ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አለማቀፍ yeshama ማብራት ስነስርዓት
አራት የቪአይፒ (VIP) ጥበቃወች ፋኖን ተቀላቀሉ።

የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ከወገናችን ጋር አንዋጋም በማለት ከአድማ ብተና ተቋም በመውጣት ፋኖን የተቀላቀሉት፦
1 መልካሙ አድኛው
2 አሸናፊ ጥጋቡ
3 እንዳለው አበበ
4 እሱባለው አቅነው  የተባሉ ሲሆኑ ፦
➢ 04 ክላሽ 
➢06 ቦንብ
➢03 የወገብ ትጥቅ
➢06 ካዝና
➢270 የክላሽ ተተኳሽ መሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ወደ ወገኖቻቸው የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች  ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
2🙏1
ከመብረቅ ክ/ጦር የተሰጠ የሃዘን መግለጫ

"በጓዳችን ድንገተኛ ሞት ልባችን ተሰብሯል ፤ ትከሻችንም ቀሏል !!"
ህዳር 02/2018 ዓ.ም የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ አርኖ ጋርኖ በተባለችው ከተማ ላይ የፀጥታ ተግባርን በማከናወን ላይ በነበረበት ወቅት የጠላትን የእጅ አዙር ተልእኮ ሳያነግብ እንዳልቀረ በተጠረጠረ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆነው አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት ከፍሏል።
ጀግናው ጓዳችን አርበኛ መልካሙ ሞላ ከመሪዎቹ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በቀናኢትና በታዛዥነት መስዋእትነት እስከከፈለበት ጊዜ ድረስ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ነበር።
ጓዳችን ትግሉ ከተጀመረ አንስቶ ከመብረቅ ክ/ጦር አመራሮችና አባላት ጋር በመሆን ሚካኤል ደብር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ሰማይ ስር የመጀመሪያውን ድሽቃ መማረክ የቻለ ክንዳችን ነበር።
የክ/ጦራችን ብልህና ጠንካራ አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን አርበኛ መልካሙ ሞላና ሌሎች እልፍ ጀግኖች አርበኞቻችን የከፈሉለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንተጋለን።

➢ለወዳጅ ፣ ለቤተ ዘመዱ እንዲሁም ለትግል አጋሩ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ህዳር 4/2018 ዓ.ም
2🙏1💔1
በአፋብኃ በላይ ዕዝ ጠላት ተደመሰሰ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ተማረኩ!!

የአፋብኃ በላይ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ከባ/ዳር ጎንደር መስመር በወታደራዊ አጀብ ሲጓጓዝ የነበረ ኮንቮይ ኃይል ላይ በተለያዩ ቦታዎች በሰነዘረው የተጠና ማጥቃት ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።

አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ምት ለመቋቋም ያግዙኛል በሚል በግዳጅ የሰበሰበውን ግብስብስ ሰራዊት በተጨማሪነት ከባ/ዳር ጎንደር በማንቀሳቀስ ላይ ባለበት ከአዲዘመን ማክሰኝት በሚገኝ የመግደያ ቀጠና በማስገባት ብርቱ ምት ሊደርስበት ችሏል።

🔸 ህዳር 03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ጀምሮ ከባህር ዳር ጎንደርና ከጎንደር ባህር ዳር በርካታ ቁጥር ያላቸው ሎጀስቲክና ሰራዊት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በማንቀሳቀስ ላይ እያለ አርኖ ጋርኖ የተሰኘ ልዩ ቦታ እንደደረሰ የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አንድ አካል የሆነው ነብዩ አሳምነው ብርጌድ የአርኖ ጋርኖ ከፍተኛ ቦታዎችን በመጠቀም በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አድርሰዋል።
በጥቃቱም ቁጥሩ ለጊዜው በውል ያልተቻለ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
የ5ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በመሩት ውጊያ ከተመዘገበው አመርቂ ድል በተጨማሪ የጠላት ኃይል ተመልሶ መውጫ እንዳያገኝ በመዝጋት ሌላ ቀጠና ለተሰናዳ ደፈጣ ጠላት ተጋላጭ እንዲሆን ተደርጓል።

🔸ከአርኖ ጋርኖው ጥቃት አምልጠው ሰብሃ ገብርኤል የደረሰው የጠላት ሰራዊት በ5ኛ ኮር የመብረቅ ክ/ጦር አካል በሆነው ቁልቋል በር ብርጌድ አማካኝነት ለዳግም ጥቃት ተዳርጓል።አያሌዎችም ላይመለሱ ሲደመሰሱ ቀሪዎቹ አካላዊ ጉዳት ተከናንበው ሊያፈገፍጉ ተገደዋል።
ድንገተኛ ጥቃት የገጠመው ጠላት የአስር አለቅነት ማእረግ ያለው ጌታሁን ወርቁ የተባለ አመራሩን እስከነ ሙሉ ትጥቁ አስማርኳል።
በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች የደረሰበትን አሰቃቂ ምት መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን አርሶ አደሮችና በህፃናት ላይ የበቀል በትሩን አሳርፏል። በዚህም የንፁሃን ጥቃት አንድ የ9 ዓመት ህፃንን ጨምሮ ስምንት ንፁሃን ወገኖችን የዓብይ አገዛዝ ታጣቂዎች በግፍ ረሽነዋል።

🔸ከአርኖ ጋርኖ እስከ ሰብሃ ገብርኤል የፋኖዎችን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም አቅቶት በንጹሃን አማሮች ላይ የበቀል ጥሙን አወራርዶ ወደ ጎንደር በመፈርጠጥ ላይ እያለ ፈረንጅ ውሃ ከተባለው ቦታ ላይ የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ንስር ብርጌድና ራስ አሞራው ውብነህ ብርጌዶች በደፈጣ ስልት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ሲቀጠቅጡት አምሽተዋል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት እያጀበ ይዟቸው ከቦታው ያደረሳቸውን 3 ተሽከርካሪዎች ከጫኑት ስንቅና ትጥቅ ጋር የተማረከ ሲሆን ብዙ ቁጥር ያለው ኃይሉ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ህዳር 04/2018 ዓ.ም
🙏3
"እራበን፣ ህፃናት ልጆቻችን ምግብ ከቀመሱ ብዙ ቀናትን አስቆጥረዋል" ተፈናቃይ ወገኖች!

ከተፈናቃዮቹ መካከል አንዳንዶች፡ የሚቀመስ ባለመኖሩ የልጆቻቸውን "የራበኝ" ድምፅ መስማት አቅቷቸው እራሳቸውን በገመድ አንቀው ማጥፋታቸው ነው የተነገረው።

ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ከአራቱም የወለጋ ዞኖች እንዲሁም ከምዕራብ ሸዋ ዞን በማንነታቸው ምክኒያት ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ላይ ተጠልለው ከሚገኙ ወገኖች መካከል በርካቶች በረሃብ ምክኒያት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

"የሚላስ የሚቀመስ የለም፡ አይደለም እኛ አዋቂዎቹ ይቅርና ህፃናት ልጆቻችን ምግብ ከቀመሱ ብዙ ቀናትን አስቆጥረዋል" ነው ያሉት ተፈናቃዮቹ።

ከ2017 ዓ/ም ሚያዝያና ግንቦት ወራት ወዲህ ምንም አይነት እርዳታ እንዳልቀረበላቸው የገለፁት ተፈናቃይ ወገኖቻችን፡ "እባካችሁ በነፍሳችን ድረሱልን" ሲሉ ተማፅኖ አቅርበዋል።

ብዛታቸው ከ600 በላይ እንደሆነና በማሻ ከተማ በስድስት ካምፕ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮቹ የገለፁት።

"ከሰባትና ስምንት ወራት በፊት ይመጣ የነበረው የእርዳታ እህል ለምግብነት መዋል የማይችል፡ የነቀዘና የተበላሸ ነበር፡ አሁን ላይ እሱም ቢሆን ከተቋረጠብን መንፈቅ በላይ ሆኖታል" ሲሉ ለጣቢያችን የገለፁት ተፈናቃዮቹ፡ "እርቦናል፡ በረሃብ ምክኒያት ሕይወቱ የሚያልፈው ተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደቀን ጨምሯል፣ አንዳንዶች የልጆቻቸውን <የራበኝ> ድምፅ መስማት አቅቷቸው እራሳቸውን በገመድ አንቀው እያጠፉ ነው" ሲሉ ቃል በቃል ተናግረዋል።

ከተፈናቃዮቹ መካከል ሰርቶ ማደር የሚችሉት ከዓመታት በፊት ካምፑን ለቀው ለስራ ወደ ተለያዩ አከባቢዎች የተበተኑ ሲሆን፡ አሁን ላይ በወረዳው በስድስት ካምፕ ተጠልለው ከሚገኙት ከ600 በላይ ተፈናቃዮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት፡ ለአቅመ ስራ ያልደረሱ ታዳጊዎችና ህፃናት(በጥቃቱ እናትና አባታቸውን ያጡ የቲሞች)፣ አረጋውያን፣ በደረሰባቸው አሰቃቂ ጥቃት አካል ጉዳተኛ የሆኑና በጥቃቱ የተነሳ ለአዕምሮ ህመም የተጋለጡ መሆናቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

@መረብ ሚዲያ
💔2
ሰበር ዜና
የደጋው መብረቅ ኮር በተለያዪ ቦታዎች ላይ ድልን ተቆናጠጡ!!!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር ህዳር 4/2018 ዓ/ም አረፋዱን የፋሽስቱ ሰራዊት ተቀጥቅጧል ።

የፋሽስቱ ቅጥረኛ ሰራዊት ከተንታ እና ከደላንታ ወረዳ አሰባስቦ የተሪን በረሀን አቋርጦ ወደ ደሴ እያቀና እያለ ተሪ ላይ በደፈጣ የአሞራ ሲሳይ ተደርጓል። ከደፈጣ ምቱ የተረፈው የፋሽስቱ ሰራዊት ከፋኖዎቹ በተሰነዘረበት ጥቃት ተበታትኗል። አናብስቶቹም የጥላትን ሰራዊት እየለቀሙት ይገኛሉ።

የአማራ ምድር እሳተ ጓሞራን ደግሶ የተቀበለው የፋሽስቱ ሰራዊት እንደ እሳት እራት እየተክለፈለፉ የሚቀነደሹት የጥላት ሰራዊት የመጨረሻ የባንዳ ዋጋቸውን በፋኖዎች ክንድ እየተሰጣቸው ነው።

በተመሳሳይ ዜና
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለጦር ህዳር 4/2018 ዓ/ም የመቄት ሚኒሻ አመራሩን የሆነ አካል ተሸኝቷል።

የከተማ ሰርጀሪ ማስተሮች ከሌሊቱ 7:00 ገረገራ ከተማን ዘልቀው በመግባት የሚኒሻ አመራሩንና በርካታ የሚኒሻ አባላቶችን ወደማይቀረው ሲዖል ሸኚተዋቸዋል። የደጋው መብረቅ ኮር ከምስረታው ማግስት አንስቶ ያልነጠፈ የድል ግስጋሴው በመቄት ወረዳ ላይም ድል ማድረግ ችለዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር
ህዳር 4/2018 ዓ.ም
🙏3
የደጀን ወረዳ አመራሮች በ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በተደረገ የጠና ኦፕሬሽን ተደመሰሱ።
ህዳር 4/2018 ዓ.ም

  የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ዛምበርሃ ሻለቃ የጠላት ካምፕ ከበባ በማድረግ አነጋጉ ላይ በፈፀመችው የተጠና ኦፕሬሽን በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት ሲገደሉ የወረዳው አመራሮች ይገኙበታል። 

ምንጅ ላይ የጦር ካምፕ ያደረገው የአረመኔው ሰራዊት በምሽጉ ድንገተኛ ከበባ የተደረገበት ሲሆን የዛምበርሃ አናብስቶች በሶስት አቅጣጫ በፈፀሙት  ጥቃት ፦ 1.ተገኑ ስለሽ የደጀን ወረዳ ኢንቨስትመንት ኃላፊ 2.በላቸው ጋሹ የደጀን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ የተደመሰሱ ሲሆን ፣ተሾመ ብርሌው፣አስረሱ አዳሙ፣እሱባለው አልማው፣አወቀ ቢተው የተባሉ ሚኒሻዎችም ከተደመሰሱ 20 የጠላት ኃይሎች መካከል ይገኙበታል።

ከኦሮሚያ አቅራቢያ በተደረገው ኦፕሬሽን ድል የተቀናጀው 206ኛ ኮር የቀጠናውን ትግል ቅርፅ መቀየር የሚያስችል እንቅስቃሴ በመጀመር አገዛዙን ሽብር ውስጥ የከተተውን ሌላኛውን ፈጣን የከበባ ጥቃት በማድረግ 8 የጦር መሳሪያ፣የወገብ ትጥቅ፣ ጥይት፣ወታደራዊ ቦርሳ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ሲማርክ 8 የአረመኔው ሰራዊት ከባድ ቁስለኛ አድርጓል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🙏2
በቤተመንግስት ዙሪያ ጥበቃ የነበሩ የሪፐብሊካን ጋርዱ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ትናንት ህዳር 3/2018 ዓ.ም  ሁለት ቁልፍ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ቡልጋ ክፍለጦር  ተስፋ ብርጌድ ተቀላቅለዋል።

  በቤተመንግስት በጀት የሚተዳደሩ በሀገረ ፈረንሳይ የሰለጠኑ ሁለት ወሳኝ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት የፋኖን ትግል በይፋ ተቀላቅለዋል።ሁለት ኤ.ኬም 105 ጥቁር ክላሽንኮቭ መሳሪያ በመያዝ ከተገፈዉ አማራ ህዝብ ጎን ተሰልፈዋል ተብሏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!
🙏3
የአገዛዙ ሰራዊት አባላት አሁንም ወደ ፋኖ እየኮበለለ ይገኛል።

አዲስ የተቋቋመችዉ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 12 ኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑ ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮርን በዛሬዉ እለት ተቀላቅለዋል።

ይች ክፍለ ጦርም በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ(አባ ናደዉ) ዘመቻ ሙሉ በሙሉ መደምሰሷ እና የክፍለ ጦሯ አዛዥ ቁስሎ እንዳመለጠ እና ምክትል አዛዡም መማርኩም አይዘነጋም። አሁን እየኮበለለ ያለው በአዲስ መልክ የተደራጀው የክፍለጦሯ ሰራዊት ነው::

ኮብልለዉ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮርን የተቀላቀሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባለት
1. 10 አለቃ እሸት ሽመልስ 12ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ ጓድ መሪ
2. ወርቁ ይቻል 12 ኛ ክ/ጦር 3 ኛ ሻለቃ አባል
3. መሰረት አብራራዉ 12 ክ/ጦር 3 ኛ ሻለቃ አባል

አገዛዙን ከድተዉ ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት የሰራዊት አባላቶችም እኛ የ አንድ ግለሰብ ወንበር አስጠባቂ አንሆንም ብለን ወጥተናል አሁንም የአገዛዙ የሰራዊት አባላት እስካሁን ተሸዉዳቹሃል ከአሁን በኋላ እንድትነቁ እና ወደ እዉነተኛ ትግል ወደ አለበት አማራ ፋኖ በሁሉም ቀጠና እንድትቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዉ እኛም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮርን ተቀላቅለን ይህን ስርዓት ገርስሰን ለመጣል ዝግጁ ነን ብለዋል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ
ህዳር 4/3/2018
🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር


ሰበር የድል ዜና!!!

በትናንትናው እለት ህዳር 3/2018 አናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ አማሀድንግል ብርጌድ በአርበኛ አሰፋ አለምቀንና በአርበኛ ደርሴ አጉማስ እየተመራ እንዲሁም አይሸሽም ብርጌድ በአርበኛ አሌ መጋቢያው እየተመራ በአገዛዙ ዘራፊና አራጅ ቡድን ላይ ከፍተኛ ድልን እየተጎናፀፉ ይገኛሉ።

የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሀይል መነሻውን ከጎንደር ፣ከጭልጋ፣ ከነጋዴባህርና ከሽንፋ ተውጣጦ በግልፅ አይን ያፈጠጠ ጥርስ ያገጠጠ ዝርፊያ ለመፈፀም ንብረትና ቅርስ ለማውደም እና የአርሶአደሩን ትጥቅ ለማስወረድ የመጨረሻ የሚለውን የዘር ማፅዳትና የማሸበር ተግባሩን በአማራ ህዝብ ላይ የጥለቻ ጥግን ለመፈፀም ያለውን ግብስብስ ሀይልና የብልፅግና አሸርጋጅ ምስለኔዎችን ይዞ ወደ ምእራብ ጎንደር አዳኝ አገር ጫቆ እና ምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሻሽጌ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ይህንኑ የአረመኔነት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቀጠናው ቢገባም የፋኖ ሰራዊት ከማህበረሰቡ እና አባት አረበኞች ጋር በመተጋገዝ የእግር እሳት ሆኖበት እንደ ልቡ በቀጠናው እንዳይንቀሳቀስ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ አሁን ላይ መውጫ መግቢያ አጦ እየተጨነቀ ይገኛል።

ይህ ከተለያየ ከተማ ተሰባስቦ ወደ ቀጠናው የገባው የአንበጣ ስብስብ ደም መጣጭ ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ እየፈፀመ ያለው ፀረ አማራ ቡድን አዳኝ አገር ጫቆ ገኒ ከምትባል ከተማ በመግባት ያልፈፀመው ፀያፍ ተግባር የለም። በየ አርሶአደሩ ቤት ክፍችኝ በመግባት እየዘረፉ፣የበሉትን እየበሉና የተረፈውን እንደ ዝንዠሮ እያበላሹ ከፍተኛ ንብረት ያወደሙ ሲሆን ሁለት አርሶአደሮችን ታደሰ መስፍን እና በቀለ ተገኘ የሚባሉ በማታ ከመኖሪያ ቤታቸው አውጥተው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ከገደሉ በኃላ በጩቤ አርደው ጥለዋቸው ተገኝቷል።ሌላኛው በገኒ ከተማ በየ ቤቱ ክፍችኝ በመግባት በገንዘብ ከ3ሚሊዬን ብር በላይ በንግድ ቤቶችና በመኖሪያ ቤቶች ከመዝረፋቸው ባሻገር የብዙ ቤቶችን በርና መስኮት አውድመዋል፤ የቤት እቃዎችን ሰብረዋል፣አቃጥለዋል። በተጨማሪም ገኒ ከተማ ላይ ከ2 በላይ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በማታ ስአት የገጠር አርሶአደሮችን መንደር በማፈን 4 መሳሪያ የዘረፉ ሲሆን በእለተ እሮብ በረት ውስጥ ያሉ 2 በሬዎችን ከአርሶአደሩ በመንጠቅ አርደው ሊበሉ ችለዋል።

የአምሀድንግል ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ሙሉጌታ ዋለልኝ ከቦታው እንዳሳወቀው ቀጠናው የገባው ይህ የክፉ ስርአት አራማጅ የአውሬው ተገዥ ሰራዊት በእንቅስቃሴው ሁሉ በደፈጣና በመደበኛ ውጊያ በየደረሰበት ሙሉ ቀኑን እየተቀጠቀጠ አመራርን ጨምሮ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ በየቦታው አስከሬኑን እያዝረከረከ ይገኛል። እንዲሁም አሁን ላይ ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ በሁሉም ቀጠና ሙሉ ሰራዊቱን ስምሪት በመስራት ጠላት ከገባ ላይወጣ ማህበረሰቡንም በማስተባበር ከበባ ውስጥ በማስገባት ክፉኛ ከፍተኛ በትር እያረፈበት ይገኛል።

በትናንትናው እለት ህዳር 3/2018 በአምሀድንግልና በአይሸሽም ብርጌድ የተገኘ ድል:
የሞተ = 26 በላይ
የቆሰለ = 32በላይ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 4/2018
🙏3