የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram
ትንሽ ዕረፍት
ምን ይፈጠር ይሆን ባንኖር ዛሬ'ንኳ
ይታይ ይሆን እንዴ ህይወት ስውር መልኳ
እስትንፋስ ቢቋረጥ እንጃ ምን ይቀራል
እጃችን ሳይነካው...
የደፈረሰ አለም መች በኛ ይጠራል?
እንጃ....
እንዲህ ምንባክነው ኑረት ሞት እስኪሆን
በማን እንቅልፍ ላይ ቅዠት ሆነን ይሆን
ምናለ ብንማር
ዘመም ሲያደርገን መኖር ወደ ገደል
ከሞታችን ጋራ ኑሮን ማደላደል
አለም አስር ላትሆን በልታን ላትጠረቃ
ምን ይለናል ህይወት እዚጋ ቢያበቃ።

@getmtg
@getmtg
1

ስለማላጎድል

ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡

አልጋ ስር ሳይቀር ቤቱን ብጥር አድርጌ አፅድቻለሁ፡፡

የቶሸሸውን እቃ ሰብስቤ አጥቤያለሁ፡፡

አልጋዬን በስርዓቱ አነጥፌአለሁ፡፡

ልብስና ጫማዎቼን ለነድያን ለመስጠት እንዲያመች አድርጌ በኩርቱ ፌስታሎች አሰናድቼ በሩ ስር አስቀምጫለሁ፡፡

ሦስት ሳምንት ሙሉ ችላ ብዬ የከረምኩትን ውሃ እያንጠባጠበ የሰነበተ የሽንት ቤቱን የእጅ መታጠቢያ ቧንቧ እንኳን ባለሙያ ጠርቼ አሠርቻለሁ፡፡

ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡

ሕይወቴን ሙሉ እናንተ ቤተሰቦቼ ላይ ሸክም ሆኜ መኖሬ ሳያንስ አሁን ደግሞ የቆሸሸና የተዝረከረከ ነገር ትቼላችሁ መሄድ አልፈለግኩም፡፡

ስንት ዘመን ሙሉ ቆሻሻዬን ስታጸዱ፡ ገመናዬን ስትሸፍኑ የኖራችሁት ይበቃችኋል፡፡

አስክሬኔን መስኮት አጠገብ ያለው ሶፋዬ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ ብዙ ክኒኖች ወስጄ ለመሞት የመረጥኩት ፡ በጽዳት የቆየሁበትን ቤት ላለማቆሸሽ ነው፡፡በተለይ ግን መከረኛዋ ተመላላሽ ሠራተኛዬ ጌጤ፡ ጠዋት መጥታ በሩን ከፍታ ስትገባ በደም ተዘፍቄ፡ ወይ ተንጠልጥዬ አይታኝ በድንጋጤ ክልትው እንዳትል ነው፡ አምስት አመት ሙሉ አንዴ ሰው፡ አንዴ አፈር እየሆንኩ ያሰቃየኋት ይበቃታል፡፡

ዐውቃለሁ፡ ነገ ጠዋት እኔ ባልኖርም ጀምበር በሰዓቷ ትወጣለች፡፡ ሕይወትም ምንም እንዳልተፈጠረ፡ አንድም ሰው እንዳልጎደለ ዑደቷን ትቀጥላለች፡፡

ለዚህ ነው ልሄድ የወሰንኩት፡ በመሞቴ ምንም ስላማላጎድል፡ የትም ስለማልጎድል፡ ማንንም ስለማላጎድል፡፡

(ዥዋ ዥዌ)

@getmtg
@getmtg
😭4

"ሕይወት ጠባሳችን ዕድሜ ልክ አብሮን እንዲኖር እንጂ ...ዕድሜ ልክ ስናለቅስበት እንድንኖር አትፈቅድልንም፡፡ ካለቀስንም እየኖርን እንድናለቅስ ነው የምታደርገን፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)
@getmtg
@getmtg
💯4
እስኪ ልጠይቅህ
ከሞትክ በኋላ ኑሮ'ንዴት ይዞሀል
ያለህበት ቦታ ምኑ ይገዛሀል
ቤትህስ እንዴት ነው በልክ የሰሩልህ
ለመድከው ሞቀልህ?
ልብስ ሲሆን ጊዜ አፈር ምን ምን ይላል
መከዳ ሲያረጉት ድንጋዩስ ይደላል?
መቃብር ይሞቃል መኖርያ ሲያረጉት
ምስጥ ወዳጅ ይሆናል ቀርበው ቢላመዱት?
መልስልኝ እስኪ...
የምትፈልገውን ህይወት አሳማሪ
ምን ይናፍቅሀል ከኔ ተጨማሪ
ከአለም የተለየ አካልህ ምን አጣ
ንገረኝ ግዴለም ይዤልህ እንድመጣ።

@getmtg
@getmtg
5🔥2

"ማፍቀር ማለት በጨለማ ሰማይ ላይ ከፈሰሱት ኅልቆመሳፍርት ከዋክብት፤ አንዷን መርጦ እንደ ጨረቃ ማግዘፍ ነው፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)

Join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yebrhanambatheater
https://t.me/yebrhanambatheater
2🔥1
።።።።።
እኔ ምልሽ...
ታስታውሺ ይሆን ንገሪኝ እውነቱን
የህፃናት መዝሙር ያን እንኳን የጥንቱን
በዛ በበጋ(*2)
እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ...
አሁን አይደል የሚገባኝ..
ኑሮዬ ሳያንሰኝ ስቃዬን ልጨምር
ያመት ዕቅዴ ላይ"ፍቅር"የምደምር
ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ምስኪን ታዳጊ
በበጋ በሙቀት እጮኛ ፈላጊ
አይሰለቸኝ ቀኑ አያደክመኝ መንገድ
ላይዘልቅልኝ ነገር በልጅነት መውደድ
ስንከራተት ኖሬ..
ዘመን ጨላለመ ፀሀይዋም ጠለቀች
እድሜም አይገፋም ጨረቃ ግማሽ ነች።
አሁንስ ትዝ አለሽ...
መሸበትና ሰው ቤት ገባ
ልጅቷን አያት ተከናንባ🧕
በልብሽ ለማደር ሲመሻሽ ገባሁ
ተከልለሽ ባይሽ ልጠልፍሽ አደባሁ
ትዝ አለሽ ያ ደፋር...
እንደ'ንግድነቱ መከበር ሳያንሰው
ያሳዳሪውን ልብ የሚያስኮበልል ሰው
ደግሞ...
መውደድሽ ሳያንሰኝ ማሰቤ ሳይበቃ
የማስኮበልልሽ ለሊት በጨረቃ
እኔን የገረመኝ
በተከበርሽበት ሀገር እንዳትኖሪ፤
ባደግሽበት ደብር እንዳትቀበሪ፤
አምነሽ መከተልሽ ጨለማ ሳትፈሪ።
የ'ድላችን ማነስ
የኔ አንቺን ይዞ ዓባይ ድረስ መምጣት፤
ያባትሽ ርግማን የፈጣሪ ቅጣት፤
በበጋ ውሀ ሞልቶ መሻገርያ ማጣት።
ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ግፈኛ ወጣት
ከቤቷ አስወጥቶ ለሒያጅ የሚሰጣት
በቆምኩበት የፍቅር ዕንባ እያለቀስኩ
ዕጣ'ድሌን እየረገምኩ እየወቀስኩ
ቀና ብዬ ሳያት ሙሉ ናት ጨረቃ
አንቺን ግማሽ ጎኗን ከ እጆቼ ነጥቃ
ምናይነት ገድ ነው?
የደረሰሽ ዕጣ የደረሰኝ ዕድል
ወንዝ'ንኳ ሲሞላ ፍቅር የሚያጎድል
ይኸው...
አንቺም የለሽ አትመጪም ተመልሰሽ
ወዶ መገፋቱ ቀድሞስ መች አነሰሽ
እኔም አለሁ...
ሌቱ አልበቃኝ ቀኑ ጉዟችንን ስስል
እኔና አንቺን ከመዝሙሩ ሳመሳስል
አንዲሁ ነን እኔና አንቺ...
መውደድ ውሉን ሳያሳጣን
ፍቅራችን ነው የሚያሰቀጣን።

በዛ በበጋ በዛ በበጋ......
6
የጠፉት_በጎች....‼️

ለአንዷ በግ ብሎ፣ ከሰማይ ወረደ፤
አንዷን በግ ሊታደግ፣ እንደበግ ታረደ፤
አንዷን በግ አድኖ፣ ወደ አባቱ ሄደ።

የምፅአት ቀን ደርሶ፣ መለከት ሲነፋ፤
ዘጠና ዘጠኙ፣ የገቡበት ጠፋ።
.
የገቡበት_ጠፍቶ፣ ዘጠና ዘጠኙ፤
ታስሰው ታስሰው፣ ከሲኦል ተገኙ!!!


✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
8
አንቺዬ...
እንባሽን አርገሽው መሰናበቻ ቃል
ስቃዬ እንደ ትንፋሽ መች ተቆጥሮ ያልቃል
መጥተሽ ብታይልኝ
ያረጀ ጋዜጣ ያለቀ ሲጋራ ይዤ በመዳፌ
ጥርሴ እሰከማይታይ በ ጢም ተከቦ አፌ
እብድ ተብዬልሽ ስም ወቶልኝ ባገር
ስሜ ከምላሴ ጠፍቶኝ እስክቸገር
ኸሊቁ እንደረሳው ይሁን ብሎት ርጉም
አንዲህ ነው ብዥ ያልኩት በሰው አይን'ንደ ጉም
መጥተሽ ብታይልኝ...
ጥራር መስሎልሻል ያረፍሽበት ደረት
የምትወጂው ጉንጬስ መቼ ስጋ አለበት
ደግሞ...
ከፍጥረቱ ሁሉ ውል እንዳለሽ ነገር
ግዑዛን መች ቀሩ አንቺን ለመዘከር
የተዋወቅንበት ቡና ቤት በረንዳ
ብዙ ያለፍንበት የቤታችን ጓዳ
አብረን የሔድንበት ጭር ያለ ጎዳና
አትሞ አስቀምጦት የግሮችሽን ዳና
ባለፍኩበት ቁጥር ይታዘበኝ ይዟል
ብቻዬን ሳዘግም መንገዱም ተክዟል
እኔ ምልሽ...
ሴቶቹ በሙሉ እንዴት ነው ሚያስጠሉት
አንቺ እንደነበርሽም አንዲህ ነው ሚመስሉት?
የጋበዝኩሽ ዘፈን ፍቅሬ እያልኩኝ ውዴ
ዛሬ እንደምሰማው ሙሾ ነበር እንዴ?
ያ የምንወደው የ ሻይ ቤቱ ወንበር
ያኔም እንደ ዛሬ ይቆረቁር ነበር?
አቤት መመሳቀል ወየው ቅርፅ ማጣት
አንቺ ሔደሻል ብሎ እግዜር ምድርን ቀጣት።
እንዲህ እንዲህ እያልኩ...
የፃድቃን ትውውቅ የሌለው ቀጠሮ
ካገናኘን ብዬ ጉዳት ቁስሌን ቆጥሮ
መንገድ ላይ ነው ምውል ስመላለስበት
ብትመጪልኝ ምን አለበት
ደሞ መንገዱ ዳር...
አንዱ ህፃን ቆሞ ተመዘን ይለኛል
የሚመዘን አካል መች ከኔ ይገኛል
ጉዴ መች አለቀ
የ ህዝቡ ሲገርመኝ
የልጁ ሲገርመኝ ሚዛኑ አሸሞረ
ኪሎዬን ሊነግረኝ 80 ቆጠረ
ምንድነው ሰማንያ ስቴጅ የቀደድነው?
ከተሰየመበት ዙፋን ያወረድነው?
ብቻዬን ሆኜ ነው 80 የሆነው?
ወይስ ናፍቆትሽን አንድ ለይ መዘነው?
ግዴለም ተሳስቷል..
ስጋ የተባለ ከአካሌ አስኪጠፋ
ተይው ደናውን ልብስ ካልሲዬ'ስኪሰፋ
ምንምን ብዬልሽ መች ሰው እመስላለሁ
ብቻ በተስፋ አለሁ።
ብትመጪ ምናለ...
ጥዑም ፍቅራችንን ቆፈን አቆራምዶት
መንገደኛ ሲያልፈው ረግጦ ተራምዶት
ጨክነሽ ላትተይው ቆርጬ ላልረሳው
እስኪ ምናለበት መጥተሽ ብናነሳው።
10

በመንደር ሲያልፍ ተጠርዞ
‎አይተነፍስ ጭንቅ አርግዞ

‎እጥፍ ቀንበር በጫንቃው ላይ
‎ችግር አየው በግዞት ላይ

‎የዛሬ ወላጁን የነገ ውላጁን
‎በልተው ያድሩ ዘንዳ የሚጠብቁ እጁን

‎ሀገር የሚያቀናው ባዶ እግሩን ተጉዞ
‎ለጓዶቹ ደስታ እሱ ግን ተክዞ

‎ሰማይ ቢደፋበት መች አላማው ሊነጥፍ
‎ቢቸነክሩትም አይችል ቃሉን ሊቀጥፍ

‎ቢቀጥንም ጠጅ ነው ለሺ ይበቃል አንዱ
‎ወንድ ልጅ ማሰሪያው ወንድ ልጅ ገመዱ

✍️ Zemed
@getmtg
@getmtg
6
፡ old man says

አንድ ጎልማሳ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁት ፥ ሴቶች ለሚፈልጉት ሰው እንዴት እንደሚያቀሉት ብታይ ኖሮ መልፋትህን ታቆም ነበር። አጸፋ የሌለው ፍቅር በወንፊት ላይ ውሀን ለመቅዳት እንደመሞከር ነው ። ወንፊቱም አይሞላ አንተም ውሀ ይዘህ አትሄድም። እሷም ፍቅርህ ዋጋው አይገባት አንተም የራስህ አታደርጋትም። ወንድ ልጅ ሳለህ ምን ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዳለብህ እወቅ አለበለዝያ ፍቅርም ያልቃል ፍላጎትም ይነጥፋል የጓጓህለት ሁሉ መልኩን ስታይ እንደማይረባ ትረዳለህ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

✍️ Zemed
@getmtg
@getmtg
5👏1💯1
:
አቅጄ ነበረ በልኬ ሰፍቼ
‎አጣማጅ አቻዬን ከ'ቅዴ ከትቼ
‎በውጣ ውረዴ በጎንበስ ቀናዬ
‎ነገን እያሳየሽ የቆምሽ ከኋላዬ
‎ነብስሽ እና ነብሴ አንዳች ሳይሞክሩ
‎እንደተላመዱ ምነው ቢፋቀሩ
‎ቀናት ሲጋልቡ  ፣ አዝማናት ሲረግቡ
‎ጣፋጭ ቃሎቻችን ከጎታ ሳይገቡ
‎ልጆቻችን አድገው በወግ ሳያገቡ
‎ይሄን ሁሉ ሳላይ ፍፃሜ ትንቢቱን
‎ባንኜ ሳልነቃው የህልም ዓለም 'ሌቱን
‎እንዳላጣሽ ፈራሁ ያይኖቼን ማረፊያ
‎ወይ አላሳስርሽ እን ስርቆት ዝርፊያ
‎አልተክልሽም ነገር እንደ ደጅ አበቦች
‎ይዤሽ አልዞር ብትሆኝ እንደ ደሜ ስሮች
‎እና ምን ተሻለ፥
‎እንደው እንደ ዘበት እንደ አፍ ወለምታ
‎ሳይጨነቁበት እንዳስተጋቡት ቃል እንደ ቀን እፎይታ
‎ምነው ቢታከሙት አንቺጋራ መንተው የልብን ወለምታ
‎እውነትን ተናገርሁ አምነሽ ተቀበይኝ
‎እኔ መሽቶብኛል አንቺም አሳድሪኝ።

✍️ Zemed
@ getmtg
@getmtg
7👏2🔥1