የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

አንዳንድ ሰው ለአንዴ እሹሩሩ ካልከው ዘላለም የደገስክለት ይመስለዋል፡፡

@getmtg
@getmtg
👍6

የስኬት የምኞቷን ግብ
‎ቀድማ ነው ማበጃጀቷ
‎መዋብን ታውቅበታለች
‎ልባም ናትና ልጅቷ

@getmtg
@getmtg
5

‎መቼ ጠፋኝ ኑሮ አመሉ
‎አይበግረው መውጣት መውረድ
‎አይመችም ሁሌ አይሞላ
‎አንዴ ሲል ሞቅ አንዴ በረድ

‎መረሳሳት አይባልም
‎ቅድሚያ ላሉት ሲሆን ጊዜ
‎አንድ ሰሞን ሲያጠፋፋ
‎ላይቀር ዳግም መጠያየቅ
‎ሄድ ብሎ መለስ ነው መኖር ዙሩን እያሰፋ

@getmtg
@getmtg
👍4🔥2

።።።።።።።።። ፍኖተ- በቀል ።።።።።።።።።።

ምን አለች አንዷ የኮራችብክ ዛሬ ስትቀር
ምን መለሱልህ የለመንካቸው  አሁን ስትከብር

ይሰግዱልሀል የተፀየፉህ ይዘህ ስትመጣ
ይዘምራሉ የናቁህ ሁሉ አምረህ ስትወጣ

ለመሳሰሉት ለነዚህ ትሎች ስርህ ለበዙ
ማምለጥ ከፈለክ አትሽሻቸው ስኬት ነው መርዙ!

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
4👏4🔥2

ይለፍ ያልነው ቀን አልፎ
‎               የሻትነው ቀን እስኪመጣ
‎ብቻ ግን በመጠበቅ ውስጥ
‎                     ተስፋችን ተስፋ እንዳያጣ

@getmtg
@getmtg
3🔥3🥰2

በየትኛው ርዕስ በየትኛው ሀሳብ እንዲሁም በየትኛው picture ይፃፍላችሁ?

inbox
👇👇👇👇👇
@amen1995

@getmtg
@getmtg

ያቺ እናት ጉብለ ወጣት
‎ከታቀፈችው ልጇ ጋር
‎ ፀባይ ከመልኳ ተዳምሮ
‎በቅፅበት ልቤን ስትገዛው
‎በመውደድ ዜማ ስንሳፈፍ
‎ በእሷነት ዋጋ ቀኔ አምሮ

‎እግሬ ወደእሷ እያመራ
‎ቀድሞኑ ባየኋት ቦታ
‎ ቀርቤ ባያት ደግሜ
‎ጨለማው ልቤ ነግቶለት
‎ቀስ በቀስ መስመሩን ያዘ
የፈራረሰው አለሜ

‎የተስፋ ልቧን አጉድፎ
‎ቢተዋት የልጇ አባት
‎ ባይልም እንኳን ከዚህ አለሁ
‎አለማግባቷን እያሰብኩ
‎እሷኑ እስከነልጇ እጅጉን አፍቅሬአታለሁ

@getmtg
@getmtg     
11

sometimes
the apology
never comes
when it is wanted

and when it comes
it is neither wanted
nor needed

- you are too late

(Rupi Kaur)

@getmtg
@getmtg
2👍2
1

‎አለኝ ያልኩት ጭላጭ ተስፋ
‎                 አይዞህ ብሎ ያፅናናኛል
‎ይለፍ ያልኩት ይህ ጊዜ አልፎ
‎              ነገን ማየት ያጓጓኛል

‎የናፈቀኝ ቀና መንገድ
‎ ሌላ መልኬን ሌላ ገፄን
‎የነበረኝ ያን ፈገግታ
‎ የልጅነት ያፍላ ሳቄን

‎ጊዜ ደርሶ ያጎደለውን
‎ ቀን መልሶ እስኪክሰው
‎ያጓጓኛል ነገን ማየት
‎ እንዳሰብኩት አድርጎኝ ሰው

@getmtg
@getmtg
5👍1

ልዕለ መልካምነትሽ
‎እፁብነትን ከትቦ
‎                ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
‎እንደ ፅጌ አበባዋ
‎     የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
‎                    የማትጠገብ መአዛ

‎እኔ ከጎንሽ ያለሁ
‎የውስጤን አውነት አምቄ
‎                  ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
‎በወንድምነት ሽፋን
‎ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
‎                ችዬ እንኳ የማልለይሽ    
‎   
‎የልቤን መንገር ያቃተኝ
‎ብታውቂው የማጣት ስጋት   
‎             ዝም ብል የጭንቄ በደል
‎ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ         
‎               ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል

‎ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
‎አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
‎              ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
‎ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
‎ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
‎                ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ

‎ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
‎ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
‎ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
‎አፌ ግን ፈራ መናገር
  የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ

@getmtg
@getmtg
10

ባንታጭም ለ"አብሮ"
‎ ባንሆንም አንድ ላይ
‎መፈፀሙ ላይቀር
‎ የተፃፈው ከላይ

‎ኑሮ መንገዳችን
‎ ቢሆንም ለየቅል
‎ ..... ለዛሬዋ ቀንህ ......
‎"መልካም ልደት" የሚል
‎ አለኝ የምኞት ቃል
‎  
@getmtg
@getmtg
9

ዘመን መጥቶም ቢሄድ
‎ጊዜ 'ማይለያቸው ምርጥ ጓደኛሞች
‎ያንዱ ለአንዱ ብርታት
የክፉም የደጉም ተካፋይ አለሞች

‎በአንድ ጣሪያ ታቅፈው
‎ኑሮ መሰረቱን በህብረት ያቆሙ
‎ትጋት ያፀናቸው
ተደጋግፎ ማለፍ ሰርክ እያጣጣሙ

‎ሲኖሩት ነው እንጂ
‎ቢሰማ ቢነገር ቃል የማይገልፃቸው
‎እስከ ጥግ ድረስ
ጓደኝነት ዋጋው ትርጉሙ የገባቸው

‎ እነሱ እንዲህ ናቸው😊

@getmtg
@getmtg
8

ሆነሽ ሳለ
‎ቆንጂዬ ልጅ
‎      'ምታሳሳ 'ምትወደድ
‎ቢኖርሽም አፍቃሪ ልብ
‎    መልካም ሀሳብ ቀና መንገድ

‎ወትሮ እኔን መንከባከብ
‎               ባይታክትሽ ማስደሰቱ
‎እውነት እውነት እልሻለሁ
‎         ማፍቀር ላልችል ደከምሽ እቱ

‎እያሰብኩኝ የሆንሽውን
‎         እየታየኝ ውበት መልክሽ
‎ያለሽን ግልፅ ፅኑ አቋም
‎                  የሚደነቅ ፀባይ ልክሽ

‎እየጣርኩኝ ላለማጣት
‎ ካንቺ ደጃፍ እግሬ እንዳይቀር
‎ላይሆንልኝ ደከምኩ እንጂ
‎    አይቻልም ታግሎ ማፍቀር     

@getmtg
@getmtg         
9

በኑሮ በሕይወት መንገድ
‎       ቢበዛ ህመም እንቅፋት
‎                ቢፈትን ችግር አበሳ
‎ካለው ከነበር በላይ
‎እጥፉን ይሸለመዋል
‎              የሰው ልጅ ወድቆ ሲነሳ

@getmtg
@getmtg
9

neither of us is happy
but neither of us wants to leave
so we keep breaking one another
and calling it love

(Rupi kaur)
@getmtg
@getmtg
👏41😁1
አልፈቀድክም'ንጂ ፈጥረህ ስትለቀን
መኖር ሲሰለቸን ከ'ለታት ባንዱ ቀን
ፈቅደህ ቢሆን ኖሮ...
በራሳችን መንገድ ወዳንተ እንድንመጣ
ባዶ መቅረት ነበር የዚች ምድር ዕጣ

@getmtg
@getmtg
13🔥8🤔2

‎ምንም አትበል
‎ዝምታ ነው እኔና አንተን የሚያግባባን
‎መጣላቱ ይቅር እንጂ
‎                    ባናወራስ ምን አገባን

‎ከአንደበቴ ቃል ሳይወጣ
‎የሆንኩትን ሳልናገር      
‎            ልብህ ቀድሞ ያውቅልኛል
‎እኔም ደግሞ ......
‎ምን እንደሆንክ ለመረዳት
‎ አንዴ አይንህን ማየት ብቻ ይበቃኛል

‎ቃል አንተንፍስ ተው አናውራ
‎ እንዳይብሰን ሁሉም ይቅር
‎ከስሙኝ ባይ ድምፀት ይልቅ
‎             ዝምታ ነው የእኛ ፍቅር

@getmtg
@getmtg
7👏3

ተሸፍነሽ እንኳን
ፊትሽ ተደንቅሮ የደመና እንቅፋት
‎እንደሙሽራ እንስት
‎ አማረባት እንጂ አትባይም ከፋት

@getmtg
@getmtg
8