ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!

7ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ልዩ ኦፕሬሽን በአገዛዙ ጥምር ሀይል ላይ ከፍተኛ ድልን ማግኘት ተቻለ።
በልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከአፀደማርያም እና ሻሁራ ከተማ መሽጎ የነበረው 66ኛና 62ኛ ክ/ጦ የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ፣ተስቦ በአንድ የሞት ወረዳ ከገባ 7ኛ ቀኑን አስቆጥሯል። አልሞት ባይ ተጋዳይ ከገባበት መውጣት ሲያቅተው ባለበት ቦታ ሆኖ ፎቶ እየተነሳ ጭራሽ አፀዳሁ፣ማረክሁ፣በተንኋቸው እያለ በየሚዲያው መቀባጠሩ ግልፅ ነው። ሆኖም ግን እንዲህ እያለ የማፊያ የሚድያ ስራ እየሰራ ባለበት ቅፅበት በተመሳሳይ ቀን ከአድዋ ክ/ጦ እና ከኮሩ ተወርዋሪ የተውጣጣው የፋኖ ነበልባል ሰራዊት ወደ አፀደማርያም የመሸገውን ጥምር የወንበዴ ስብስብ መትና ቁስለኛ አድርጎ ከከተማው ማስወጣት ሲቻል በሁለተኛ ደረጃ በአድዋ ክ/ጦ በተመሳሳይ ስአት ከበባ ውስጥ የገባውን አረመኔ ቡድን ሲያበራዩት ውለዋል።

ይህ በእንዲህ አንዳለ ከትናንት ጥቅምት 23/2018 ከስአት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24/2018 ከጧቱ 4:00 ድረስ ይህኑ መግቢያና መውጫ ያጣው የአገዛዙ ጥምር አረመኔ ቡድን ወደ መጣበት ለመሸሸትና ለማምለጥ ሌሊቱን ጨምሮ ጥረት ቢያደርግም በአይበገሬዎቹ የአማራ የቁርጥ ልጆች አድዋ ክ/ጦ ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ተወርዋሪ ጋር በመጣመር እያዟዟሩ መግቢያ መውጫ አሳጥተውት ውለው አድረዋል። ሌቱን በሙሉ ሲኳትን አድሮ መውጫ በር ሲያመቻች ቢያድርም አነጋጉን በተከፈተበት መብረቃዊ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ እየተዝረከረከ፣ የያዘው ተሽከርካሪ ኦራል ፣አምቡላንስ ሁሉ ተመቶበት እየቀባጠረ እግሬ አውጭኝን ፈርጥጦ አውጣኝ አውጣኝ እያለ ሻሁራ ከተማ ከመሸገበት ምሽግ ሊገባ ችሏል።
የአገዛዙ ይህኑ ፀረ አማራ ቡድን ሸሽቶ ወደ መጣበት ሻሁራ ከተማ ለመግባት ሲያደርግ በነበረው የኋሊት ሩጫ በተከፈተበት ተኩስ የተገኘ ድል:
ሙት = 18 ፣
ቁስለኛ= 24 እና ሲጎዝበት የነበረው
2 ኦራልና 1 አምቡላንስ ቦዲያቸው ሙሉ በሙሉ ሊጎዳ ችሏል።
ሌላኛውና 2ኛው አውደ ውጊያ ሁለቱ የካራማራ እና የአጣናው ዋሴ የክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ አከለ አርበኛ ግዛት ከቦታው እንዳደረሱን በምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ መተማ ከተማ የተደረገው አውደ ውጊያ አመርቂ ድልን አስገኝቷል።
አናብስቶቹ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦ አሳምነው ብርጌድ እና አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ተካ ብርጌድ ጋር በመጣመር ጥቅምት 23/2018 አመሻሹን 12:00 ስአት ጀምሮ ጠላት ወደ መሸገበት መተማ ከተማ ተወርውሮ በመግባት እስከ ሌሊቱ 6:00 ድረስ ሲፋለሙት አድረዋል። በዚህ ልዩ የማታ ኦፕሬሽን የአገዛዙን ማፊያ ቡድን ክፉኛ መውጫ መግቢያ አጥቶ፣ የብልፅግናው አመራርም በየስርቻው ተደብቆ ሲሸበር እና ከባድ በትርም ሲያርፍበት አመሻሽቷል።
በዚህ የጣምራ የሌሊት ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:
ሙት=12 ሲሆን
ቁስለኛ =21 ሆኗል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 24/2018
🙏21
ሰበር ዜና!

ቀኝአዝማጅ ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር
እና
አንሻ ክፍለ ጦር የዋድላ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ኮንን ተቆጣጠሩ!

ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት የጀመረው ትንቅንቅ በፋኖ አሸናፊነት የዋድላወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ኮንን ፋኖ ተቆጣጠረ። የፋሽስቱ ሰራዊት ምንም ጥምር ሀይልን ተጠቅሞ በዙ23፣በሞርተርና በመድፍ ታግዞ ከረፋዱ 3:00 እስከ 11 ሰዓት የዘለቀ ውጊያ ቢያደርግም የእሳት ቁራጮቹ ፋኖዎች ምንም አይነት የምድር ሀይል ሳያስቆማቸው ከጥላት ምሽግ ሰብረው በመግባት ለቁጥር የሚታክት የጥላት ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ የዋድላ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ኮን ከተማን ተቆጣጥረዋል።

የማይነጥፍ የድል ዥረትን ለጆሮ እያሰሙ፤ብርቱ ክንዳቸውን በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ እያሳረፉ የሚገኙት ፋኖዎች የብልፅግናን ስርዓት እምሽክ ድቅቅ በማድረግ የማያዳግም የድምሰሳ እርምጃ ወስደዋል። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር የአንሻ ክፍለ ጦርና
የቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን ይህ ቀራችሁ የማይባል ድልን ተቀናጅተዋል።


አንሻ ክፍለ ጦርና ቀኝአዝማጅ ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦሮች ሁለት የአንድ ሳቲም ገፅታ ሆነው በጥላት ላይ ነድድ እሳት ጭረው አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥለውታል። ከጋሸና አጥር ግቢ እስከ ኮን እየከነፉ የጥላትን ሰራዊት እያነካከቱት የሚገኙት ግስላዎቹ በዛሬም እለት ዋድላ ወረዳ ኮን ከተማ ድረስ ዘልቀው የሽመልስ አብደሳን ስጋት ቅልቦች የአሞራ ሲሳይ አድርገውታል። በርካታ ሰራዊት የተደመሰሰበትና ቁስለኛ የሆነበት የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛውን በአይሱዚ መኪና ወደ ጋሸና ከተማ ሲያግዝ ውሏል።

የደጋው መብረቅ ኮር ከመመስረቱ ጀምሮ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የማይነጥፍ ብስራትን በድል ቀለም ከታሪክ ኑባሬ እየከተበ ይገኛል። ለፋኖ አንድነት ፋና ወጊ ሆኖ ብቅ ያለው የደጋው መብረቅ ኮር የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጥላት የሆነውን የብልፅግናን አከርካሪ ሰባብሮ በደረቱ እያፏቀቀ የሚሽመደመድ የክረምት አግቢ የእድሜ ባለፀጋ ከንቱ አድርገርውታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ሰይድክፍለ ጦር እና ቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
🙏2🔥1
ዞብል አምባ 5ተኛ ሻለቃ የደጋው መብረቅ አሃዶች ጋር በመጣመር ምኒልክ ዕዝ ኮን ከተማን ዳግም በተቆጣጠረበት ተጋድሎ የበኩሏን አስተዋጽኦ በማድረግ ድል አስመዘገበች::

ዛሬ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ከሮቢት በመነሳት ጥናት በተደረገ ውጊያ ዞብል አምባ 5ተኛ ሻለቃ የአገዛዙን ዙፍን ጠባቂ ሃይልና የአረጋ ከበደን ሆድ አደር ሚሊሻና አድማብተና ከሮቢት ከተማ እስከ ኮን ወረዳ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ያደረገች ሲሆን በአሁኑ ስአት ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ተኛ ሻለቃ ከደጋው መብረቅ አሃዶች ጋር በመሆን ኮን ከተማን ተቆጣጥራለች::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የጥላት ሃይል እሬሳውን እና ቁስለኛውን በመጣል ወደ ጋሸና ከተማ እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
2🙏1
የተሽከርካሪ ክልከላ ማሳሰቢያ።
ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ቡልጋ ክፍለጦር እና ነጎድጓድ ክፍለጦር የተሰጠ አስቸኳይ ማሳሰቢያ።

የብልፅግናው ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት የአማራን ህዝብ ትጥቁን ብቻ ሳይሆን ቀበቶውንም አስፈታለሁ በሚል ድንፋታ ወደ ክልሉ ዘው ብሎ በመግባት በአየር ኃይል፣በሜካናይዝድ እና በእግረኛ ሰራዊቱ መፋለም ከጀመረ ሁለት አመታትን አልፎ ሦስተኛ አመቱን ሊደፍን እነሆ አራት ወራት ብቻ ይቀሩታል።

ሆኖም የአማራን ህዝብ ከተባለው በተቃራኒው አቅሙንና የትግል ስልቱን በመቀያየር ሊያጠፋው የመጣውን አራዊት ሰራዊት ከነ ሙሉ አቅሙ በገባበት እየዋጠ እያስቀረው ይገኛል።

ስለሆነም በዚህ ምት የተበሳጨው አረመኔው የብልፅግና ሰራዊት በተለምዶ ሰሜንሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ህዝቡ በረሀብ ሲጎዳ አንበረክካለሁ በሚል ከሚከተሉት አምስት በሮች አራቱን በሮች ህዝቡ እንዳይንቀሳቀስ ላለፉት 2ሳምንት በላይ ዝግ ያደረገ ሲሆን ፤
1ኛ.ከጊናገር 👉ታሞ👉 ሶጠን(ጎራዴ)
2ኛ. ከጊናገር👉አሳግርት👉ቀይአፈር👉ጌልጌላ
3ኛ.ከጊናገር👉ወና👉ሜጢ
4ኛ.ከአሳግርት👉ሰኞ ገበያ👉ሀሙስ ገበያ👉ፅጌሬዳ👉ጫጫ(ደብረብርሃን ዝገግ የተደረጉ ሲሆን ከጊናገር👉ደብረብርሃን የአማራን ህዝብ ለመፍጀት እንዲያገለግል የአገዛዙን ሎጀስቲክና ተጨማሪ የሰው ኃይል ለማመላለስ ክፍት ሆኖ ይገኛል።

በመሆኑም ከ24/02/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም መንገዶች እስከሚከፈቱ ድረስ ከጊናገር 👉ደብረብርሃን ያለው ዋና መንገድ ከአንቡላን ውጭ ላሉ ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናል።
ይህንን ክልከላ ተላልፎ በሚገኝ አሽከርካሪ ወይም የአሽከርካሪ ባለንብረት ለሚወሰደው እርምጃ ክፍለጦሮቹ ኃላፊነት የማይወስዱ ሲሆን ችግሩ ፈጥኖ የማይፈታ ከሆነ በቀጣይ ወሳኝ እና አስተማሪ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
  
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
3👍2
ምዕራብ ጎጃም ቋሪት ወረዳ  ዶክተሩ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ ።

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ  የ102ኛ ኮር አካልበሆነው ገረመው ወንዳውክ  በሚያስተዳድረው  ገ/ማርያም ከተማ ወደ ወይበይኝ እንዲሁም ከገነት አቦ ከተማ ወደ ቦረቦር እንቅስቃሴ ያደረገ ቢሆንም ነበልባሎቹ የገረመው ወንዳውክ ልጆችን ክንድ መቋቋም ያቃተው አረመኒያዊ የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሀንን በአደባባይ ረሸነ፡፡
ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ሰራዊት የመጣበት አላማ ሳይሳካለት ሲቀር ምንም አይነት ከትግሉ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ግለሰቦች ድብደባና ግድያ እንዲሁም ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ 4 ሞተሮችን በማቃጠል  አረመኒያዊ ተግባባሩን ፈፅሟል፡፡
በግፍ ከተረሸኑት መካከል፡-
- አስማረ ግዛቸው የተባለ የወይበይኝ ጤና ጣቢያ የፋርማሴ ባለሙያ የነበረ ፋኖን ታክማለህ በሚል ከጤና ጣቢያ አውጥተው በአደባባይ ረሽነውታል
- ገቦየ መኩ የተባለ የወይበይኝ ቀበሌ ነዋሪ የነበረ የአዕምሮ በሽተኛ የነበረ  የአዕምሮ በሽተኛ መሆኑን እያወቁ ከገበያ ማህል ተረሽኗል፡፡

በአጠቃላይ የነበልባሎቹን የገረመው ወንዳውክ ልጆችን እጅ መቋቋም ያቀተው የአዛዙ ሰራዊት ንፁሀንን ከመረሸን በተጨማሪ የወይበይኝ ጤና ጣቢያ፣የወይበኝ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት እንዲሁም ሱቆችን በመዝረፍ የአረመኒያዊ ተግባር ጥግ አሳይተዋል፡፡
(በላይ ሞገስ የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ተወካይ ህዝብ ግንኙነት)

ይህን አረመኔያዊ ስርዓት የአማራ የሆነውን እና  አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት  እየሰራ መሆኑን  ካረጋገጥን ዓመታትን ያሳለፍን በመሆኑ ተረድተን በዱር በገደሉ እየተዋደቅን  አይቀጡ ቅጣት እየቀጣነው እንገኛለን። በመሆኑም  አማራ የሆነ ሁሉ በየትኛውም መንገድ ሕዝባችንን ለማዳን  በሚችለው  ሁሉ ሊታገል  ይገባል።

በተመሳሳይ ሁኔታ  የ102ኛ ኮር አካል የሆኑት ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ፒኮሎ ከተማ እና ቆጋ ግድብ ላይ ሲርመሰመስ በነበረ ጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም በአረመኔው ሰራዊት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራን ማድረስ ችለዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

        ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
6
ሰበር ዜና!

ደጀን ክፍለ ጦር እስታይሽ ከተማን ተቆጣጠረ!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ከጥላት ጋር ባደርጉት የ24 ሰዓት ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ዛሬ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ሌሊቱን የፋሽስቱን ሰራዊት 360° ድግሪ በመክበብ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የፈፀሙ ሲሆን የጋዞ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን እስታይሽ ከተማን ከፋሽስቱ ሰራዊት ነፃ አውጥተው ሌሊቱን ከተማዋን ተቆጣጥረዋል።

አስታይሽ ላይ ስሩ የተቆረጠው የፋሽስቱ ስርዓት አሁንተገኝ ወረዳ ላይ ራሱን ችሎ እዳይቆም ተደርጓል። አሁንተገኝ ወረዳ ላይ ያለው ወራሪ የእስታይሽ ወንድሙን ሞትና በትር ሲሰማ ሌሊቱን እግሬ አውጭኝ ብሎ ሸሽቶ አድሯል።

አሸባሪው ስርዓት ከዚህ ቀደም በፋኖዎች ተይዞ የነበረው የእስታይሽን ከተማ መካናይዝ ሀይል ተጠቅሞ በድሮን ታግዞ የገባ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በደጀን ክፍለጦር ድንገተኛ የ360° የሌሊት ከበባ የብልፅግናን ሰራዊት በመደምሰስ ሌሊቱን እስታይሽን መቆጣጠር ተችሏል።
በጥላት ላይ የደረሰውን የሞራል፣የቁስና የአካል እድሁም የህይዎት ኪራሳና ጉዳት በዝርዝር እና በቁጥር የምንመለስበት ይሆናለ።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
5🙏3
ሰበር ዜና

ከጋዞ ወረዳ እስታይሽ ከተማ እስከ ቦያ ሀሙሲት የፋሽስቱን ሰራዊት የመልቀም ስራ ሰኮንዶች ሁሉ ሳይባክኑ በተወሰደው ውጤታማ እርምጃ የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል፤የሚኒሻና ፖሊስ(ባንዳዎች) ጥምር የባንዳ ሃይል ገሚሱ ተደምስሶ ገሚሱ ተበታትኗል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር
ጥቅምት 25/2018 ም/ዓ ከረፋዱ ላይ
ከእስታይሽ  ወደ ጋሸና ሲፈረጥጥ በነበረ የጥላት ሰራዊት ላይ ደጀን ክፍለ ጦሮች ባደረጉት አሳዶ ጥላትን ማጥቃት እና ማጥፋት የእርምጃ ሂደት  ቦያ እየተባለች በምትጠራ ቦታ ላይ የብልፅግናው ጥምር ሰራዊት  መብረቃዊ ጥቃት ተፈፅሞበታል። በዚህ መብረቃዊ ጥቃት የፋሽስቱ ፓትሮል በአልሞ ተኳሽ ፋኖዎች ሲመታ ከአስር በላይ የፋሽስቱ ሰራዊት ሙት በቦያ ምድር ላይ ተቀብረዋል።በርካታ ቁስለኞቹን ወደ ጋሸና በመኪና ጭኖ ፈርጥጧል።

ከፋኖዎች የደረሰበትን ከባድ ጥቃት ለማስቀልበስ የፋሽስቱ ስርዓት ከሰማይ ድሮን ከምድር መድፍና ዙ23ትን ተጠቅሞ ቦያ ላይ የፋኖዎችን መብረቃዊ ጥቃት ራሱን ለመከላከል ቢሞክርም ከመደምሰሱ የፋኖዎችን ክንድ የሚያስቆም ምድራዊ ሀይል አልተገኘም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዋድላ ወረዳ ኮን ከተማ፣በጋዞ ወረዳ እስታይ ከተማ እና ሌሎች ፋኖ ነፃ ባወጣቸው ቦታዎች ከጥላት የተገኙ የጥላት መገልገያ መኪኖች፤የጥላት አልባሳቶችና የጥላት ሰነዶች በምስል ጭምር በዝርዝር የምንመለስባቸው ይሆናል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
🙏2
ግጭት ጠማቂው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ “ድሬዳዋ ከተማ የኦሮሚያ ነበረች” የሚል ንግግር መናገራቸው ይታወቃል። ይህ ንግግራቸው በሶማሌ ተወላጆች ዘንድ ከባድ ቁጣን እንደቀሰቀሰ ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ተመልክቷል።

በግጭት ጠማቂነታቸውና በደካማ አመራርነታቸው እንዲሁም በዘረኛና በሙሰኛ አገዛዝ ስርዓታቸው የሚታወቁት ዐብይ አህመድ፡ ሰሞኑን በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ "ድሬዳዋ ከተማ የኦሮሚያ ነበረች" ሲሉ ተናግረው ነበር።

በዚህም በሶማሌ ወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን፡ ወጣቶቹ ባካሄዷቸው ሕዝባዊ መድረኮችና ባገኟቸው የሚዲያ አማራጮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን በስድብ እስከመወረፍ የደረሰ ትችት ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል።

ይሄንን ተከትሎ የሶማሌ የጎሳ መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "ድሬዳዋ የኦሮሚያ ነበረች" ለሚለው ንግግራቸው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፡ ያለበለዚያ የወጣቱን ቁጣ ተከትሎ ለሚፈጠረው ቀጣይ ሁኔታ የለንበትም" ሲሉ አሳስበዋል።

የንፁኋንን ደም በገፍ ካላፈሰሱ መንግስታቸው የሚፀና አይመስላቸውም የሚባልላቸውና የተዛቡ የታሪክ ትርክቶችን በመናገር ግጭት መጥመቅ፡ ግጭት ቀስቅሶ ንፁኋንን መጨፍጨፍ፡ መዋሸትና መላላክ ልዩ ምልክታቸው እንደሆነ የሚነገርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፡ "የኦሮሞ ሕዝብን ትጠላላችሁ" በሚል ከዚህ ቀደም በርካታ የሶማሌ ወጣቶችን እያፈኑ ደብዛቸው እንዲጠፋ ማድረጋቸው ሲነገር ቆይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡ በሶማሌ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ መካከል ከዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረው ደም አፍሳሽ የእርስ በእርስ ግጭት ዳግም እንዲጀመርና አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁኋኖች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ፡ ሚሊዮኖች እንዲፈናቀሉና ሀብት ንብረታቸው እንዲወድም አበክረው እየሰሩና እያሴሩ እንደሆነ ነው መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የሶማሌ ተወላጆች የገለፁት።

@መረብ
3💔1
የመን ድንበር ላይ ከ10ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መታየታቸው አለምን አስደንግጧል።

ወጣቶቹ ኢትዮጵያ ሀገራቸው በጦርነትና በሙስና እንዲሁም በአንድ ብሔር የበላይነት ምስቅልቅሏ ስለወጣ ሀገሪቷን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ነው የታወቀው።

ብዛታቸው ከ10ሺ እንደሚልቅ የተነገረ ሲሆን፡ ብዛታቸውንና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ አለም ደንግጧል።

ያላባራ(እሱንም የእርስ በእርስ) ጦርነት፣ ሙስናና አድሎአዊ አሰራር፣ የብሔር የበላይነትና ባለጊዜነት፣ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ወጣቱን ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገውታል።

ተወልዶ ባደገበት አከባቢ የመኖርና ሀብት ንብረት የማፍራት እድሉን በአገዛዙ የተነፈገ ሕዝብ፡ ከፊት ለፊቱ ሌላ ሞት እንዳለ እያወቀም ቢሆን ያንን ለመጋፈጥ ወስኖ ስደት የሚሉትን የመከራ ቋት ይጀምራል።

ሀገር በአላዋቂዎችና በመሀይማን ስትመራ ትውልዷ ይመክናል፣ እርስቷ ይደፈራል፣ እሴቷና ባህል ወጓ ይናዳል።

የነ ዐብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ሕዝቡን ሀገር አልባ አድርጎታል።
💔2