የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

"መቼስ ለትዝታ ሩቅ የሚባል _ላለመድረስ ከፈለጉም ቅርብ የሚባል ቦታ የለም፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)

@getmtg
@getmtg
👍43👏1

ሰው በምን ይጽናናል?

‎ዘፈን ካልዘፈነ
‎ግጥም ካልገጠመ
‎ካላንጎራጎረ . . .
‎አንድ ልቡን ካ'ንዱ ካላከራከረ
‎ካላመካከረ
‎ሰው በምን ይጽናናል?
‎እንጃ . . .
‎አያዝን ይሆናል፡፡
‎አይከፋው ይሆናል፡፡

‎ (መስፍን ወንድወሰን)

@getmtg
@getmtg
3

ቀን ሲመጣ ሊለይለት
‎ሲያሰናዳ ለድል ድግስ የነፃነት ሽርጉዱ
‎ተው ብለውት ተው ላልሰማ
‎አሻፈረኝ እምቢኝ ላለ
አድዋ ነው ቅን መንገዱ!

Mekdi
@getmtg
@getmtg
7

ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)
ዋ! ....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....

ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና....

ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤

ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-አልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!

ዋ! .... ዓድዋ ....
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በሰው-በሰው!

ዋ! .... ዓድዋ ....

ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና።

.... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....

(የካቲት - ፲፱፻፷፬ - ዓድዋ)
6🔥1

"ጊዜ ዝቅ ሲያደርግ መርዶህን እንኳን ደህና ሰው አያረዳልህም፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)
@getmtg
@getmtg
6🔥1

የጀግና ሚስት
(ሕይወት እምሻው)

ልጇን ወገቡ ላይ አቅፋና በዐጥንታም ዳሌዋ ደግፋ፡ ሰላላ እግሮቹ በዳሌዋ ግራና ቀኝ እየዋለሉ ወደ ቢሮው ገባች፡፡ ልጁ ታቅፎ ለመሄድ ስለሚተልቅ፡ ረጅሙን መንገድ በእግሩ ለመሄድ ደግሞ ገና ስለነበር፡ አንዴ እያወረደች አንዴ እያቀፈችው ነው እዚህ የደረሰችው፡፡

ጦርነቱ ካበቃ በኋላ እናትና ልጅ በዚህ ሁኔታ፡ እዚህ ቢሮ ሲመላለሱ ዛሬ ዘጠነኛ ጊዜያቸው ነው፡፡

ባለቤቷና ሌሎች ጓዶቹ ከአዛዣቸው ጋር የተነሡት የቡድን ፎቶግራፍ ጨለምለም ባለው ኮሪደር ግድግዳ ላይ አሁንም ድረስ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡

የባሏን በጦር ሜዳ መሰዋት በተረዳች በዐስራ አምስተኛው ቀን ባሎቻቸውን ጦር ሜዳ ላይ ካጡ ሌሎች ሴቶች ጋር በምሬት ስታነባ፡ እኚሁ የጦር አዛዥ በወታደራዊ አልባሳት ተሸልመውና በሜዳይ ተንቆጥቁጠው፡ ተቀባብለው ወደሚጠብቋቸው ካሜራዎች በመቅረብ፡ "ባሎቻችሁ በእውነት ጀግኖች ናቸው፡፡ ለሀገራቸው ክብርና አንድነት ሲሉ ጥለው ወድቀዋልና ሀገራቸው ውለታቸውን አትረሳም፡ ሁሌም ከጎናችሁ ነን" እንዳሉ አስታወሰች፡፡

ከጥቂት ወራት በኋላ፡ የርስበርሱ ጦርነት አብቅቶ ሰላም ወረደ ተባለ፡፡ እኚሁ የጦር አዛዥ ከዐማፂው የጦር መሪ ጋር ሲሣሣቁና ሲጨባበጡ በቴሌቪዥን መስኮት ተመለከተች፡፡

ገና ወደ ቢሮው ስትገባ በመሰላቸት ያያት የካሳ ክፍያ አስተባባሪ መኮንን፡ እንደ ሌላው ጊዜ ፋይሏን ለመክፈት እንኳን ሳይሞክር፡ ካንገት በላይ ሰላምታ ሰጣትና፡

"ወይዘሮ ልዩነት! ጦርነቱ ካበቃ ወዲህ ዐዳዲስ የካሳ ክፍያ ጥያቄዎችን መቀበል አቁመናል፡፡ ስለዚህ እየተመላለስሽ በከንቱ ባትደክሚ ይሻላል፡፡ በመልሶ ማልማት ስራ ተጠምደናል፡ ሌላም ብዙ ስራ አለብን" አላት፡፡

ልጇን አንጠልጥላ ከጊቢው ስትወጣ ለመጫን ከተሰለፉት ሚኒ ባሶች አንዱ የግርማ ተፈራን ቤተሰቦቼን ዐደራ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲጫወት ሰማች፡፡

ለሀገሬ ስታገል ለድንበሯ

ተኝቻለሁ እኔም ካፈሯ

ስለድል ታሪኬ ስታወሱ

ቤተሰቦቼን እንዳትረሱ

እንዳይራቡብኝ እስታውሱልኝ

እንዳይራቆቱ አልብሱልኝ

እንዳይቸገሩ ልጆቼ

ዐደራ ብያለሁ ወገኖቼ

(ዥዋ ዥዌ)
@getmtg
@getmtg
3🔥3

"ማውራትም ወሬ ማደናቀፍም በልካቸው የተሰጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ የብዙኃኑ መክሊት፤ ሕይወት ይስፋውም ይጥበበውም ከሕመሙ ጋር በዝምታ መቀመጥ ነዉ_!!"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)

@getmtg
@getmtg
🔥61
።።።።።።ነብየ ቅዠት።።።።።

ጤዛ ለማየት ማታ ጉዞ
ዱላ ፍለጋ ሌባ ይዞ

ቅጠል ማሳመር ስር በጥሶ
ግመል መንትፎ አጎምብሶ

ስርቆት መሞከር እያሳሉ
ፆሞ መጸለይ እየበሉ

ዛሬ ቢሳኩ እኚህ ሁሉ
ችግሮቻችሁ ይፈታሉ!

አሜን አትሉም?

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
10

አትምጣ ግዴለም
‎          ትመጣለህ ብዬ አልጠብቅህ ይቅር
‎ከቶ አትሄድም ነበር
‎        አለኝ ያልከው መውደድ ቢሆንብህ ፍቅር

@getmtg
@getmtg
9

"የሰላም ትክክለኛ ትርጉም ረብሻ አለመኖር አይደለም፤ መነሻው ፍቅር የሆነ ረብሻ በነፍስ ውስጥ እንደመዓበል መተራመሱ ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰላም ውሃው እንደደረቀ ወንዝ ነው፡፡ በሰላም ውስጥ ወንዝ መፍሰስ አለበት፤ ወንዙን ሊሻገሩ የሚታገሉ ነፍሶች መኖር አለባቸው፤ በውሃው ውስጥ የሚጋጩ የሚሳሳሙ ድንጋዮች መኖር አለባቸው፤ አሳዎች መኖር አለባቸው፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)
@getmtv
@getmtg
🔥5👍1
ትንሽ ዕረፍት
ምን ይፈጠር ይሆን ባንኖር ዛሬ'ንኳ
ይታይ ይሆን እንዴ ህይወት ስውር መልኳ
እስትንፋስ ቢቋረጥ እንጃ ምን ይቀራል
እጃችን ሳይነካው...
የደፈረሰ አለም መች በኛ ይጠራል?
እንጃ....
እንዲህ ምንባክነው ኑረት ሞት እስኪሆን
በማን እንቅልፍ ላይ ቅዠት ሆነን ይሆን
ምናለ ብንማር
ዘመም ሲያደርገን መኖር ወደ ገደል
ከሞታችን ጋራ ኑሮን ማደላደል
አለም አስር ላትሆን በልታን ላትጠረቃ
ምን ይለናል ህይወት እዚጋ ቢያበቃ።

@getmtg
@getmtg
1

ስለማላጎድል

ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡

አልጋ ስር ሳይቀር ቤቱን ብጥር አድርጌ አፅድቻለሁ፡፡

የቶሸሸውን እቃ ሰብስቤ አጥቤያለሁ፡፡

አልጋዬን በስርዓቱ አነጥፌአለሁ፡፡

ልብስና ጫማዎቼን ለነድያን ለመስጠት እንዲያመች አድርጌ በኩርቱ ፌስታሎች አሰናድቼ በሩ ስር አስቀምጫለሁ፡፡

ሦስት ሳምንት ሙሉ ችላ ብዬ የከረምኩትን ውሃ እያንጠባጠበ የሰነበተ የሽንት ቤቱን የእጅ መታጠቢያ ቧንቧ እንኳን ባለሙያ ጠርቼ አሠርቻለሁ፡፡

ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡

ሕይወቴን ሙሉ እናንተ ቤተሰቦቼ ላይ ሸክም ሆኜ መኖሬ ሳያንስ አሁን ደግሞ የቆሸሸና የተዝረከረከ ነገር ትቼላችሁ መሄድ አልፈለግኩም፡፡

ስንት ዘመን ሙሉ ቆሻሻዬን ስታጸዱ፡ ገመናዬን ስትሸፍኑ የኖራችሁት ይበቃችኋል፡፡

አስክሬኔን መስኮት አጠገብ ያለው ሶፋዬ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ ብዙ ክኒኖች ወስጄ ለመሞት የመረጥኩት ፡ በጽዳት የቆየሁበትን ቤት ላለማቆሸሽ ነው፡፡በተለይ ግን መከረኛዋ ተመላላሽ ሠራተኛዬ ጌጤ፡ ጠዋት መጥታ በሩን ከፍታ ስትገባ በደም ተዘፍቄ፡ ወይ ተንጠልጥዬ አይታኝ በድንጋጤ ክልትው እንዳትል ነው፡ አምስት አመት ሙሉ አንዴ ሰው፡ አንዴ አፈር እየሆንኩ ያሰቃየኋት ይበቃታል፡፡

ዐውቃለሁ፡ ነገ ጠዋት እኔ ባልኖርም ጀምበር በሰዓቷ ትወጣለች፡፡ ሕይወትም ምንም እንዳልተፈጠረ፡ አንድም ሰው እንዳልጎደለ ዑደቷን ትቀጥላለች፡፡

ለዚህ ነው ልሄድ የወሰንኩት፡ በመሞቴ ምንም ስላማላጎድል፡ የትም ስለማልጎድል፡ ማንንም ስለማላጎድል፡፡

(ዥዋ ዥዌ)

@getmtg
@getmtg
😭4

"ሕይወት ጠባሳችን ዕድሜ ልክ አብሮን እንዲኖር እንጂ ...ዕድሜ ልክ ስናለቅስበት እንድንኖር አትፈቅድልንም፡፡ ካለቀስንም እየኖርን እንድናለቅስ ነው የምታደርገን፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)
@getmtg
@getmtg
💯4
እስኪ ልጠይቅህ
ከሞትክ በኋላ ኑሮ'ንዴት ይዞሀል
ያለህበት ቦታ ምኑ ይገዛሀል
ቤትህስ እንዴት ነው በልክ የሰሩልህ
ለመድከው ሞቀልህ?
ልብስ ሲሆን ጊዜ አፈር ምን ምን ይላል
መከዳ ሲያረጉት ድንጋዩስ ይደላል?
መቃብር ይሞቃል መኖርያ ሲያረጉት
ምስጥ ወዳጅ ይሆናል ቀርበው ቢላመዱት?
መልስልኝ እስኪ...
የምትፈልገውን ህይወት አሳማሪ
ምን ይናፍቅሀል ከኔ ተጨማሪ
ከአለም የተለየ አካልህ ምን አጣ
ንገረኝ ግዴለም ይዤልህ እንድመጣ።

@getmtg
@getmtg
5🔥2

"ማፍቀር ማለት በጨለማ ሰማይ ላይ ከፈሰሱት ኅልቆመሳፍርት ከዋክብት፤ አንዷን መርጦ እንደ ጨረቃ ማግዘፍ ነው፡፡"

(ከዕለታት ግማሽ ቀን)

Join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yebrhanambatheater
https://t.me/yebrhanambatheater
2🔥1