ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ድረስ ሞላ የትግሉን አሁናዉ ሁኔታ በማስመልከት ያስተላለፈዉ መልዕክት!!!!!!
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ኃ/ማርያም ማሞ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀዳጀ።

ከጧቱ ጀመሮ እስካሁን ድረስ ዉጊያዉ የቀጠለ ሲሆን የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለጦር በሸዋ ቡልጋ ሀገረማርያም ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ነፋስ አምባ ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል።

የአጋዚ ኮማንዶ፣የሚሊሺያ እና የአድማ ብተና አባላት ላይ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠር የጠላት ሀይል ተደምስሷል።በአዉደዉጊያ ሁለት አንቡላንስ የጥምር ጦሩ ሙት እና ቁስለኛ ይዞ ወደ ሀገረ ማሪያም ከተማ ሆስፒታል ይዞ መግባቱ ተረጋግጧል።

ዉጊያዉ አድማሱን አስፍቶ የቀጠለ ሲሆን የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል።በሸዋ ቡልጋ የገበዉ የአገዛዙ ሰራዊት አብዛኛው ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ተከትሎ ጠላት ከቡልጋ ሀገረማሪያም ከተማ እና ከዙኖ መናገሻ ደብረብርሀን ከተማ በርካታ ሰራዊት ይዞ ቢገባም የሃይለማርያም ማሞ ልጆች የመጣዉን ጠላት በሚገባ እያናገሩት ይገኛሉ።

ዝርዝሩን እንመለስበታለን!!!!!

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ዶምፅ!!
🙏42
ዘመቻ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው !

ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ስም የተሰየመ ዘመቻ በማወጅ በኮሩ ስር ያሉ ክፋለጦሮችን ልዩ ዘመቻ በተመሳሳይ ሰዓት ውጊያ በመክፈት የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰበት ይገኛል::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር

ከመብረቅ ክፋለጦር አንድ ሻለቃ
ከአምሓራ ሳይንት መቅደላ ክፋለጦር 4ሻለቃ
ከታቦር ተራራ ብርጌድ አንድ ሻለቃ
ከኢ/ር ደሳለኝ አሰፋ ክፋለጦር አንድ ሻለቃ የተውጣጣ ጥምር ኃያል በተመሳሳይ ሰዓት የፋሽስቱ ሰራዊት ላይ የተጀመረው "ዘመቻ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው " በሚንቀሳቀስበት በነበረው አምሓራ ሳይንት ግንባር የታለመ ግብ ያለው ሲሆን ገና ከጅምሩ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም በበርካታ ድሎች ታጅቦ ፍልሚያው ተጠናክሮ ቀጥሏል::

በዘመቻው የመጀመሪያ ቀን ከቀኑ 9፡00 እስከ ጠዋቱ 1፡00 ሰአት ለተከታታይ 15 ሰዓታት ድረስ እጅግ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን ከኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ የመጣችው ሻለቃ ከመካነሰላም ከተማ ተነስቶ ሽፋን ሊሰጥ የገሰገሰውን ጥምር ጦር ቀይ ዋሻ ( ጓሳ) ላይ ወገቡን ብላ መልሳዋለች። በተመሳሳይ መልኩ ከታቦር ተራራ ብርጌድ የመጣችው አንድ ሻለቃ ከአምሓራ ሳይንት በወርቅ ማውጫ በኩል ገብቶ ሊያግዝ የነበረውን ጥምር ጦር ድባቅ መታዋለች።

የተቀረው ሻለቃ ሙሉ ለሙሉ መሀል ሳይንት ወረዳ( ዴንሳ ) በመግባት ቀድሞ በኮንክሪት የተሰራ ምሽግ ውስጥ የገባውን የአድማ ብተና እና የሚኒሻ ኃይል እንደቅጠል አርግፎታል።

በዚህ እልህ አስጨራሽ የኮንክሪት ምሽግ ለመስበር በተደረገ ተጋድሎ አድማ ብተና 17 የሞተ ፣ 9 ከባድ ቁስለኛ ማረግ የተቻለ ሲሆን ሚኒሻ እና ፓሊስ 5ት የሞተ ከባድ ቁስለኛ 2 ማረግ ተችሏል። በዚህ የኮንክሪት ምሽግ ሰበራ ተጋድሎ በወገን ኃይል በኩል 2ት ቀላል ቁስለኛ እና 1 የፋኖ አባል ተሰውቷል።

ዛሬ ጠዋት ደሞ 3ት ሚኒሻ ማስከዳት ተችሏል።

ዝርዝሩን በማስረጃ ይዘን እንመለሳለን!

ዘመቻ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ተጠናክሮ ይቀጥላል !

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር

ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም
👍31🙏1
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በዘመቻ ኮማንዶ ደምሰው ከተማው ከፍተኛ የጦር ሜዳ ድል አስመዘገበ::

በምዕራብ ወሎ ግንባር መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ ከትናንት ማለትም ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው ትንቅንቅ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት የመሀል ሳይንት ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ደንሣ ከተማ ውስጥ መግባቱ ተርጋግጧል::

ከኮሩ ሰራዊት መካከል የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣ የመብረቅ ክፍለ ጦር እና የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የተወሰኑ አሃዶች ተውጣጥተው በሰሩት ኦፕሬሽን እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከ30 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን 1 የአድማ ብተና ሻለቃ መሪ እና 1 ሻምበል መሪ እንዲሁም 3 የወረዳ አመራሮችም አብረው እስከወዳኛው ተሸኝተዋል:: የተደመሰሰው ጠላት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ይገመታል::

በኦፕሬሽኑ 11 የጠላት ምርኮኛ እንደተያዘም ነው ለማረጋገጥ የተቻለው::

በምኒልክ ዕዝ ም/ዘመቻ መሪ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ፣ በዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ እና በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ በአርበኛ አብነው ታደሰ እንዲሁም በዕዙ ወታደራዊ አማካሪ በሻለቃ ክንዱ ሰውነት የተመራው የደንሣው ኦፕሬሽን የጠላት 4 ከባድ ምሽጎች የተሰበሩበት መሆኑም ታውቋል:: በከተማይቱ ዳር ማለትም በጎራደ ሽነት፣ በዙሀ፣ በጎጃም በር እና በሙያ እና ቴክኒክ ጠላት ያዘጋጃቸው ምሽጎች ሙሉ በሙሉ ተሰብረዋል::

ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ንብረቶች በኮሩ ሰራዊት እጅ ገብተው ወደ ፋኖ የጦር ሰፈር የተወሰዱ ሲሆን በኮሎኔል መብሬ የተመራው የጠላት ኃይል ከእስከዛሬው በበለጠ አኳኃን ከባድ ሰብአዊ ኪሳራ ጭምር እንደደረሰበት ነው የውስጥ ወታደራዊ ምንጮች የገለፁት::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏1
"አማራውን እርስ በእርሱ ደም አቃብተነዋል"

ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል) ፈተን እንለቅበታለን።
ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ

ሚሊሻ ሆኖ ከፋኖ ቤተሰብ ያልገደለ የለም በተመሳሳይ ፋኖ ሆኖ ከሚሊሻ ቤተሰብ ያልገደለ የለም ። በአማራ ባህል ደግሞ ደም ሳይመልሱ መቅረት እንደነውር የሚቆጠር ነገር አለ ፣ ስለዚህ አሁን ላይ ዕርስበርስ ለግድያ የሚፈላለጉ ደመኞች ሆነዋል፥ ፋኖን አጥፋልን ብለን የምንለምነው ሚሊሻ አይኖረንም ለራሱ ሲል የራሱን ህይወት ለማትረፍ ሲል ያለምንም ክፍያ ፋኖን ያሳድድልናል።በእንደዚህ አይነት መንገድ እጃችንላይ ያለውን ገንዘብ ለሚሊሻ ከመበተን ድነናል፣ ገንዘቡን ለገዳ ልዩ ኮማንዶ ማሰልጠኛ እና መሳሪያ መግዣ ይውላል። አማራ ከዚህ በሗላ ከነሙሉ ክብሩ በአባገዳ ልጆች ፊት የሚቆምበት ዘመን አብቅቷል ማንም አባከና የሚለው ሰው አይኖርም። ቀደም ብየ እንደነገርኳችሁ አማራ ከዚህ በኋላ እስከምፅዓት ድረስ ምንም አይነት የፖለቲካ ወሳኔ ሰጭነት ሚና እንዳይኖረው አድርገን ሰርተናል አንዳንዶች ይሄን ስንል መታበይ ይመስላቸዋል ነገር ግን ፖለቲካውን የሰራነው ሰዎች ስለምናውቀው ነው። ከእንግዲህ ኦሮሞ ማድረግ ያለበት ስትበድለው ከነበረችው ሚኒሊክ ሰራሽ ሐገር ቁጭ ብሎ ካሳ መቀበል ብቻ ነው። ከኦሮሞ ጋር ሰላም ፈጥሬ እኖራለሁ የሚል አካል ካለ እሱን እንቀበላለን ነገር ግን አካሔዱ የሚሆነው ኦሮሞ በሚወስንለት ማነኛውም ህግና ድንጋጌ ሊመራ እና ሊተዳደር አምኖ ከተቀበለ ብቻ ይሆናል። ይሄን ካልተቀበለ ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል)ፈተን እንለቅበታለን ማለት ነው።

-ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ገዳ ልዩ ኮማንዶ የምርቃት ስነስርዓት ላይ የተናገሩት።
3👎1💔1
ሰበር ዜና!

በሁለት ተሽከርካሪ ተጭኖ ከለሚ ወደ ጀማ በመጓዝ ላይ ያለ የአገዛዙ መከላከያ አራዊት ሰራዊት ጃሎታ በተባለች ቦታ ተደመሰሰ።

የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አፄ ዘርዓ-ያዕቆብ 1ኛ ኮር ቃኝዎች በRPG እና ቦንብ በወሰዱት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት በሁለት መኪና ተጭኖ ወደ ጀማ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ጃሎታ በተባለች ቦታ ከነ ተሽከርካሪው ማጋየት ተችሏል።

እድል ቀንቷቸው የተረፉት የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይሎች ሙሉ ለመደምሰስ ከፍተኛ ትንቅንቅ እየተደረገ ሲሆን ዝርርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
6🙏6
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለከተማ ልዩ ቦታው ውሃ ጋን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው የሚሊሻ ካምፕ ላይ ከባድ ጥቃት ተፈፅሞ በርካታ የሚሊሻ አባላት ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ጥቅምት 03/2018 ዓ/ም ንጋት ላይ ሲሆን፡ ደቂቃዎችን በፈጀ ኦፕሬሽን ነው በሚሊሻ አባላቱ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ የተቻለው ተብሏል።

በከተማዋ ውሃ ጋን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በነበረ የሚሊሻ ካምፕ ላይ ጥቃቱን የፈፀሙት በአፋብኃ አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ 6ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኙት የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ አባላት መሆናቸውንም የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
🙏3
በንፁሐን ላይ የድሮን ጥቃት ደረሰ

ፋይሽቱ ኃይል አዴት አቅራቢያ በምትገኘው ሮብገበያ ተብላ በምትጠራ ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት ንፁሐንን አርሶአደሮች መገደላቸው ታውቋል።

የአሻራ ምንጮች ከቦታው እንዳረጋገጡት ከሆነ ከቀኑ 6:00 ሰዓት አካባቢ ዛሬ ጥቅምት  03/2018 ዓ.ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት አቅራቢያ ልዩ ስሟ ሮብገበያ በተባለች ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም የቀንድ ከብቶችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን የአይን እማኞች ለአሻራ ገልጸዋል።
ዘራፊወች ላይ እርምጃ ተወሰደ::

ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰአት ላይ በመሸንቲ መስመር ልዩ ቦታው መቶ ካብ ተብሎ የሚጠራው ቦታ በፋኖ ስም የተለያዩ ዝርፊያወችን ሲፈፅሙ የነበሩ የአረመኔው ስርዓትና አሽከር ተባባሪ የሆኑ አካላት ላይ የጣናዉ መብረቅ ብርጊድ ቃኝና መሃድስ ባደረጉት የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን ደረጀ ሞላ የተባለ ሚሊሻ እስከወዳኛዉ የተሸኘ ሲሆን በዚህ ቀጠና ላይ ያለውን የሚፈፀሙትን ወንጀሎች በመከታተል ቀጣይነት ያለው እርምጃ ለመውሰድ ብርጌድ በትኩረት እየሰራ ሲሆን ህዝቡ ማንኛውን ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩን በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

   ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም
4🙏1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ በተለያዩ አዉደዉጊያዎች ድል አደረገ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ዓፄ ዘረ ያቆብ አንደኛ ኮር የኮሩ ቃኝዎች በአገዛዙ ሁለት ተሽከርካሪ ተጭኖ ከለሚ ወደ ጀማ በማጓዝ ላይ እንዳለ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል።

በሌላ መረጃ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ኃ/ማርያም ማሞ ክፍለጦር በሸዋ ቡልጋ ሀገረማሪያ በስድስት ቦታዎች አዉደዉጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል።

ትናንት መስከረም 2/2018 ዓ.ም ከጧቱ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ድረስ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሲደረግ ዉሏል።

አዉደዉጊያ ከሀገረማሪያም ወጣ ባሉ እንደ ሾላገብያ፣ነፋስ አንባ፣ዛላዘንባባ፣ቁምድንጋይ፣የኔ ቾክ እና ስላሴ ሰፈር የተደረገ ሲሆን በእነዚህ አካባቢዎች በተደረገ አዉደዉጊያ በአገዛዙ ጥምር ጦር ሀይል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

ሁለት ተሽከርካሪ አንቡላስ ሙትና ቁስለኛ የአገዛዙ ጥምር ጦር ወደ ሀገረማሪያም ሆስፒታል የገባ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገዱ የአጋዚ ኮማንዶ አባላት ደግሞ ወደ ጦር ኃይሎች ተወስደዋል።

ዝርዝሩን ማታ 2:00 በመረጃ ቲቪ ይጠብቁን!!!!

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!
🙏3