ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር


ሰበር የድል ዜና!!!

በትናንትናው እለት ህዳር 3/2018 አናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ አማሀድንግል ብርጌድ በአርበኛ አሰፋ አለምቀንና በአርበኛ ደርሴ አጉማስ እየተመራ እንዲሁም አይሸሽም ብርጌድ በአርበኛ አሌ መጋቢያው እየተመራ በአገዛዙ ዘራፊና አራጅ ቡድን ላይ ከፍተኛ ድልን እየተጎናፀፉ ይገኛሉ።

የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሀይል መነሻውን ከጎንደር ፣ከጭልጋ፣ ከነጋዴባህርና ከሽንፋ ተውጣጦ በግልፅ አይን ያፈጠጠ ጥርስ ያገጠጠ ዝርፊያ ለመፈፀም ንብረትና ቅርስ ለማውደም እና የአርሶአደሩን ትጥቅ ለማስወረድ የመጨረሻ የሚለውን የዘር ማፅዳትና የማሸበር ተግባሩን በአማራ ህዝብ ላይ የጥለቻ ጥግን ለመፈፀም ያለውን ግብስብስ ሀይልና የብልፅግና አሸርጋጅ ምስለኔዎችን ይዞ ወደ ምእራብ ጎንደር አዳኝ አገር ጫቆ እና ምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሻሽጌ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ይህንኑ የአረመኔነት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቀጠናው ቢገባም የፋኖ ሰራዊት ከማህበረሰቡ እና አባት አረበኞች ጋር በመተጋገዝ የእግር እሳት ሆኖበት እንደ ልቡ በቀጠናው እንዳይንቀሳቀስ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ አሁን ላይ መውጫ መግቢያ አጦ እየተጨነቀ ይገኛል።

ይህ ከተለያየ ከተማ ተሰባስቦ ወደ ቀጠናው የገባው የአንበጣ ስብስብ ደም መጣጭ ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ እየፈፀመ ያለው ፀረ አማራ ቡድን አዳኝ አገር ጫቆ ገኒ ከምትባል ከተማ በመግባት ያልፈፀመው ፀያፍ ተግባር የለም። በየ አርሶአደሩ ቤት ክፍችኝ በመግባት እየዘረፉ፣የበሉትን እየበሉና የተረፈውን እንደ ዝንዠሮ እያበላሹ ከፍተኛ ንብረት ያወደሙ ሲሆን ሁለት አርሶአደሮችን ታደሰ መስፍን እና በቀለ ተገኘ የሚባሉ በማታ ከመኖሪያ ቤታቸው አውጥተው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ከገደሉ በኃላ በጩቤ አርደው ጥለዋቸው ተገኝቷል።ሌላኛው በገኒ ከተማ በየ ቤቱ ክፍችኝ በመግባት በገንዘብ ከ3ሚሊዬን ብር በላይ በንግድ ቤቶችና በመኖሪያ ቤቶች ከመዝረፋቸው ባሻገር የብዙ ቤቶችን በርና መስኮት አውድመዋል፤ የቤት እቃዎችን ሰብረዋል፣አቃጥለዋል። በተጨማሪም ገኒ ከተማ ላይ ከ2 በላይ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በማታ ስአት የገጠር አርሶአደሮችን መንደር በማፈን 4 መሳሪያ የዘረፉ ሲሆን በእለተ እሮብ በረት ውስጥ ያሉ 2 በሬዎችን ከአርሶአደሩ በመንጠቅ አርደው ሊበሉ ችለዋል።

የአምሀድንግል ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ሙሉጌታ ዋለልኝ ከቦታው እንዳሳወቀው ቀጠናው የገባው ይህ የክፉ ስርአት አራማጅ የአውሬው ተገዥ ሰራዊት በእንቅስቃሴው ሁሉ በደፈጣና በመደበኛ ውጊያ በየደረሰበት ሙሉ ቀኑን እየተቀጠቀጠ አመራርን ጨምሮ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ በየቦታው አስከሬኑን እያዝረከረከ ይገኛል። እንዲሁም አሁን ላይ ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ በሁሉም ቀጠና ሙሉ ሰራዊቱን ስምሪት በመስራት ጠላት ከገባ ላይወጣ ማህበረሰቡንም በማስተባበር ከበባ ውስጥ በማስገባት ክፉኛ ከፍተኛ በትር እያረፈበት ይገኛል።

በትናንትናው እለት ህዳር 3/2018 በአምሀድንግልና በአይሸሽም ብርጌድ የተገኘ ድል:
የሞተ = 26 በላይ
የቆሰለ = 32በላይ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 4/2018
🙏3
የአሳምነው ክፍለጦር እና የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ድል አስመዘገቡ::

የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር እና የምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር አሃዶች ዛሬ ህዳር 4/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ወሳኝ ወታደራዊ ቦታ የሆነችውን በቅሎ ማነቂያ ለማጥቃትና ለመቆጣጠር የመጣን ጠላት ሙትና ቁስለኛ አድርገው ወደመጣበት ወልድያ ዙሪያ መልሰውታል::

በተጋድሎው የአሳምነው ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ እና ዞብል አምባ ክፍለጦር 7ኛ ሻለቃ በጥምረት የመጣውን ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰው ወደመጣበት በመመለስ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታቸው የሆነችውን በቅሎ ማነቂያ አስከብረዋል::

የፋሽስቱ ብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እንደተለመደው የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ መድፍ በማስወንጨፍና ድብደባ በመፈፀም ንፁሃን ላይ ጉዳት ከማድረስ ባሻገር ቤትና ንብረት እንዲሁም እንስሳቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በቀል ሲበቀል ውሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 4/2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ጠላትን ተናንቀዋለች።

ህዳር4/2018 ዓ.ም

ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ወደ ቸርተከልና ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመነሳት በሌላ አቅጣጫ በየቦ ወደ ሊባኖስ ቀበሌ ለመግባት በመድፍ የታገዘ ሙከራ ያደረገው የአረመኔው ሰራዊት ከደብረ ማርቆስ የተነሳውን ጠላት በመነጠል ውጊያ የከፈተችው የ14ኛ ክፍለ ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ ሙትና ቁስለኛው አሸክማ ወደ መጣበት አጣድፈዋለች።

ትስስር ፈጥሮ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል በሁለት ግንባር እንዲወጠር የተደረገ ሲሆን ከደብረ ኤልያስ ወደ ቸርተከል የተንቀሳቀሰው ጠላት መሉ ለሙሉ ከበባ ውስጥ ገብቶ እየተጨነቀ ይገኛል። ጠላት የደረሰበትን ከበባ ለመጣስ ተደጋጋሚ የሆነ የመድፋና የሞርተር ድብዳ በማድረግ ወ/ሮ ዜማ በቃል የተባለችን የልጆችን እናት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ!
የ206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራሳቸውን ነፃ አውጥተው ፋኖን የሚቀላቀሉ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ ነው።

ከፋሽስቱ ሰራዊት እየፈረሱ ፋኖን የሚቀላቀሉ ሰራዊቶች የ12ኛ እና የ93ኛ ክፍለ ጦር የሆኑት ሰራዊቶች የብልፅግናን ጭቆና ከትከሻቸው ላይ አራግፈው በመጣል ወደ አማራ ፋኖ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮርን የሚቀላቀሉ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ከቀን ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል። በጥቅምት ወራት የመባቻ ማግስት እስከ ህዳር አራት የፋሽስቱን ስርዓት እየከዱ የደጀን ክፍለጦርን የተቀላቀሉ ሀይሎች ስድስት ደርሰዋል። ራሳቸውን ከሞትና ከጥፋት በመታደግ የፋሽስቱን ስርዓት አገልጋይነትን በመጠየፍ የብልፅግናን ቤት ንቀው ወደ ህዝብ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

የስርዓቱን አስከፊነትና ጨፍጫፊነት የመሰከሩ ሲሆን" ከአሁን በኋላ የፋሽስቱን ወበር ለማስጠበቅ የሜንገብረው የህይዎት ዋጋ የለም።" ሲሉ ገልፀዋል። አስቀጥለውም በፋሽስቱ ስርዓት ውስጥ ተጨቁነውና ተደፍጥጠው ያሉ ወታደሮች ባገኙት አጋጣሚ ፋኖን ይቀላቀሉ እራሳቸውን ነፃ ያውጡ" ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 4/2018 ዓ.ም
2👍1
🔶 ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አርሴማ ላይ በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመ።
በትላንትናው እለት ህዳር 4/2018 ዓ.ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ፭ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ቃኘው ብርጌድ ፤ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ጅብ አስራ ማርያም ብርጌድ እና ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ቃኘው ሻለቃ በመቀናጀት ምንዝሮ ልዩ ስሙ አርሴማ ከተባለው ቦታ ላይ በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
በጥቃቱ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሰራዊቱ ቁስለኛውንና አስከሬኑን በመተው ወደ ጠዳ ከተማ ፈርጥጦ ገብቷል።
በዚህም የተነሳ ቁስለኛውንና አስከሬኑን ለማንሳት ተጨማሪ የጠላት ኃይል ከጠዳ ከተማ ተነስቶ ውጊያው ከተካሄደበት ቦታ በመድረስ በወገን ሃይል ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎቹ ፋኖዎች የለመደውን የሽንፈት ካባ አከናንበውታል።
በውጊያው ከተገኙ ድሎች መካከል
** 06 የሞተ
** 08 ክፋኛ የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ

ህዳር 05/2018 ዓ.ም
2🙏1
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ የኦርቶዶክሳውያንን የሰንዴ ክምር በእሳት እያጋዩት ነው።

ዝምታ የበዛበት የአርሲዉ ጭፍጨፋ??!!!
💔2
እነሆ የዕድሜ ልክ የፅናት አባት አርበኛ መሳፍንት ተስፉን መልዕክት በወርድ ለፈለጋችሁ።

ከአርበኛ መሳፍንት የተላለፈ ወቅታዊ መልዕከት
**********
ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ፣ እንድያ ህይወቴን ለመስጠት የተዘጋጀሁላችሁ የመኖሬ ሚስጥር የሆናችሁ የአማራ ህዝብ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በሙሉ የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ፡፡

ከእኔ አብራክ የተወለዱ ልጆቼ፣ የአማራ ህዝብ የመንፈስ ልጆች አርበኛ ጌትነት እና አርበኛ ገብረ መሰዋት የተሰማችሁ ሀዘን ከፍተኛ እንደሆነ በተለያየ መንገድ ደርሶኛል፡፡

በእርግጥ ሀዘኑን የጀግና አባት፤ ለሀገር የቆሙ እልፍ ጣይ አባት፣ ሁሌ በበርሀ እና ስደት ሆና ያሳደገ አባት ሆናችሁ ስታስቡት እጅግ መሪር ነው፤ ግን ደሞ ጣፋጭ መሪር ነው:: ሁኔታውን መሪሪ የሚያደርገው ስለማራነት እና ለሐገር በሚደረግ የህይወት መሰዋዕትነት ውስጥ ከአብራክህ የወጡ ጀግና ልጆችህን በእርጅና ዘመንህ እያጣህ ስትሄድ ነው፡፡ ይህ እራስን ለትግል አቅርቦ እንደመሰዋት አይደለም ይህ በጦር ሜዳ ተፋልሞ እንደ መቁሰል አይደለም፤ ይህ መሸነፍ እና እንደ ማሸነፍ አይደለም እጅግ ጥልቅ ጀግንነት የሚጠይቅ እንጂ፡፡ ሆኖም ግን እኔ አባታችሁ ይህን መሪር ሀቅ ወደ ጣፋጨነት የምቀደረው ከአባቶቼ በወረስኩት ለህዝብ ለነፃነት፤ ለእምነት፣ ለሀገር መኖር እጅግ በጣም ጥልቅ ጀግንነት እና ቆራጥነት የሚጠይቅ መሰዋዕትነት እንደሆነ ስለማምን ነው።

የተከበራችሁ ወገኖቼ ሀዘን ገብቶታል ብላችሁ እንዳታስቡ ምክንያቱም በልጆቼ መሰዋት ውስጥ፣ ሁሌ የሚታዩኝ የአማራን ህዝብ ወደ ክብሩ ሲመለስ ነው፣ ሀገሬ ኢትዮጵያ ከባንዳዎች እጅ ወጥታ የቀደመው ክብሯ ተመልሶ በአለም ፊት ከፍ ብላ መታየቷ ነው፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚያምነው እምነቱ በነፃነት አምልኮ የሚመኛትን መንግስተ ሰማያታት እወርሳለሁ ብሎ በሙልዑነት በሀገሩ ሲኖር ማየት ነው።

በአሁኑ ሰዓት ለአማራ ህዝብ እና ለሀገር የሚደረግ መሰዋዕትነት ተራ መሰዋዕትነት አይደለም ሰው በጠፋበት ዘመን ፤ እናቶች በሚቃትቱበት ዘመን፤ ሴት ልጆች ድረሱልኝ በሚሉበት ዘመን፤ አዛውንት የሚያደርጉት አጥተው በሚያስቅሱበት ዘመን፤ ክርስቲያኖች ሰው አውጣልን እያሉ በሚማፀኑበት ዘመን የሚከፈል እንቁ መሰዋዕትነት ነው፡፡ መለኪያም የለውም፡

የምወዳችሁ የአማራ ህዝብ ሆይ በልጆቼ መቃብር ላይ ቆሜ ይህንን የአባትነት ጥሪ እና መልዕክት እንድትቀበሉኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

1. በትንንሽ እውነቶች ትልልቅ እውነቶችን አትሽጡ ወይም አትግደሉ ፡- ይህ ማለት- ማንኛውም ሰው የሚያነሳው እውነት ይኖረዋል፤ ለምሳሴ እራስን መለወጥ፣ ለቤተሰብ ቋሚ ገቢ እንዲኖር ማድረግ፣ የግል ክብሩን መጠበቅ፣ የራሱን የትግል ስልት መቀየስ፣ የሚባሉ እውነቶች አሉት። መገንዘብ የሚገባን ግን እነዚህ እውነቶች የሚኖሩነት ሀገር እና ህዝብ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ስለሀገር፣ ስለህዝብ፤ ስለ እምነት መኖር ከላይ ከተቀመጡት እውነቶች ጋር ሲነፃፀር ትንንሽ እውነት ናቸው፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ግን በእነዚህ ትንንሽ አውነተሰ ትልልቅ እውነትን መግደል ነው፡፡ ይህ የአማራንት መገለጫ አይደለም:: የአባቶቻንም አደራ እንዲህ እንደ እንሰሳ እንድንኖር አይደለም:: ልጄ ጌትነት የተሰዋው እሱ ለትልቁ እውነት ሲኖር ለትንንሽ ነገር የሚኖሩ የባንዳዎች አስተሳሰብ ውጤት ነው::

2. የአማራ ህዝብ መዳኛ የሆነውን ትጥቃችሁን (አንድነትን) በወሬ፤ በሴረኛ፤ በስሜታዊነት፤ ባለማወቅ፤ በስርዐት አልበኝነት እና በራስ ወዳድነት አትናዱት፦ አማራ ትልቅ ህዝብ ነው። ትልቅነቱ የመነጨው በአማኝነቱ በታማኝነቱ ነገርን ከስሩ በማየቱ/ማስተዋሉ/፤ በማገናዘቡ እና ትልቁን እውነት ይዞ በአንድነት ጥላትን በማሸነፉ እንጂ ሰው ሆኖ በመፈጠሩ ብቻ አይደለም፡፡

3. የተግባር ሰው ሁኑ፤ በጣም ቀላሉን መንገድ አትምረጡ - በጣም ቀላሉ መንገድ መናገር እና መተቸት ነው፡፡ ይህ ለአማራነት አይመጥንም። አማራነት ለሚያውቁት እውነት “በመመነን" ወይም በመኖር ነው የሚገለፀው፡፡ የወንድምህን ሌብነት ጨዋ በመሆን አሳየው፣ እንዳይሰርቅ ሥርዐት በመዘርጋት አግዘው፣ በመምከር አስተምረው እንጂ እንደ ሰይጣን ቆሻሻ ቃላቶችን በመጠቀም አይሁን፡፡ ተግባርህ እንጂ ስድብህ እንዳላስተማረ አይተኸዋል፡፡

4. የተሰዉ ልጆቼን፣ በዱር በገድል ስለእናንተ የተሰዉ እህት ወንድሞቻችሁን እና በትግል ላይ ያሉ አርበኞችን የምትወዷቸው ከሆን የሚከተሉት ጥያቄዎችን በውስጣቸሁ ሁል ጊዜ አንሱ፡፡

የእኔ ልጅ ጌትነትና ሌሎች ፋኖዎች ስለወገናቸው ቃል እንደገቡት እናንተ የሚጨፈጨፈው አማራ እንዲድን ምን ቃል ገባችሁ?

የእኔ ልጅ ጌትነት እና ስለ አማራ የተሰዉ ፋኖዎች የገቡትን ቃል በማክበር አንድኛ ሂወታቸውን እንደሰጡ እናንተስ ምናችሁን መሰዋዕት አደረጋችሁ?

ወንድሞቻችሁ በየበረሀው እየተሰዉ እኛ አንድ ሆነን እንዳንታገል የሚያደርገን ሀደል ከአማራ ህዝብ በልጦ ነው? አማራ ችግር የመፍታት ጥበብ አጥቶ ነው? አማሪ በድርጅት እና በአሰራር ሥርአት ብቻ ማሸነፍ እንደሚችል ጠፍቶት ነው? ወይስ በሴት ልጆቹ ጡት መቆረጥ ተደስቶ ነው? እነዚህን ጥያቄዎች መልሳችሁ አንድ ሀየሰል የገነባችሁ እለት የልጆቼን ደም እንደመለሳችሁልኝ አቆጥረዋለሁ።

የተከበራችሁ ወገኖቼ እኔ እድሜ ልኬን ስታገል ኖሬ የቀረኝ እድሜ አጭር ነው። በህይወት እስካለሁ ድረስ ለህዝቤ እራሴን መሰዋዕት አድርጌ አቀርባለሁ። ለመላው አማራ እና ኢትዮጵያውያን የማስተላልፈው ትልቅ መልዕክት ይህ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረን ሰው እየነቀሰ ሰው የሚተከል፣ እምነት የሌለው፣ ሀገር የሚጠላ፤ የሰው ህመም የማያመው፣ በሰው ልጅ ሞት የሚሳለቅ፣ ገድሎ በእሬሳ ላይ የሚቀልድ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ የቅደም ተከተል ጉዳይ እንጂ ማንም እንደማይተርፍ ላረጋገጥላችሁ እወዳለሁ::

በመሆኑም የአማራ ልጆች የሆናችሁ እና ለገል ጥቅማችሁ ስትሉ ከመንግስት ጋር ሆናችሁ ወገናችሁን የምትገድሉ አማሮች ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢል አማራ ማሸነፉ ስለማይቀር፤ የእኛ ህይወት ህያው ሆና በወርቅ መዝገብ ሲመዘገብ እናንተ በምትሞቱለት ጥላታችሁ ተገድላችሁ የውሻ ሞት ሞታችሁ ልጆቻችሁም የባንዳ ልጆች ተብለው ሲወገዙ እንዳይኖሩ ከወንድሞቻችሁ ጋር ይቅር ተባባሉ እና በአንድ ተሰለፉ። የውስጥ ባንዳዎች መርሳት የሌለባችሁ ጀግናን ስትሰዉ ህያው ታደርጉታላችሁ እንጂ አትገድሉትም፣ ይልቁንም እናንተ የውሻ ሞት ስለምትሞቱ ጀግናን ጠብቁትና እራሳችሁን ከአደጋ ጠብቁ:

በመጨረሻን የአማራ ብርቅዬ ልጆች የሆናችሁ ነፍጥ አንስታችሁ በተለያዩ መስመር የምትታገሉ ፋኖዎች የአማራ ህዝብ እጣ ፈንታ በእጃችሁ ነው። የአማራ ህዝብ ከጎናችሁ በመሆን አለምን ያስደመመ ንቅናቄ ከተደረገበት ከሁለት አመታት በኋላ ያለው የአማራ ስቃይ የታሪካችሁ አካል ነው የሚሆነው:: አደናቅፎ የጣላችሁን መንገድ አትከተሉ። ስለሆነም በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ ሆናችሁ እንድትታገሉ በተሰዉት ሁለት ልጆቼ ለአማራ ሲሉ በተሰዉ መላው የአማራ ፋኖ ታጋዮች እና በመላው የአማራ ሥም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

አርበኛ መሣፍንት ተስፉ
🙏31
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

ሻለቃ መሪው በፋኖዎች በቁጥጥር ስር ዋለ!

ህዳር 05/2018ዓ.ም

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር ተከዜ ክፍለ ጦር መረጃን በማነፍነፍ የ61ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሻለቃ ምክትል መሪ የሆነው መቶ አለቃ በእውቀቱ ምስጋናው ከድልብ ወደ ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም ከተማ በሚወስደው መንገድ ዴንሳ ከተማ ላይ በተከዜ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ህዳር 04/2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል።

ይህ ግለሰብ ላስታ ወረዳ ኩልመስክ ከተማ ላይ ከዚህ በፊት ስምንት ንፁሃንን የረሸነና ያስረሸነ፣የብዙ ወጣቶችን አካል ያጎደለ፣የአባውራ ሴቶችን የደፈረ፣ህዝባዊ መድረክ ላይ በይፋ ኩልመስክ ከተማን ጥቁር አለብሳታለሁ እያለ ማህበረሰቡ ላይ ግልፅ የስነ ልቦና ጫና ያደርስ የነበረ፣ከነጋዴው ብሎም ከማህበረሰቡ ሙስና የሚቀበልና የግል ጥቅሙን የሚያግበሰብስና ፍፁም ስነ ምግባር የጎደለው ጥቁር አማራ ነበር።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 05/ 2018 ዓ.ም
👍3