፡
ልዕለ መልካምነትሽ
እፁብነትን ከትቦ
ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
እንደ ፅጌ አበባዋ
የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
የማትጠገብ መአዛ
እኔ ከጎንሽ ያለሁ
የውስጤን አውነት አምቄ
ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
በወንድምነት ሽፋን
ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
ችዬ እንኳ የማልለይሽ
የልቤን መንገር ያቃተኝ
ብታውቂው የማጣት ስጋት
ዝም ብል የጭንቄ በደል
ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ
ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል
ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ
ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
አፌ ግን ፈራ መናገር
የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ
@getmtg
@getmtg
ልዕለ መልካምነትሽ
እፁብነትን ከትቦ
ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
እንደ ፅጌ አበባዋ
የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
የማትጠገብ መአዛ
እኔ ከጎንሽ ያለሁ
የውስጤን አውነት አምቄ
ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
በወንድምነት ሽፋን
ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
ችዬ እንኳ የማልለይሽ
የልቤን መንገር ያቃተኝ
ብታውቂው የማጣት ስጋት
ዝም ብል የጭንቄ በደል
ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ
ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል
ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ
ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
አፌ ግን ፈራ መናገር
የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ
@getmtg
@getmtg
❤10
፡
ሙሾ ላመለጠ ወጣትነት
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ሳይደምን ይዘንባል
ይዶፋል
ከደጃፌ ግርጌ የሕይወት ጎርፍ ያልፋል
የክንፌ ርጋፊ
አንድ የላባ ነዶ
ያካሌ ቅራፊ
የቀረ ተጎርዶ
ተጠርጎ ሲወሰድ በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
ሲጋልብ በፊቴ ይህ የውሀ ሰጋር
ጀንበሬን አየኋት
ተጠርጋ ሰትሄድ ከሰርዲን ጣሳ ጋር
የልጅነት ቅርሴ
ድዴ ያባረራት ያች የወተት ጥርሴ
ካሮጌ ቆርኪ ጋር አብራ ተቀላቅላ
ባረፋ ተከባ በጎርፍ ጀልባ ታዝላ
ስትሄድ እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
የመጀመሪያዋ የጉንጬ ላይ ቡግር
የመጨረሻዋ የራሴ ላይ ጠጉር
ከሳር ከትቢያው ጋር እንደተቃቀፉ
በጎርፍ ጀርባ ላይ እየተንሳፈፉ
እንደዋዛ ሲያልፉ
በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
@getmtg
@getmtg
ሙሾ ላመለጠ ወጣትነት
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ሳይደምን ይዘንባል
ይዶፋል
ከደጃፌ ግርጌ የሕይወት ጎርፍ ያልፋል
የክንፌ ርጋፊ
አንድ የላባ ነዶ
ያካሌ ቅራፊ
የቀረ ተጎርዶ
ተጠርጎ ሲወሰድ በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
ሲጋልብ በፊቴ ይህ የውሀ ሰጋር
ጀንበሬን አየኋት
ተጠርጋ ሰትሄድ ከሰርዲን ጣሳ ጋር
የልጅነት ቅርሴ
ድዴ ያባረራት ያች የወተት ጥርሴ
ካሮጌ ቆርኪ ጋር አብራ ተቀላቅላ
ባረፋ ተከባ በጎርፍ ጀልባ ታዝላ
ስትሄድ እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
የመጀመሪያዋ የጉንጬ ላይ ቡግር
የመጨረሻዋ የራሴ ላይ ጠጉር
ከሳር ከትቢያው ጋር እንደተቃቀፉ
በጎርፍ ጀርባ ላይ እየተንሳፈፉ
እንደዋዛ ሲያልፉ
በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ
@getmtg
@getmtg
👏3❤2
Forwarded from 🚶♂️📚לֵוִי
በYouTube መተናል🎉🎊!
#ሳይኮሎጂያዊ..
#ፍልስፍናዊ.. እና
#ሐይማኖታዊ.. እሳቤዎችን በሰፊው የምንዳስስበትን..
እንዲሁም፦ በአጫጭር ድርሰቶቼ ውስጥ የተገለፁትን ገፀባሕርያት ከሳይኮሎጂ አንፃር የምንገመግብበትን የYouTube channel subscribe በማድረግ እናስመርቀው 🙏
https://youtube.com/watch?v=UYS5BsR-0g0&si=GVthq0_J5oHs-gA1
YouTube
የእናንተ ዝግጅት ብቻ ይቀረናል!
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
ብቻዬን ትተሺኝ
ላትመለሽ ነገር መች በቃኝ መናፈቅ
ልማዴ አድርጌው ማይመጣ መጠበቅ
እጠብቅሻለሁ እንዴት ልግለፅልሽ
ትናፍቂኛለሽ እንደምን ልበልሽ
የራበው አስቀዳሽ ትግስት የነፈገው
ከካህኑ ምላስ ዕትው የምትል ቃል እንደሚፈልገው
በዛሬ ቀመር ውስጥ ከሰው አንቺን ባጣ
ትናፍቂኛለሽ እንደ ትላንትና ደግሞ'ንደማይመጣ
ትናፍቂኛለሽ...
ኩልል እንደምትል የውሀ ጠብታ
ሀሩር ያነደደው ዘማች እንደሚሻት የ ዓይኑ ውልብታ
ትናፍቂኛለሽ...
አርባ ቀን አርባ ሌት እንደፆመ መናኝ
ቀን እንደረዘመው ካምላኩ እስኪገናኝ
እጠብቅሻለሁ
ነፍስና ስጋዬን ፈጥሮት ለኩነኔ
ዘመኑ ሲታደስ እያረጀሁ እኔ
ልክ'ንደ መስከረም
ከነሀሴ ዝናብ አበባ እንዳገኘ
የኔም ጥበቃዬ ባንቺ ከተዳኘ
ብቻ ምን ልበልሽ እጠብቅሻለሁ
ያለፈው ዘመኔ...
ስቴጅ ያፈረስሽው እንደ ጥንት መንደር
ዛሬ መመለስሽ ላያስክሰው ነገር
@getmtg
@getmtg
ላትመለሽ ነገር መች በቃኝ መናፈቅ
ልማዴ አድርጌው ማይመጣ መጠበቅ
እጠብቅሻለሁ እንዴት ልግለፅልሽ
ትናፍቂኛለሽ እንደምን ልበልሽ
የራበው አስቀዳሽ ትግስት የነፈገው
ከካህኑ ምላስ ዕትው የምትል ቃል እንደሚፈልገው
በዛሬ ቀመር ውስጥ ከሰው አንቺን ባጣ
ትናፍቂኛለሽ እንደ ትላንትና ደግሞ'ንደማይመጣ
ትናፍቂኛለሽ...
ኩልል እንደምትል የውሀ ጠብታ
ሀሩር ያነደደው ዘማች እንደሚሻት የ ዓይኑ ውልብታ
ትናፍቂኛለሽ...
አርባ ቀን አርባ ሌት እንደፆመ መናኝ
ቀን እንደረዘመው ካምላኩ እስኪገናኝ
እጠብቅሻለሁ
ነፍስና ስጋዬን ፈጥሮት ለኩነኔ
ዘመኑ ሲታደስ እያረጀሁ እኔ
ልክ'ንደ መስከረም
ከነሀሴ ዝናብ አበባ እንዳገኘ
የኔም ጥበቃዬ ባንቺ ከተዳኘ
ብቻ ምን ልበልሽ እጠብቅሻለሁ
ያለፈው ዘመኔ...
ስቴጅ ያፈረስሽው እንደ ጥንት መንደር
ዛሬ መመለስሽ ላያስክሰው ነገር
@getmtg
@getmtg
👍6❤5
፡
ልብስ ሰፊዋ
(በሕይወት እምሻው)
በከተማው አደባባይ እምብርት ላይ የተሰቀለው ባንዲራ ብዙ ክረምትና በጋ ስለተፈራረቀበት ተጎሳቁሏል፡፡ በክረምት ዝናብ ረጥቧል፡ በበጋ አቧራ አድፏል፡ በሃሩር ንዳድ ገርጥቷል፡፡ በነፋስ ሳቢያ ተቀዷል፡፡ ግን ማንም ልብ ያለው፡ ማንም ደንታ የሰጠው አልነበረም፡፡
ፖለቲከኞቹ "በትላልቅ ጉዳዮች" ተጠምደዋል፡፡
ወታደሮቹ የሀገሪቱን ድንበር ከጠላት እየጠበቁ ነው፡፡
የመንፈስ አባቶች ነፍሳትን ከሲኦል በማዳን፡ ሕዝቡ ደግሞ ኑሮውን በማሸነፍ ሩጫ ተጠምደዋል፡፡
ከአደባባዩ በስተግራ በኩል ጥግ ላይ ምስኪን ልብስ ሰፊ ግን በባንዲራው ጉዳይ ተብከንክናለች፡፡
አንድ ቀን ከሰዐት በኋላ በአጠገቧ በጥድፊያ የሚያልፈውን ቁመተ ሎጋ ሰው አስቆመችና ባንዲራውን እንዲያወርድላት ጠየቀችው፡፡
"ለምን?" ብሎ ጠየቃት፡፡
"ለምን ...? እያየኸው .... እጅግ ቆሽሿል፡ ቀለሞቹ መለየት እስኪያቅት ገርጥቷል፡፡ በዚያ ላይ ተቀዷል፡፡ ቀለሞቹን መመለስ ባልችል እንኳን፡ ቢያንስ አጥቤ ልስፋው ብዬ እኮ ነው ... ልብስ ሰፊ እኮ ነኝ" ብላ መለሰችለት፡፡
ሰውዬው ሣቀና እንዲህ አላት፡
"ምንሸ ተነካና? ባንዲራ አይደል ... ምን አገባሽ ... የድሃ ቅንጡ ነሽ ባክሽ ... እስቲ መጀመሪያ የተቀደደ ልብስ ስፊና የራስሽን ቀዳዳ ድፈኚ ... የደላሽ!"
ጭንቅላቷን ባለመስማማት ነቀነቀች፡፡
"ግን እኮ ተቀዷል ... " ከማለቷ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡
ጥቂት ካሰበች በኋላ
ሁለት የጎዳና ጎረምሶችን ብር አስጨብጣና ምሰሶውን እንዲወጡ አድርጋ፡ ባንዲራውን አስወረደች፡፡
አጠበችው፡ ሰፋችው፡፡ ልጆቹ መልሰው እንዲሰቅሉላት ካደረገች በኋላ ሲውለበለብ እየተመለከተች ፈገግ ብላ፡ "ጎበዞች! እንደ ቀድሞ ግርማ ሞገሱ ባያስደነግጥም ከቀዳዳ እና ከቆሻሻው ይሄ ይሻላል" አለች፡፡
በነጋታው ከዚህ በፊት ዐይታቸው የማታውቅ ሰዎች አዲስ ባንዲራ ይዘው መጡ፡፡ አጥባና ሰፍታ የሰቀለችውን ባንዲራ አውርደው ጣሉና በአዲሱ ተኩት፡፡
አንዱን ፈራ ተባ እያለች ተጠጋችውና፡ "ምነው እስከዛሬ ሳታዩት ገና እስተካክዬው ስሰቅለው ልትተኩት መጣችሁ?" ስትል ጠየቀችው፡፡
ሰውዬው ዞርም ብሎ ሳያያት፡
"ለዐይን ይቀፋል፡፡ እንዲህ እንደነገሩ የተጣፈ ባንዲራ በዋና አደባባያችን ላይ ተሰቅሎ ማየት በጣም ይቀፋል" ብሎ መለሰላት፡፡
(ዥዋ ዥዌ)

😁4❤3