የግጥም ጥግ
768 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram
የግጥም ጥግ
፡ ያማል! ‎ (በሰለሞን ሳህለ) ‎ ‎እና እንደነገርኩሽ ‎የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ ‎የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ ‎ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ ‎ከተስፋ ጉልላት ተከፍቶ እንደመውደቅ ‎ተአምር በበዛባት በዚች ቧልተኛ አለም ‎ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም ‎ ‎አውቶቢሱ ያማል ‎ሚኒባሱ ያማል ‎ላዳ ታክሲው ያማል ‎የማይጎል የሰው…

        ህመምህ አሞኛል
                 (አሌክስ አብርሃም)

የጥበብን ቀኝ እጅ
                   በቀኝ አጁ የዘየረ
ነብዩ ሰለሞን ያማል ይል ነበረ

ቆሞ ሲጠብቃት ቀርታበት ወዳጁ
አንድ እሷ የምትሞላው ኦና ቢሆን ደጁ
ግትልትል መኪናው
ታክሲው አውቶቢሱ
የሰው ግሳንግሱ
የሰው አጋሰሱ
ለአይኑ አልሞላ ብሎት ለተራበች ነፍሱ
            .... ያማል ይል ነበረ .....

በአይኖቿ አንቀልባ
በእንባ መቀነቻ
               ተስፋ እንደቋጠረ
ማዶ ማዶ እያየ
በተሰበረ ቅስም ያማል ይል ነበረ

እኔ መች ተሰማኝ የጓዴ ህመሙ
የታባቴ ገብቶን የጥበቃ ጥሙ
ዛሬ ግን አወኩት
ብቻዬን ባወራው እብድ ይሉኛል ብዬ
ህመምን ላለፍካት
ህመሜን ላኩልህ በአረቄ ጠቅልዬ

እይውልህ ጓዴ
ያቺ የነገርኩህ ልጅ የፍቅር እትብቴ
ለተስፋዬ ደብር ያኖርኳት ፅላቴ
በራችንን ዘግተን
ሲንቆረቆር ህልሜ ሲንቆረቆር ህልምህ
ትዝ አይልህም ጓዴ
እልፍ ዝምበል ያልኩህ
     ...........  እሷ
የሰው ሁሉ ዳና የእሷ ነው እያልኩኝ
ከበሬ ሲርቁ ተስፋ እያሶረድኩኝ
የጠበኳት ፍቅሬ መቼ ለታ መጣች
ጓዴ ሃሌሉያ የኔ ፀሀይ ወጣች
ከምዕራብ አድማስ ብርሀኗን ነዛች

ተዘግቶ የነበረ በሬ ተከፈተ
ገድሎኝ የነበረው ብቸኝነት ሞተ
ሊተን የነበረ የመውደዴ ተስፋ
ፀጉሬ ጫፍ ላይ ሲደርስ ተመልሶ ፋፋ
ጥቋቁር ተራሮች ፍቅሬን የጋረዲ
የእግሯን ዳና ሰምተው ከፊቴ ተናዱ
ጓዴ ሀሌሉያ አበቦች ደመቁ
የመከኑ ምንጮች ኩል ውሃ አፈለቁ
በጠራራ ግንቦት አደይ ምድሩን ሞላ
          ምን ልበልህ ሌላ
      ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

እኔ እምልህ ጓዴ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
                    ነበር አይደል ያልከው?!
ከመቅረት የባሰ
አመጣጥ እንዳለ አንተ መች አወከው

እና የነገርኩህ ልጅ
መኖሬን እረስታ
     በሬን ክፍቱን ትታ
እግዜር የሰማውን
         የእምነት ቃሏን ክዳ
  ከባዕድ ተዛምዳ ከባዕድ ተዋልዳ
  "አንተ እስካሁን አለህ"
            አትለኝ መሰለህ

ልሙትልህ ጓዴ
   እንዲህ ነው ያለችኝ
          ቁልቁል እያየችኝ
እንዲህ ናህ ቅፅበቷ

እሷ ከፊቴ አለች
የጎደፈ እምነቷን በቃል እያጠበች
ውራጅ ፍቅሯን ገዝቶ ደረቱን የነፋ
          ፈረንጅ ጎኗ ቆሟል
ከእሷና እሱ ኃላ
ተራራ ሸንተረር ዛፍ ቅጠሉ ታሟል
        ደመናውም ደክሟል
ከደመናው በላይ
አፉን በእጁ ይዞ እግዜርም ተደሟል
         ወቸ ጉድ እያለ

ፈረንጁ ......
እጁን መክሊቴ ላይ ጣል አርጎ ያየኛል
ያኔ ያልከው ህመም ጎኔን ይወጋኛል
የምትወዳትን ልጅ በሌላ መታቀፍ
ከዚህ በላይ ስቃይ ከዚህ በላይ መቅፈፍ

ምናለበት እሱ ግዴለም ይቀፋት
በፈራረሰ ቤት ጭቃው በረገፈ
በንፁህ ልቦና በቀን ባልጎደፈ
አንዲት አግዳሚ ላይ
             ጎን ለጎን ተቀምጠን
አንድ እርሳት ተካፍለን
            አንድ መፅሃፍ ገልጠን

የአበበን በሶ የጫላን ስል ጩቤ
እኔ እንጂ የማስታውስ
                      ልቤ ላይ ከትቤ
ፈረንጁ ምን እዳው ከሀዲን ያስከዳው
የአየለን ብርታት የጫልቱን እንስራ
በቀዳዳ ጣራ
ጉንጯ ላይ ያረፈች የምታምር ጮራ
ቆዳዋ ላይ ያሉ ገራገር ስስ ፀጉሮች
ጥቁር ሰሌዳ ላይ
ተስፋን የሚቃርሙ የልጅነት አይኖች
አርፈው የማይቆሙ ተወዛዋዥ እግሮች
እሱ መች አያቸው
ከአንጎሉ ጥልቀት
በትዝታ መረብ መች አጠመዳቸው
ምቾት ያደለበው ስጋዋን ይቀፈው
እንደመሲህ ካባ
በእምነት የምነካው
ሰገባ ቀሚሷን በድፍረት ይግፈፈው
ከሰማይ የራቁኝ
ጡቶቿ መካከል በእፎይታ ይረፍ
            በአርያም ይንሳፈፍ

ልሙትልህ ጓዴ ከጎኔ ብትኖር
እናቷን ጨረቃ
ያስባለህ ህመምህ
በጠራራ ፀሀይ ይነሳብህ ነበር

እኔ ተነሳብኝ
ሴጣን ወሰወሰኝ ከጎኔ ብትኖር
እናቷን ጨረቃ
ያስባለህ ህመምህ
በጠራራ ፀሀይ ይነሳብህ ነበር

እኔ ተነሳብኝ
ሴጣን ወሰወሰኝ
እከካም ክህደት
የምፎክትበት ጥፍርህን አውሰኝ

የኔና እሷን ነበር ዛሬ ያላወራው
እናቱን ሸለቆ እናቱን ተራራው
ከፊቴ የቆመው እናቱን ፈረንጁ
ወገቧን ያቀፈው እናቱን ቀኝ እጁ

ስማኝማ አንተ ሰው
የሚወዱትን ሰው
ቀጥሮ እንደመጠበቅ አልነበረ ያልከው?!
ከመቅረት የባሰ
አመጣጥ እንዳለ አንተ መች አወከው

አይዞን ወዳጄ ......
ያው እንዳንተ ደጃፍ ኦና ሆኗል ደጄ
አሁን ናፍቀኸኛል
እጠብቀው የለኝ ትጠብቀው የለህ
እንገናኝና አረቄ እየጠጣን
ግጥም እንፃፍለት
    ለድህነታችን ጥበቃን ላሳጣን
እናቱን ድህነት
እናቱን ጥበቃ

            ............ በቃ!

@getmtg
@getmtg
👏6

ለምን መሄድ አስፈለገ
‎ ዳግም ዞረሽ ልትመጪ
‎ምን ሊፈይድ መመላለስ
‎ተደላድለሽ ላትቀመጭ
‎ ወይ ጠቅልለሽ ላትወጪ

‎አንቺን ልተው ስፍጨረጨር
‎ካረፍሽበት ከልቤ ላይ
‎ ሊጠፋ ሲል መልከ ገፅሽ
‎በአዲስ ተስፋ ይሞላኛል
እንደ ተራ ቀላል ነገር
‎ መጣሁልህ የሚል መልስሽ

‎ተይ ግድ የለም .....
‎ቁምነገሬን ችላ ብለሽ
‎ በነፍሴ ላይ አትቀልጂ
‎እኔን ብለሽ ከመጣሽ ነይ
‎ካልተመቸሽ ልሂድ ካልሽም
‎ ላትመለሽ ሆነሽ ሂጂ

@getmtg
@getmtg
🔥31👏1
👍3👏2

እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
...... ስልጠናው ሳይኖርህ

በሚያድጥ ዳገት ላይ በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች ሳይፎርሹ መቅለብ
ደርዘን ሙሉ አሎሎ
አሎሎ ቢጠፋ እሾህ ተድበልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ማለፍ ሹልክ ብሎ

እንደ ህልም እሪታ በሰለለ ገመድ
...... ባንድ እግር መራመድ

ይሄን ሁሉ አድርገህ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሃል አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ

ምንም ባትታደል አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ .....
ያልተራገፈ ጥርስ ያልተሰበረ ቅስም  
የድል ሳቅህን ሳቅ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ አጨብጭብ ለራስህ

@getmtg
@getmtg
👍52

ባቅምህ እየተጣጣርክ
‎የኑሮ ስሩን አጠንክር
ክንድህን ለስራ አበርታ
‎ምርኩዝህ ይሆንልሃል
‎ነገ ላይ እድሜ ሲያዳክም
ጉልበትህ የከዳህ ለታ

‎እይበት ደስታ አለምህን
‎ስኬትን ተጎናፀፈው
በራስህ ይበልህ ደሰ ደስ
‎በላብህ ሰርተህ ስትበላ
‎ እንዲያ ነው አንጀትህ የሚደርስ

@getmtg
@getmtg
👍32

ከልቡ ነው መውደድ ጥጉ
‎ምርቃቱ ደርሶ የሚያኖር
ቁጣው እንኳ 'ሚያለመልም
‎መሰረቱን ጠበቅ አርጎ
‎ስብዕናን 'ሚገነባ ማንነትን የሚቀልም

‎በርትቶ የሚያበረታ
‎ምክሩ ከክፉ የሚያርቅ
የሚያበቃ ለቁምነገር
‎ለፍቶ ደክሞ ያሳደገ
‎እንዴትስ ከሀሳብ ይጠፋል
መች ይረሳል ያባት ነገር

‎አባት እኮ ......
‎ለልጁ እንቁ ጌጡ ነው
መመኪያ ምሳሌነቱ
‎ክብርና ሞገስ የሞላው
‎ ያረገ ፍቅርን እምነቱ

‎ይመራል በቀና መንገድ
‎ያሳያል ስኬት ጥበቡን
‎ተዘርቶ የተጠበቀ
‎በብቃት ማፍራት ማበቡን

‎አባት እኮ ......
‎ባይታይ ሀሳብ ሲገባው
‎ይዞት ነው ውስጡን በውስጡ
‎አክብረው ለወደዱት ሰው
‎ስቀው ነው ፍቅር የሚሰጡ

‎በርትቶ እያበረታ
‎አለሁ እያለ የሚያፀድቅ
የሚያበቃ ለቁም ነገር
‎እንዴትስ ከሀሳብ ይጠፋል
መች ይረሳል ያባት ነገር

Mekdi
@getmtg
@getmtg
6

"ትክክለኛ አባትነት በአንድ አካል ሶስት ዘመን ላይ የሚኖር ማንነት ነው፡፡ ትላንታችንን የሚያሻግር፡ ዛሬአችን ላይ እንደ እሳት አጥር ከቦን የሚቆም፡ ነጋችንን ከተሻለ ድልና ተስፋ ጋር የሚያጋባ፡ አባትነት በሰማይ ያለው አምላክ ምድራዊ ምሳሌ መሆን ነው፡፡"

"አልተዘዋወረችም"
@getmtg
@getmtg
7

መንገድ ወሳጅ መላሽ
‎               ሰው ግን በዛው ቀሪ
"‎እንዴት?" ካልሺኝ .....
‎             ያንቺን መጥፊያ ተናገሪ

@getmtg
@getmtg
3👏1

ጩኸት

እጣ ክፍሌ ሆኖ የአርባ ቀን እድሌ
በችግር መከራ በሀጢያት ኩነኔ;
ስኖር በዚህ አለም ሰላም እንደራቀኝ፣
ይኸው አሁን ደግሞ ጩኸት አስጨነቀኝ።
 ከውጪ
ሰዉ አራዊቱ አእዋፍ ነፍሳቱ
ማሽኑ መኪናው አውሮፕላን ጀቱ
ሙዚቃው ዳንኪራው የመንገድ መብራቱ;
በአይን በጆሮዬ ገብተው ሲራኮቱ
ሰላሜን አጣለሁ
ስጋዬ ረክሳ ከምድራዊ ሲኦል ደርሼ መጣለሁ።
 
ደግሞ እሱን ሸሽቼ
ከሰው ተለይቼ
 ጭር ባለ ቦታ ብቻዬን ቁጭ ስል
ደግሞ ሌላ ጩኸት ደግሞ ሌላ ቁስል
ከራሴው ከውስጤ ይመጣና ደርሶ
ያቃጭልብኛል ፀፀትን ተላብሶ።
ህሊናዬ ልቤ አንጎል አእምሮዬ
 ለውስጥ ህዋሶቼ ለውስጥ አይን ጆሮዬ
ሀጥያቴን በደሌን ከፍ አርገው እያሰሙ
 በትናንትና እንጨት ቁስሌን እያደሙ
ነፍሴን ሰላም ነስተው ሲኦል ይከቷታል
እርኩስ ነች እያሉ በአንድነት ያሟታል።
 
እና እኔ ከወዴት ልኑር እና እኔ  ከየትስ ልግባ፣
በየሄድኩበት ሁሉ ጩኸት አብሮኝ ከገባ
ዝምታን መቼ ላገኘው ፀጥታ መቼ ሊመጣ፣
ከውስጥም ከውጭም ያለው እሪታ ከኔ ሳይወጣ
በርታ አይዞህ በማለት  ሁሌ ከምታደርቁኝ፣
እስኪ ሰዎች ለአንድ ቀን 
ጩኸት ከማይደርስበት ወስዳቹ እኔን ደብቁኝ።

please ደብቁኝ።
 
  Abosina
@getmtg
@getmtg
3👏2👍1

"ምቾት ችግሩ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስን አለመፍቀዱ፡ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች መውረድን አለመፈለጉ ነው፡፡ ምቾት ጥሩ ቢሆንም ከደረጃ ላለመውረድ የሚያስከትለው ትግል በራሱ ጭንቀት ፈጥሮ ቆይቶ ምቾትን መልሶ መንሳቱ አይቀርም፡፡ በምቾት ወስጥ ምቾት የለም!"

‎ "ሰበዝ"
@getmtg
@getmtg
👍41

የፍቅር ትሩፋት

በጣም የምታምር ቆንጆ ልጅ አፍቅሬ
ፍቅሬን ሳላዋያት ሳልነግራት ደፍሬ
ሁልጊዜ እንደ ጭራ ስከተላት ኖሬ
የምትጥለውን ስሰበስብላት ልክ እንደ ቁራሌ።

 የብስኩት ወረቀት የማስቲካ ልጣጭ
 ከአፏ የወደቀ ከረሜላ ጣፋጭ
 ያለቀ እስኪርቢቶ የተጣለ ደብተር
 በነዛ ውብ እግሮች የተረገጠ አፈር
 ከማር አንደበቷ የሚወጡ ቃላት
 ልክ እንደ እግዜሩ ቃል የምጠብቅላት
 እኔ የሷ ዩኔስኮ የቅርሷ ጠባቂ
 ቤቴም ወመዘክር የትዝታ ጊቢ።

እሷ የነካችውን ሰብስቤ ሰብስቤ
ፈጣሪም እረድቶኝ ደፈረና ልቤ
መውደዴን ብነግራት ፍቅሬን ባካፍላት
በመጀመሪያ ላይ ቀልድ ነው የመሰላት
ኮስተርተር አልኩና ስነግራት ደግሜ
እሷም ኮስተር ብላ“አትቀልድ ወንድሜ ”
ብላኝ እርፍ አለች በቁጣ ደንፍታ
የጆክ ውሃ አንስታ በፊቴ ላይ ደፍታ በጥፊ ተማታ።

እኔ ጅል አፍቃሪ ውዴ ፍቅሬ እያልኩ
ለካስ እኔ ለሷ ወንድሟ ነበርኩ
ይኸው እሱም ቀርቶ ዛሬ ተሰረዝኩ

ትዝታዋም ጠፋ ቅርሷም ቅርስ አልሆነ
የልጅት አፍሪቃ ወንድሟ ከሆነ
ፍቅሯ ባለቤቷ መሆኑ ካለፈኝ
ቆሻሻ ነው እንጂ እኔ ከሷ ፍቅር ሌላ ምን ተረፈኝ።

Abosina
@getmtg
@getmtg
4👏3

..... አንተ ልጅ ዝምታህ .....

‎አንተ ልጅ ዝምታህ
‎ከመናገር በላይ ቃላት ሆኖ አየሁ
‎ዝም ስትል ጊዜ
‎ ድምፅህን አገኘሁ
‎ታስታውስ እንደሆን
‎ከዝምታ አለም ውስጥ
‎ ጩኸትም መኖሩን
‎አንደበት ዝም ሲል
‎ እውነት መታፈኑን
‎ ..... ነግሬህ ነበረ .....

‎ጭንቅህ ባይታይም
‎የውስጥህን ሁነት ጥርስህ ቢሸፍነው
‎የመምሰል እይታ
‎ አይንን ቢያታልለው
‎ለኔ ግን
‎ካሳየኸው ሳቅ ስር ጭንቅህ ይታየኛል
‎የውስጥህ ኡኡታ ገንኖ ይሰማኛል
‎ ..... እንዴት ካልከኝ ደግሞ .....
‎መስሎ መታየትን መሆን አይተካውም
‎ከማየቴ በላይ
‎ማስተዋሌ ሲበልጥ አይኔን አላምነውም

‎መናገርን ባትመርጥ
‎ብቻህን ብትገኝ ቢበዛም ዝምታህ
‎መዳንን ፍለጋ
‎ለራስህ የምትነግረው
‎ ብዙ ነገር አለህ

@getmtg
@getmtg
7

ከሄድኩበት ከዛው አለም
‎                  ካለሁበት ቦታ እስክገኝ
‎ገፄ ባይንህ እስኪገለጥ
‎                 ሙዚቃ ውስጥ ና ፈልገኝ

@getmtg
@getmtg
3
..."አባዬ" (ልጅ)

..."አቤት" (አባት)

..."በግ አስተኝተን፡ አርደን፡ ደሙን አፍሥሰን፡ በጥብስ እና በቅቅል አርገን ስንበላው ነፍሱን በማጥፋታችን ሀጥያት አይሆንብንም?"(ልጅ)

..."ምን ስትል አሰብከው ልጄ? እረ አይሆንብንም።" (አባት)

..."እንዴ አባዬ እየገደልን አደለ እንዴ፡ እንዴት ሀጥያት አይሆንብንም?" (ልጅ)

..."ምን መሰለህ ልጄ... እንዴት ላስረዳህ?... ሞት እኮ በር እንጂ መጨረሻ አይደለም፡ በጉን ስንበላው በኛ ውስጥ መኖሩ ይቀጥላል እንጂ ጨርሶ አይሞትም" (አባት)

..."እረ እረ አባዬ ደሞ እንደዚ አለ እንዴ?" (ልጅ)

...."አዎ! እውነት ስልህ ፥ ያው የበላነው ተስማምቶን ሀይል እና ጉልበት አግኝተን፡ አካላዊ እድገት እያመጣን አይደል የምንኖረው ፡ ያ ታድያ እኮ በኛ ኖረ ማለት ነው ልጄ" (አባት)

..."እሺ እና ጋሽ ጀንበሬ እንደውም ባለፈው በለሊት ወደስራ ሲሄዱ ጅብ የበላቸው ጅብ ሆነው እየኖሩ ነው ማለት ነው አባዬ?" (ልጅ)

..."ወይ ጉድ ዛሬ እንደው ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት...ማነሽ 'አልማዝ ነይ እስኪ ይሄን ልጅ ወደዛ ወስደሽ ገላግይኝ'...አልሞት አልኩህ?" (አባት)

..."ምን አልክ አባዬ?" (ልጅ)

..."ምንም ወዲህ ነው የእራት ሰዓት ደርሷል እናትህን ወስደሽ አብይው እያልኳት ነው....'አንቺ አልማዝ ነይ እኮ ነው ምልሽ'. ..አትሰማኝም እንዴ?" (አባት)

..."እና ንገረኛ አባቴ ጋሽ ጀንበሬ ጅብ ሆነዋል ማለት ነው? የባቢ አባት ጅብ ናቸው ማለት ነው?" (ልጅ)

..."ሆሆ! ደሞ ነገ ት/ት ቤት ሄደህ 'የባቢ አባት ጅብ ሆኑ እንጂ አልሞቱም ብሏል አባዬ' ልትል ነው ሆሆ! ደሞ ከጎረቤቶቼ አቆራርጠኛ! በል በል የለም ያልኩህን እርሳው በቃ እንደውም ሀጥያት ነው ከንግዲህ በግ የሚባል አናርድም።. ..ግልግል እንደውም ተወዷል...ሆ! በገዛ እጄ...ቆይ እዛ ት/ት ቤት ምን ስትማሩ ነው የምትውሉት?" (አባት)

..." እርሳው? አባዬ ደሞ አንዴ ነግረኸኝ እንዴት ነው ምረሳው?...ደሞ ት/ት ቤት ሳይሆን አንተ እኮ ነህ የነገርከኝ በግን ስንበላው እኛን እንደሚሆን...ት/ት ቤት ምን አጠፉ....ህእ!"  (ልጅ)

..."ማ? እኔ አልወጣኝም! አይወጣኝምም!. ..ምን ይላል ይሄ...በል ጥፋ ከዚ. ..ድራሽ አባክ ይጥፋና...አትሄድም!".....

By Mikiyas Beshada Kebede
😁5

አንፃር ፫
(ኤፍሬም ስዩም)

እስከ ዛሬ ድረስ
የዛን ጊዜ ክብሬ
የነበረው ፍቅሬ
በነበር ቢቀርም . . . እንደነበር አለ
እውነት ከእኔ በቀር
' ነበር ' ያንቺ መንታ መሆኑን የሚያውቅ
ከቶ ምን ሰው አለ?

@getmtg
@getmtg
👏2

በግ ተራ እና ትዝታዎቹ
(ዘማርቆስ)

ግቢ የመግባት ዕድሉን ያገኘ ስለ በግ ተራ ማወቅ አይከብደውም።ሄዶም ባይጎበኘው ሄደው ስለጎበኙት መስማቱ አይቀርምና!'በግ ተራ' የሚለው ሐረግ ከቦታው ጋር ያለውን ግንኙነትና ለምን ይህ ስያሜ እንደተሰጠው ባላውቅም አንዳንድ ውስጠ አዋቂዎች እንደነገሩኝ ከሆነ 'በ-ግተራ' ከሚለው በመነሳት  ወደ 'በግ ተራ' በሂደት እንደተደረሰ ነግረውኛል።የሌሎቹን ስለማላውቅ ከዚህ በታች ስለ በግተራ የማወጋው ሁሉ የኔን ጊቢ ብቻ የሚመለከት መሆኑን እወቁልኝ።
    ፍሬሽ እያለሁ አንድ ጎደሎ ቀን የሆነ ጎደሎ ትምህርት ላጠና ቤተመፃህፍት ገባሁ...ወግ አይቀር!አስችሎኝ እስከ እኩለ ሌሊት አምሽቼ ልወጣ ብድግ ስል አንድ ያገሬ ልጅ ከርቀት ''ጠብቂኝ" አለኝ...  ከሰዎች ጋር ተቀምጬ ከማወራው እየተራመድኩ የማወራው ይስበኛል።ስለ ግቢው...ስለ ቤተሰብ...ስለ 'ዲፓርትመንት' ምርጫችን...እየተጨዋወትን...ምን አስቦ እንደያዘኝ ያልገባኝን እጁን መንጭቄ ሳላስለቅቀው...እየተጨዋወትን...በመሀል ጣቱ የመዳፌን መሀል በስሱ እየነካኝ...እየተጨዋወትን...እጄን ለቆ እጁን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጎት...የደረት አጥንቴን መነካካት ሲጀምር...መጨዋወት አቆምን።
"ምን እየሆንክ ነው?" አላልኩም...ሲነካኩ ዝም ብለው ደርሰው በሰው ማላከክማ አጉል ፅድቅን መሻት ነው።
"ምን እየሆንን ነው ጃል?"
"እንጃ"...ብሎኝ ከመንገዱ ዳር ተቀመጠ።ልክ እናቷ ሹርባ ልትሰራት ተደላድላ እንደምትቀመጥ ጉብል እግርና እግሩ መሃል መሬት ላይ ዘጭ ብዬ ተቀመጥኩ...እስከዚህ ሰዓት ድረስ በግ ተራ ስለመሆኔ አላወቅሁም...ጨለማው...ፀጥታውና ንፋሱ ይህ ነው የማይባል ሰላም አለው...እጁ የማያርፍ ወዳጅ አየሩን ካልበጠበጠው በቀር።ደረቴ ላይ ቆሞ የነበረውን ጉዞ ሊቀጥል ሲል የሆነ ቅውጥ ያለ ባህላዊ ሙዚቃ በስፒከር ከፍቶ የሚንቀሳቀስ ሰው ድምፅ ተሰማን...ወዲያው 'ፀሐይ ለምኔ' የሚያስብል ባትሪ ፊታችን ላይ ተተኮሰ። ይህ ባትሪ ከበራብኝ በኋላ በገጠመኝ Post Traumatic Stress የተነሳ ለረጅም ጊዜ ባህላዊ ዘፈን ስሰማና የእጅ ባትሪ ሳይ Heart attack ይገጥመኝ ነበር።
"ኧረግ ኧረግ ኧረግ...አተ!ምናባታችሁ እያረጋችሁ ነው?"አለን ፀሐይ በእጄው ሜትሮ።ምንም እያደረግን ነው ብንላቸው ባትሪያቸው ካሳያቸው ምስል በላይ ላያምኑን የሚጠይቁን ነገርስ?'እየሾረበኝ ነው' ልበል?ወይስ ትከሻዬን እያሸኝ?ሜትሮው በፍጥነት እየተራመደ ሲቀርበን እጅና እግሬን ታስሬ ከተራራ የተፈነቀለ አለት ሊጫነኝ ቁልቁል እየተምዘገዘገ የሚወርድ መሰለኝ... በማይሆን ሰዓት ሰንፈህ የምታውቅ ወዳጄ ካለህ በቃ ያ ጭንቀትህ ነው የጨነቀኝ።
"ምንም እያደረግን አይደለም" አልኩ አንገቴን ቀብሬ።
"እና በዚህ ምሸት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?" አለና ድምፁን በሚችለው ልክ ከፍ አድርጎ ተጣራ።
"አተ ድንበሩ...ኧረ ድንበሩ ዉዉ..."
"ኧኧኧይ" ከወዲያኛው ጫፍ
"ኧረ ናማ ናማ...ና አንድ በልልኝ"
"ኧረ ምን መጣ?"
"ናማ ወዲህ መርፌና ክር ሁነው ያዝኳቸው" ሲል ሲምዘገዘግ የቆየው ድንጋይ መሃል አናቴን የተረተረኝ ያህል ሰማይ ምድሩ ጭውውውው አለብኝ።ድንበሩ ወጣት ነው።ዕድሜውን በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ገመትኩት...
"እስቲ አይ.ዲ. ወዲህ በሉ" አለ ከመምጣቱ
"አልያዝንም" በአንድ ድምፅ
"አምጡማ ልቤን አታውልቁኝ...ዶርምም ቢሆን ተከትየ መቀበሌ ስለማይቀር አጉል አትድከሙ"...መታወቂችንን ሰጠን...እያፈራረቀ ተመለከተውና
"ሚኒሊክ" አለ
"አቤት" አለ ወዳጄ
"ስሙንስ ይዘኸዋል...ጥምብ አሽከር!"አለ በቁጣ...'አምላክ ሆይ መንችኮ አልለቅም ከሚል ስድብ ሰውረኝ' ስል
"መዓዛ" አለኝ
"አቤት"
"ድንቄም መኣዛ!ውትፍ ሸሌ!" አለኝ።አቤቱ ህዝብህን አድን!
"እስቲ አሁን ምን እናርጋችሁ?" አለ ባለ ባትሪው
"ምን አደረግን ቆይ?" አለ ሚኒሊክ
"ዝም በል!የሌባ አይነ ደረቅ!ምን ስታረግ ነው የያዝኩህ?እጅህን እጡቷ ስር ከተህ ስታፍተለትል አይደለም?በል እስቲ ካድ!"
"ኧረ እንደዛ አይደለም'ኮ..."አለ የኔ አልሞት ባይ ተጋዳይ።
"ዝም በል በቃ ሚኒሊክ...እየውላችሁ ወንድሞቼ...ጥፋት አጥፍተናል...ይቅርታ እንጠይቃለን...በዚህ ሰዓት ዶርም ወይም ላይብረሪ እንጂ እዚህ አልነበረም ቦታችን...ለዚህ ደግሞ መቀጣት አለብን...ስለዚህ ተገቢውን ቅጣት ቅጡንና ሸኙን"አልኩኝ ለስለስ ብዬ።ድርበሩ ተብዬው
"እሱማ የት ይቀርልሻል!?ከቅጣቱ በፊት ግን መመከር ስላለባችሁ መታወቂያችሁን ለተማሪ ህብረት ፕሬዝደንቱ እሰጠውና ጧት ቢሮው ሄዳችሁ ታወሩታላችሁ" ሲለን በምን ቅፅበት እግሩ ላይ እንደወደቅሁ አላስታውስም...ከልደታ ማርያም አንስቼ እስከ ቅዱስ ማርቆስ አርባ አራቱን ጠርቼ እንባ ቀረሽ ልመና ለመንኩት።
"የናንተ ይበቃል አሳልፋችሁ አትስጡን...ወይ በጉልበት ስራ ወይ በገንዘብ ቅጡን...በማርያም...በአላህ...በጌታ..."ቅብጥርጥሬ ወጣ።
"ተነሽ ያንችን ብር የሚፈልግ የለም...መጀመሪያ ስትልከሰከሽ ባልተገኘሽ"አቤት የሚጠቀማቸው ቃላት ሲዘጉ!
ባለ ባትሪው ጣልቃ ገብቶ "ተዋት በቃ...ይች ካላበደች ድጋሚ አትገኝም የሷን ስጣትና የሱን አይ.ዲ. አቆየው...ያበጠ ልቡ ሲተነፍስ እንሰጠዋለን" አለ።
"ኧረ እኔ'ኮ አላጠፋሁም አላልኩም "አለ ሚኒሊክ።በዝምታ የኔን መታወቂያ መለሰልኝና
"አይደለም በለሊት በቀን እንዳላይሽ ከዚህ ልጅ ጋር...ሂጅ አሁን ጊቢ!" አለኝ።ዞር ብዬ ሳላይ ኩምሽሽ ብዬ ገባሁ።ሚኒሊክ...ስራህ ያውጣህ!
  ከሶስት አመታት በኋላ  በተማሪ ህብረት ስር የስነምግባር ዘርፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ሆኜ ተመረጥኩና ከሳምንት ሶስት ቀን በግ ተራንና አካባቢውን ከሌሎች የኮሚቴው አባላት ጋር እየዞርኩ ማሰስ ስራዬ ሆነ።አንድ ቀን እዚያች እኔ የተያዝኩባት አካባቢ እየተዘዋወርን እያለ አንዳንድ ቪድዮዎች ላይ የምናውቃቸውን ድምፆች አይነት የሰማን መሰለንና ጆሮአችንን ቀስርን አዳመጥን...ድምፁ ራሱ ነው...ከጎኔ ከቆመው ጓደኛዬ ሀሰን ያንን ፀሐይ ለምኔ ባትሪ ተቀብዬ ተገግ ሳደርገው...ድንበሩ ከአንዲት ልጅ ጋር ምሳር ባንገቴ ተያይዟል።
"ኢስታክፊር አላህ!" አለ ሀሰን።በቅፅበት ባትሪውን መለስ አድርጌ
"ወንድም ስትጨርሱ ብቅ በሉ ቢሮ እንጠብቃችኋለን" ብዬ ባልደረቦቼን ሰብስቤ ዘወር አልኩ።
😁3

‎ከልቧ ነው መውደድ ልኳ
‎ፀጋነት ነው ያላት ፍቅር
‎ከሁሉም ነገር ይልቃል
‎ድምቀት ነች ለኖረችበት
‎እሷነት ቤትን ያሞቃል

‎እጅጉን ለፍታ ብትደክም
‎ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
‎ጎሎባት ሙሉ ልታደርግ
‎ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ

‎እናት እኮ ......
‎ቢርባት ከራሷ ቀድማ
‎ለልጇ ሰጥታ የምታጎርስ
‎ጥረቷ ከቶ የማይላላ
‎መውደዷ የማይደፈርስ

‎ፍቅር ነው ሁለ ነገሯ
‎ሁልጊዜም ትታወሳለች
‎ጠብቃ ለማኖር ስትል
‎እሷነት ዋጋን ከፍላለች

‎ህያው ነፍስ ልትገነባ ነው
ብትዝል ብትንገላታ
‎ለልጇ ስትል የምትኖር
እናት ነች ድንቅ ስጦታ

Mekdi
@getmtg
@getmtg
6👍2

ላንተ ብዬ ምንም ያልሆንኩ
‎           ለኔ ሲሆን ሙሉ ልብህ
‎አለሁ እያልኩ ከአንተ ጠፋሁ
‎           መጣሁ እያልኩ ቀረሁብህ

@getmtg
@getmtg
👍53