ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ዋግሹም ብርጌድ በሆድ አድር ሚኒሻ እና ፖሊስ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፈ!!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ዋግሹም ብርጌድ አማራነታቸዉን በምስር ወጥ በሸጡ ፖሊስ እና ሚኒሻ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።

መነሻዉን ዋግህምራ ዞን ድሃና ወረዳ አምደ ወርቅ አድርጎ ዋግሹም ብርጌድን አፍናለሁ ብሎ ቢመጣም ጀግኖቹ የሃይሉ ከበደ ልጆች አባም አቦ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ሲቀጠቅጡት ዉለዋል።

ዉጊያዉም ዛሬ ማለትም ጥር 3/2018 ዓ.ም ከ ጧቱ 2:00 - 8:30 የፈጀ ሲሆን በዚህም 20 ሚኒሻ እና ፖሊስ እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ 15 የሚሆኑ ባንዳዎችን ምርኮ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 37 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏2
የተማረኩ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ወደ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል ገቢ ተደረጉ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወግድ እና ከላላ ወረዳ ውስጥ ባለፉት ቀናት በሰራው ኦፕሬሽን በርካታ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን መንገድ መሪዎቹ የሆኑት የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ተማርከዋል:: ፋኖን እናጠፋለን ብለው ከጠላት አብረው ሌት ተቀን ንፁሀን ወገኖቻችንን ሲገድሉ እና ሲያስገድሉ ከርመው በስተመጨረሻ እጃችን ላይ ወድቀዋል:: እነዚህ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች አሁን ላይ የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን በስልጠናው መሀል አስተያየታቸውን የለገሱት በጥቅሉ የተናገሩት እስካሁን በሄዱበት መንገድ እና በፈፀሙት ድርጊት እጅጉን እንደተፀፀቱ ነው::

ምርኮኞቹ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል የሚሰጣቸውን ስልጠና እንዳጠናቀቁ ወደ ማህበረሰቡ ይመለሳሉ ተብሏል:: ፋሽስቱ አብይ አህመድ አማራን በአማራ ለማስመታት የሚያደርገው ጥረት አካል የሆነውን ፕሮጀክት ለማሳካት ደፋ ቀና የምትሉ የፀጥታ ኃይል አባላት በአስቸኳይ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ ሲል ኮሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህን ጥሪ ባለመቀበል ከጠላት ጎን የተሰለፉት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል::


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2
ከደሴ በስተምዕራብ ወግድ ወረዳ ውስጥ ንፁሃን አማራዎች በፋሽስቱ አብይ ሰራዊት ተረሸኑ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የፋኖ ኃይል በሰነዘረበት ጥቃት ታህሳስ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በርካታ አባላቱን ያጣው የጠላት ኃይል አፀፋዊ ምላሽ በሚመስል መልኩ ንፁሐን ላይ አሰቃቂ እርምጃ ወስዷል::

በዚህ የጠላት የጭካኔ እርምጃ ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣት አስማማዉ (ቀዮ) ተረሽኗል:: ወጣቱ ወግድ ከተማ ውስጥ አሳንቡሳ እና ቦንቦሊኖ በመጥበስ ይተዳደር የነበረ የሁለት ልጆች አባት ነው:: ለአስማማው እና መሰል ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ፈንታ መንግስት ተብየው አካል በየዕለቱ ነፍሳቸውን እየቀጠፈ ነው::

ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ወግዲ ከሀይስኩል አለፍ ብሎ የአምላኬ ካብ የተባለ ስፍራ ላይ አረቡ አህመድ የሚባል ወጣትን የብልጽግና ታጣቂዎች በግፍ እረሽነውታል:: ደረሳውን የረሸኑት የፋኖ መረጃ ነህ ብለው ነው::

ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እሮቢቴ የሚባል አካባቢ የደቡብ ወሎ ዞን ፓራ ኮማንዶዎች ሌሊት 10 ሰአት ተነስቶ ከመካነሰላም ወደ ወግዲ ይጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ላይ ተኩስ ከፍተው እረዳቱን ሲገድሉት ሹፌሩ ከባድ ቁስለኛ ሆኗል::

ይህም ብቻ አይደለም ከወር በፊት አንድት ለወሊድ ወደ ጤና ተቋም በተሽከርካሪ እየተጓዘች የነበረች እናትን እረሽነዋል::

በወረዳው ውስጥ ሰኮሩ ቀጠና ሼህ ያሲን የተባሉ ታዋቂ የኃይማኖት አባት እና ሌሎች ደረሳዎች ከዚህ ቀደም በጠላት ተረሽነዋል:: በአበየ ጉርባ ቀጠናም በገዛዛ አቦ መውጫ በኩል አንድ ቄስ እና ሌሎች ንፁሓን በግፍ ተረሽነዋል::

በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ወንጀል እየፈፀመ ያለው የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ መንግሥት በየጊዜው የንፁሓንን ደም እያፈሰሰ መሆኑን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር ይገነዘብ ዘንድ በሚዲያ፣ ዲፕሎማሲ እና አድቮኬሲው ዘርፍ ሁሉም የአማራ ልጅ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚችሉትን ያደርጉ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
💔1
"አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!"

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ያስተላለፈው መልዕክት!!

የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋን ተከትሎ ለህዝባችን የደህንነት ዋስትና ለመሆን ዱር ቤቴ ብለን ጠብመንጃ አንስተን ወደ ጫካ እና በርሃ የገባነው ህዝብን የማዳን አላማን አንግበን መሆኑ ይታወቃል። በበኩላችን የምንሞትለትን አላማ ጠንቅቀን ስለምንረዳ ይህን አላማ ለማሳካት የሚያስችል ፅናት ተላብሰን ትግላችንን ቀጥለናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅርብ ወራጆች ደግሞ በየተራ ወደ ጠላት እየገቡ መሆናቸውን ታዝበናል።

ትግል ያለ አላማ እና ፅናት እንደማይሰምር ሁሉ፤ አላማ ቢስ የሆኑ ልፍስፍሶች ወደ ጠላት ሲገቡ ልንረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር የትግሉ ሜዳ እየፀዳ መምጣቱን ነው። በትግሉ ሜዳ ላይ በፅናት መቆየት የሚችሉት አላማ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባል። አላማ ከሌላቸው ብዙኃን ይልቅ አላማ ያላቸው ጥቂቶች ለድል ይበቃሉ። የአማራ ህዝብ አሁን ላይ እየሆነ ባለው ነገር ሳይደናገር እና ሳይደናገጥ በእኛ በልጆቹ ሙሉ እምነት እንድኖረው የምናሳስበው የፀና ህዝብ አሸናፊ እንደሚሆን ስለምናውቅ ጭምር ነው። የትግሉ ሂደት መሰናክል የበዛበት መሆኑን አምነን መሰናክሎችን ሁሉ በፅናት ለማለፍ ቆርጠን እንደ ህዝብ መነሳት ይገባናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አማራዊ አንድነታችንን ማንበር ስንችል እና የጋራ መግባባት ላይ ስንደርስ ነው።

ባቡሩ ሲጓዝ በየፌርማታው የሚወርዱ ተሳፋሪዎች እንደሚኖሩ ተገማች ነው። ይህን ትግል እንደ ባቡር ቆጥረነው በየፌርማታው የሚወርደው ተሳፋሪ ጉዳይ ሊያሳስበን እንደማይገባ ለማስታወስ እንወዳለን::

በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር ወደ ጠላት የሚገቡ አካላት ለክዳታቸው እንደ ሰበብ የሚቆጥሩት በዋናነት ጌቶቻቸው የሚሰጧቸውን አጀንዳ መሆኑ ነው። ስለዚህ እነሱ ከጅምሩ የጠላት እንጅ የእኛ አልነበሩም ማለት ነው። የጠላትን አጀንዳ ከጠብመንጃ ጋር ተሸክመው ላይ ታች ሲሉ የነበሩ ስለሆኑ እነሱ ቢመጡ ቢሄዱ ምንም ሊደንቀን ሊጨንቀንም አይገባም።

ጥርሳችንን ነክሰን በመታገል የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈልን ለአማራ ህዝብ የደህንነት ዋስትናዎች ለመሆን እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ ቆርጠን የተነሳን በመሆናችን እስከመጨረሻዋ የድል ብስራት ከአላማችን ዝንፍ እንደማንል እያረጋገጥኩኝ "አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!" እንድሉ አበው እኛም ምንም አይነት አጀንዳ ቢወረወር ከጠላት ጎን ልንሰለፍ እንደማንችል እሙን ነው።

ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ
የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
3🙏2
ሰበር ዜና!

ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ ዋግሹም ብርጌድ 46 የአገዛዙን ፖሊስና ሚሊሻ በመደምሰስና 58 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር አካል የሆነው ዋግሹም ብርጌድ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ድሃና ወረዳ 010 ቀበሌ አባም አቦ ቀጠና ጥር 03/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅ የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂ የሆኑትን የድሃና ወረዳ ፖሊስና ሚሊሻ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።

መነሻውን ከድሃና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ወደ 010 ቀበሌ አባም አቦ ቀጠና በመንቀሳቀስ ዋግሹም ብርጌድ ፋኖዎችን አፍናለሁ በሚል የተንቀሳቀሰው የወረዳው ፖሊስና ሚሊሻ አባላት መረጃው ቀድሞ የደረሰው የብርጌዱ ወታደራዊ መረጃ ክፍል ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ሊያፍን የመጣውን የጠላት ኃይል በተቃራኒው ከበባ ውስጥ በማስገባት አንድም ኃይል ሳይቀር እንዲደመሰስ፣እንዲቆስልና እንዲማረክ ተደርጓል።

በዚህ አውደ ውጊያ 46ቱ ሲደመሰስ፣29ኙን በማቁሰል ሁለት አመራሮችን ጨምሮ 24ቱ ሊማረኩ ችለዋል። በተያያዘም 32 ክላሽንኮፍና 16 የቃታ መሳሪያ በድምሩ 48 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣2860 ተተኳሽ፣56 የወገብ ትጥቅ ተማርኳል። ከምርኮኞቹ መካከልም የድሃና ወረዳ ፖሊስ ምርመራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር ሸጋ አያናውና የድሃና ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ምስጋናው ይገኙበታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4/2018 ዓ.ም
4🙏1
ሰበር ዜና

ከ5 በላይ አጎራባች የወረዳ ህዝብ በሚሳተፍበት የወልድያ ከተማ ታላቅ የገበያ ቀን የአገዛዙ ሃይል የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ነው::

በዛሬው እለተ ማክሰኞ በወልድያ ከተማ የገበያ ቀን ቢሆንም ከኢንዱስትሪ መንደር/ማር ማቀነባበሪያው ከማለዳው ጀምሮ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ከጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ የውርድንብር ድብደባ እየፈፀመ ነው::

የፈሪ ነገር ሆኖበት የፋኖን ጦር ፊትለፊት መጋፈጥ ሲያቅተው በሩቁ በሚያስወነጭፈው የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ንፁሃን ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ ነው::

ዝርዝር መረጃ ከእዙ እንደደረሰን የምናደርሳችሁ ይሆናል::
💔1
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ዛሬ ጥር 5/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ደረሳዎችን ጨምሮ ወጣቶችን በሃይል እያፈሰ ወደ ጦር ማሰልጠኛ እያጋዘ ይገኛል::

ተከታዩ ቪዲዮ በዉጫሌ ንፁሃንን በተለይ ደግሞ 'የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፋኖ ጠል ነው' የሚል ስሁት ትርክቱን ለማሳየት በመምረጥ ወደማሰልጠኛ እየወሰዷቸው ነው:: የፍኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የ እምነት ልዩነትን በማስፋት ግጭት ለመቀስቀስ እየጣረ የሚገኘው ስርአቱ የመዘዘው የመጨረሻ ካርዱ ቀድሞ የተነቃበት በመሆኑ ችግሩ አልተፈጠረም::

በተለይ የ እምነት ልዩነት ውበት እንጅ ችግር ያልሆነበት የወሎ ማህበረሰብ አገዛዙ እየሄደበት ያለውን የግጭት ቅስቀሳ አጀንዳ እየተጠየፈ ከህልውና ትግሉ ጎን እየቆመ ነው::
💔1