፡
ልብስ ሰፊዋ
(በሕይወት እምሻው)
በከተማው አደባባይ እምብርት ላይ የተሰቀለው ባንዲራ ብዙ ክረምትና በጋ ስለተፈራረቀበት ተጎሳቁሏል፡፡ በክረምት ዝናብ ረጥቧል፡ በበጋ አቧራ አድፏል፡ በሃሩር ንዳድ ገርጥቷል፡፡ በነፋስ ሳቢያ ተቀዷል፡፡ ግን ማንም ልብ ያለው፡ ማንም ደንታ የሰጠው አልነበረም፡፡
ፖለቲከኞቹ "በትላልቅ ጉዳዮች" ተጠምደዋል፡፡
ወታደሮቹ የሀገሪቱን ድንበር ከጠላት እየጠበቁ ነው፡፡
የመንፈስ አባቶች ነፍሳትን ከሲኦል በማዳን፡ ሕዝቡ ደግሞ ኑሮውን በማሸነፍ ሩጫ ተጠምደዋል፡፡
ከአደባባዩ በስተግራ በኩል ጥግ ላይ ምስኪን ልብስ ሰፊ ግን በባንዲራው ጉዳይ ተብከንክናለች፡፡
አንድ ቀን ከሰዐት በኋላ በአጠገቧ በጥድፊያ የሚያልፈውን ቁመተ ሎጋ ሰው አስቆመችና ባንዲራውን እንዲያወርድላት ጠየቀችው፡፡
"ለምን?" ብሎ ጠየቃት፡፡
"ለምን ...? እያየኸው .... እጅግ ቆሽሿል፡ ቀለሞቹ መለየት እስኪያቅት ገርጥቷል፡፡ በዚያ ላይ ተቀዷል፡፡ ቀለሞቹን መመለስ ባልችል እንኳን፡ ቢያንስ አጥቤ ልስፋው ብዬ እኮ ነው ... ልብስ ሰፊ እኮ ነኝ" ብላ መለሰችለት፡፡
ሰውዬው ሣቀና እንዲህ አላት፡
"ምንሸ ተነካና? ባንዲራ አይደል ... ምን አገባሽ ... የድሃ ቅንጡ ነሽ ባክሽ ... እስቲ መጀመሪያ የተቀደደ ልብስ ስፊና የራስሽን ቀዳዳ ድፈኚ ... የደላሽ!"
ጭንቅላቷን ባለመስማማት ነቀነቀች፡፡
"ግን እኮ ተቀዷል ... " ከማለቷ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡
ጥቂት ካሰበች በኋላ
ሁለት የጎዳና ጎረምሶችን ብር አስጨብጣና ምሰሶውን እንዲወጡ አድርጋ፡ ባንዲራውን አስወረደች፡፡
አጠበችው፡ ሰፋችው፡፡ ልጆቹ መልሰው እንዲሰቅሉላት ካደረገች በኋላ ሲውለበለብ እየተመለከተች ፈገግ ብላ፡ "ጎበዞች! እንደ ቀድሞ ግርማ ሞገሱ ባያስደነግጥም ከቀዳዳ እና ከቆሻሻው ይሄ ይሻላል" አለች፡፡
በነጋታው ከዚህ በፊት ዐይታቸው የማታውቅ ሰዎች አዲስ ባንዲራ ይዘው መጡ፡፡ አጥባና ሰፍታ የሰቀለችውን ባንዲራ አውርደው ጣሉና በአዲሱ ተኩት፡፡
አንዱን ፈራ ተባ እያለች ተጠጋችውና፡ "ምነው እስከዛሬ ሳታዩት ገና እስተካክዬው ስሰቅለው ልትተኩት መጣችሁ?" ስትል ጠየቀችው፡፡
ሰውዬው ዞርም ብሎ ሳያያት፡
"ለዐይን ይቀፋል፡፡ እንዲህ እንደነገሩ የተጣፈ ባንዲራ በዋና አደባባያችን ላይ ተሰቅሎ ማየት በጣም ይቀፋል" ብሎ መለሰላት፡፡
(ዥዋ ዥዌ)
@getmtg

😁4❤3
፡
ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)
ዋ! ....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና....
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-አልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ! .... ዓድዋ ....
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በሰው-በሰው!
ዋ! .... ዓድዋ ....
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና።
.... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
(የካቲት - ፲፱፻፷፬ - ዓድዋ)
ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)
ዋ! ....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና....
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-አልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ! .... ዓድዋ ....
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በሰው-በሰው!
ዋ! .... ዓድዋ ....
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና።
.... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
(የካቲት - ፲፱፻፷፬ - ዓድዋ)
❤6🔥1
፡
የጀግና ሚስት
(ሕይወት እምሻው)
ልጇን ወገቡ ላይ አቅፋና በዐጥንታም ዳሌዋ ደግፋ፡ ሰላላ እግሮቹ በዳሌዋ ግራና ቀኝ እየዋለሉ ወደ ቢሮው ገባች፡፡ ልጁ ታቅፎ ለመሄድ ስለሚተልቅ፡ ረጅሙን መንገድ በእግሩ ለመሄድ ደግሞ ገና ስለነበር፡ አንዴ እያወረደች አንዴ እያቀፈችው ነው እዚህ የደረሰችው፡፡
ጦርነቱ ካበቃ በኋላ እናትና ልጅ በዚህ ሁኔታ፡ እዚህ ቢሮ ሲመላለሱ ዛሬ ዘጠነኛ ጊዜያቸው ነው፡፡
ባለቤቷና ሌሎች ጓዶቹ ከአዛዣቸው ጋር የተነሡት የቡድን ፎቶግራፍ ጨለምለም ባለው ኮሪደር ግድግዳ ላይ አሁንም ድረስ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡
የባሏን በጦር ሜዳ መሰዋት በተረዳች በዐስራ አምስተኛው ቀን ባሎቻቸውን ጦር ሜዳ ላይ ካጡ ሌሎች ሴቶች ጋር በምሬት ስታነባ፡ እኚሁ የጦር አዛዥ በወታደራዊ አልባሳት ተሸልመውና በሜዳይ ተንቆጥቁጠው፡ ተቀባብለው ወደሚጠብቋቸው ካሜራዎች በመቅረብ፡ "ባሎቻችሁ በእውነት ጀግኖች ናቸው፡፡ ለሀገራቸው ክብርና አንድነት ሲሉ ጥለው ወድቀዋልና ሀገራቸው ውለታቸውን አትረሳም፡ ሁሌም ከጎናችሁ ነን" እንዳሉ አስታወሰች፡፡
ከጥቂት ወራት በኋላ፡ የርስበርሱ ጦርነት አብቅቶ ሰላም ወረደ ተባለ፡፡ እኚሁ የጦር አዛዥ ከዐማፂው የጦር መሪ ጋር ሲሣሣቁና ሲጨባበጡ በቴሌቪዥን መስኮት ተመለከተች፡፡
ገና ወደ ቢሮው ስትገባ በመሰላቸት ያያት የካሳ ክፍያ አስተባባሪ መኮንን፡ እንደ ሌላው ጊዜ ፋይሏን ለመክፈት እንኳን ሳይሞክር፡ ካንገት በላይ ሰላምታ ሰጣትና፡
"ወይዘሮ ልዩነት! ጦርነቱ ካበቃ ወዲህ ዐዳዲስ የካሳ ክፍያ ጥያቄዎችን መቀበል አቁመናል፡፡ ስለዚህ እየተመላለስሽ በከንቱ ባትደክሚ ይሻላል፡፡ በመልሶ ማልማት ስራ ተጠምደናል፡ ሌላም ብዙ ስራ አለብን" አላት፡፡
ልጇን አንጠልጥላ ከጊቢው ስትወጣ ለመጫን ከተሰለፉት ሚኒ ባሶች አንዱ የግርማ ተፈራን ቤተሰቦቼን ዐደራ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲጫወት ሰማች፡፡
ለሀገሬ ስታገል ለድንበሯ
ተኝቻለሁ እኔም ካፈሯ
ስለድል ታሪኬ ስታወሱ
ቤተሰቦቼን እንዳትረሱ
እንዳይራቡብኝ እስታውሱልኝ
እንዳይራቆቱ አልብሱልኝ
እንዳይቸገሩ ልጆቼ
ዐደራ ብያለሁ ወገኖቼ

❤3🔥3
፡
ስለማላጎድል
ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡
አልጋ ስር ሳይቀር ቤቱን ብጥር አድርጌ አፅድቻለሁ፡፡
የቶሸሸውን እቃ ሰብስቤ አጥቤያለሁ፡፡
አልጋዬን በስርዓቱ አነጥፌአለሁ፡፡
ልብስና ጫማዎቼን ለነድያን ለመስጠት እንዲያመች አድርጌ በኩርቱ ፌስታሎች አሰናድቼ በሩ ስር አስቀምጫለሁ፡፡
ሦስት ሳምንት ሙሉ ችላ ብዬ የከረምኩትን ውሃ እያንጠባጠበ የሰነበተ የሽንት ቤቱን የእጅ መታጠቢያ ቧንቧ እንኳን ባለሙያ ጠርቼ አሠርቻለሁ፡፡
ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡
ሕይወቴን ሙሉ እናንተ ቤተሰቦቼ ላይ ሸክም ሆኜ መኖሬ ሳያንስ አሁን ደግሞ የቆሸሸና የተዝረከረከ ነገር ትቼላችሁ መሄድ አልፈለግኩም፡፡
ስንት ዘመን ሙሉ ቆሻሻዬን ስታጸዱ፡ ገመናዬን ስትሸፍኑ የኖራችሁት ይበቃችኋል፡፡
አስክሬኔን መስኮት አጠገብ ያለው ሶፋዬ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ ብዙ ክኒኖች ወስጄ ለመሞት የመረጥኩት ፡ በጽዳት የቆየሁበትን ቤት ላለማቆሸሽ ነው፡፡በተለይ ግን መከረኛዋ ተመላላሽ ሠራተኛዬ ጌጤ፡ ጠዋት መጥታ በሩን ከፍታ ስትገባ በደም ተዘፍቄ፡ ወይ ተንጠልጥዬ አይታኝ በድንጋጤ ክልትው እንዳትል ነው፡ አምስት አመት ሙሉ አንዴ ሰው፡ አንዴ አፈር እየሆንኩ ያሰቃየኋት ይበቃታል፡፡
ዐውቃለሁ፡ ነገ ጠዋት እኔ ባልኖርም ጀምበር በሰዓቷ ትወጣለች፡፡ ሕይወትም ምንም እንዳልተፈጠረ፡ አንድም ሰው እንዳልጎደለ ዑደቷን ትቀጥላለች፡፡
ለዚህ ነው ልሄድ የወሰንኩት፡ በመሞቴ ምንም ስላማላጎድል፡ የትም ስለማልጎድል፡ ማንንም ስለማላጎድል፡፡

😭4