞርተር እና በድሽቃ የታገዘ ጦርነት ቢከፍትም አልሳካ ሲለው የዘውትር የዘረፋ ተግባሩንና መንገድ ላይ የተገኜ አርሶ አደር በመደብደብና በማሰር የማህበረሰብ ንብረት እንደ በርበሬ፣ ሽሮ፣ እንቁላል፣ ልብስ፣ ስልክ፣ ጫማ፣ አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ በግድ አርሶ አደር አስገድደው 10,000  ሽህ ብር ዘርፈውና ይህን ግፍ ፈፅመው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት  ተመልሷል።

በሌላ ግንባር የኮረማሹን ውጊያለማስቀየስ ወደ ዛላ ዘባባ ከሀገረማሪያም ቀረውን የብልፅግናው ዙፋን አሥጠባቂ ሰራዊት አሰልፎ ቢቀሳቀስም በቀጣናው በነበሩ አባት አርበኞች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ የተመለሰ ሲሆን:- በዚህም ውጊያ አንድ የሚሊሻ አባል የሆነውን ስሙ ጌታሁን ተረፈ የተባለውን ባንዳ እረምጃ ተወስዶበታል።

  ኃልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር
                      ሪፖርተር ክፍል
🙏2
የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት አባይዳር ላይ ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናገደ!!!

በትናንትናው እለት ጥር 14/2018 የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን ቋራ ወረዳ ደለጎ እና በሙር ከተማ በማድረግ ወደ አባይ ዳር እንቅስቃሴ ላይ ባለበት ወቅት አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ፣ ካራማራና ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦሮች ከኮሩ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ አየልኝ ጋር በመሆን በጋራ በሰሩት ወታደራዊ ኦፕሬሽን አባይዳር ላይ የአገዛዙን አረመኔ ፀረ አማራ ሰራዊት መውጫ መግቢያ በማሳጣት በነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች ሽንፈትን ከማስተናገዱ ባሻገር ተተኳሾችንና የእጅ ስልኮችን በየ ቦታው እየጣለ ወደ አባይዳር ከተማ ፈርጥጦ ገብቷል።

በዚህ አውደ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 12
ቁስለኛ = 18
ከ600 በላይ የብሬን ተተኳሽ እና በርካታ ቁጥር ያለው የእጅ ስልክ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥር 15/2018
🙏1
የ206ኛ ኮር ህግና ስነ-ስርዓት ክፍል ለ14ኛ ክ/ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባላት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ

የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህግና ስነ-ስርዓት ክፍል በተሻሻለው የድርጅቱ ህግና ደንብ መሰረት የፀደቀውን የህግና ስነ-ስርዓት መመሪያ ሰነድ ለሰራዊቱና ለዓመራሩ በማቅረብ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

ኮሩ በሚመራቸው ክ/ጦሮች ባሉ ሻለቃዎች የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ተሳታፊ በማድረግ እየተሰጠ ባለው ስልጠና ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከልና ወንጀለኛን ተጠያቂ በሚያደርጉ የህግና ስነ -ስርዓት ጉባኤ ወንጀለኛ መቅጫ ድንጋጌዎች ዙሪያ ለሰራዊቱ በተፈጠረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአመራሩ እና በሰራዊቱ መካከል የነበሩ የአሰራር ግልፀኝነትን እንደሚቀርፍ ታውቋል።

ትግሉን ወጥ በሆነ ድርጅታዊ የህግ ድንጋጌ መምራትና ማስተዳደር ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በህግ አግባብ መቆጣጠር ከማስቻሉም ባሻገር የሚሰጡ ስልጠናዎች ሰራዊቱን በግብረ ገብነትና ዲስፒሊን ለማነጽ  እንደሚረዳ ተገልጿል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!

የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

@ባየ ደስታ
🙏1
"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ"

፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል።

የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሁነን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፋና በደል ተመልክተናል ያሉት የጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ስርዓቱን ለቀው ትግሉን ለመቀላቀል እንቅፋት እንደሆነባቸው የተናገሩ ሲሆን ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአንድነት ብስራት ተከትሎ በግንባር ቀደምነት ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግራችን ተጉዞን ጎጃም ገብተናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ  አዛዦች ጥሪ አቅርበዋል።

የአረመኔውን ስርዓት በተቀናጀ መልኩ እያፈረሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር 61ኛ ክላሽ ከጠላት የተቀበለ ሲሆን የሰራዊት አባላትን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

@የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ባየ ደስታ
1🙏1
60 የሚሊሻ አባላት 2ብሬንና 45 ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ።

አንድነቱ በተበሰረ ማግስት በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየፈራረሱ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቀጠናዎች ብልፅግና ሲያሳድዳቸዉ የነበሩ ኃይሎች ታጥቀዉ ራሳቸውን ከአረመኔዉ መንግስት ጥቃት ሲከላከሉ የቆዩ፣ በመተከል አዉራጃ ዳንጉር ወረዳ በሻለቃ ሲሳይ ገነት ሲመሩ የነበሩ 60 የአገዉ ተወላጅ ወንድሞቻችን አባላትና መሪዉ ሻለቃ ሲሳይ ገነት በቀን 14/05/2018 ዓ.ም 2 ብሬን እና ከ45 በላይ ክላሽንኮቭ በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦርን በመቀላቀል አረመኔዉን የአብይ አህመድ መንግስት ስርዓት በማዉገዝ እስከመጨረሻው ለማስወገድ ቃል መግባታቸውንም አስታዉቀዋል።

በተመሳሳይ

1ኛ) ከድር አብዲ
2ኛ) ገመቹ ገመዳ
3ኛ) ሀይሉ ሙንየ እንግዳ
4ኛ) ምኒችል ቡችል ፀጋ ከ601ኛ ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር እና 6ኛ ዕዝ 605 ኮር 14ኛ ክፍለ በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅሉ ሲሆን
5ኛ) ጌታው መሌ
6ኛ) ታደሰ ደሴ የሚባሉ ምሊሻዎች ደግሞ ከሸበል በረንታ በመውጣት 201ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።

ጋንታመሪዎች የፋኖን አንድነት ሲሰሙ በዛሬው ዕለት እየተቀላቀሉን ይገኛሉ።
፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል።

ብልፅግና ካንፕ ያለው ሙሉ በሙሉ እየፈራረሰ ይገኛል። ቀሪዎችም በቡድን ፋኖን ለመቀላቀል ምቹ ሁኔታ እየጠበቁ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። በብልፅግና ቤትም ፍፁም መተማመን በመጥፋቱ እየተረበሸ ይገኛል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏1
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል ገዳሙን አጃቢ ጨምሮ አራት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቀሉ::

የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር አመራር የሆነው ኮሎኔል ገዳሙ አጃቢ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ በመያዝ እና 83ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ የሆነው ሌላኛው አባል እንዲሁም ሌሎች ሁለት ሶስት ክላሽ በመያዝ ባጠቃላይ አራት የአገዛዙ ወታደሮች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

በተመሳሳይ ዜና
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::

የ35ኛ ክፍለ ጦር እንደጉም ተበትና አልቃለች። ከተለያዩ አሀዶች አውጣቶ ኮማንዶዎች ቢያመጣም ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሶስት የሰራዊቱ አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል።

በሌላኛው ግንባር ደግሞ
ስምንት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::

የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት "አፋብን" መመስረትን ተከትሎ ስምንት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

የፋኖን አንድ መሆንና የመሪ ድርጅቱ አፋብን መመስረትን ተከትሎ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በሰፊው ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን ስምንት አባላቶቹ ሰባት ክላሽ፣ 1400 ተተኳሽ፣ ሰባት የወገብ ትጥቅና ስድስት F1 ቦምብ ይዘው ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
🙏1