፡
ልዕለ መልካምነትሽ
እፁብነትን ከትቦ
ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
እንደ ፅጌ አበባዋ
የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
የማትጠገብ መአዛ
እኔ ከጎንሽ ያለሁ
የውስጤን አውነት አምቄ
ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
በወንድምነት ሽፋን
ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
ችዬ እንኳ የማልለይሽ
የልቤን መንገር ያቃተኝ
ብታውቂው የማጣት ስጋት
ዝም ብል የጭንቄ በደል
ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ
ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል
ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ
ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
አፌ ግን ፈራ መናገር
የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ
@getmtg
@getmtg
ልዕለ መልካምነትሽ
እፁብነትን ከትቦ
ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
እንደ ፅጌ አበባዋ
የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
የማትጠገብ መአዛ
እኔ ከጎንሽ ያለሁ
የውስጤን አውነት አምቄ
ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
በወንድምነት ሽፋን
ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
ችዬ እንኳ የማልለይሽ
የልቤን መንገር ያቃተኝ
ብታውቂው የማጣት ስጋት
ዝም ብል የጭንቄ በደል
ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ
ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል
ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ
ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
አፌ ግን ፈራ መናገር
የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ
@getmtg
@getmtg
❤10