ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር በትምህርት ማስጀመር ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር ያደረገዉ ዉይይት!!!
2🙏2
የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር የክረምት አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎችና የተሰሩ ስራዎች
//
ክ/ጦራችን ክረምቱን ወራት በአግባቡ ስራ ሰርቶ ለቀጣይ  የትግል አመት ጠንካራ ሆኖ ለመውጣት እቅድ ነድፎ ነበር ክረምቱን የተቀበለው።በመሆኑም በሰኔው መጨረሻ የጠቅላይ እዙ በዛጎች ጉባኤውን ካጠናቀቀ በሗላ ዘመቻ ሰማዕታት መታወጁ ይታወቃል።በመሆኑም የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር በቀጥታ እዛው ጉባኤው በተጠናቀቀ ዕለት ወደተግባር የተገባው።
የክ/ጦራችን መሪም ከወግ ይልቅ ተግባር የሚቀድመው አርበኛ ተሾመ አበባው ወዲያውኑ ሰኔ 27/2017 ዓም የተራራው ራስ ጉና እና አንበሳው ጋይንት ክ/ጦሮችን በመያዝ ጉና በጌምድር ክ/ድንጋይ በመግባት ድልን ተቀዳጀ።
በዚህ አውደ ውጊያ የተገኙ፦
👉2 ዲሽቃ
👉 ብሬን እና ስናይፐር
👉በርካታ ክላሽ
👉በርካታ ተኳሽ
👉በርካታ ምርኮኞች ሲያዙ ሌላው ተደምስሷል።
🎤ወዲያውኑ መቀጠዋን ለመያዝ አጃ ሰፍሮ ሲርበደበድ በመቆረጡ ምክንያት ለቆ በለሌት የጠላት ሀይል ደ/ታቦር ገብቶ አደረ።
2/ ደጋ_መልዛ እብናት
ክ/ጦራችን ሳይውል ሳያድር ከክምር ድንጋይ ድል መልስ በቀጥታ ተጉዞ እብናት ወረዳ ደጋ መልዛ ላይ ከጠላት ጋር ተፋለመ።
በዚህ ፍልሚያ እጅ ከአፍ የሚያስጭን አጃኢብ የተባለለት ድል ተመዘገበ።
የተገኙ ድሎች
👉1 ዲሽቃ
👉1ሞርተር
👉ከ100 በላይ ምርኮኛ
👉ኮሎኔል ሁሴን ጨምሮ ከ200 በላይ የደመሰሰ
👉በርካታ የቡድን መሳሪያ ብሬን ስናይፐር
👉ከ270 በላይ ክላሽ
👉በርካታ ተተኳሽ ተገኝቷል።
ከጋ መልዛ በቀጥታ እብናት በመግባት ለ2 ቀናት ወረዳውን ተቆጣጥሮ ከደብረታቦር የመጣን ጠላት ተጨማሪ ደምስሶ የማረከናበርካታ ሚኒሻ የተደመሰሰበት ሆኗል።

3/ቋሊሳ_ድርኳዜ
ክ/ጦራችን የአመራር ሪፎርም ለማድረግ የእብናት ወረዳ ንዕስ ከተማ ወደሆነችው ቋሊሳ አቅንተን ነበር።በመሆኑም ይሄ እምነት የለሽ ሰይጣን የፍልሰታ በዓል በሰላም እንዳይውሉ በሚል በሰፈር ካብኔ እየታዘዘ ወደ ቋሊሳ በሌሊት ሲጓዝ አድሮ ቋሊሳ ይደርሳል።እኛም ጦራችን ቦታ ቦታ አስይዘን ድርኳዜ ከሚባል ቦታ ከበባ አድርገን መቁላት ጀመርን ጠላት ቋሊሳ የመግባት ህልሙ ጨልሞበት ወደሗላም ወደፊትም ፈቀቅ ማለት ተሳነው።ነሐሴ 15 ውሎውን ሲቀጠቀጥ ዋለ።ወደማታ በጀርባው ስንቆርጠው ከእብናት ተጨማሪ ይዞ ሲመጣ ግማሽ ሐይል ገላ መታጠቢያ አስቀምጠን ስለነበርን በደፈጣ ሲለበለብ እንኳን ሊቀበል ወደ እብናት አይግባኙን ፈረጠጠ።የተቆረጠው ሀይልም የጣለውን እየጣለ አይግባኙን 38ኪሜ እየሮጠ እብናት አስገባነው።
የተገኙ ድሎች
👉ስይፐር
👉ከ60 በላይ ክላሽ
👉7 የተማረኩ
👉75 በላይ የተደመሰሱ በጅምላ ማህበረሰቡ የቀበራቸው
👉48 ቁስለኞች 23ቱ ከባድ ተብለው ባህር ዳር የገቡ
👉የመከላከያ ሪፖርተር የተገደለ
ሲሆን ገላ መታጠቢያ የተመቱት እስከ እብናት በየመንገዱ ደም እያዘራ የደከመውን ራሱ እየረሸነ የተረፈው እብናት ገብቷል።
  🎤የተሰሩ ማህበራዊ አገልግሎቶች
ትምህርት በአዲ አመት እንዲመርለት ህዝቡ በጠየቀው መሰረት ትምህርት ቤቶችንና ቅጥር ግቢያቸውን ማህበረሰቡን በማስተባበር እንዲፀዱ አድርገናል።
በተለይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያሉባቸውን አካባቢዎች ቋሊሳ፣ገላ መታጠቢያ፣ደጋ መልዛ፣አጊሳ_መቀጠዋ ት/ቤቶቹና ከተሞቹ እንዲፀዱ ሆኗል።
መምህራኖችና አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች ሲመጡ ምቹ እንዲሆን ማረፊያ ዶርሞች እንዲስተካከሉ ተደርጓል።
   በቀጣይ በጠላት ግዴለሽነት የተሰባበሩ ወንበሮች እንዲጠገኑና አግዳሚ ወንበሮች እንዲሰሩ እየተደረገ ነው።
    ሐምሌ 25/2017 ዓም

©መልካሙ ጣሴ
🙏32
በሽምግልና ስም የአማራ ህዝብን ትግል ጠልፎ ለመጣል አማራጭ ያደረገዉ አገዛዙ ብልፅግና ሴራ ተገልጦበታል።

እየተደረገ ባለዉ የህልዉና ተጋድሎ በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ ቀጠናዎችን መቆጣጠር ብሎ ህዝባዊ አስተዳደር በመመስረት ህዝብን ማገልገል የቻለዉ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል የአገዛዙን ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ሹማምንቶችን እንቅልፍ ነስቷል።

ከሰሞኑ በወልቃይት ጠገዴ በሽምግልና ስም ተዕልኮ ተቀብለዉ ፋኖን ለማስኮብለል የሞከሩ ሽማግሌዎች በፋኖ ፍፁም ወንድማዊ እና ጨዋነት በተሞላበት መልዕኮ ትምህርት ተሰቷቸዉ ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

በአገዛዙ ብልፅግና ተልዕኮ ይዘዉ ፋኖን እጅ እንዲሰጥ ለማድረግ ወደ ፋኖ ቀጠና የገቡት ሽማግሌዎች በአገዛዙ በኩል ስለ ፋኖ ያልተገባ ተልዕኮ ተሰቷቸዉ ቢመጡም ወሬዉ ሌላ ተግባሩ ሌላ ሁኖ አግንተነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለጦር አካል የሆነዉን የፅናት ወልቃይት ጠገዴ ብርጌድን በተልዕኮ ሊያስኮበልሉ የነበሩ ሽማግሌዎች በብርጌዱ ፍፁም ጨዋነት ትምህርት ተሰቷቸዉ እንዲሁም የብርጌዱን ቁመና እና ሰራዊቱን በመጎበኝት እና ሰራዊቱ በቀጠናው እየሰራ ያለዉን በጎ ስራ ጭምር በመመልከት ለፋኖ አድናቆትን ችረዋል።

በአገዛዙ የተባልነዉ ፋኖ ዘራፊ፣ሌባ እና ማህበረሰቡን የሚበደል እንደሆነ እና ይህ ተግባር አይጠቅማቹህም ብላቹህ ሰብካቹህ አምጡ ተብለን ነበር የመጣነዉ ከቦታዉ መተን ያየነዉ ግን በተቃራኒዉ ነዉ ሲሉ ሽማግሌዎቹ ተናግረዋል።

መንግስት ይዋሻል ሲባል አይዋሽም ብለን እናምን ነበር አሁን ግን መንግሰት ዉሸታም እና ለህዝብ የማይጨነቅ መሆኑን መረዳት ችለናል በማለት አስረድተዋል።

ፋኖ የማህበረሰቡን ችግር በመፋፍታት እና ፍትሐዊ ፍርድ በመስጠት የአማራ ህዝብ የነፃነት ታጋይ መሆኑን በአይናችን ተመልክተናል እኛ ወደዚህ ስንመጣ ፋኖ አምስት እና ስድስት ናቸዉ ተብለን ነበር የመጣነዉ መሬት ላይ ተገኝተን የተመለከትነዉ ግን መላ ህዝባችን ፋኖ መሆኑን ነዉ  ይህን እዉነት በማየታችን እንዲሁም የመንግስትን ዉሸት እና ፕሮፖጋንዳ በልኩ ማየታችን እድለኞች ነን ሲሉ የተመለከቱትን ተናግረዋል።

ፋፁም ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ተቀብለዉን በቦታው ያለዉን እዉነት በማስተማር ፋኖ ለህዝብ የወጣ፣ለፍትህና ነፃነት የሚዋደቅ መሆኑን በተግባር በማየታችን በመንግሥት በኩል ተቀብለን ይዘነዉ የመጣን መረጃ ፍፁም ስህተት ስለሆነ ህዝብችንን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።

ፋኖ የተግባር ሰራዊት መሆኑን ላልገባቸዉ እንድናስረዳ የምንገደድበትን እዉነት ተመልከተናል ከህዝባችን ጎን እንቆማለን በማለት እዉነታዉን መስክረዋል።

ይህንን በጎ ተግባር በማስተማር እና በተግባር በማሳየት ሽማግሌዎችን አስተምረዉ ወደ ቦታዉ የመለሱ የፋኖ አመራሮችን ባልተገባ መልኩ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶባቸዋል።

በትግበር ስራቸዉን አሳይተዉ ያስመሰከሩ እንደ እነ አርበኛ አንተነህ ድረስ ያሉ እንቁ አርበኞችን የአገዛዙ ልሳናት በብስጭት መልኩ ስም ለማጥፋት ሞክረዉ ነገር ግን ሳይሳካላቸዉ ቀርቷል።

ሽማግሌዎቹ በአገዛዙ ተይዘዉ ፋኖ በድሎናል ኑ ተናገሩ በሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸዉም እዉነትን መካድ ከሽማግሌ አይጠበቅም እዉነታዉ ከፋኖ እና ከህዝቡ ነዉ ያለ ሂዳቹህ ህዝቡን ጠይቁት ሲሉ ምላሽ ሰተዋል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆነዉ እና በሽማግሌዎቹ ልብ ዉስጥ የገበዉ አርበኛ አንተነህ ድረስ በኩል ሊደረግ የተሞከረዉ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሽማግሌዎቹ ምስክርነት መክሸፍ ችሏል።
3🙏1
"ግዙፍ የኮማንዶ ኃይል ተመረቀ"!

በአፋጎ 5ኛ ክ/ር ወምበርማ ብርጌድ ለ7 ወር ያክል ያሠለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ።
🙏2
ዘመቻ ሰማዕታት በድል እንደቀጠለ ነው !!

በዛሬው ዕለት እሁድ ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ማጥቃት ሰባተኛ ሀዲስ አለማየሁ ክፍለጦር በሶስት ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል ።

1/ ኮርክ ከተማ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ገብታለች ።
2/ ሉማሜ ከተማ ውስጥ በመግባት አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ተደርጓል ።
3/ አምበር ከተማ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት ፈጽሟል ።

4/ የሶስተኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር እና የአራተኛ ጃዊ ክፍለጦር አባላት በጋራ በመሆን ወርቅ ሜዳ ላይ በነበረው ሰራዊት ላይ በፈጸሙት ጥቃት የሻምበል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ተደምስሷል ።

በአውደ ውጊያው የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና እግረኛ የጠላት ሰራዊት ተማርኳል ።

በዝርዝር ይዘን እንመለሳለን !!

ክብር ለሰማዕታት !!
3🙏1
ሰበር ዜና
ፋኖን ለማስኮብለል የተላኩት ሽማግሌዎች "ፋኖ እዉነትኛ የፍትህ፣የነፃነት አርበኛነዉ" ሽማግሌዎች አርበኛ አንተነህ ድረስ በሽማግሌዎቹ ተመስክሮለታል
👍2
ሰበር ዜና
ፋኖን ለማስኮብለል የተላኩት ሽማግሌዎች "ፋኖ እዉነትኛ የፍትህ፣የነፃነት አርበኛነዉ" ሽማግሌዎች አርበኛ አንተነህ ድረስ በሽማግሌዎቹ ተመስክሮለታል
🙏2
📌የክቡር ሰማዕቱ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው አንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ!

"ንፁህ ትግል ታግዬ ነው መሞት የምፈልገው" በሚል ንግግሩ ይታወቃል። ክቡር ሰማዕቱ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው።

"የተቆጣ ነብር ቆፍጣና ጦረኛ፣
ሀገሩ ወሎ ነው ጎጃም ድንበርተኛ"
በሚል ባላገር ስንኝ ከቋጠረላቸው ከጀግኖቹና ከደጎቹ ቀየ አማራ ሣይንት ነው ትውልዱና እድገቱ።

ሀገሬው አይደለም የወንድ ጀግና እንደ አራስ ነብር የሚሶረፉ የሴት ጀግኖችንም ማፍራት ያውቅበታል። ለዛም ነው አዝማሪው፦

"በአብራራው አንቀልባ ወንድ ልጅ አዝላለች
የአማራ ሳይንቷ እሷው ትሆናለች" ሲል ስንኝ የቋጨላት።

አከባቢው፦
"ማን ያመጣልኛል?
ከሳይንት ነጭ ጤፍ ከቦረና ስንዴ፡
አሰሱን ገሰሱን አልበላ አለ ሆዴ" የሚል ስንኝ የተቋጠረለትም እንዲሁ በዋዛ አይደለም። ይልቅስ በመንደሩ ጀግናም፣ ጀግና ሆኖ ሐቀኛም፣ አራሽ አንደፋራሽም ስለሚበቅል ነው።ቀጠናው የጤፍ እና ስንዴ አምራቾች ምድር እንዲሁም የአልሞ ተኳሾች እርስተ ጉልት ነው።ይህ አካባቢ ወንድ ልጅ ሲወለድ ተኳሽ እና አራሽ አንደፋራሽ እንዲሆን በማለት ተፈጥሮም የምታሽቃሽጥበት አካባቢ ነው።

አዎ!
ሣይንትን ለጀግንነት ማን አምቶት?

"ሳይንት አፋፉ ላይ የተሰራ ቤት
ግድግዳው ጠብመንጃ ክዳኑ ጥይት" ይባላል። የሳይንት ሰው ቤቱም፣ የቤቱ ክዳንም፡ ጥይት ስለሆነ የከፋው ቀን፣ ፍትህ ተጓደለ ብሎ ያሰበ ቀን ከቤቱ ግድግዳ የያስቀመጠውን መሣሪያ ፈልፍሎ መዥረጥ ያደርግና ዱር ቤቴ ይላል።

በማይጨው ጦርነት ወቅት፦
"አይኑ መነጽር ጠብመንጃው ሆዳም
ነጭ ሰው ገዳይ ደባልቄ ካዳም"
የተባለለት ስመጥር ዘማች አርበኛ የበቀለውም ከዚሁ ከቦረና ሳይንት አውራጃ ነው።

ድሮስ የአማራ ሣይንት ምድርን ሐቀኛ ጀግኖችን ለማፍራት መች ታምቶ ያውቃል? መጠርጠሩስ?

"የሳይንቶች ዘር የዋጩ ጥሪት፡
ልቡ ድፍን ነው እንደ መድሀኒት" ሲሉ ጎበዞች ያንጎራጎሩት፡
"እወቀረዋለሁ ጥርሴን በጥይት፡
የጀግና ልጅ ሀገር አማራ ሳይንት" ሲሉ ኮረዳዎች የተቀኙት እኮ ለዋዛ አይደለም።

ሀገር ምድሩ ጀግና እና እህል ማብቀል ያውቃል። ወትሮውንስ የአማራ እናት መች ነጥፋ ታውቅና?

"ንፁህ ትግል ታግዬ ነው መሞት የምፈልገው" በሚል ንግግሩ የምናስታውሰው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው የዚሁ አከባቢ ፍሬ ነው።

ይህ የኛ ዘመን አብሪ ኮከብ፣ ይህ የዘመናችን የነፃነት ፋና ወጊ፣ ይህ የዘመናችን እንቁ የጦር ገበሬ፣ ፀረ ባንዳና ፀረ ሆዳም፣ በአማራ ሕዝብ ላይ የወደቀውን የሞት ቀንበርን ለመስበር ለሦስትና አራት ዓመታት በዱር በገደሉ ሲዋደቅ ከርሞ በመጨረሻም በሞቱ ሞትን ገድሎ የክብር ሞት ሸማን ከተጎናፀፈ እንሆ ዛሬ ድፍን እንድ ዓመትን አስቆጥሯል።

ቀኝ አዝማች ይታገሱ በጦር ሜዳ የተዋጋው የብልፅግናው ቡድን ያሰለፈው ወታደርን ብቻ አይደለም። ጎጠኝነትንና አድርባይነትን እንዲሁም ሆዳምነትንም ጭምር እንጂ። ለዚህ ደግሞ ከሕወሓት ወረራ ጀምሮ ተጋድሎ የፈፀመባቸው አውደ ግምባሮች አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ። ገንዘብና ወንበር ሲያይ ሰፍ ያላለ...ሕልውናውን በምስር ወጥ ያልቀየረ...እንቁ ጀግና።

ይህ ተወርዋሪ ምሽግ ደርማሽ ጀግና፡ ክንዱን ከተንተራሰ እንሆ ዛሬ ነሐሴ 25/2017 ዓ/ም ድፍን አንድ ዓመት ሞላው።

በርግጥ ሀገሬው ሰው አማኝና ታማኝም ነው።ይህ ፍጣሮቱም በያዝነው የሕልውና ትግል ብቻ እንኳን ካንዴም ሁለቴ ዋጋ አስከፍሎታል።

አርበኛ ቀኝ አዝማች ይታገሱ የተገደለው፡ ከውጊያ ውሎ ተመልሶ አረፍ እንዳለ አምኖ አቅርቧቸው በነበሩ የሕዝብ አደራን በምስር ወጥ በሸጡ ባንዳዎች ነው።
ሀገሬው የዚህ ብስጭት ሳይወጣለት፡ የአርበኛ ይታገሱ ቀኝ እጅ የነበሩት ሳጅን አደም አሊም እንዲሁ አምነው ባቀረቧቸው ተከድተው ከተሰዉ ወራቶች ተቆጥረዋል።

አሁንም በቀጠናው የሚገኙ ጀግኖችን ለመጠበቅ ጥንቃቄ ይሻል።የአማራ እናት "ጀግና ወላዲቱ" ተብላ ተሞግሳ ሲያበቃ፡ እስከመቼ "የሟቹ እናት" ተብላ ትጠራ?

በርግጥ አርበኛ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው አንድ ሆኖ በክብር ወድቆ፡ ሺህ ሆኖ በቅሏል። በሱ ስም እየፎከሩ ምሽግ የሚሰብሩ ጀግኖች እልፍ ናቸው።

ምድር ቃጢ በሆነችበት ውጊያ መኃል
"ዘራፍ ...የይቴ ወንድም፡
እንበለው እንጂ መሸሽ አይወድም"
እያሉ እየፎገሉ ከምሽግ ምሽግ የሚወረወሩ ጀግኖችን ያየ ሰው በርግጥ አርበኛ ይታገሱ አልሞተም አለ ብሎ ቢከራከር አይፈረድበትም። ትክክል ነው እልፍ አዕላፍ ጀግኖችን አፍርቷል።

ክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ነፍስህ በሰላም ትረፍ!

ስለ ህፃን አይሻ ሰይድና ስለ ሕዝቧ የተከፈለ ወጣትነት!

ክብርና ዘላለማዊ ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!

ዘገባው የመረብ ሚዲያ ነው!
🙏4
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ፤

"እኔ ብሞት ደሜን የምትመልሱት ገዳዬን ገድላችሁ ሳይሆን የአማራ ህዝብን ነፃ አውጥታችሁ ነው" በማለት በህይወት ሳለ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋውን ህልፈት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ እለት አስመልክቶ የተላለፈ ድርጅታዊ መልዕክት:-

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አዛዥ እንዲሁም የመሀል ሳይንቱ አትሮንስ ብርጌድ አዛዥ የነበረውና ቀደም ብሎም ከምስራቅ አማራ ፋኖ (2013 ዓ.ም) ጀምሮ በትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሆኖ ጀብዱ የፈፀመው የቦሩ ሜዳው ውጊያ ፊታውራሪ እና ፅኑው ታጋይ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በድህረ ሰሜኑ ጦርነት ወቅት የያኔው ምስራቅ አማራ ፋኖ የሰጠውን ግዳጅ ተቀብሎ ወደ ትውልድ አካባቢው መሀል ሳይንት ወረዳ በማቅናት ወጣቶችን በማንቃት እና በመመልመል እንዲሁም በፋኖነት በማደራጀት ጉልህ ሚና ተጫውቶ በወርሀ መጋቢት 2015 ዓ.ም ይፋዊ የህልውና ፍልሚያ ስንጀምር እሱም ባለበት ግንባር ኃይሉን ሸክፎ ቀጥታ ወደ ትግሉ በአዲስ መልኩ መግባቱ ይታወሳል::

የህልውና ትግሉ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ወራት በፅናት እና በጀግንነት በውጊያ ሜዳው ላይ ታይቶ አምና ልክ በዛሬው እለት ማለትም ነሀሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በባንዳ በተተኮሰ ጥይት በድንገት ያጣነው የትግል ጓዳችን እና ወንድማችን ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በትግሉ ሂደት የሚከፈለው መስዋዕትነት በጠላት በተተኮሰ ብቻ ሳይሆን በወገን ጥይት ጭምር ሊሆን እንደሚችልና በሁለቱም አቅጣጫ ለሚተኮስ ጥይት ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል:: በወገን ባለጋራ እጅ መሞት የትግሉ ሜዳ እንድጠራ በር የመክፈት መስዋዕትነት ሲሆን ጀብዱ ፈጽሞ ጥሎ እንደ መውደቅ ማለትም ልክ በጠላት እጅ እንደመሞት ያለ ክቡር መስዋዕትነት ነው::

ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በጆፌ ኢትዮጵያኒስቱ ኃይል ሳይታለል በአማራ ብሔርተኝነት እና በእውነት ፍፁም አልደራደርም ብሎ አሰላለፉን አሳምሮ ለወሎ ቤተ አማራ ፋኖ አንድነት የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ የከፈለ አርበኛ ብቻ ሳይሆን ንፁህ ትግልን ታግሎ በማለፍ ሌሎች ንፁህ ታጋዮችን ማፍራት የቻለ የህልውን ትግሉ ደማቅ ምልክትም ነው:: የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሰራዊት እና አመራሮች ለፋኖአዊ አንድነት እና ለአማራዊ እሴት ያላቸውን ትልቅ ቦታ አስረጅ የሆነው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ንፅህና እና እውነት የታጋዩ እና የትግላችን መሰረት መሆኑን ማሳያነቱ አያጠራጥርም::

ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በምዕራብ ወሎ ግንባር መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ በተለምዶ አህዮ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ሰኞ ገበያ የተባለ ስፍራ ላይ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመምራት ላይ ሳለ አንድ ቅጥረኛ ባንዳ ግለሰብ በተኮሰው አውቶማቲክ ጥይት ተመትቶ ቢሰዋም ባንዳው ላይ የመሀል ሳይንቱ አትሮንስ ብርጌድ አባል የሆነ ጀግና ጓድ በጀት ፍጥነት እርምጃ መውሰዱን እንዲሁም በማግስቱ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ከመፈፀሙ የተወሰኑ ሰዓታት ቀደም ብሎ የክፍለ ጦሩ አካል የሆነው ታቦር ተራራ ብርጌድ ሰራዊት ከመሀል ሳይንት ወረዳ ቀጥሎ የሚገኘው አማራ ሳይንት ወረዳ ውስጥ ፓትሮል በማቃጠል ከአንድ ቲም ያላነሰ ጠላትን በመደምሰስ 3 ክላሽ እና 1 ብሬን ከነ ሽልንሼሉ መማረኩ አይረሳም:: በእለቱ እለት እና በማግስቱ ደሙ የተመለሰለት ጓዳችን እና የትግል ወንድማችን ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው በህይወት ሳለም ሲናገር የነበረው "እኔ ብሞት ደሜን የምትመልሱት ገዳዬን ገድላችሁ ሳይሆን የአማራ ህዝብን ነፃ አውጥታችሁ ነው" በማለት ነበር:: በዚህም መሰረት ለነፃነት እና ለህልውና የሚደረገው ትንቅንቅ እና የሚከፈለው መስዋእትነት ቀጥሎ ሰራዊታችን በየእለቱ ጀብዱ እየፈፀመ መሆኑን ያስታውሷል::

"ገንዘብ ስታዩ አትደንግጡ" የሚለውን የዋርካው ምሬ ወዳጆ ወርቃማ ምክር በመተግበር ለገንዘብ ባለመደንገጥ በእውቀት እና በታማኝነት እንዲሁም በጀግንነት ታግሎ በንፅህና ያለፈው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው "ሲርባቸው ይመጣሉ" ያሉን ወገኖችን ጭምር አሳፍሮ የመለሰ የሀቅ እና የእውነት ታጋይ በመሆኑ ሁሌም ስሙ ሲዘከር በአርአያነትም በየመድረኩ በክብር ሲጠራ ይኖራል::

ለቀጠናዊ መናበብ እና ለአማራዊ አንድነት ልዩ ቦታ በመስጠት አንድ የፋኖ ድርጅት እንድፈጠር ለማድረግ ደፋ ቀና ሲል የነበረ መሆኑም አይረሴ ነው::

ከምስራቅ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ፋኖወች ጋር ቀጠናዊ ትስስር በመፍጠር ለአማራዊ አንድነት መደላድል ሲፈጠር የነበረው ይህ ጀግና ያፈራው ሰራዊት በምዕራብ ወሎ ግንባር ከመሀል ሳይንት ተነስቶ ወግዲ እና መካነሰላም እንዲሁም ከላላ እና መቅደላ ብሎም ተንታ እና ሌሎች አጎራባች ወረዳወች ድረስ ታሪክ ሰርቷል፤ እየሰራም ነው::

የአንድነት ሀዋርያው፣ በእውነት እና እውነት ይታወቅ የነበረው...ጎጥ እና ጥቅም የማይበግረው ከገንዘብ ይልቅ ህዝብን አስቀዳሚው ንፁሁ ታጋይ ቢሞትም ስሙ አልተቀበረም፤ ትግሉም ተቀጣጥሏል እንጅ አልቀዘቀዘም::


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሀሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
👍42