የግጥም ጥግ
768 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

ልታጠምድ
እንደ ንብ
በትነህ አበባ
ልታስገባኝ ከአፍህ
እንደ አውራ ዶሮ
ብትጭርም ገለባ

በመዋለል ውለህ
በናፍቆት ስታድር ስራን እያበዛህ
እልፍ ጠላት ሳይሆን
ልብ ነው የገዛህ

እመነኝ!😊

@getmtg
@getmtg
👏4

ለቀልድ አንተ ስትል
‎              ቃልህን ሳልቆጥር
‎               ስቄልህ እያለፍኩ
‎አንተ ያነሳኸውን
‎       ለቀልድ ባነሳ
‎               መጥፎ ተብዬ አረፍኩ
‎                   
ለምን¿

@getmtg
@getmtg
😁51

i know it's hard
believe me
i know it feels like
tomorrow will never come
and today will be the most
difficult day to get through
but i swear you will get through
the hurt will pass
as it always does
if you give it time and
let it so let it
go
slowly
like a broken promise
let it go

"Rupi Kaur"

@getmtg
@getmtg
4

የኔ እህት አዚህ ሰፈር ነሽ?
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ የሰፈራችን ባለሱቅ የሆነ ቀን በበሩ ሳልፍ "ወንድሜ" ብሎ  በአክብሮት  ጠራኝና  እዚህ ሰፈር ነው የምትኖረው? ብሎ ጠየቀኝ! "አወ" አልኩት እንዴት ረሳኝ ብየ በመገረም! የረዢም አመት ደንበኛየ ነበር። ቀጠል አድርጎ
ሲጃራ ታጨሳለህ እንዴ?
አይ አላጨስም
አቁመህ ነው?
አይ ከመጀመሪያውም አላጨስም
ጫትስ ትቅማለህ እንዴ?
አይ አልቅምም
አቁመህ ነው?
ቅሜ አላውቅም! ለምንድነው ግን የምትጠይቀኝ አልኩ ገርሞኝ ። ጥያቄየን ችላ ብሎ

እ...የስልክ ካርድ ከኔ ትወስድ ነበር እንዴ?
አወ (ደግሞ እውነቴን ነው ከሱ ሱቅ ነበር የምገዛው)

ባለስንት ነበር የምትገዛው? 
ባለመቶም ፣ ባለ ሃምሳም ...ባለ ....

ተወው አስታወስኩ! የመቶ ብር ካርድ አለብህ  ስምህን መዝገብ ላይ አይቸዋለሁ
ማነው ስሜ ?
ስምህ ምን ያረጋል ጋሸ? ዋናው ካርዱ ነው ....😀

በኋላ ስሰማ ይሄ ሚስኪን ባለሱቅ አእምሮውን ታሞ አማኑኤል ሆስፒታል ገብቶ ነበር አሉኝ። ሚስቱን ነበር ሱቁ ውስጥ ለረዢም ጊዜ የማያት! እና  ዘለግ ላለ ጊዜ ታክሞ ከአማኑኤል ተሽሎት ወጣ። ሁሉ ነገር ተስተካክሎ አንድ ነገር ብቻ ትንሽ ልክ አልመጣለትም እየተባለ ይወራል። ማንኛውም በሱቁ በር የሚያለፍ ሰው ዱቤ ወስዶ ያልከፈለው  ይመስለው ስለነበር እያስቆመ አጭር መስቀለኛ ኢንተርቪው ያደርጋል። ከምንም በላይ ግን ያሳቀቀን እትየ ማርታን ጠርቶ ጠየቃት የተባለው  ነገር ነው። እትየ ማርታ ዕድሜዋ 40 የተሻገረ ዘናጭ ሴት ናት!
"እህቴ ይቅርታ እዚህ ሰፈር ነሽ?" አላት
አወ ምን ልርዳህ? አለች በሚያምር ፈገግታ
ፔሬድ ማየት አቁመሻል እንዴ  ወይስ ታያለሽ ? አበደች ...
"ስድ ምናባህ አገባህ?" በኋላ ባሏ ተነግሮት ሊያናፍጠው ወደሱቁ ሲሄድ "ሞዴስ በዱቤ ወስዳ ያልከፈለችኝ መስሎኝ ነው ጋሸ ! ግን ከመጣህ አይቀር  ታጨሳለህ እንዴ.....😀"

@getmtg
@getmtg
😁7

ሄደሽ ሄደሽ
‎     ሰው መሆን ላይ ስትደርሺ
‎ እየሞተ ያሻገረሽ
‎              ድልድይ ልቤን እንዳትረሺ

@getmtg
@getmtg
6

ን...ቁ...ባ...ይ

ሲጎስሙ ንጉሥ ስሜን
እንኳን ወርቅ አትነካም ሰሜን

አልልም ውርደትን አሜን
ይጎንጩ ይጠጡት ደሜን

አላውቅም ምህረት ፈፅሞ ልንገራችሁ ግልጡን
እናንተ ብትሆኑ ካሳን እኔ 'ምሆነው ሽጉጡን
   
ሲያሻ 'ፈትልሀለሁ እንደ ባዘቶ ጥጥ በ'ጅ እንደቀለለ
     ከፈለኩም ጥሜ አዘፍንሁለሁ   እንደያንጓለለ

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
4🔥1👏1

you ask
if we can still be friends
i explain how a honeybee
does not dream of kissing
the mouth of a flower
and then settle for its leaves

- i don't need more friends

(Rupi Kaur)

@getmtg
@getmtg
2

የአፍ አትቁጠር
‎ከጆሮ አልፎ ውስጥህ ያድምጥ
‎አይንህ ሳቄን
‎ልብህ ደግሞ
‎       እንባዬን ይይ የጭንቄን ምጥ
‎                        
@getmtg
@getmtg
👍4

ቀጨኔ አድባርሽ ማነው
(አስታወሰኝ ረጋሳ)

"ጋራው ሚካኤል ባይሰማን
ጋሽ ቸሬ ባለውቃቢው
የኛን ልመና አይዘነጋም
በጨለማ ሹክ ያሉት ፀሎት
እስኪፈታ ጀንበር አትነጋም"

ብለውኝ ለሊቱን ሙሉ
ካደምኩት ተሰዋ እንቅልፌ
   ሲነጋስ_!? 
ትዝታዋ እንጂ  የለችም እሷ ከቅፌ፤

እግዚአብሔር አብ ከተራራው ጫፍ
ሞገሱን ይዞ ተቀምጧል
ፀበሉን እያፈለቀ
የስንቱን የንባ ሀዘን ውጧል!

ታዲያሳ እግዚሐርዬ
የኔ እና የሷን ነገር ምነው!
በቶሎ ያልፈጠምክልኝ
ጠንቋይ ቤት ሂዷል ብለህ ነው!?

ከእንጦጦ ዳገት እስከ ሾላ ጫፍ 
እሷው ነች በሩቁ ተለጥፋልኝ
እንግዲህ ማምጣት ካቃተህ
በል ቶሎ አይኔን አጥፋልኝ

ማዞሪያን ስዞረው ውዬ
በቅርበት እሷን ካላየው
አይን አለኝ ማለት ምንድር ነው!?

"ሸክላ ሰሪ ናት" ቢሉኝ
  አፈር ሆኜ ምነው ብታፍሰኝ
በማርያም ወንዝ ውሃ አልቆጥቁጣኝ
ክንዷ ላይ ብታንተርሰኝ

ሸማዬን ላንተ አላነጥፍም
ከንግዲስ ግጥም አልጥፍም

/አምጣልኝ አልኩህ አምጣልኝ/

እምቢየው እሷ ከሌለች
ብቻዬን አልባረክም
እንግዲህስ አምላክ ነህ ብዬም
ለክብርህ ዣንጥላ አልልክም

ብትፈልግ ሲኦል ወርውረኝ
አድርገኝ ለሚፋጅ ቅጣት
አይበልጥም እሷን ከማጣት።

@getmtg
@getmtg
3

የዚህ ቀን ሲሳይ እለቱ
‎ክርስቶስ እሰይ ተወልደ
‎ሀጥያት ስር ጨልመን ሳለን
‎ሊያድነን ምድር ወረደ

‎በሄዋን የደፈረሰው
በድንግል ማርያም ሊጠራ
‎የጥፋት ታሪክ ሊታረም
‎በቤቴልሄም ተወልዷል
‎ክርስቶስ መዳኒ አለም

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል🙏

@getmtg
@getmtg
9
ባለቅኔ ነበርኩ
ባለኝ ሰዓት ቅኔ
ያ...ኔ!

ቅኔ ይሏት እርግብ
አፍኜ ስመግብ
ስታዜም ስሰማት
መዝሙሯን ስቀማት
ቀምቼ ሳፏጨው
የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤
የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ
ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤
እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል
ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል
የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ
ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ
ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ
በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ።

ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ
ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ
የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ
ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ
በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል
ምስኪን! ኪን እርግቤ
እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል?

ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን
ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን
ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት
በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥

ግን አልሆነልኝም
አልጮህ ድምፅ የለኝም
ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል
አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል?
ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል?

እውነት!

ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ!
ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ
ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ
አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ
ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ
ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ
አንድ እርግብ ነበረች፤
አሁን ግን የለችም!
ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች።

ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ

ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ
ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ።

(Red-8)
👍51👏1

ቅርቤ ሆነህ አለሁ ስትል
ከደስታዬ ምን ሰረቀኝ
‎ሰላም ሆኜ የምገኘው
‎ ከሩቅ ሆነህ ስትናፍቀኝ

@getmtg
@getmtg
5

what is stronger
than the human heart
which shatters over and over
and still lives

(Rupi Kaur)
@getmtg
@getmtg
🔥2

ደስታ ቢራቢሮ
(በእውቀቱ ስዩም)

ደስታ ቢራቢሮ
እኔ ጀብደኛ አዳኝ
ስትከንፊ ስከተል የእድሜ መንገድ ከዳኝ

ሳሎኔ ዱር ሆኖ
በግንድ በቅርንጫፍ በሣር ተሸፍኖ
ከኮርኒሴ በታች ወፍራም ጭጋግ ሰፍኖ
እኔም እድሜ ልኬን የማያድግ ሕፃን

እድገቱ
ቁመቱ
ባስማት የተገታ
ነጋ ጠባ ዝላይ ሁለዜ ጨዋታ
በሄደበት ለማጅ
ነፋስን በመንፊት ውሀን በጨርቅ አጥማጅ

ዓመት ታመት ጮርቃ
ለሹመት የማይታጭ ለዋስ የማይበቃ
ሆኘ ቀረሁ በቃ?

ደስታ ቢራቢሮ
በጣቶቸ ማሀል ቀለምሽ ተነነ
ተከትዬሽ ስከንፍ ላባዬ በነነ
ክንፌ ተመለጠ
ጥላሽን ሳሳድድ ዘመኔ አመለጠ፡፡

@getmtg
@getmtg
👍2👏21

አንዳንድ ሰው ለአንዴ እሹሩሩ ካልከው ዘላለም የደገስክለት ይመስለዋል፡፡

@getmtg
@getmtg
👍6

የስኬት የምኞቷን ግብ
‎ቀድማ ነው ማበጃጀቷ
‎መዋብን ታውቅበታለች
‎ልባም ናትና ልጅቷ

@getmtg
@getmtg
5

‎መቼ ጠፋኝ ኑሮ አመሉ
‎አይበግረው መውጣት መውረድ
‎አይመችም ሁሌ አይሞላ
‎አንዴ ሲል ሞቅ አንዴ በረድ

‎መረሳሳት አይባልም
‎ቅድሚያ ላሉት ሲሆን ጊዜ
‎አንድ ሰሞን ሲያጠፋፋ
‎ላይቀር ዳግም መጠያየቅ
‎ሄድ ብሎ መለስ ነው መኖር ዙሩን እያሰፋ

@getmtg
@getmtg
👍4🔥2

።።።።።።።።። ፍኖተ- በቀል ።።።።።።።።።።

ምን አለች አንዷ የኮራችብክ ዛሬ ስትቀር
ምን መለሱልህ የለመንካቸው  አሁን ስትከብር

ይሰግዱልሀል የተፀየፉህ ይዘህ ስትመጣ
ይዘምራሉ የናቁህ ሁሉ አምረህ ስትወጣ

ለመሳሰሉት ለነዚህ ትሎች ስርህ ለበዙ
ማምለጥ ከፈለክ አትሽሻቸው ስኬት ነው መርዙ!

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
4👏4🔥2

ይለፍ ያልነው ቀን አልፎ
‎               የሻትነው ቀን እስኪመጣ
‎ብቻ ግን በመጠበቅ ውስጥ
‎                     ተስፋችን ተስፋ እንዳያጣ

@getmtg
@getmtg
3🔥3🥰2

በየትኛው ርዕስ በየትኛው ሀሳብ እንዲሁም በየትኛው picture ይፃፍላችሁ?

inbox
👇👇👇👇👇
@amen1995

@getmtg
@getmtg

ያቺ እናት ጉብለ ወጣት
‎ከታቀፈችው ልጇ ጋር
‎ ፀባይ ከመልኳ ተዳምሮ
‎በቅፅበት ልቤን ስትገዛው
‎በመውደድ ዜማ ስንሳፈፍ
‎ በእሷነት ዋጋ ቀኔ አምሮ

‎እግሬ ወደእሷ እያመራ
‎ቀድሞኑ ባየኋት ቦታ
‎ ቀርቤ ባያት ደግሜ
‎ጨለማው ልቤ ነግቶለት
‎ቀስ በቀስ መስመሩን ያዘ
የፈራረሰው አለሜ

‎የተስፋ ልቧን አጉድፎ
‎ቢተዋት የልጇ አባት
‎ ባይልም እንኳን ከዚህ አለሁ
‎አለማግባቷን እያሰብኩ
‎እሷኑ እስከነልጇ እጅጉን አፍቅሬአታለሁ

@getmtg
@getmtg     
11