የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

you ask
if we can still be friends
i explain how a honeybee
does not dream of kissing
the mouth of a flower
and then settle for its leaves

- i don't need more friends

(Rupi Kaur)

@getmtg
@getmtg
2

የአፍ አትቁጠር
‎ከጆሮ አልፎ ውስጥህ ያድምጥ
‎አይንህ ሳቄን
‎ልብህ ደግሞ
‎       እንባዬን ይይ የጭንቄን ምጥ
‎                        
@getmtg
@getmtg
👍4

ቀጨኔ አድባርሽ ማነው
(አስታወሰኝ ረጋሳ)

"ጋራው ሚካኤል ባይሰማን
ጋሽ ቸሬ ባለውቃቢው
የኛን ልመና አይዘነጋም
በጨለማ ሹክ ያሉት ፀሎት
እስኪፈታ ጀንበር አትነጋም"

ብለውኝ ለሊቱን ሙሉ
ካደምኩት ተሰዋ እንቅልፌ
   ሲነጋስ_!? 
ትዝታዋ እንጂ  የለችም እሷ ከቅፌ፤

እግዚአብሔር አብ ከተራራው ጫፍ
ሞገሱን ይዞ ተቀምጧል
ፀበሉን እያፈለቀ
የስንቱን የንባ ሀዘን ውጧል!

ታዲያሳ እግዚሐርዬ
የኔ እና የሷን ነገር ምነው!
በቶሎ ያልፈጠምክልኝ
ጠንቋይ ቤት ሂዷል ብለህ ነው!?

ከእንጦጦ ዳገት እስከ ሾላ ጫፍ 
እሷው ነች በሩቁ ተለጥፋልኝ
እንግዲህ ማምጣት ካቃተህ
በል ቶሎ አይኔን አጥፋልኝ

ማዞሪያን ስዞረው ውዬ
በቅርበት እሷን ካላየው
አይን አለኝ ማለት ምንድር ነው!?

"ሸክላ ሰሪ ናት" ቢሉኝ
  አፈር ሆኜ ምነው ብታፍሰኝ
በማርያም ወንዝ ውሃ አልቆጥቁጣኝ
ክንዷ ላይ ብታንተርሰኝ

ሸማዬን ላንተ አላነጥፍም
ከንግዲስ ግጥም አልጥፍም

/አምጣልኝ አልኩህ አምጣልኝ/

እምቢየው እሷ ከሌለች
ብቻዬን አልባረክም
እንግዲህስ አምላክ ነህ ብዬም
ለክብርህ ዣንጥላ አልልክም

ብትፈልግ ሲኦል ወርውረኝ
አድርገኝ ለሚፋጅ ቅጣት
አይበልጥም እሷን ከማጣት።

@getmtg
@getmtg
3

የዚህ ቀን ሲሳይ እለቱ
‎ክርስቶስ እሰይ ተወልደ
‎ሀጥያት ስር ጨልመን ሳለን
‎ሊያድነን ምድር ወረደ

‎በሄዋን የደፈረሰው
በድንግል ማርያም ሊጠራ
‎የጥፋት ታሪክ ሊታረም
‎በቤቴልሄም ተወልዷል
‎ክርስቶስ መዳኒ አለም

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል🙏

@getmtg
@getmtg
9
ባለቅኔ ነበርኩ
ባለኝ ሰዓት ቅኔ
ያ...ኔ!

ቅኔ ይሏት እርግብ
አፍኜ ስመግብ
ስታዜም ስሰማት
መዝሙሯን ስቀማት
ቀምቼ ሳፏጨው
የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤
የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ
ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤
እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል
ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል
የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ
ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ
ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ
በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ።

ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ
ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ
የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ
ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ
በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል
ምስኪን! ኪን እርግቤ
እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል?

ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን
ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን
ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት
በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥

ግን አልሆነልኝም
አልጮህ ድምፅ የለኝም
ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል
አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል?
ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል?

እውነት!

ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ!
ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ
ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ
አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ
ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ
ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ
አንድ እርግብ ነበረች፤
አሁን ግን የለችም!
ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች።

ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ

ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ
ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ።

(Red-8)
👍51👏1

ቅርቤ ሆነህ አለሁ ስትል
ከደስታዬ ምን ሰረቀኝ
‎ሰላም ሆኜ የምገኘው
‎ ከሩቅ ሆነህ ስትናፍቀኝ

@getmtg
@getmtg
5

what is stronger
than the human heart
which shatters over and over
and still lives

(Rupi Kaur)
@getmtg
@getmtg
🔥2

ደስታ ቢራቢሮ
(በእውቀቱ ስዩም)

ደስታ ቢራቢሮ
እኔ ጀብደኛ አዳኝ
ስትከንፊ ስከተል የእድሜ መንገድ ከዳኝ

ሳሎኔ ዱር ሆኖ
በግንድ በቅርንጫፍ በሣር ተሸፍኖ
ከኮርኒሴ በታች ወፍራም ጭጋግ ሰፍኖ
እኔም እድሜ ልኬን የማያድግ ሕፃን

እድገቱ
ቁመቱ
ባስማት የተገታ
ነጋ ጠባ ዝላይ ሁለዜ ጨዋታ
በሄደበት ለማጅ
ነፋስን በመንፊት ውሀን በጨርቅ አጥማጅ

ዓመት ታመት ጮርቃ
ለሹመት የማይታጭ ለዋስ የማይበቃ
ሆኘ ቀረሁ በቃ?

ደስታ ቢራቢሮ
በጣቶቸ ማሀል ቀለምሽ ተነነ
ተከትዬሽ ስከንፍ ላባዬ በነነ
ክንፌ ተመለጠ
ጥላሽን ሳሳድድ ዘመኔ አመለጠ፡፡

@getmtg
@getmtg
👍2👏21

አንዳንድ ሰው ለአንዴ እሹሩሩ ካልከው ዘላለም የደገስክለት ይመስለዋል፡፡

@getmtg
@getmtg
👍6

የስኬት የምኞቷን ግብ
‎ቀድማ ነው ማበጃጀቷ
‎መዋብን ታውቅበታለች
‎ልባም ናትና ልጅቷ

@getmtg
@getmtg
5

‎መቼ ጠፋኝ ኑሮ አመሉ
‎አይበግረው መውጣት መውረድ
‎አይመችም ሁሌ አይሞላ
‎አንዴ ሲል ሞቅ አንዴ በረድ

‎መረሳሳት አይባልም
‎ቅድሚያ ላሉት ሲሆን ጊዜ
‎አንድ ሰሞን ሲያጠፋፋ
‎ላይቀር ዳግም መጠያየቅ
‎ሄድ ብሎ መለስ ነው መኖር ዙሩን እያሰፋ

@getmtg
@getmtg
👍4🔥2

።።።።።።።።። ፍኖተ- በቀል ።።።።።።።።።።

ምን አለች አንዷ የኮራችብክ ዛሬ ስትቀር
ምን መለሱልህ የለመንካቸው  አሁን ስትከብር

ይሰግዱልሀል የተፀየፉህ ይዘህ ስትመጣ
ይዘምራሉ የናቁህ ሁሉ አምረህ ስትወጣ

ለመሳሰሉት ለነዚህ ትሎች ስርህ ለበዙ
ማምለጥ ከፈለክ አትሽሻቸው ስኬት ነው መርዙ!

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
4👏4🔥2

ይለፍ ያልነው ቀን አልፎ
‎               የሻትነው ቀን እስኪመጣ
‎ብቻ ግን በመጠበቅ ውስጥ
‎                     ተስፋችን ተስፋ እንዳያጣ

@getmtg
@getmtg
3🔥3🥰2

በየትኛው ርዕስ በየትኛው ሀሳብ እንዲሁም በየትኛው picture ይፃፍላችሁ?

inbox
👇👇👇👇👇
@amen1995

@getmtg
@getmtg

ያቺ እናት ጉብለ ወጣት
‎ከታቀፈችው ልጇ ጋር
‎ ፀባይ ከመልኳ ተዳምሮ
‎በቅፅበት ልቤን ስትገዛው
‎በመውደድ ዜማ ስንሳፈፍ
‎ በእሷነት ዋጋ ቀኔ አምሮ

‎እግሬ ወደእሷ እያመራ
‎ቀድሞኑ ባየኋት ቦታ
‎ ቀርቤ ባያት ደግሜ
‎ጨለማው ልቤ ነግቶለት
‎ቀስ በቀስ መስመሩን ያዘ
የፈራረሰው አለሜ

‎የተስፋ ልቧን አጉድፎ
‎ቢተዋት የልጇ አባት
‎ ባይልም እንኳን ከዚህ አለሁ
‎አለማግባቷን እያሰብኩ
‎እሷኑ እስከነልጇ እጅጉን አፍቅሬአታለሁ

@getmtg
@getmtg     
11

sometimes
the apology
never comes
when it is wanted

and when it comes
it is neither wanted
nor needed

- you are too late

(Rupi Kaur)

@getmtg
@getmtg
2👍2
1

‎አለኝ ያልኩት ጭላጭ ተስፋ
‎                 አይዞህ ብሎ ያፅናናኛል
‎ይለፍ ያልኩት ይህ ጊዜ አልፎ
‎              ነገን ማየት ያጓጓኛል

‎የናፈቀኝ ቀና መንገድ
‎ ሌላ መልኬን ሌላ ገፄን
‎የነበረኝ ያን ፈገግታ
‎ የልጅነት ያፍላ ሳቄን

‎ጊዜ ደርሶ ያጎደለውን
‎ ቀን መልሶ እስኪክሰው
‎ያጓጓኛል ነገን ማየት
‎ እንዳሰብኩት አድርጎኝ ሰው

@getmtg
@getmtg
5👍1

ልዕለ መልካምነትሽ
‎እፁብነትን ከትቦ
‎                ምሉዕ መልክሽን ያወዛ
‎እንደ ፅጌ አበባዋ
‎     የሆንሽ የእንቡጧን ጠረን
‎                    የማትጠገብ መአዛ

‎እኔ ከጎንሽ ያለሁ
‎የውስጤን አውነት አምቄ
‎                  ሳታይኝ ሰርቄ የማይሽ
‎በወንድምነት ሽፋን
‎ከራሴው ሰርቀሽ ያኖርሽኝ
‎                ችዬ እንኳ የማልለይሽ    
‎   
‎የልቤን መንገር ያቃተኝ
‎ብታውቂው የማጣት ስጋት   
‎             ዝም ብል የጭንቄ በደል
‎ብትይዢኝ ለራሴ የምተርፍ         
‎               ከተውሺኝ ዙሪያዬ ገደል

‎ብትፈቅጂ እሺ ብትይኝ
‎አድርጎኝ ብገኝ ዘብ ቋሚ
‎              ለፍቅርሽ ዘለአለም ታጋይ
‎ንግስቴ ሆነሽ ብትከብሪ
‎ፅድቅ ነው ለኔ በረከት
‎                ብኖር ሆኜልሽ አገልጋይ

‎ለደስታሽ ችቦ ለኩሼ
‎ከሀዘንሽ ድባብ ሸሽጌ
ከልዬ ልክ እንደ ጋሻ
‎ሁሉንም ብሆንልሽ ስል
‎አፌ ግን ፈራ መናገር
  የፍቅሩን ማረፊያ ሲሻ

@getmtg
@getmtg
10