ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ፅናት ክፍለ ጦር ከአማራ ፋኖ አንድነት ማግስት በርካታ የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር በጥላት ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድና ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ጥር 12/2018 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ እንጥጉና ቀበሌ ላይ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:30 በዘለቀ አውደ ውጊያ በብርሀኑ ጁላ የሚመራው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ከ29 በላይ የተደመሰሰ ሲሆን ከ47 በላይ ቁስለኛ ተደርገዋል።

ከጉባላፍቶ ወረዳ ኩረታ፣ከተንታ ወረዳና ከደላንታ ወረዳ በገፍ አሰባስቦ በሶስት አቅጣጫ የመጣን የፋሽስቱን ሰራዊት መቀበሪያው የእንጥጉና ተራራዎች ሲሆኑ በህይዎት የተረፈው ወደየመጣበት ተመልሷል::

በምርኮኛና በጥቅመኛ የሚመራው የፋሽስቱ ሰራዊትን የፅናት ክፍለጦር ክንደ ብርቱ ፋኖዎች ከበባ ውስጥ በማስገባት ለጅብ እራት አድርገዋቸዋል። ከፋኖዎቹ የደረሰበትን የተጠናከረና ረዝም ሰዓት የፈጀ ድብደባ መቋቋም የተሳነው የፋሽስቱ ሰራዊት አዳሩን አመራሮቹ ራስህን አውጣ የሚል ትዛዝ አውርደውለት ወደየመጣበት ፈርጥጦል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 13/2018 ዓ.ም
🙏3
የፋኖን አንድነት በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮችም ጭምር ናቸው።

ፋኖ አንድ ወጥ ድርጅት መስርቶ አንድነቱን ባወጀ ማግስት የአገዛዙ ጦር በገፍ እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል።

የፋኖን አንድ መሆን በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው በመከራ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብና ሌሎች የዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር ብልፅግና አገዛዝ ተጠቂ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ አገዛዙን እያገለገሉ የሚገኙ ወታደሮችና ወታደራዊ አዛዦችም ጭምር ናቸው።

የአገዛዙ ወታደሮች በጉጉትና በተስፋ ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት የብስራት ዜና መሰማቱን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው::

ኦፕሬተር ምድብተኛው እና ም/አስር አለቃ አመራሩ በጎጃም ግንባር ፋኖን  ተቀላቅለዋል።

በስቦ ማስከዳት ጥር13/2018 ዓ.ም
ስንጠብቀው የነበረው አንድ ድርጅት እና መሪ በመመረጡ በርካቶች በቀጣይነት እንደሚቀላቀሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

በዚህም:-
1ኛ) ም/አስር አለቃ አብዱ ማርቆስ … 25ክ/ጦር … ክላሽ
2ኛ) ራቡማ ነጋ ... 25ኛ ክ/ጦር ከቢቡኝ ወይንውሃ 54ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን
3ኛ) አብዲ አህመድ ... 75ኛ 02 ሬጅመንት 4ኛ) ወንዴ ሀብቴ ..… 75ኛ 02 ሬጅመንት ወደ 74ኛ ክ/ጦር ፋኖን ተቀላቅለዋል።

የአገዛዙን ቅጥረኛ አባላት በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ የሚፈፅመውን ዝርፊያና እንግልት በመቃወም ፋኖን ተቀላቅለዋል።

@አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር  ሕዝብ ግንኙነት
🙏31
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮ የመጀመሪያ ስብሰባውን አደረገ።

ጥር 09 ቀን 2018 ዓ. ም በይፋ መመስረቱ የተገለፀው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል።

የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላለፉት 30 ወራት በነበረው የትግል ሂደት በነበሩ የእርስ በእርስ ሽኩቻወች እና አለመግባባቶች እንዲሁም የአደረጃጀት ልዩነቶች ምክንያት ለተፈፀሙ ጥፋቶች የእርስ በእርስ የይቅርታ መርሀ ግብር በማከናወን ውይይቱ ተጀምሯል።

በፍፁም መተማመን እና ጓዳዊነት የተጀመረው ውይይትም የድርጅቱ ቀሪ የአመራር መዋቅር ስለሚዋቀሩበት ሁኔታ፣ የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) ያቀረበውን የአደረጃጀት ጥያቄ፣ የቀጠና እና የዕዝ ስያሜወችን በተመለከተ፤ የሰራዊት እና የነባር ዕዞችን ውህደት እንዲሁም የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ፍኖተ ካርታ ዝግጅትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርጎ የስራ መመሪያወችን ሰጥቷል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏7
በቅንነት ለተነሱ ጥያቄዎች ብሎም በተመሰረተው አንድነት የበገኑ ልዩነት ፈጣሪዎች ላነሷቸው እርባናቢስ ሃሳቦች የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ አመራሮችሁነኛ ምላሽ ሰተዋል::

የእዙ ከፍተኛ አመራሮችሳርበኛ ራስ ደረጀ በላይ : ኮሎኔል አበራ አዛናው እና አርበኛ ሰለሞን አጣናው በተንቀሳቃሽ ምስል በታገዘ መግለጫቸው ለትግሉ ደጋፊዎች በሳል ማብራሪያ ሰተዋል:: ለክርስትና እምነት ተከታዮች የ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ የጀመሩት አመራሮቹ ለተፈጠረው አንድነትም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል:: እስካሁን በተናጠል በመቆየታችንም ይቅርታ እንጠይቃለን ነው ያሉት::

የድርጅታችን አፋብን መሪዎችን ከአራቱም አቅጣጫዎች ተወያይተንና መክረንበት ሁሊም በአቅሙና በልኩ እንዲቀመጥ አድርገናል ያለው አርበኛ ራስ ደረጀ በላይ ለዚህም ያለምንም ሽኩቻና ሴራ የተፈፀመ ነው ብሏል:: በኛ የተነሳ ተለያይታችሁ ነበር : እኛ አንድ ስንሆን መሬት ላይ ያለው ህዝባችንም ሆነ ውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችንም አንድ ሊሆኑ ይገባል ሲል መልእክት አስተላልፏል::

ማጣት የሌለብንን አርበኞች አጥተንና ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለን ያመጣነው አንድነት ነው ያለው አርበኛ ሰለሞን አጣናው ቓላችንን ለመፈፀመ ለድርጅታችን የሚመጥኑ ሰዎችን መድበን እኛም ከሰራዊታችን ጋር ሆነን ለማዋጋት ያሳለፍነው ውሳኔ ነው ብሏል:: በመሆኑም ሁላችሁም ከመንደርተኘነትና ጎጠኝነት እንዲሁም ከመበሻሸቅ ወጥታችሁ ድርጅታችንን እንድትደግፉ ሲል ጥሪ አቅርቧል:: ኣማርኛ መናገርና ስለሚፅፉ ብቻ ሊከፋፍሉን የሚሞክሩ ፀረ አማራዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲልም አሰጠንቅቋል::

አንድ ሳንሆን በመቆየታችን በህዝባችን ላይ ለደረሰው በደልና እልቂት ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል የጀመረው አርበኛ ኮሎኔል አበራ አዛናው በምርጫ የሚያታግሉንን ሰዎች የሰጠን ሲሆን ትልቁ ስራ ከታች ያለውን አደረጃጀት መስራትና ጦሩን ማደራጀት በመሆኑ በማሰልጠን : በመገንባትና ከላይ የሚዎርድ ተዛዝን በመቀበል ግዳጃችንን ለመወጣት እንሰራለን ብሏል::

ለጠላት መርዶ ለወዳጅ አንጀት አርስ የሆነው የአማራ ፋኖ አንድነት ከተመሰረተ እነሆ 4ኛ ቀን ተቆጥሯል::

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ !
🙏41
ከጋሸና ወደ ፍላቂት ሲንቀሳቀስ በነበረ እራሱን አድማ ብተና እያለ በሚጠራ ሰራዊት ላይ አንሻ ክፍለ ጦር ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ::

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በአንሻ ክፍለ ጦር ቃኝ ሻለቃዎች! በጥላት ሰራዊት ላይ በተጠና የደፈጣ ኦፕሬሽን በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል!

የአማራን ህዝብ ክዶ በሆዱ እየተገዛ ባለው እራሱን አድማ ብተና እያለ በሚጠራው የአረጋ ከበደ ሰራዊት ላይ ጥር 13/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ ወቄታ ላይ በተወሰደ እርምጃ ዘጠኙ ሲደመሰሱ ሰባት ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።

ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት በዘለቀ ውጊያ የፋሽስቱ ወበር አስጠባቂ ሰራዊት አካል የሆነው አድማበትን ሙት ጓዱን ሳያነሳ ወደ ፍላቂት ከተማ ፈርጥጧል።የአማራን ህዝብ በባንዳነት ባህሪው ከፋሽስቱ የአብይ ሀይል ጋር አብሮ ሲወጋና ሲያስወጋ በነበረ አካል ላይ ተጠናክሮ እየተወሰደ ባለ ኦፕሬሽን በወቄጣ ዳግም ተደግሟል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 13/2018 ዓ.ም
🙏2
ደጀን ክፍለ ጦር እስታይሽ ከተማ ዙሪያ ጠላት ላይ ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ድል አስመዘገቡ::

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በደጀን ክፍለ ጦር እስታይ ከተማ ዙሪያ በርካታ የጥላት ሰራዊትን እምሽክ ተደርጓል!

ጥር 13/2018 ዓ/ም መነሻውን ከጋሸና አድርጎ ሲግተለተል በነበረ በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ በተደረገ ሽኝት ደማቅ ታሪክ ተሰርቷል!

ደጀን ክፍለ ጦር ፅናት ሻለቃ አድስጌ በተባለች ቦታ ላይ የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት የአማራን ህዝብ ሊጨፈጭፍ የመጣውን የጁላን ሰራዊት በ11 እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በአስራ ሶስቱ ላይ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል:: ምንም እንኳን ጠላት እንቅስቃሴው በዙ-23 ታጅቦ ቢሆንም ቅሉ ከፋኖ ባሩድ ፈፅሞ እራሱን ሊታደግ አልቻለም።

ስለሆነም በደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በተለያዬ ቦታ ላይ በደረሰበት መራር በትር የተነሳ በማንኛውም ቦታ በንፁሀኖች ላይ "አማራ ናችሁ ብያለሁ አማራ ናችሁ" በማለት ወጣቱን እየገደለና እየደበደበም የውርድንብር ፍርጠጣውን ተያይዞታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 13/2018 ዓ.ም
🙏3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛው ድርጅታዊ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት:-

፩) የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ፖሊት ቢሮው አርበኛ እስክንድር ነጋ ያቀረበውን ማመልከቻ መርምሯል። በዚህም አርበኛ እስክንድር በግለሰባዊ ችግር ምክንያት ድርጅቱ በመደበበት የኃላፊነት ቦታ ላይ መቀጠል እንደማይችል ይልቁንም በድርጅት አባልነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑን እና የሚጠበቅበትን ሀላፊነቶችና ግዴታዎች በሙሉ እንደሚፈፅም ጠቅሶ ያቀረበው ጥያቄ በነፃ ፈቃዱ እና ፍላጎቱ የቀረበ መሆኑን ፖሊት ቢሮው አረጋግጧል።

ሆኖም ግን ማመልከቻው ለፖሊት ቢሮው በደረሰበት ቅፅበት ለሚዲያ የወጣበት መንገድ የድርጅቱን አሰራር የሚጥስ እና ያልተገባ ትኩረት ለማግኘት የተደረገ መሆኑን ፖሊት ቢሮው ገምግሟል። ግለሰቡም ማመልከቻው ከአሰራር ውጭ በሚዲያ በኩል ይፋ መደረጉ ስህተት መሆኑን ላነጋገሩት የፖሊት ቢሮ አባላት አሳውቋል። እንዲሁም የድርጅታችን ምስረታ ይፋ በሆነ ማግስት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳዮች እያሉ ይህ ጥያቄ  መቅረቡ ግዜውን የጠበቀ አለመሆኑን አምኖበት በቃል ይቅርታ ጠይቋል።

በመሆኑም አሳማኝ ምክንያቶች ካሉም እንኳን ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ ሲገባው ከሌሎች አስቸኳይ የህልውና አጀንዳ በላይ ይህ ጉዳይ የድርጅቱ የመጀመሪያ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ ፖሊት ቢሮውን ያሳዘነው ቢሆንም ግለሰቡ በአባልነት ብቻ ለመቀጠል ያቀረበውን ማመልከቻ ፖሊት ቢሮው ተቀብሎታል። ፖሊት ቢሮዉ ለአርበኛ እስክንድር ተሰጥቶ በነበረው የኃላፊነት ቦታ ላይ ሌላ ሰው የሚተካ ይሆናል።

፪) የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ውክልና እንዲኖረው ወስኗል።

፫) በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ በተጠቀሰው መሠረት የአባት አርበኞች ምክር  ቤት መዋቅር እንዲቋቋም ውሳኔ ተላልፏል። ዝርዝር ጉዳዩን በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ላቀረበው ጥሪ የጋምቤላ  ታጣቂ ኃይሎች ጥምረት ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ እንደሚሠራ አሳውቋል።

ይሄ ታጣቂ ኃይል ጋምቤላ ክልል ከማጃንግ እና ጋምቤላ ከተማ ውጭ ያሉ 3 ዞኖችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ኃይል ነው።

በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አካባቢዎች እና ህዝቦች ፀረ ብልፅግና ትግል ለማድረግ ለጀግናው የአማራ ፋኖ ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት ተዘጋጅቷል ።

አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ፀረ አማራ የሆኑ የትርክት ፣ የሐይል ፣ የፖለቲካ አቋሞችን በመቀየር ሁሉም ሐይሎች ፣ ሁሉም የፖለቲካ ትግሎች ፣ ሁሉም ትርክቶች ፀረ ብልፅግና እንዲሆኑ አድርጓል ።

ገና የደረሰብንን ውድመት በበቂ ሳናስረዳ ፣ ገና ያለንን ሰፊ መልካአምድር ሳንጠቀም ፣ ገና ያለንን የተፈጥሮ ሐብት ለትግሉ ማዋል ሳንጀምር ፣ ገና ሚሊዮን ወጣቶችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ሳናስታጥቃቸው ፣ ገና ዕውቀታችንን እና ጥበባችንን ፍልስፍናችንን ከተፈጥሯዊ ጀግንነታችን ጋር ሳናጣምራቸው ጠላቶቻችን የቆሙባቸውን የህልውና ምሰሶዎች አፍርሰን ፣ የገነቡትን ሁለንተናዊ ፀረ - አማራነት ደርምሰን ለድል እየበቃን ነው ።

ማሳሰቢያ :- ትግሉ አብይን ከመጣል ባሻገር ረጅም የትውልድ ቅብብሎሽ በአዳዲስ ተለዋጭ ስልቶች እየተመራ እስከ ዓለም ፍፃሜ ይቀጥላል ።

@መረብ ሚዲያ
🙏2