ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ፤

"እኔ ብሞት ደሜን የምትመልሱት ገዳዬን ገድላችሁ ሳይሆን የአማራ ህዝብን ነፃ አውጥታችሁ ነው" በማለት በህይወት ሳለ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋውን ህልፈት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ እለት አስመልክቶ የተላለፈ ድርጅታዊ መልዕክት:-

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አዛዥ እንዲሁም የመሀል ሳይንቱ አትሮንስ ብርጌድ አዛዥ የነበረውና ቀደም ብሎም ከምስራቅ አማራ ፋኖ (2013 ዓ.ም) ጀምሮ በትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሆኖ ጀብዱ የፈፀመው የቦሩ ሜዳው ውጊያ ፊታውራሪ እና ፅኑው ታጋይ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በድህረ ሰሜኑ ጦርነት ወቅት የያኔው ምስራቅ አማራ ፋኖ የሰጠውን ግዳጅ ተቀብሎ ወደ ትውልድ አካባቢው መሀል ሳይንት ወረዳ በማቅናት ወጣቶችን በማንቃት እና በመመልመል እንዲሁም በፋኖነት በማደራጀት ጉልህ ሚና ተጫውቶ በወርሀ መጋቢት 2015 ዓ.ም ይፋዊ የህልውና ፍልሚያ ስንጀምር እሱም ባለበት ግንባር ኃይሉን ሸክፎ ቀጥታ ወደ ትግሉ በአዲስ መልኩ መግባቱ ይታወሳል::

የህልውና ትግሉ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ወራት በፅናት እና በጀግንነት በውጊያ ሜዳው ላይ ታይቶ አምና ልክ በዛሬው እለት ማለትም ነሀሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በባንዳ በተተኮሰ ጥይት በድንገት ያጣነው የትግል ጓዳችን እና ወንድማችን ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በትግሉ ሂደት የሚከፈለው መስዋዕትነት በጠላት በተተኮሰ ብቻ ሳይሆን በወገን ጥይት ጭምር ሊሆን እንደሚችልና በሁለቱም አቅጣጫ ለሚተኮስ ጥይት ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል:: በወገን ባለጋራ እጅ መሞት የትግሉ ሜዳ እንድጠራ በር የመክፈት መስዋዕትነት ሲሆን ጀብዱ ፈጽሞ ጥሎ እንደ መውደቅ ማለትም ልክ በጠላት እጅ እንደመሞት ያለ ክቡር መስዋዕትነት ነው::

ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በጆፌ ኢትዮጵያኒስቱ ኃይል ሳይታለል በአማራ ብሔርተኝነት እና በእውነት ፍፁም አልደራደርም ብሎ አሰላለፉን አሳምሮ ለወሎ ቤተ አማራ ፋኖ አንድነት የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ የከፈለ አርበኛ ብቻ ሳይሆን ንፁህ ትግልን ታግሎ በማለፍ ሌሎች ንፁህ ታጋዮችን ማፍራት የቻለ የህልውን ትግሉ ደማቅ ምልክትም ነው:: የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሰራዊት እና አመራሮች ለፋኖአዊ አንድነት እና ለአማራዊ እሴት ያላቸውን ትልቅ ቦታ አስረጅ የሆነው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ንፅህና እና እውነት የታጋዩ እና የትግላችን መሰረት መሆኑን ማሳያነቱ አያጠራጥርም::

ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በምዕራብ ወሎ ግንባር መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ በተለምዶ አህዮ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ሰኞ ገበያ የተባለ ስፍራ ላይ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመምራት ላይ ሳለ አንድ ቅጥረኛ ባንዳ ግለሰብ በተኮሰው አውቶማቲክ ጥይት ተመትቶ ቢሰዋም ባንዳው ላይ የመሀል ሳይንቱ አትሮንስ ብርጌድ አባል የሆነ ጀግና ጓድ በጀት ፍጥነት እርምጃ መውሰዱን እንዲሁም በማግስቱ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ከመፈፀሙ የተወሰኑ ሰዓታት ቀደም ብሎ የክፍለ ጦሩ አካል የሆነው ታቦር ተራራ ብርጌድ ሰራዊት ከመሀል ሳይንት ወረዳ ቀጥሎ የሚገኘው አማራ ሳይንት ወረዳ ውስጥ ፓትሮል በማቃጠል ከአንድ ቲም ያላነሰ ጠላትን በመደምሰስ 3 ክላሽ እና 1 ብሬን ከነ ሽልንሼሉ መማረኩ አይረሳም:: በእለቱ እለት እና በማግስቱ ደሙ የተመለሰለት ጓዳችን እና የትግል ወንድማችን ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በህይወት ሳለም ሲናገር የነበረው "እኔ ብሞት ደሜን የምትመልሱት ገዳዬን ገድላችሁ ሳይሆን የአማራ ህዝብን ነፃ አውጥታችሁ ነው" በማለት ነበር:: በዚህም መሰረት ለነፃነት እና ለህልውና የሚደረገው ትንቅንቅ እና የሚከፈለው መስዋእትነት ቀጥሎ ሰራዊታችን በየእለቱ ጀብዱ እየፈፀመ መሆኑን ያስታውሷል::

"ገንዘብ ስታዩ አትደንግጡ" የሚለውን የዋርካው ምሬ ወዳጆ ወርቃማ ምክር በመተግበር ለገንዘብ ባለመደንገጥ በእውቀት እና በታማኝነት እንዲሁም በጀግንነት ታግሎ በንፅህና ያለፈው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው "ሲርባቸው ይመጣሉ" ያሉን ወገኖችን ጭምር አሳፍሮ የመለሰ የሀቅ እና የእውነት ታጋይ በመሆኑ ሁሌም ስሙ ሲዘከር በአርአያነትም በየመድረኩ በክብር ሲጠራ ይኖራል::

ለቀጠናዊ መናበብ እና ለአማራዊ አንድነት ልዩ ቦታ በመስጠት አንድ የፋኖ ድርጅት እንድፈጠር ለማድረግ ደፋ ቀና ሲል የነበረ መሆኑም አይረሴ ነው::

ከምስራቅ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ፋኖወች ጋር ቀጠናዊ ትስስር በመፍጠር ለአማራዊ አንድነት መደላድል ሲፈጠር የነበረው ይህ ጀግና ያፈራው ሰራዊት በምዕራብ ወሎ ግንባር ከመሀል ሳይንት ተነስቶ ወግዲ እና መካነሰላም እንዲሁም ከላላ እና መቅደላ ብሎም ተንታ እና ሌሎች አጎራባች ወረዳወች ድረስ ታሪክ ሰርቷል፤ እየሰራም ነው::

የአንድነት ሀዋርያው፣ በእውነት እና እውነት ይታወቅ የነበረው...ጎጥ እና ጥቅም የማይበግረው ከገንዘብ ይልቅ ህዝብን አስቀዳሚው ንፁሁ ታጋይ ቢሞትም ስሙ አልተቀበረም፤ ትግሉም ተቀጣጥሏል እንጅ አልቀዘቀዘም::


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሀሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
👍42
እየጨመረ የመጣው ቀጠናዊና የውስጥ ስጋት፤ የአማራ ፋኖ አንድነት አስፈላጊነት በሻለቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ
እየጨመረ የመጣው ቀጠናዊና የውስጥ ስጋት፤ የአማራ ፋኖ አንድነት አስፈላጊነት በሻለቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ
🙏2
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የኦርቶዶክሳውያን ግድያ መቀጠሉን ምእመናን ተናገሩ።

የ75 ዓመት የእድሜ  ባለፀጋው  ካህን  ማንነታቸዉ ባልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም  በአሰቃቂ  ሁኔታ ተገድለዋል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት በመሰራንጄ  ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት
ቀሲስ ንጉሴ ወልደ መድኅን ማንነታቸዉ ባልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ሌሊት በአሰቃቂ  ሁኔታ መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።።

የ75 ዓመት አረጋዊው ካህን ደከመኝ  ሰለቸኝ  ሳይሉ ከልጅነት እስከተገደሉበት  ቀን  ድረስ  ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከዲቁና እስከ ቅስና አገልግለዋል።

በአገልግሎት ዘመናቸውም ዳሪሙ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር  አሠርተው  ለአገልግሎት  ማብቃታቸው ተጠቅሷል።

የቀሲስ ንጉሴ ወልደ መድኅን ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

በምስራቅ  አርሲ ሀገረ  ስብከት በሮቤ ወረዳ እየተባባሰ የመጣዉን የኦርዶክሳዉያን መከራ እና ሞት የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸዉ  በተደጋጋሚ  ጊዜ የአካባቢው  ምእመናን ጥሪ ቢያቀርቡም  አሁንም  ድረስ  የኦርቶዶክሳውያን  ግድያና  መከራ  እንዳላበቃ  ከምእመናኑ  አንደበት  ተገልጿል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
5
ሰበር ዜና

ፋኖ በምህረት ገብቷል በሚል ድስኩር ፈንጠዝያ ላይ የዋለው የአገዛዙ ጥምር ሃይልን የጎንደሬ በጋሻው ከፍለ ጦር ቴውድሮስ ብርጌድ አባላት ደስታውን ወደ ለቅሶ ቀይሮለታል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዛሬ ነሀሴ 25 /2017 ዓ/ም ከጠዳ ዩኒቨርስቲ ምረት የገቡ ፋኖዎች ተሀድሶ በሚል ድስኩር ከህዝብ በዘረፋት ሀብትና ንብረት የአገዛዙ አመራሮችና ወንበር አስጠባቂ ሀይሎች በድግስ ፈንጠዝያ ውለው ከቀኑ 11 ሰዓት ወደ ማክሰኝት ከተማ ሲያመሩ የቴውድሮስ ብርጌድ አባላት ምንዝሮ ቀበሌ ላይ ደፈጣ በመያዝ ጥጋባቸውን ወደ ለቅሶ ቀይረውታል።

የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ ብርጌድ ጀግኖች ዛሬ የአገዛዙን ጥምር ሀይል የቁርጥና ቢራ ጥጋባቸውን እንደ ጎማ በማፈንዳት አስተንፍሰው ከስምንት ኪሎ ሜትር በላይ አስፈርጥጠው ሰባቱን ወደሞ*ት ሸኝ*ተው 12ቱን ከባድና ቀላል ቁስለኛ አድርገው የሀዘን ማቅ ውስጥ ጥሏቸዋል።

በውጊያው ጠዳ ዩንቨርስቲ ለአቀባበል የመጡ አመራሮችና የአገዛዙ ባለስልጣናትም በፍራቻና በድንጋጤ ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወደ ጎንደር ከተማ ፈርጦጠው ሂደዋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር : የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
3🙏2
ሰበር

ኮለኔል ገመቹ ወለጋ ላይ ተሸኝቷል።
እርማቹህን አውጡ እኛ እርም አንበላም።

ነሐሴ 25/2017ዓ.ም

ቢዛሞ ሚዲያ
6🙏3
#የሃይማኖት_አባቶችን_መግደል_ያልተጻፈ_ሕግ_ኾኗል!

ባለፉት ሰባት አመታት ታላላቅ የሃይማኖት አባቶችን እያደኑ መግደል፣ ግድያውንም ማዳፈን ዋና ተግባር ኾኗል።

ቅዳሜ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 5:00 በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሮቤ ወረዳ፣ መሰራንጄ አቦ የሚገኘው የኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የኾኑት የ78 ዓመት አረጋዊ ካህን መምሬ ንጉሴ ወ/መድኅን በቤታቸው በታጣቂዎች በጥይት ተደብድበው ተግድለዋል። ኦሮሚያ ክልል በተለይ አርሲ ዞን የደም መሬት ኾኗል። መግሥትም መንግሥታዊ መዋቅርም የለም ቢባል ማጋነን አይኾንም። እጅግ በተናበበ መልኩ በየቀኑ በሚባል ደረጃ የሃይማኖት አባቶች ይታገታሉ፤ ለሌሎች መቀጣጫ እንዲኾኑ በአሰቃቂ ኹኔታ ይገደላሉ። አኹን አኹን እንዲያውም ግድያው ወደመለመድ/normal/ ደረጃ ደርሷል።

በተያያዘ መልኩ እሑድ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ክ/ከተማ የሚገኘው የጎጆ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የድጓ መምህር የሆኑት መምህር አፈወርቅ አበባው ምሽት 1:00 ላይ በተለምዶ ጣፎ አደባባይ፣ ገደራ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደቤታቸው በመግባት ላይ ሳሉ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ከቤተሰብ ምንጮች ማረጋገጥ ችለናል። መ/ር አፈወርቅ የአንድ ልጅ አባት ነበሩ።

በሩቅ እንሰማው የነበረው አሰቃቂ ግድያ ዋና ከተማችን ሰተት ብሎ መግባቱ የሰነበተና እየተለመደ ያለ እውነት ቢኾንም በአደባባይ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ የሃይማኖት አባት በዓለም የድፕሎማቲክ ከተማ አንዷ በኾነችው አዲስ አበባ ተድበስብሶ መታለፉ መላ ሕዝብ በምን ዓይነት የሞት ጥላ ሥር እንደሚኖር ጉልህ ማሳያ ነው።

እናት ፓርቲ እንዲኽ ያለውን የሃይማኖት አባቶች ላይ ያነጣጠረና ከጫካና ከከተማ የተቀናጀ ግድያ በጽኑ ያወግዛል፤ ለሞቱት ነብስ ይማር እያልን ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን እንመኛለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
💔1😭1
በአፋጎ የ5ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ ብርጌድ ከስድስት ወራት በላይ ያሠለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎችን አስመረቀ።
🙏2

‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ የትግሉን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ ውይይት አካሄደ
‎================
‎የአፋብኅ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አጼ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር የሚኒልክ ብርጌድ ሶስት ሺ አለቃ፥ የአባት አርበኞች እና የጎበዝ አለቆች በተገኙበት የትግሉን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ ውይይት አካሄደዋል።

‎ውይይቱ የተካሄደው የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና መሪ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፥ የእዙ ምክትል ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ አሳለፍ ደስታ፥ የአጼ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር መሪ ፊታውራሪ ልመነው ዘውዴ እና የአጼ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው።

‎በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ዋና መሪ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ሰራዊቱ ለማይቀረው ግዳጅ ሁለተናዊ ዝግጅት አድርጎ የድል ዋንጫ ለማንሳት መዘጋጀት አለበት  ሲሉ አሳስበዋል።
‎ጠላትን ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀን አንገት የምናስደፋበት አቅም ፈጥረናል ያሉ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ጉድጓድ የቆፈረ ማንኛውም አካል በቆፈረው ጉድጓድ የሚቀበርበት ዋዜማ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
‎የአማራ ህዝብ በጦርነት ተሸንፎ አያውቅም ያሉት ኢንጅነሩ የድል ዋንጫውን በአጭር ጊዜ ለማንሳት ከአመራሩ እና ከሰራዊቱ የሚጠበቁ ያሏቸውን ሀሳቦች በዝርዝር አቅርበዋል።

‎በውይይቱም ሀሳባቸውን የሰጡት የሰራዊት አባላት ጦርነት ለአማራ ሕዝብ የባህል ጨዋታ መሆኑን በመግለጽ ከሰራዊቱ፥ ከማህበረሰቡ፥ ከአባት አርበኛው እና አመራሩ የሚጠበቁ ጉዳዮችን በአስተያየትና ጥያቄ መልክ አንስተው መልስ ተሰጥቶባቸዋል።

‎ከሰራዊቱ አባላት፥ አባት አርበኛ እና ጎበዝ አለቃ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች መልስ የሰጡት አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ በየቦታው ትንኮሳ የሚፈጥሩ አካላት ከአራት ኪሎ ተልእኮ ተቀብለው የመጡ ተላላኪ የሸኔ አባላት መሆናቸውን ተገንዝበን ጉዟችንን ወደ አባቶቻችን ርስት የዳዊት ከተማ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

‎አያይዘውም ኢንጅነሩ የአባቶቻችንን ርስት ተረክበን የብልጽግናን የጥፋት ቡድን ግባተ መሬት ከፈጸምን በየቦታው የሚነሱ ትንኮሳዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሰላማዊ አውድ ይመለሳሉ ሲሉ ተናግረዋል።

           ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
🙏31