✢መጀመሪያ የሌለው እግዚአብሔር መጀመሪያ ላላቸው ችግሮቻችን ኹሉ መፍትሔ ነው።✢
አንድ ሰው ሱሰኛ ቢኾን ሱስ የጀመረበት የመጀመሪያ ዕለትና አጋጣሚ አለው። ይኽ ብቻ አይደለም። ሱስ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት የኾነው ሰውና በሱስ ወጥመድ ያጠመደችው ዕፅም ትኹን መጠጥ፥ ማየትም ትኹን መስማት፥ ማሰብም ትኹን መዳሰስ ...... ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጋት የተጠቀማት ያቺ መጀመሪያ አላት።
እስኪ በዝምታ ኾነን፤ ዕያወቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት አርግዘናቸው ልንገላገላቸው ያልቻልናቸው ችግሮቻችንን ስህተቶቻችንን በአጠቃላይ ወደ መልካም ልንቀይራቸው የምንፈልጋቸውን ጠባዮቻችንን ሥራዎቻችንን ለአፍታ ልብ እንበላቸው እናስተውላቸው። ኹሉም መነሻ አላቸው። መድረሻም አላቸው። ኹሉም አድራሻቸው ይታወቃል።
አድራሻው የሚታወቅ ወንጀለኛ ከፖሊስ አያመልጥም። የትም ይኹን፤ አድራሻው እስከታወቀ ድረስ በቁጥጥር ስር መዋሉ አይጠረጠርም።
ተወዳጆች እግዚአብሔር የእያንዳንዳችንን የኃጢአቶቻችንን አድራሻ ያውቃል። ምን ቀን፣ በምን ምክንያት፣ እንዴት ኀጢአት ውስጥ እንደተዘፈቅን ያውቃል።
የኀጢአቶቻችንን መነሻ ምክንያት ጠንቅቆ ያውቃል።
ተወዳጆች እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው። ማንኛውም ፍጥረት በእግዚአብሔር ከመፈጠሩ በፊት ህልውና አልነበረውም። ስለዚህ በሚታየውም በማይታየውም ዓለም ውስጥ የሚኖር ኹሉ ከእግዚአብሔር በታች ነው። እኛም ኀጢአቶቻችንም ጭምር።
እውነት ነው ኀጢአትን እግዚአብሔር አልፈጠራትም። ሰው ዕፀ በለስ በልቶ አመጣት እንጂ። ኀጢአት የእኛ ያለመታዘዝ የሥራችን ውጤት ናት። ስለዚህ እኛ ከእግዚአብሔር በታች ከኾንን ኀጢአትም ከእግዚአብሔር በታች ናት። ይኽ ብቻ አይደለም። ኀጢአት ከእኛም በታች ናት።
ችግሩ "ለሰይጣን አትስጠው ሥልጣን" እንደተባለ በገዛ እጃችን በራሳችን ላይ አነገሥናት እንጂ ከእኛ አትበልጥም።
"ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባዕድ ሥር የለው" ነው ነገሩ።
እኛ ግን በተለያየ ምክንያት ሥልጣን ስለሰጠናቸው ኀጢአቶቻችን እንደ ጥቅምት ብርድ እጅና እግራችንን አሳስረው አስቀመጡን። ስለዚህ ተስፋ የሚባል ነገር ማየት አልቻልንም።
መፍትሔው ግን አንድ ነው። መጀመሪያ የሌለው እግዚአብሔር መጀመሪያ ላላቸው ችግሮቻችን ኹሉ መፍትሔ ነው። ሐኪሙ እርሱ ነው። መድኃኒቱም ራሱ ነው።
ለሐኪም ይነግሩታል። እስኪ በጣም ታመን ሐኪም ቤት የሄድንበትን ጊዜ እናስታውስ። የቱ ጋር እንደሚያመን፣ እንዴት እንዳመመን፣ ከመቼ ጀምሮ የሕመም ስሜት እንደተሰማን ቅልስልስልስ እያልን "ዶክተርዬ" ብለን እያቆላመጥን መሬት ኾነን በታላቅ ትሕትናና ልመና ይፈውሰንም አይፈውሰንም ምንም ማረጋገጫ በሌለን.... ምድራዊ ሐኪምን እንደሚያድነን አምነን ሕመማችንን እንናገራለን።
ምነው ታዲያ እግዚአብሔርን በብስጭት እንናገረዋለን? ምነው ታዲያ በጥርጣሬ እንለምነዋለን? ምነው ታዲያ የሚያዝልንን የነፍስ መድኃኒቶች ጾም፣ ጸሎት፣ ንስሐ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ እንስታጉላለን? የታይፎድ መድኃኒት አይቋረጥም እያልን የምንሽቆጠቆጥ እኛ ለነፍሳችን መድኃኒት ምነው ፊት ነሣነው!
አሁን ላለንበት የመከራ ሕይወት እግዚአብሔር ተጠያቂ አይደለም። አንድ ታማሚ ሐኪሙ ያዘዘውን መድኃኒት ሳይወስድ ሐኪሙ አላዳነኝም ማለት አይችልም። መጀመሪያ እግዚአብሔር ጋር አቀራረባችንን እናስተካክለው። ልመናችን በትሕትና ይኹና። ከዚያ የታዘዘልንን መድኃኒት በሰዓቱ እንውሰድ። ያለጥርጥር መጀመሪያ ያላቸው ኀጢቶቻችን መጀመሪያ በሌለው ፈጣሪያችን ይቅር ይባላሉ።
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb

Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤2🥰2👏2🔥1🎉1🤩1
✢ፎርሜሽናችንን እናስተካክል✢
በእግር ኳሱ ዓለም በአንድ ቡድን ዐሥራ አንድ ተጨዋቾች ቢጫወቱም በዓለማችን የምናውቃቸው ታላላቅ የሚባሉ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ያሉባቸው ቡድኖች ግን ተጋጣሚያቸውን ኹል ጊዜ እንዳሰጉ ነው።
ለአንዱ፤ ለዚያ ጎበዝ ለተባለው ተጨዋች ሲባል የቡድኑ አሰላለፍ (formation) ይቀየራል። ይስተካከላል። ምክንያቱም የጎበዙ ተጨዋች መኖር ለቡድኑ አሸናፊነት አስፈላጊ ስለኾነ። ማንም ይኽንን አይቃወምም።
የሚገርመው ግን ኳስ ተጨዋቹን ያመነውን ያኽል እንኳ በሕይወታችን ሰልፍ ላይ እግዚአብሔርን አለማመናችን ነው። በኑሯችን ስንትና ስንት ግጥሚያ ነው ያለብን? ስንትና ስንት የውድድር ሜዳዎች ነው የሚያጋጥሙን? በእሊኽ ኹሉ የሕይወት ግጥሚያዎቻችን የእግዚአብሔር መኖር አስፈላጊ ነው። በሕይወት ጨዋታ የጨዋታ ብልጫም አሸናፊነትም የምናገኘው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሲኾን ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሲኾን የኳስ ቁጥጥራችን ይጨምራል። ኳሱን ከመረቡ በቀላሉ ማገናኘት ያስችለናል።
ጥያቄው እኛ ለእግዚአብሔር የሚመች አሰላለፍ ተሰልፈናል ወይ ነው?
ድል እንፈልጋለን የድል ፎርሜሽን ግን አልሰራንም።
የምንውልበት ቦታ፣ የምንመለከታቸው ነገሮች፣ የምንሰማቸው ድምፆች፣ የምናስባቸው ሀሳቦች፣ የምናደርጋቸው ድርጊቶች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳይሰለፍና እንዳይረዳን የሚያደርጉ ስለኾኑ መደሰት የለ፥ ዕረፍት የለ፥ ሰላም የለ፥ ተስፋ የለ፥ እንዲኹ ስንጨነቅ አሸናፊነትን እንደናፈቅን መሽቶ ይነጋል።
ማሸነፍ ከኾነ የምንፈልገው የኀጢአት፣ የዕንቅልፍ፣ የስንፍና ፎርሜሽናችንን ወደ ጽድቅ፣ ወደ ጸሎት፣ ወደ ንባብ፣ ወደ ጾም፣ ወደ ንስሐ ፎርሜሽን እንቀየር ፤ ለእግዚአብሔር የሚመች አሰላለፍ እንሰለፍ።
ያን ጊዜ የጨዋታ ብልጫውም፣ ግቡም፣ ኮከብ ጎል አግቢነቱም፣ ዋንጫውም የእኛው ይኾናል።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡

❤3🥰2👏1
✢ወይ ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ✢
የድሃ ምሬት እንዲህ ነው፤"ወይ ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ"።
ሀብታም የመኾን ጥሙ የሚቆርጥለት ከሀብታም በመወለድ አልያም ከሀብታም በመጠጋት እንደኾነ ስለሚያስብ።
ሰው የደኸየበትን ነገር ይፈልጋል። በገንዘብ ከኾነ የደኸየው ገንዘብ ይፈልጋል።
አሁን እኛ የደኸየንበት ነገር ምንድን ነው? የምንፈልገው ሀብት ምንድን ነው?
ገንዘብ ነው? ሰላም ነው? ከሱስ መውጣት ነው? እውነተኛ ወዳጅ ነው? ቤት ነው? ንብረት ነው? ዕውቀት ነው? ጥበብ ነው? ምንድን ነው የምንፈልገው?
እኛ እኮ ካለው ተወልደናል። በዐርባ እና በሰማንያ ቀናችን ኹሉ የእርሱ ከኾነ ከባለጸጋው ከእግዚአብሔር በጥምቀት ተወልደናል። የአባታችን የኾነ ኹሉ የእኛ ነው።
ባለጸግነት ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ነው።
ሰላም በማን ነው? በእግዚአብሔር ነው።
ችግሮችን የመቋቋምና የማሸነፍ ኀይል ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ነው።
ያለጥርጥር ኹሉን መቻል ኀይልን በሚሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
ታዲያ ለምንድን ነው በሥጋም፣ በነፍስም፣ በመንፈስም የደኸየነው?
የወለደንን እግዚአብሔር ተወልደን ስለራቅነው ነው። በጸጋ ልጆቹ ነን ግን እንደአባት አልቀረብነውም።
ልጆች ሳለን ልብስ ቢያስፈልገን አባታችንን "ልብስ ካልገዛህ" ብለን ግድ እንለዋለን። ልብሱን እስኪገዛልን ድረስ በጩኸትም በዕንባም በመለማመጥም ዕረፍት እንነሣዋለን። ልመናችንን የምናቆመው ልብሱን የገዛ ዕለት ነው።
እግዚአብሔር አባታችን ነው ካለን፤ አሁን አልፋታ ብሎ የተጋባንን ክፉ ሥራችንን ለምን ያኽል ጊዜ እንዲያስወግድልን ለምንነው? እንዴት ባለጩኸት ጠራነው? እንዴትስ ብለን በዕንባ ተማጸንነው?
ሊቁ አምብሮስ እንዲህ ይላል "ዕንባ ይቀበላል እንጂ አይለምንም"
አባታችን እግዚአብሔር ከገባንበት የኀጢአት ሱስ እስኪያወጣን ድረስ በዕንባ ጩኸት እንጠጋው። በምስጋና እንጠጋው።
መቼም አባት ነው በደስታችን ጊዜም በምስጋና እንጠጋው።
ካለው ከእግዚአብሔር ተወልደናል ካለው ከአባታችን ከእግዚአብሔር መጠጋት ይቀረናል።
በዕንባ በምስጋና እንጠጋው።

❤4🔥1
✢እግዚአብሔር በእኛ አይለካም✢
አንድን ወታደር "ልጅህ ፈሪ ነው? ደፋር?" ተብሎ ቢጠየቅ " እንዴ የኔ ልጅማ ወንዱ አንበሳው" ብለው ይመልሳል። ምክንያቱም ልጁን በልጁ አቅም ሳይኾን በራሱ ዐይን ስላየው ነው። ልጁ እኮ ዕልም ያለ ፈሪ ሊኾን ይችላል። ግን የእርሱ ጀግንነት በዘር ወደ ልጁ እንደሄደ ስለሚያስብ የልጁን ፈሪነት ለመቀበል ይቸግረዋል።
እንዲህ ያለ አመለካከት ሳናውቀው እግዚአብሔርንም በእኛው ልክ የመለካትና የማየት በሽታ አምጥቶብናል። ይኽ በጣም አደገኛ ነገር ነው።
አንዳንዶቻችን የኾነ ነገር የማይሳካ ወይም የተበላሸ፣ያለቀለት፣ የደቀቀለት ሲመስለን " እንግዲህማ ምን አዲስ ነገር ይመጣል? እግዚአብሔር ረስቶኛል። አሁንማ ረፍዷል።" እንላለን።
ይኽንን ስንል ቅንጣት እንኳ ኀፍረትም ፍርሃትም አይሰማንም።
ለእግዚአብሔር ረፍዷል ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር አርፍዷልስ ትርጉሙ ምንድን ነው?
እኛ ተጋድመን ቅዳሴ እንደሚረፍድብን እግዚአብሔር የሚያረፍድ ነው እንዴ የሚመስለን?
ቆይ ምን ለማለት ፈልገን ነው?
በቦታ እንኳ ካየነው አንድ ሰው የሚያረፍደው በተመሳሳይ ሰዓት በአንድ ቦታ መገኘት ባለመቻሉ ምክንያት ካለበት ቦታ ወደሌላኛው ቦታ በሚሄድበት ጊዜ ነው።
እና እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ አለና ነው የሚያረፍደው? ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የኾኑለትን አምላክ ነው በመከራችን ቦታ የለኽም የምንለው?
ማርፈድ እኮ ከጊዜ በኋላ ለተፈጠሩ በጊዜ ውስጥ ለሚኖሩ ለፍጡራን የሚቀጽል ነው። ታዲያ ጊዜን የፈጠረውን አባታችንን ነው አርፍደሃል የምንለው?
እግዚአብሔር አይዘገይም። አይቀርምም። የሚሰራበት የራሱ የኾነ ጊዜ አለው።
ያለጊዜዋ የተቀጠፈች ፍሬ ኹሉ ትመራለች። ሕመምም ትኾናለች። የእግዚአብሔርን ጊዜ ሳትጠብቅ የምትሰራ ስራ ኹሉ ትጠፋለች። ታጠፋለችም።
የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ጊዜ እንጠብቅ።

👍4🔥1
"ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈጽሞ አትለይ። የትኛውም ተቋም የቤተክርስቲያንን ያህል ሥልጣን የለውም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ድኅነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤3👍3
ቀመረ ሥላሴ በቀመረ ሰብእ ሊጠፋ አይችልም። ቤተ ክርስቲያንን የሚያዞራት፣ የሚመራትና የመሠረታት ዘለዓለም ሥላሴ ነው። እምነታችን በእዚህ ነው።
እኛ ግን ከዚህች ቤተ ክርስቲያን ጎን ባለመኾንና የእርሷ እውነተኛ አገልጋዮች ባለመኾን ከዘለዓለማዊ ሕይወት ዕድል ፈንታ ጽዋ ተርታ እናጣለንና እንኳን ሥጋውያን መንፈሳውያን አካላት ከማይችሏት፤ ድል ማድረግ መነሻዋም መድረሻዋም ከኾነላት አሸናፊው እግዚአብሔር ከመሠረታት ከአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን እንቁም።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
እኛ ግን ከዚህች ቤተ ክርስቲያን ጎን ባለመኾንና የእርሷ እውነተኛ አገልጋዮች ባለመኾን ከዘለዓለማዊ ሕይወት ዕድል ፈንታ ጽዋ ተርታ እናጣለንና እንኳን ሥጋውያን መንፈሳውያን አካላት ከማይችሏት፤ ድል ማድረግ መነሻዋም መድረሻዋም ከኾነላት አሸናፊው እግዚአብሔር ከመሠረታት ከአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን እንቁም።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤5👍1🔥1
Forwarded from Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ
ኦርቶዶክሳዊ ክህነትና አንድነት አንዲቀጥል የምትሹና ከዘር ጣዖት በላይ የሆናችሁ ሁሉ ይህን ምስል ፕሮፋይላችሁ በማድረግና በብሔር ስም በመንግሥት የሚካሄደውን የኦርቶዶክስን ዘር የማጥፋት ሁለገብ ፖለቲካዊ ጥቃት እንቃወም። ፍትሕ ስክናገኝና መግደልና ማፈናቀል፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘረኞች በፖለቲካው አምሳል ማደራጀት አንሰኪቆም ይህን ፕሮፋይ አንቀይርም ብለን ቃል እንግባ
#StopReligiousGenocideInEthiopia
ይህን ታግ በመጠቀም የተቃጣብንን ሃይማኖታዊ ጥፋት በሁሉም የሚዲያ አይነቶች በተለይ በተዊተር ዘመቻ በአስቸኳይ እንጀምር

👍1
"ካህን የዓለም ኹሉ የጋራ አባት እንደመኾኑ፥ እንደሚያገለግለው እንደ እግዚአብሔር ለኹሉ ሊጨነቅ ይገባዋል።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
❤5
"የመግዛት ጽኑ ፍላጎት የኑፋቄ እናት ናት። የሥልጣን ፍቅርን ያህል ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍላት ምንም ነገር የለም።..... ሌሎችን ለማዳን ከማይፈልግ ክርስቲያን የበለጠ ቀዝቃዛ ነገር የለም። ሌሎችን ለማዳን ምንም ጥረት የማያደርግ ክርስቲያንን ከማየት የበለጠ የሚያስደነግጥ ነገርም የለም።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
አገልጋይ መስዬ ለሰዎች ብታይም፤
አንተ ግን መቅደስህ ደጅህ አታየኝም።
ከገረገራው ስር በደል የሸሸገኝ፤
ከቤትህ ቁጭ ብዬ የጠፋሁ ባርያህ ነኝ።
https://t.me/getseseb
አንተ ግን መቅደስህ ደጅህ አታየኝም።
ከገረገራው ስር በደል የሸሸገኝ፤
ከቤትህ ቁጭ ብዬ የጠፋሁ ባርያህ ነኝ።
https://t.me/getseseb
❤2👍2
በመጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስም ሲታሰሩ አይተናል። አባቶቻችንም የነርሱ ተከታዮችና የነርሱ ሥልጣን ያላቸው ናቸውና መከራውን ይካፈላሉ። እኛም እውነተኞች ልጆች ከኾን አይቀርብንም።
የአባቶቻችንን መታሰር እግዚአብሔር ካልፈቀደው ቅዱስ ጴጥሮስን በሌሊት በተዘጋ እስር ቤት ያስወጣው መልአክ አልሞተም፤ ዛሬም አለ፤ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ ማኅበሩ ይቀላቅላቸዋል።
ይልቅስ ኹላችንም ከገባንበት የኀጢአት እስር ቤት በንስሐ እንውጣ። ከኀጢአታችን እንዲያወጣን የሚላክ መልአክ የለም። ወደንና ፈቅደን እንደቆሸሽነው ወደንና ፈቅደን ነውና የምንነጻው። ንስሐ ላለመግባት ከእኛ ውጪ ማንም ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም።
እውነተኞች ከኾንና እውነተኞች መኾን ከፈለግን ከገባንበት የኀጢአት እስር ቤት በንስሐ እንውጣ።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
ገጸ ሰብእ
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
የአባቶቻችንን መታሰር እግዚአብሔር ካልፈቀደው ቅዱስ ጴጥሮስን በሌሊት በተዘጋ እስር ቤት ያስወጣው መልአክ አልሞተም፤ ዛሬም አለ፤ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ ማኅበሩ ይቀላቅላቸዋል።
ይልቅስ ኹላችንም ከገባንበት የኀጢአት እስር ቤት በንስሐ እንውጣ። ከኀጢአታችን እንዲያወጣን የሚላክ መልአክ የለም። ወደንና ፈቅደን እንደቆሸሽነው ወደንና ፈቅደን ነውና የምንነጻው። ንስሐ ላለመግባት ከእኛ ውጪ ማንም ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም።
እውነተኞች ከኾንና እውነተኞች መኾን ከፈለግን ከገባንበት የኀጢአት እስር ቤት በንስሐ እንውጣ።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
ገጸ ሰብእ
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍2
ለራስ ያልተነገረ መፈክር ለሌላ ቢነግሩት ጥቅሙ የቱ ጋር ነው? ሰሚው ቢፈጽመው ተናጋሪው ያበላሸዋልና። በየአጀንደው ፎካሪው ብዙ ነው። ወጥ የማይደፋ ጉልበት ተይዞ ምን ቢፎክሩ ምን ሊመጣ?
ቤተ ክርስቲያን እኮ አሸንፋለች። እርሷ ጉልበታም ነች። ከእርሷ መንፈሳዊ ጉልበት ሳንሳተፍ ብንፈርጥ ብንነሣ ትርፉ መላላጥ ነው።
እኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንጂ ጉልበት የሌለን ቤተ ክርስቲያንስ ጉልበታም ነች። ኀጢአትን በመስራት መንፈሳዊ ጉልበታችን እጅጉን ተዳክሟልና።
ወንድ ነኝ የሚል፤ ጀግና ነኝ የሚል፤ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነኝ የሚል እስኪ ራሱን ያሸንፍ!
ድል ሳያደርጉ ፉከራ ለመነሣሣት እንጂ ጉልበት ለማግኘት አይጠቅምም።
ክርስቲያን ከኾነኽ ኀጢአትህን ወግተኽ ጣላት፤ ቆርጠኽ ለያት።
ይኽ ደግሞ ሥራ እንጂ መፈክር ብዙ አይጠይቅም።
ወንዱ! ሴቷ! ቅድሚያ ከራስ!
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
ቤተ ክርስቲያን እኮ አሸንፋለች። እርሷ ጉልበታም ነች። ከእርሷ መንፈሳዊ ጉልበት ሳንሳተፍ ብንፈርጥ ብንነሣ ትርፉ መላላጥ ነው።
እኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንጂ ጉልበት የሌለን ቤተ ክርስቲያንስ ጉልበታም ነች። ኀጢአትን በመስራት መንፈሳዊ ጉልበታችን እጅጉን ተዳክሟልና።
ወንድ ነኝ የሚል፤ ጀግና ነኝ የሚል፤ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነኝ የሚል እስኪ ራሱን ያሸንፍ!
ድል ሳያደርጉ ፉከራ ለመነሣሣት እንጂ ጉልበት ለማግኘት አይጠቅምም።
ክርስቲያን ከኾነኽ ኀጢአትህን ወግተኽ ጣላት፤ ቆርጠኽ ለያት።
ይኽ ደግሞ ሥራ እንጂ መፈክር ብዙ አይጠይቅም።
ወንዱ! ሴቷ! ቅድሚያ ከራስ!
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
🔥3👍2
ነነዌ ለመዳን የሦስት ቀን ሱባኤ በቅቷታል። በዚህ የእግዚአብሔርን መሐሪነት ብቻ ሳይኾን የነነዌን ሕዝብ ታላቅ ጸጸትንም እንመለከታለን። እግዚአብሔር አይለወጥም። ዛሬም እኛ ኢትዮጵያውያን ቸሩ መድኃኔዓለምን ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዕንባ ብንማጸነው የነደደብንን እሳት ውሃ ያደርግልናል። የተቃጣብንን ያስታግስልናል።
ሦስት ቀን እናልቅስ።
ሦስት ቀን ኪዳን እናድርስ።
ሦስት ቀን እናስቀድስ።
ሦስት ቀን ምሕላ እናድርስ።
ሦስት ቀን እንስገድ።
ሦስት ቀን እንመጽውት።
ሦስት ቀን እንጹም።
ሦስት ቀን ቅዱሳት መጻሕፍት እናንብብ።
ሦስቱን ቀን በቅዱስ ሥጋው በክቡር ደሙ እንሰረው።
ከዚያም ወደትፋታችን ሳንመለስ በዚኹ የንሥሐ መንገድ ወደ እግዚአብሔር እንገሥግሥ።
" በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለ ምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለ ምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? "
ትንቢተ ኢሳይያስ 50:2
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ. 1)
----------
16፤ ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፥
. . .
18፤ ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
ሦስት ቀን እናልቅስ።
ሦስት ቀን ኪዳን እናድርስ።
ሦስት ቀን እናስቀድስ።
ሦስት ቀን ምሕላ እናድርስ።
ሦስት ቀን እንስገድ።
ሦስት ቀን እንመጽውት።
ሦስት ቀን እንጹም።
ሦስት ቀን ቅዱሳት መጻሕፍት እናንብብ።
ሦስቱን ቀን በቅዱስ ሥጋው በክቡር ደሙ እንሰረው።
ከዚያም ወደትፋታችን ሳንመለስ በዚኹ የንሥሐ መንገድ ወደ እግዚአብሔር እንገሥግሥ።
" በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለ ምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለ ምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? "
ትንቢተ ኢሳይያስ 50:2
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ. 1)
----------
16፤ ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፥
. . .
18፤ ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤3👍2👏1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ

👏2
ሰዎች "ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቁር ልበሱ ብሏል ወይ?" እያሉ እንደኾነ ሰማኹ። መልሳችን አዎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን ወንዱም ሴቱም ጥቁር ለብሶ እንዲጾም አዞናል። ምናልባት ይህ ጥያቄ የመጣው መግለጫው በፋና፣በዋልታ፣በኢቲቪ ወዘተ ሚዲያዎች ስላልተላለፈ ሊኾን ይችላል። አሁን ጣቢያችንን ወደራሳችን የምንመልስበት ጊዜ ነው። በነዚያ ሚዲያዎች የእግዚአብሔር ድምፁ መሰማት ካቆመ ቆይቷል። ወደራሳችን ልብና ወደራሳችን ሚዲያ እንመለስ።
አይደለም ጥቁር ይቅር ይበለን እንጂ ማቅም ልበሱ ብንባል እንለብሳለን።
ጥቁር መከራ ነው።
ጥቁር ጽናት ነው።
ጥቁር አይመረመሬነት ነው።
ጥቁር ጀግንነት ነው።
ጥቁር ውበት ነው።
ጥቁር እውነት ነው።
ጥቁር እውቀት ነው።
እኛም የጥቁር ልጆች ጥቁሮች ነን።
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
https://t.me/getseseb
አይደለም ጥቁር ይቅር ይበለን እንጂ ማቅም ልበሱ ብንባል እንለብሳለን።
ጥቁር መከራ ነው።
ጥቁር ጽናት ነው።
ጥቁር አይመረመሬነት ነው።
ጥቁር ጀግንነት ነው።
ጥቁር ውበት ነው።
ጥቁር እውነት ነው።
ጥቁር እውቀት ነው።
እኛም የጥቁር ልጆች ጥቁሮች ነን።
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤11👏2👍1🥰1
በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ኹለት አምላክ አይቀመጥም። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ በወንጌል እንደነገረን ባሪያ ለኹለት ጌቶች ሊገዛ አይችልም።
በአንድ ሀገርም ኹለት ሲኖዶስ አያስተዳድርም። ኹለት መንበርም አይኖርም። ኹለት ፓትርያርክም አይመራም።
አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ መንበር፣ አንድ ፓትርያርክ፣ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብቻ።
እንዲህ ብለን አናቆምም። በሕይወታችንም አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው አምላካችን። እኛ የክርስቶስ እንጂ የሰይጣን ባሮች አይደለንም።
በኀጢአት ምክንያት ዲያብሎስ ጌታው የኾነለት ኹሉ በንስሐ በር ወደ ክርስቶስ ባርያነት ይመለስ።
አንድ ጌታ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ።
አንዲት ሃይማኖት፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ።
አንዲት ጥምቀት፤ የሥላሴ ልጅነት።
አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ሐዋርያት የሰበሰቧት።
አንድ መንበር፤ መንበረ ኢትዮጵያ።
አንድ ፓትርያርክ፤ እጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።
አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ዘሀገረ ኢትዮጵያ።
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
https://t.me/getseseb
በአንድ ሀገርም ኹለት ሲኖዶስ አያስተዳድርም። ኹለት መንበርም አይኖርም። ኹለት ፓትርያርክም አይመራም።
አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ መንበር፣ አንድ ፓትርያርክ፣ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብቻ።
እንዲህ ብለን አናቆምም። በሕይወታችንም አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው አምላካችን። እኛ የክርስቶስ እንጂ የሰይጣን ባሮች አይደለንም።
በኀጢአት ምክንያት ዲያብሎስ ጌታው የኾነለት ኹሉ በንስሐ በር ወደ ክርስቶስ ባርያነት ይመለስ።
አንድ ጌታ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ።
አንዲት ሃይማኖት፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ።
አንዲት ጥምቀት፤ የሥላሴ ልጅነት።
አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ሐዋርያት የሰበሰቧት።
አንድ መንበር፤ መንበረ ኢትዮጵያ።
አንድ ፓትርያርክ፤ እጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።
አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ዘሀገረ ኢትዮጵያ።
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢
#አንድ_ሰው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
🙏7
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡
ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
አንድ ሰው
ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
አንድ ሰው
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
🙏3
Forwarded from ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ::
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡
በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡
በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡
ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡
እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡

ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡
ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡
ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡
በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡
በመግለጫውም፡-
፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡
፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡
በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡
ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡