፡
ከልቧ ነው መውደድ ልኳ
ፀጋነት ነው ያላት ፍቅር
ከሁሉም ነገር ይልቃል
ድምቀት ነች ለኖረችበት
እሷነት ቤትን ያሞቃል
እጅጉን ለፍታ ብትደክም
ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
ጎሎባት ሙሉ ልታደርግ
ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ
እናት እኮ ......
ቢርባት ከራሷ ቀድማ
ለልጇ ሰጥታ የምታጎርስ
ጥረቷ ከቶ የማይላላ
መውደዷ የማይደፈርስ
ፍቅር ነው ሁለ ነገሯ
ሁልጊዜም ትታወሳለች
ጠብቃ ለማኖር ስትል
እሷነት ዋጋን ከፍላለች
ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
ከልቧ ነው መውደድ ልኳ
ፀጋነት ነው ያላት ፍቅር
ከሁሉም ነገር ይልቃል
ድምቀት ነች ለኖረችበት
እሷነት ቤትን ያሞቃል
እጅጉን ለፍታ ብትደክም
ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
ጎሎባት ሙሉ ልታደርግ
ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ
እናት እኮ ......
ቢርባት ከራሷ ቀድማ
ለልጇ ሰጥታ የምታጎርስ
ጥረቷ ከቶ የማይላላ
መውደዷ የማይደፈርስ
ፍቅር ነው ሁለ ነገሯ
ሁልጊዜም ትታወሳለች
ጠብቃ ለማኖር ስትል
እሷነት ዋጋን ከፍላለች
ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
❤6👍2
፡
ናፈቅሽኝ
በእውነት ናፈቅሽኝ
በቃ! ከመሬት ተነስቶ
ያ ውበትሽ መጥቶ
ውልብ አለ በአይኔ ከሀሳቤ ገብቶ
ፈገግታ ሳቅሽም ደምቆ እየታየኝ
ያ የሚያምረው ጉንጭሽ
ሳመኝ ሳመኝ ሲለኝ
አይኖችሽ ታወሱኝ
የፍቅር ፍላፃ ጨረር እየተፉ
ጮቤ የሚያስረግጡኝ
ከአይኖቼ ላይ ሲያርፉ
ቅኔው ንግግርሽ አንደበትሽ ማሩ
ደርሶ ንፍቅ አለኝ
ድምፅሽን አድምጦ በፍቅር መስከሩ
መአዛሽ ታወሰኝ ጠረንሽ ናፈቀኝ
በሀሴት መንኮራኩር
ሰማይ የሚያመጥቀኝ፡፡
ከአንገትሽ ስር ውትፍ
በእጆቼ እቅፍ
መአዛሽን ስቤ ወደ ሰማይ ክንፍ
ማለት ሲናፍቀኝ ላይሽ ሳስብ ግና
መቼም አላገኝሽ የሌላ ነሽና፡፡
ናፍቆቴም ቅዠት ነው
ህልም እልም ብያለሁ
ሳይተኙ ማለምን ባንቺ አግኝቼዋለሁ
ባይሆን በምትኩ
በውኔ እያለምኩ በህልሜ ኖራለሁ።
✍Abosina
@getmtg
@getmtg
ናፈቅሽኝ
በእውነት ናፈቅሽኝ
በቃ! ከመሬት ተነስቶ
ያ ውበትሽ መጥቶ
ውልብ አለ በአይኔ ከሀሳቤ ገብቶ
ፈገግታ ሳቅሽም ደምቆ እየታየኝ
ያ የሚያምረው ጉንጭሽ
ሳመኝ ሳመኝ ሲለኝ
አይኖችሽ ታወሱኝ
የፍቅር ፍላፃ ጨረር እየተፉ
ጮቤ የሚያስረግጡኝ
ከአይኖቼ ላይ ሲያርፉ
ቅኔው ንግግርሽ አንደበትሽ ማሩ
ደርሶ ንፍቅ አለኝ
ድምፅሽን አድምጦ በፍቅር መስከሩ
መአዛሽ ታወሰኝ ጠረንሽ ናፈቀኝ
በሀሴት መንኮራኩር
ሰማይ የሚያመጥቀኝ፡፡
ከአንገትሽ ስር ውትፍ
በእጆቼ እቅፍ
መአዛሽን ስቤ ወደ ሰማይ ክንፍ
ማለት ሲናፍቀኝ ላይሽ ሳስብ ግና
መቼም አላገኝሽ የሌላ ነሽና፡፡
ናፍቆቴም ቅዠት ነው
ህልም እልም ብያለሁ
ሳይተኙ ማለምን ባንቺ አግኝቼዋለሁ
ባይሆን በምትኩ
በውኔ እያለምኩ በህልሜ ኖራለሁ።
✍Abosina
@getmtg
@getmtg
👍5❤2
፡
When I Go
(by Donna Ashworth)
When I go
Don't learn to live without me
Just learn to live with my love
In a different way
And if you need to see me
Close your eyes
Or look in your shadow
When the sun shines
I'm there.
Sit with me in the quiet
and you will know
That I did not leave
There is no living
When a soul is blended
With another
When I go
Don't learn to live without me
Just learn to look for me in the
moments.
I will be there!
@getmtg
@getmtg
When I Go
(by Donna Ashworth)
When I go
Don't learn to live without me
Just learn to live with my love
In a different way
And if you need to see me
Close your eyes
Or look in your shadow
When the sun shines
I'm there.
Sit with me in the quiet
and you will know
That I did not leave
There is no living
When a soul is blended
With another
When I go
Don't learn to live without me
Just learn to look for me in the
moments.
I will be there!
@getmtg
@getmtg
❤5
፡
ላንቺ
(ኤፍሬም ሥዩም)
ቅጠሎች ታውቂያለሽ
ቅጠል
ለምለም ቅጠል
ከግንድ የነበሩ
ንጹህ አረንጓዴ ሆነው የነበሩ
ውብ አበባ ሆነው ተፈጥሮን ያበሩ
ቅጠሎች ታውቂያለሽ?
ቅጠል
ለምለም ቅጠል፡፡
(እነዚያ ቅጠሎች) • • •
ግንድ ላይ እያሉ አንቺን ይመስላሉ
ለምልመው እያሉ አንቺን ያክላሉ
'ርጥብ ፅጌ እያሉ ካንቺ እኩል ነበሩ
በንፋስ አለንጋ ሳይሰባበሩ
ለምለሞች ነበሩ፡፡
ቅጠሎች አይተሻል
በነፋሳት ንዴት ከግንድ የወደቁ
ወድቀው የደረቁ
ባ'ላፊ አግዳሚው እግር የደረቁ
ቅጠሎች አይተሻል
አበቦች አይተሻል
ማንን ይመስላሉ ምንን ያወራሉ?
የእርጅናን ስጋት ለማን ይነግራሉ? • • •
ውበት አልነበሩ
ለምለም አልነበሩ
ቅጠል አልነበሩ
ከጊዜ ዋልካ ላይ
ተገፍተው ሳይወድቁ ሳይሰባበሩ
እንዳንቺ አልነበሩ፡፡
የሚገርምሽ ነገር
የጊዜ ተአምር • • •
ቅጠሎች ከጣለው
ታላቁ ግንድ ላይ
አዳዲስ ቅጠሎች ማበብ ጀምረዋል
ቅጠል የሚረገጥ
አረንጓዴ 'ማይወድ
አላፊው አግዳሚው ባ'ይኑ ያሻቸዋል
ከግንዱ ስር ካሉት
ደረቅ ቅጠሎች ላይ
ሁለት ፍቅረኛሞች ተኝተውበታል፡፡
መሬት ላይ የተኙት
ቅጠል ላይ የተኙት ሁለቱ ፍቅረኞች
እርጋፊ ቅጠል
ከመሬት አንስተው ባ'ውራ ጣት ሲሰብሩ
የጊዜን ምንነት
ልብ ባለማለት ካንቺ እኩል ነበሩ፡፡
ምንም እንዳይገርምሽ፡፡
@getmtg
@getmtg
ላንቺ
(ኤፍሬም ሥዩም)
ቅጠሎች ታውቂያለሽ
ቅጠል
ለምለም ቅጠል
ከግንድ የነበሩ
ንጹህ አረንጓዴ ሆነው የነበሩ
ውብ አበባ ሆነው ተፈጥሮን ያበሩ
ቅጠሎች ታውቂያለሽ?
ቅጠል
ለምለም ቅጠል፡፡
(እነዚያ ቅጠሎች) • • •
ግንድ ላይ እያሉ አንቺን ይመስላሉ
ለምልመው እያሉ አንቺን ያክላሉ
'ርጥብ ፅጌ እያሉ ካንቺ እኩል ነበሩ
በንፋስ አለንጋ ሳይሰባበሩ
ለምለሞች ነበሩ፡፡
ቅጠሎች አይተሻል
በነፋሳት ንዴት ከግንድ የወደቁ
ወድቀው የደረቁ
ባ'ላፊ አግዳሚው እግር የደረቁ
ቅጠሎች አይተሻል
አበቦች አይተሻል
ማንን ይመስላሉ ምንን ያወራሉ?
የእርጅናን ስጋት ለማን ይነግራሉ? • • •
ውበት አልነበሩ
ለምለም አልነበሩ
ቅጠል አልነበሩ
ከጊዜ ዋልካ ላይ
ተገፍተው ሳይወድቁ ሳይሰባበሩ
እንዳንቺ አልነበሩ፡፡
የሚገርምሽ ነገር
የጊዜ ተአምር • • •
ቅጠሎች ከጣለው
ታላቁ ግንድ ላይ
አዳዲስ ቅጠሎች ማበብ ጀምረዋል
ቅጠል የሚረገጥ
አረንጓዴ 'ማይወድ
አላፊው አግዳሚው ባ'ይኑ ያሻቸዋል
ከግንዱ ስር ካሉት
ደረቅ ቅጠሎች ላይ
ሁለት ፍቅረኛሞች ተኝተውበታል፡፡
መሬት ላይ የተኙት
ቅጠል ላይ የተኙት ሁለቱ ፍቅረኞች
እርጋፊ ቅጠል
ከመሬት አንስተው ባ'ውራ ጣት ሲሰብሩ
የጊዜን ምንነት
ልብ ባለማለት ካንቺ እኩል ነበሩ፡፡
ምንም እንዳይገርምሽ፡፡
@getmtg
@getmtg
👏4❤1
፡
የኔ እህት አዚህ ሰፈር ነሽ?
(አሌክስ አብርሃም)
አንድ የሰፈራችን ባለሱቅ የሆነ ቀን በበሩ ሳልፍ "ወንድሜ" ብሎ በአክብሮት ጠራኝና እዚህ ሰፈር ነው የምትኖረው? ብሎ ጠየቀኝ! "አወ" አልኩት እንዴት ረሳኝ ብየ በመገረም! የረዢም አመት ደንበኛየ ነበር። ቀጠል አድርጎ
ሲጃራ ታጨሳለህ እንዴ?
አይ አላጨስም
አቁመህ ነው?
አይ ከመጀመሪያውም አላጨስም
ጫትስ ትቅማለህ እንዴ?
አይ አልቅምም
አቁመህ ነው?
ቅሜ አላውቅም! ለምንድነው ግን የምትጠይቀኝ አልኩ ገርሞኝ ። ጥያቄየን ችላ ብሎ
እ...የስልክ ካርድ ከኔ ትወስድ ነበር እንዴ?
አወ (ደግሞ እውነቴን ነው ከሱ ሱቅ ነበር የምገዛው)
ባለስንት ነበር የምትገዛው?
ባለመቶም ፣ ባለ ሃምሳም ...ባለ ....
ተወው አስታወስኩ! የመቶ ብር ካርድ አለብህ ስምህን መዝገብ ላይ አይቸዋለሁ
ማነው ስሜ ?
ስምህ ምን ያረጋል ጋሸ? ዋናው ካርዱ ነው ....😀
በኋላ ስሰማ ይሄ ሚስኪን ባለሱቅ አእምሮውን ታሞ አማኑኤል ሆስፒታል ገብቶ ነበር አሉኝ። ሚስቱን ነበር ሱቁ ውስጥ ለረዢም ጊዜ የማያት! እና ዘለግ ላለ ጊዜ ታክሞ ከአማኑኤል ተሽሎት ወጣ። ሁሉ ነገር ተስተካክሎ አንድ ነገር ብቻ ትንሽ ልክ አልመጣለትም እየተባለ ይወራል። ማንኛውም በሱቁ በር የሚያለፍ ሰው ዱቤ ወስዶ ያልከፈለው ይመስለው ስለነበር እያስቆመ አጭር መስቀለኛ ኢንተርቪው ያደርጋል። ከምንም በላይ ግን ያሳቀቀን እትየ ማርታን ጠርቶ ጠየቃት የተባለው ነገር ነው። እትየ ማርታ ዕድሜዋ 40 የተሻገረ ዘናጭ ሴት ናት!
"እህቴ ይቅርታ እዚህ ሰፈር ነሽ?" አላት
አወ ምን ልርዳህ? አለች በሚያምር ፈገግታ
ፔሬድ ማየት አቁመሻል እንዴ ወይስ ታያለሽ ? አበደች ...
"ስድ ምናባህ አገባህ?" በኋላ ባሏ ተነግሮት ሊያናፍጠው ወደሱቁ ሲሄድ "ሞዴስ በዱቤ ወስዳ ያልከፈለችኝ መስሎኝ ነው ጋሸ ! ግን ከመጣህ አይቀር ታጨሳለህ እንዴ.....😀"
@getmtg
@getmtg
የኔ እህት አዚህ ሰፈር ነሽ?
(አሌክስ አብርሃም)
አንድ የሰፈራችን ባለሱቅ የሆነ ቀን በበሩ ሳልፍ "ወንድሜ" ብሎ በአክብሮት ጠራኝና እዚህ ሰፈር ነው የምትኖረው? ብሎ ጠየቀኝ! "አወ" አልኩት እንዴት ረሳኝ ብየ በመገረም! የረዢም አመት ደንበኛየ ነበር። ቀጠል አድርጎ
ሲጃራ ታጨሳለህ እንዴ?
አይ አላጨስም
አቁመህ ነው?
አይ ከመጀመሪያውም አላጨስም
ጫትስ ትቅማለህ እንዴ?
አይ አልቅምም
አቁመህ ነው?
ቅሜ አላውቅም! ለምንድነው ግን የምትጠይቀኝ አልኩ ገርሞኝ ። ጥያቄየን ችላ ብሎ
እ...የስልክ ካርድ ከኔ ትወስድ ነበር እንዴ?
አወ (ደግሞ እውነቴን ነው ከሱ ሱቅ ነበር የምገዛው)
ባለስንት ነበር የምትገዛው?
ባለመቶም ፣ ባለ ሃምሳም ...ባለ ....
ተወው አስታወስኩ! የመቶ ብር ካርድ አለብህ ስምህን መዝገብ ላይ አይቸዋለሁ
ማነው ስሜ ?
ስምህ ምን ያረጋል ጋሸ? ዋናው ካርዱ ነው ....😀
በኋላ ስሰማ ይሄ ሚስኪን ባለሱቅ አእምሮውን ታሞ አማኑኤል ሆስፒታል ገብቶ ነበር አሉኝ። ሚስቱን ነበር ሱቁ ውስጥ ለረዢም ጊዜ የማያት! እና ዘለግ ላለ ጊዜ ታክሞ ከአማኑኤል ተሽሎት ወጣ። ሁሉ ነገር ተስተካክሎ አንድ ነገር ብቻ ትንሽ ልክ አልመጣለትም እየተባለ ይወራል። ማንኛውም በሱቁ በር የሚያለፍ ሰው ዱቤ ወስዶ ያልከፈለው ይመስለው ስለነበር እያስቆመ አጭር መስቀለኛ ኢንተርቪው ያደርጋል። ከምንም በላይ ግን ያሳቀቀን እትየ ማርታን ጠርቶ ጠየቃት የተባለው ነገር ነው። እትየ ማርታ ዕድሜዋ 40 የተሻገረ ዘናጭ ሴት ናት!
"እህቴ ይቅርታ እዚህ ሰፈር ነሽ?" አላት
አወ ምን ልርዳህ? አለች በሚያምር ፈገግታ
ፔሬድ ማየት አቁመሻል እንዴ ወይስ ታያለሽ ? አበደች ...
"ስድ ምናባህ አገባህ?" በኋላ ባሏ ተነግሮት ሊያናፍጠው ወደሱቁ ሲሄድ "ሞዴስ በዱቤ ወስዳ ያልከፈለችኝ መስሎኝ ነው ጋሸ ! ግን ከመጣህ አይቀር ታጨሳለህ እንዴ.....😀"
@getmtg
@getmtg
😁7
፡
ቀጨኔ አድባርሽ ማነው
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
"ጋራው ሚካኤል ባይሰማን
ጋሽ ቸሬ ባለውቃቢው
የኛን ልመና አይዘነጋም
በጨለማ ሹክ ያሉት ፀሎት
እስኪፈታ ጀንበር አትነጋም"
ብለውኝ ለሊቱን ሙሉ
ካደምኩት ተሰዋ እንቅልፌ
ሲነጋስ_!?
ትዝታዋ እንጂ የለችም እሷ ከቅፌ፤
እግዚአብሔር አብ ከተራራው ጫፍ
ሞገሱን ይዞ ተቀምጧል
ፀበሉን እያፈለቀ
የስንቱን የንባ ሀዘን ውጧል!
ታዲያሳ እግዚሐርዬ
የኔ እና የሷን ነገር ምነው!
በቶሎ ያልፈጠምክልኝ
ጠንቋይ ቤት ሂዷል ብለህ ነው!?
ከእንጦጦ ዳገት እስከ ሾላ ጫፍ
እሷው ነች በሩቁ ተለጥፋልኝ
እንግዲህ ማምጣት ካቃተህ
በል ቶሎ አይኔን አጥፋልኝ
ማዞሪያን ስዞረው ውዬ
በቅርበት እሷን ካላየው
አይን አለኝ ማለት ምንድር ነው!?
"ሸክላ ሰሪ ናት" ቢሉኝ
አፈር ሆኜ ምነው ብታፍሰኝ
በማርያም ወንዝ ውሃ አልቆጥቁጣኝ
ክንዷ ላይ ብታንተርሰኝ
ሸማዬን ላንተ አላነጥፍም
ከንግዲስ ግጥም አልጥፍም
/አምጣልኝ አልኩህ አምጣልኝ/
እምቢየው እሷ ከሌለች
ብቻዬን አልባረክም
እንግዲህስ አምላክ ነህ ብዬም
ለክብርህ ዣንጥላ አልልክም
ብትፈልግ ሲኦል ወርውረኝ
አድርገኝ ለሚፋጅ ቅጣት
አይበልጥም እሷን ከማጣት።
@getmtg
@getmtg
ቀጨኔ አድባርሽ ማነው
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
"ጋራው ሚካኤል ባይሰማን
ጋሽ ቸሬ ባለውቃቢው
የኛን ልመና አይዘነጋም
በጨለማ ሹክ ያሉት ፀሎት
እስኪፈታ ጀንበር አትነጋም"
ብለውኝ ለሊቱን ሙሉ
ካደምኩት ተሰዋ እንቅልፌ
ሲነጋስ_!?
ትዝታዋ እንጂ የለችም እሷ ከቅፌ፤
እግዚአብሔር አብ ከተራራው ጫፍ
ሞገሱን ይዞ ተቀምጧል
ፀበሉን እያፈለቀ
የስንቱን የንባ ሀዘን ውጧል!
ታዲያሳ እግዚሐርዬ
የኔ እና የሷን ነገር ምነው!
በቶሎ ያልፈጠምክልኝ
ጠንቋይ ቤት ሂዷል ብለህ ነው!?
ከእንጦጦ ዳገት እስከ ሾላ ጫፍ
እሷው ነች በሩቁ ተለጥፋልኝ
እንግዲህ ማምጣት ካቃተህ
በል ቶሎ አይኔን አጥፋልኝ
ማዞሪያን ስዞረው ውዬ
በቅርበት እሷን ካላየው
አይን አለኝ ማለት ምንድር ነው!?
"ሸክላ ሰሪ ናት" ቢሉኝ
አፈር ሆኜ ምነው ብታፍሰኝ
በማርያም ወንዝ ውሃ አልቆጥቁጣኝ
ክንዷ ላይ ብታንተርሰኝ
ሸማዬን ላንተ አላነጥፍም
ከንግዲስ ግጥም አልጥፍም
/አምጣልኝ አልኩህ አምጣልኝ/
እምቢየው እሷ ከሌለች
ብቻዬን አልባረክም
እንግዲህስ አምላክ ነህ ብዬም
ለክብርህ ዣንጥላ አልልክም
ብትፈልግ ሲኦል ወርውረኝ
አድርገኝ ለሚፋጅ ቅጣት
አይበልጥም እሷን ከማጣት።
@getmtg
@getmtg
❤3